ልጥፎች

ከሜይ 22, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአማራ ተጋድሎና የኦሮሞ ንቅናቄ።

ምስል
          ህም።                                        ከሥርጉተ ሥላሴ 22.05.2015 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ)                               „እናንተ ሴቶች ሆይ የእግዚአብሄርን ቃል ስሙ፤ ጆራችሁም የአፉን ቃል ትቀበል።“                                                      (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፳) ·          ጠብታ። „ራዕይ የሌለው መሪ ነጂ መሆን እንጂ መሪ መሆን አይችልም። (ከባለቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የተወሰደ)“ ተመስገን ብላለች ሥርጉትሻ። ቃሏ „ነጂ“ እራሷ አቤት ቅቤ ስታጠጣ። ተመስገን። ባለ ቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሰንበት ላይ ከውጪ ጉዟቸው ተመልስው እረፈት አላስፈለጋቸውም። ቀጥታ የሄዱት የውስጥን ቆሻሻ ጠረግ ለማድረግ በጋራ ከዶር ምህረት ደበበ ጋር ወደ አዘጋጁት ዓውደ የንጥህና ማስጠበቂያ ማዕከል ነበር 19.05.2018 እ.አ.አ። በቅድሚያ ግን ዶር ምህረት ደበበ እንኳን ደስ አለዎት። ምን ያህል ልቦናዎት ቅን ቢሆን ነው በጥረት ውስጥ ድል ዲል ያለለዎት። ለእርሰዎ የቀናችው ቀንም ትመጣልኝ ዘንድ እስቲ እባክዎትን ለአማኑኤል ይንገሩልኝ። „ኢትዮጵያ የአንተም የአንችም የእኔም ናት“ ተመስገን። „የኢትዮጵያን የቀደመ ክብሯ ይመለሳል!“ ተመስገን! ሌላም አንድ ተጨማሪ ተመስገን ላንሳ የዛሬ ሁለት ዓመት በአማራ የማንነት የህልውና አብዮት ላይ በተከታታይ እጽፍ ነበር። መቼም ለእኔ ቀላሉ ሥራ መጻፍ ነው። እንደ ቧንቧ ውሃ ስፈልግ መክፈት ሲያሻኝም መዝጋት እምችለው። እና ያን ጊዜ የፖለቲካ ድርጅቶችን ለመሆኑ ማንፌስቷችሁ ስለ ህጻናት ምን ይላል? ብዬ ሞግቻችሁ ነበር። ከዛ በፊትም ተዳብዬ እሰራበት