ልጥፎች

ከጁላይ 20, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

መሪነት፦ #ተጠናቆ #መፈጠርን ይጠይቃል።

 መሪነት #አቅም #መፍጠር ነው ታላቁ ተልዕኮው።  የፈጠረውን አቅምም በቅጡ ለመምራት የራሱን የምምራት #አቅም ፦ #ክህሎት ማሰልጠንም ይገባዋል።  ይህን አዋዶ ህዝብ ጠቀም ማድረግም ሌላው የመሪነት የጥበብ ዘይቤ ነው።  ሥርጉትሻ 2024/07/17   መሪነት፦ #ተጠናቆ #መፈጠርን ይጠይቃል። እንዴት ነው ሪኮመንድ የሚደረገው? እራስን #በመምረጥ ? የራሱን ከተንቆናጠጠ በኋላ ሌላውን እንደ ሥልጣን #ጥመኛ በማዬት? ለምን? ሌላው እኔ #እመጥናለሁ ወይ ተብሎም እራስ አይጠየቅም። #ፕሮቶኮሉንስ እችለዋለሁን ብሎ ማሰብም ይገባል። አሁን ጠቅላይ ሚር አብይ ንግሥናውን ሲመኙ #ፕሮቶኮሉን ጭራሽ አላሰቡበትም። ለዚህ ነው ብዙ ነገር #ልቅ የሆነው። ይህን የሚከታተል አካልም ያላቸው አይመስለኝም። #ሲነሪቲም አለ ሥርዓት ባለው መንግሥታዊ አወቃቀር። ይህን ጠሚር አብይ ልብ ያሉት ይመስለኛል። #ቀደምቶችን #ይሸኛሉ ። የሳቸውን ተሿሚወች መርጠው #እንዲያመልኳቸው ያደርጋሉ። አዲስ ነገር ፈጥረው። " #ፊልድ ማርሻል" እንደ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን። ልቅና በልዕልና የነበራቸው ቀደምት የኢትዮጵያ ጀግና መኮንኖች መ እንኳን ያልተሰጣቸውን ነው የተከወነው። የሆነ ሆኖ መሪነትም እራስን፦ አቅምን እመጥናለሁ ወይ? ብሎ መጠዬቅን ይጠይቃል። ተያያዥ ጉዳዮችም። ሥርጉትሻ 2024/07/20     መሪነት #በችሮታ ወይንም #በይሉኝታ ወይንም #በቤተሰባዊ ትስስር ወይንም በማህበራዊ ኑሮ #ቅርበት እና #ርቅት አይቸረቸርም። መሪነት #በሥርዓት - ጥልቅነት፤ በሃሳብ - #ብሩህነት ፤ በተመክሮ - #ብቃት እና #ስኬት ፤ በማድመጥ እና በማደራጀት ልዩ #ስልታዊ አቅም፤ በችሎታ እና በሃሳብ ግልፅነት እና #ጥራት ልቅና የሚወሰን ነው። ሚሊ