ልጥፎች

ከጁላይ 29, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አዲስ ቅዱስ ጸበል ከመንፈስ ሲፈልቅ የተዋህዶ ተጋድሎው ሊጋፋው አይገባም።

ምስል
መታመንን መቀበል ግማድ ነው? ግማድ ግን ሃይል ጽናት  መድህን ነው? ቀራንዮ ግማድ ነው ግን ፍቅርን ወለደ።      በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ፤ አሜን! „ነገር ግን አሁን ከጊዜ በኋዋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ጀመራችሁ፣ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤  ጊዜ አጣችሁ እንጂ ማሰብ ታስቡ ነበር። ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበትን ኑሮ  ይበቃኛል ማለትን ተምሬያለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ፤ መብዛትንም አውቃለሁ፤   በእያንድንዱ ነገርም በነገር ሁሉ መጥገብን መራብንም መብዛትንና መጉደልን  ተምሬአለሁ፤ ኃይል በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።“ (የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆላስያስ ምእራፍ ፲ ቁጥር ፲፫) ከሥርጉተ ©ሥላሴ 29.07.2018 ( ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) ·         አ ቦው ከአብዩ መንፈስ ጋር አገር ቤት ለመግባት ቅድመ ሁኔታ አያስፈልጋቸውም። ደፋር እርምጃ መራራ ነው። ሞትን ለመድፈር ሰምዕትነትን ለመፈቀድ የልብ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል። ነገ ለመሄድ ከወስን ስለምን ለነገ ሌላ ቀን ይቀጠርለታል። በዚያች ቅጽበት የፈጠሪ ውሳኔ ካለበት የትም አይቀርም ሞትም ድልም ታሪክም።  ይህ መዋል ገድለ ስለሆነ አድሉን ቅድስት ተዋህዶ ልታጣው አይገባም ባይ ነኝ ይህን የልዩ ትውፊት አዲስ የፊደል ገባታ። ስንዱ የቀደመ መንፈስ ዝግጅቱን አጠናቆ ነው የጠዬቃችሁ፤ ልጃችሁ ይህን ያህል ማይል አቋርጦ ከደጀ ሰላማችሁ ድረስ መጥቶ፤ ወደ አገር ቤት እንደ ታቦት ከብክቦ ሊወስዷችሁ ሲፈቅድ ቅብዕና ነው፤ ቅብዕ ደግሞ ሊገፋ አይገባም፤  ምርቃቱ ከነፈሰበት ...