አዲስ ቅዱስ ጸበል ከመንፈስ ሲፈልቅ የተዋህዶ ተጋድሎው ሊጋፋው አይገባም።

መታመንን መቀበል ግማድ ነው? ግማድ ግን ሃይል ጽናት 
መድህን ነው? ቀራንዮ ግማድ ነው ግን ፍቅርን ወለደ።

     በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ፤ አሜን!

„ነገር ግን አሁን ከጊዜ በኋዋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ጀመራችሁ፣ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤ 
ጊዜ አጣችሁ እንጂ ማሰብ ታስቡ ነበር። ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበትን ኑሮ 
ይበቃኛል ማለትን ተምሬያለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ፤ መብዛትንም አውቃለሁ፤  
በእያንድንዱ ነገርም በነገር ሁሉ መጥገብን መራብንም መብዛትንና መጉደልን 
ተምሬአለሁ፤ ኃይል በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።“

(የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት
ወደ ቆላስያስ ምእራፍ ፲ ቁጥር ፲፫)

ከሥርጉተ ©ሥላሴ
29.07.2018
( ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)


  • ·       ቦው ከአብዩ መንፈስ ጋር አገር ቤት ለመግባት ቅድመ ሁኔታ አያስፈልጋቸውም። ደፋር እርምጃ መራራ ነው። ሞትን ለመድፈር ሰምዕትነትን ለመፈቀድ የልብ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል። ነገ ለመሄድ ከወስን ስለምን ለነገ ሌላ ቀን ይቀጠርለታል። በዚያች ቅጽበት የፈጠሪ ውሳኔ ካለበት የትም አይቀርም ሞትም ድልም ታሪክም። 
  • ይህ መዋል ገድለ ስለሆነ አድሉን ቅድስት ተዋህዶ ልታጣው አይገባም ባይ ነኝ ይህን የልዩ ትውፊት አዲስ የፊደል ገባታ። ስንዱ የቀደመ መንፈስ ዝግጅቱን አጠናቆ ነው የጠዬቃችሁ፤ ልጃችሁ ይህን ያህል ማይል አቋርጦ ከደጀ ሰላማችሁ ድረስ መጥቶ፤ ወደ አገር ቤት እንደ ታቦት ከብክቦ ሊወስዷችሁ ሲፈቅድ ቅብዕና ነው፤ ቅብዕ ደግሞ ሊገፋ አይገባም፤  ምርቃቱ ከነፈሰበት ተኑ ይቀራል። ጊዜ ታሪክን ያበጃል። 
  • ·       ሰምዕታት ቅዱሳን አባቶቼ ሆይ! ልታደምጡኝ ብትፈቅዱ ፍላጎቴ ይሄው ነው።  አብዩ ጋር መሄድ አለባችሁ። መንፈሱም፤ ታሪኩም የማይገኝ በህልምም የማይታሰብ ነው። ለተጎዳው ሥነ - ልቦናችም ፈውስ አዲስ ከመንፈሳችን ውስጥ የፈለቀ ጸበል ነው በረከቱ። ከቶውንም ሊያልፍን አይገባም፤ ረቂቅ ነው ከዳዊት ምስብክ የፈለቀ፤ ከሰለሞን ማህልዬም የፈለቅ።   

እጅግ የምትናፍቁኝ፤ የምሳሳላችሁ በዬሰከንዱ መንፈሴ ከእናንተ ጋር የሆነው ቅዱሳን ሰማዕታት አባቶቼ ሆይ! በቅድሚያ እግዚአብሄር እንኳን ደስ አለው። የኢትዮጵያ ህዝብ ክርስትያን ህዝበ ሙስሊም፤ ህዝበ ዋቄፈታም እንኳን ደስአላችሁ። የቅድስት ቤተክርስትያናችን ፍጹም አህቲ የሆነችው የኤርትራ ኦርቶዶክስ አብያተ ቤተክርስትያንም እንኳን ደስ አላት። አፍሪካ አህጉራችንም እንኳን ደስ አላት።

ዓለምም እንኳን ደስ አላት። ፍጥረታት እና ተፈጥሮም እንኳን ደስ አላቸው። እጽዋት፤ እንሰሳት፤ ምህዋር፤ መሬት እና ሰማይ፤ ወንዞች እና ተራሮች፤ ኮረብቶች አና ሸንተረሮች፤ ጅረቶች አና ውቅያኖስች፤ አዬሩ እና ወቅታትም እንኳን ደስ አላቸው። ወርሃ ሃምሌም እንኳን ደስ አለው። አድዮም የማታዳላው እንኳን ደስ አላት። የቅድስት ተዋህዶ ልዩ መለያ የሆነው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማችንም እንኳን ደስ አለው። 




                           ኢትዮጵያ ሆይ እንኳን ደስ አለሽ!
ሰማዕታቱ አባቶቼ ሆይ! እኔ ባሪያችሁ፤ ረዳችሁ፤ ሎሌያችሁ እምለምናችሁ ቀኑ በጣም ረዘመ። ሌላው ቀርቶ ሁለቱ አንጋፋ ሃይማኖታት እስልምና እና ተዋህዶ በቀደመው ጊዜ ያን ሁሉ መከራ አሳልፈው በምን ስሌት እና ቀምር ይሆን የሰሞናቱ ቀናት ከሰላም ፋውንዴሽን ጋር ቀኑ እንዲህ አብሮ ሊደመር የቻለው?

ይሄ በፍጹም ሁኔታ ሊመረመር የማይቻለው የፈጣሪ ረቂቅ ሚስጢር ነው። ለትንሳኤ ቀን፤ ለፍሰሃ ቀን፤ ለሰናይ ቀን ለሰማያዊ የእልልታ ቀን እንዴት ቅደመ ሁኔታ ይበጅለታል?  እሱ የወደደው ይሆን ዘንድ ብላችሁ ለማስተማር ስትተጉ አልነበረምን? በእናንተ ላይ ይህ ይፈጸም ዘንድ ስለምን ሸሻችሁት?

ዛሬ የሆነው ነገር፤ የሚሆነው ነገር ሁሉ አስቀድሜ እኔ ተናግሬዋለሁኝ፤ ጽፌዋለሁኝ ሰሚ አጣሁ እንጂ፤ ይህ የሆነው በሰውኛ ሳይሆን በፈጣሪኛ ነው። ሥልጣነ ክህንትም ሆነ ሥልጣነ መንግሥት የፈጣሪው ስለሆነ ነው። ቅብዕ የልዑል እግዚአብሄር ሥጦታ ነው።  የተሰጠው በተሰጠው ጊዜ ያን መከወን ካልቻለ ምርቃት ይነሳል። እደግመዋለሁኝ የሰጠው በተሰጠው ቀን ካልሆነ የተሰጠው ምርቃት ይነሳል። ከዚህ በኋዋላ ያለውን መከራ እና ጸጸት ከፈቀዳችሁት እንደ ወሰናችሁት ይሁንላችሁ።

እርግጥ ነው የሀምሌ 19 ቀን የ2010 የኢንጂኔር ሰመኘው ከዚህ ዓለም በሥጋ መለዬት በዚህች ዕለትም አፈር የሚቀምሱባት ዕለት ናት። ይህ እጅግ ሰቅጣጭ እና የኢትዮጵያን መነግሥት የደህንነት፤ የጸጥታ፤ የዶር አብይ አህመድን ካቢኔ ችግሮችን ከቁጥጥሩ ስር ሰለመሆናቸው ጥንካሬውን ጥርጣሬ ቢያስገባው በውነቱ ትክክል ነው። 

በጠራራ ጸሐይ በአፍሪካ መዲና፤ በዓለም የብዙ ነገሮች መተንፈሻ  በሆነው አዲስ አባባ ላይ በመስቀል አደበባይ ላይ አንድ ታላቅ የተስፋ መሪ መኖሩን ሲነጠቅ ይህን ጥያቄ ማስነሳቱ ይገባል። አሜሪካ ላይ የነበረው መርዶም እንዲሁ። እንደ ሰው በጥለቀት ነገሮችን እንድንመረምር ግድ ይለናል፤ ነገር ግን ነገም ይቀጥላል፤ አይቀሬ የሆኑ በርካታ አደጋዎች ይኖራሉ … ታቅደው የሚከወን። ሥልጣን እኮ እንደ እብደትም የሚያደር ነው ... 

እኔም ይህን አስደንጋጭ ዜና ስሰማ ትዝ ያለኝ የኤርትራ ሁለት የልዑክ ቡድን ነበር። ስለሆነም መሄዳቸውን በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ እጬጌ ብፁዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቀርዮስ  እና ሌሎችም ሊቃነ ሊቃውንታት ቅዱሳን አባቶቻችን ጉዳይ ያሳስበኛ። ስጋትም አለብኝ። ይሄ ሰውኛ ነው። እንዲያውም ልዑክ ቢሄድ ይሻላል የሚል ነገር አንስቼ ነበር፤ ያን አስደንጋጭ የኢንጂነር ስመኛው በቀለን ህልፈት ስሰማ።

በተጨማሪም ትግራይ ላይ የተካሄደው ሰላማዊ ስልፍም ያ ቁርሾ፤ ያ ቂም በቀል፤ ያ የማያበቃ የመከራ ዘመን ቀጣይነቱን ዓውጇል። ስለዚህም ነው አባቶቻችን ዋስትና የጠዬቁት።

ስለሆነም ቅዱሳን አባቶቻችን ስጋት ቢኖርባቸውም የተገባ ነው። አንድ ነገር ቢሆን የመጨረሻው ጦርነት ስለሚያስነሳ። ከሁሉ የከፋው የሃይማኖት ጦርነት ስለሆነ። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በዝምታ ውስጥ፤ በተደሞ ውስጥ፤ በእምቅ ሃዘን ላይ ነው ያለችው፤ የታመቀ ያለወጣ፤ ያልተፈተሸ፤ የልተፈተን ነበልባል በዬጎጆው አለ፤ እህ ብላ አምቃ የያዘችው ሞገድ አለ ከተነሳች የሚገድባት የለም።

ጠበንጃውም፤ መትረዬሱም ሰማዕትነት ስለሚሆን ሁሉም ሞቱን ፈቅዶ ይቀበላል። ስለዚህ ከዚህ ቀኖና ተነስተውም ሊሆን ይችላል። የታማቀው ቁስል ሳይደርቅ ሌላ ቁስል ማህበረ ዲያቢሎስ እዬፈጸም እያዬነው ስለሆነ። መቼም መዳፌ ላይ ነው ያለው ያ ማህብረ ክፉ መንፈስ አይልም አዲሱ የለውጥ መንፈስ። ጥቃቶች በዬ አቅጣጫው እዬታዬ ስለሆነ ... 

መዳፉ ውስጥ ያለው ቅንነት፤ ፍቅር እና ለእግዚአብሄር መታምን ብቻ ነው። ይህ ሃይል አለው ወይ? እህ ላመነው አለው። እኔን ጠብቆ ያኖረኝ እሱ እንጂ እንደ ግራ ቀኙ የክፉዎች ማህብር አሁን የምኖረው ዕድሜ ትርፍ ነው። ካለ አንድ ክትር ነው የምኖረው … ለእኔ „የነፃነት ሃይል“ የሚባለውም ሆነ ማህበርረ ወያኔ እኩል የፈተና ዓውድ ስለሆነ …

  መስከረም 18 ቀን 2011።

ለነገሩ ስለዚህ ቀን ምን አለን በእጃችን? በሌላ በኩል እንደማስበው የአገር ቤት መግቢያው የተረዘመው አዲሱን ዓመት ውጪ የሚገኙ ልጆቻቸው፤ መከራቸውን አብረው ታግሰው አንድም ቀን ደከመን ሳይሉ እቅፍ ሽክፍ አድርገው ያገለገሏቸውን ማህበረ ምዕመናን በወግ እና በማዕረግ ምስጋና አቅርቦ ለመሰናበትም ይሆናል።  ፊት ለፊታችን ፍልስቲት የእመቤታችን ልዩ ተናፋቂ ፆም፤ የጳጉሚትም ልዩ የህማማት ክብርንም አብረው ከተከፉት ጋር ለማሳለፍ አስበው ሊሆን ይችላል።

ታላቁ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሱባኤ ፆም ፍልሰቲት ናት። እህል የረባ የማይቀመስባት፤ መሬት ላይ የሚተኛበት፤ ከሥጋ ፈቃድ ሁሉ በእግድ በንጽንህና የሚፆምባት።  ስለሆነም ጸጋውን በሱባኤ መቀበል በቅድስት ቤተክርስትያናችን የተለመደ ቀኖና ስለሆነ ለዛም ይሆናል። የሰማይ በረከት ሲመጣ በፆም፤ በሱባኤ፤ በሰጊድ መቀበል የተገባ ስለሆነ።
  
በተጨማሪም ማህበረ ምዕመናን ውጪ አብሮ ክልትምትም ሲል የነበረውን ቢያንስ አዲስ ዓመትን ለመባረከም ይሆናል ብዬ አስባለሁኝ። ቅዱስ ዮሆንስን ውጭ ላሉት ምዕመን፤ መስቀልን ደግሞ አገር ቤት ካሉት ጋር በወል አሰብውም ሊሆን ይችላል። 

ለአባቶቻችን ሚስጢር ስለሚገለጥላቸው። ይህ የእኔ ጸጋ አይደለም፤ ግን ታናሽ እህቴ ቤተ መንግሥት ትልቅ መስቀል ሲገባ አይቻለሁኝ ብላኛለች። ኤርትራ እራሷን ኤፍራታ በሚል ሥም ነው ያዬሆዋት ብላኛለች። ቤተሰባችን በህልም ያምናል። እኔም እያንዳንዱ እንቅስቃሴዬ በህልሜ ነው የምመራው። ክፉ ህልም ካዬሁኝ ሆስፒታል  ቀጠሮ ከኖረኝ ቀጠሮዬን ሁሉ እሰርዛለሁኝ። ከሌላም ሰው ጋር ቀጠሮ ከኖረኝ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ይሰረዛል።
 
ወደ ቀደመው ምለስት ሲሆን … ያ እህቴ መስቀል ቤተመንግሥት ያዬችው መስቀል ይህ ሊሆን ይችላል ብዬ አስብኩኝ። አብሮ ከቤተመንግሥት መንፈስ ጋር መጓዝ። ትልቅ መስቀል ነው ብላኛለች። የዛሬ 5 ደግሞ ቤተሰብም ያውቃል ሰማይ ላይ  እዚህ ሲዊዝርላንድ በኢትዮጵያ ሰንድቅ ዓላማ ያጨበረቁ ብዙ የሰማይ ሰረገላዎች ሰማይ ላይ እየገላቡ እኔ አይቼ እንዲሁ ነገርኳቸው።

በኋዋላ ረ/ እሮፕላን አብራሪ ጀግናዬ ሃይለመድህን አበራ እዚህ ሲዊዝ ሲገባ ያ ያዬሽው  ህልም ዕውን ሆነ ብለውኝ ነበር። እኔ ግን አሁን እንደማስበው ይህ ለአቅዱሳን አባቶች በሰማይ ላይ የተዘረጋ አክናፋት አድርጌ ተመለከትኩት።  በአዬር ነው የሚሄዱት በነግሥና መንፈስ በክብር በምስጋና፤ ሰንደቅ ዓላማችን ባለው አውሮፕላን፤ ማን ያውቃል ወደ አገር መመለሳቸውን ይሆን ቀድሞ ያዬሁት፤ … 

  • ·       ለኦህዴድ ለማውያን መታመንን ስለምን ፈቀድኩት?
እኔ ቀድሞውንም ተናግሬያለሁኝ። እኔ እኮ እንዲህ ብዬ ጥቅልል ብዬ የገባሁት የአብዩ መንፈሳቸው ጤናማ ስለሆነ ነው እንጂ በፖለቲካ ውሳኔ ላይ ሞገደኛ ነኝ። እንደ እኔ እስከዚህች ደቂቃ ድርስ  ለማውያን ነኝ ያለ ማንም የለም ከእኔ በስተቀር። ኦህዴድ አገር የመምራት አደራ የመቀበል ብሄራዊ አቅም አለው በፖለቲካ አደረጃጃቱም አብረው የሚሠሩትም ጠንካሮች ናቸው ያለ የለም ከእኔ በስተቀር።

ኦህዴድ ጭንቅላት ብቻ ሳይሆን አዕምሮም አለው ያለ ማንም የለም ከእኔ በስተቀር። ስለ ኦህዴድ መንፈስ፤ ስለ አዲሱ ለውጥ ከእኔ በላይ በተከተታይ በቋሚነት የጻፈም የሞገትም የለም ከእኔ በስተቀር። ለዚህም ነው ቀንበጥ ብሎግን ሥራ ያስጀመርኩት እንጂ ስሙ ተለጥፎ ከቆዬ ወደ ሁለት ዓመት ገደማ ምንም ሳይሰራበት ምድረ በዳ ነው የነበረው። ስሙ ብቻ ነው የነበረው። 
ስለምን ለመወሰን አላመናተሁም? ይሄ ሁሉ ከመምጣቱ በፊት ዶር ምህረት ደበበን፤ ዶር አብይ አህመድን በፍቅር ዙሪያ የታወከን መንፈስን በማጠብ እረገድ አስቀድሜ ስላጠናሁዋቸው። መንፈሳቸው ልዩ ሆኖ መንፈሴን አበቀለው።

እኔ በሥጋዊ ገጠመኝ አይደለም እኒህን የአፍሪካ መሪ የማዬው። በፍጹም መንፈሳዊነትን ነው የምከተለው። ለዚህም ነው ለውጪ አገር መንግሥታት ከማቀርበው፤ ለፈጣሪዬ ከማቀርበው አቤቱታ በስተቀር ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቅ አንድም ቀን አቤቱታ አቅርቤ አላውቅም። በፍጹም። ባምናቸው ነው አቤቱታ ያቀርብኩት። እርግጥ ነው አንጠርጥራቸው የሚሉ መንፈሶች በግልም ይላኩልኛል። ግን እኔ አልቻልኩም ለመጠርጠር፤ ጎደለ የምለውን፤ ክፍተት ነው የምለውን ግን እሞግታለሁኝ። እራሱ "የሽግግር መንግሥት፤ የ አሁኑን የተጽዕኖ ፈጣሪ ጥምር መንግሥት"ለሰከንድ ለመንፈሴ አላስጠጋውም። ስለምን ቅንነት አገሬን እንዲመራ ስለምሻ ብቻ፤ ያጠናው ፍቅር አይደለም ቅንነት ነው። 

እምነቴ እንዳ ሌላው አይደለም፤ ገጥ ለገጥ በመገናኘት፤ እጅ በመጨበጥ፤ አድራሻ በመለዋወጥ አይደለም። እኔ ሁለት ጊዜ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን አግኝቻለሁኝ። ግን አደራሻቸው የለኝም። ምን ያህል እንደተጎዳሁ ደግሞ ንጹሃን ያውቃሉ ሲታሰሩ። እኔ በማይበት መንገድ እኔን አለማዬት ነው የሰው ችግር። 
 መታመን ግን ሲፈቀድልህ ብቻ ነው። ስለዚህ የሚሆነው ሁሉ ከፈጣሪ ነው ብዬ አስባለሁኝ... 

ማመንም ሲፈቀድልት ብቻ ነው። መታመን ታማኝነት ቢሰጠንም መሆን ካልተሰጠው አይቻለውም። መጠራጠር መታመንን ይውጠዋል። ይህን ዘመን ለማዬት የሰሞናቱ ታምራት ረቂቅ ነበር። ከሌላው ይህ ማስተዋል ኑሮት ይኑር አይኑር አላውቅም። የኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ሊቃውንት በፍጹም ልቦናቸው አብይን አመኑት። ታማኝነትን ታማኝ በመሆን ነው እምንገልጸው። ከውስጥ ከሌላ በ አንዱ ብታመልጥ በሌላው ይፈሳል ... መንፈሱ ያዋኪው አንድ አይነት ነው እና ... 

ቅዱሳን አባቶቼም እምነታችሁ ሙሉ ይሆን ዘንድ እለምናችሁአለሁኝ። አውቃለሁኝ የቅድስት ቤተ ክርስትያንችን ግለት ፖሊሲያዊ እንደሆነ፤ የፖሊሲ ግላት ሥርዓት ከተዘረጋ እመኑኝ ቅንድስት ተዋህዶ እኩል ትሆናለች። ልጆቿም በዬትኛውም የሃላፊነት ቦታ የተገለሉ ስለመሆኑ ከዚህ ዘመን በላይ ምስክር የለም። እሚያስደነግጡ ነገሮች ሁሉ ታያላችሁ። በፍጹም ሁኔታ ከዘር በላይ ሃይማኖታዊ ግለትም እንደነበር አሁን ቁልጭ ብሎ እዬታዬ ነው።

የሆነ ሆኖ ትናንትን ረስቶ ዛሬን አዲስ አድርጎ ለመጀመር ሞትም ከሆነ ሄዱና ሙቱ ሰማዕትነት ነው። በመሬታችሁ ጠረናችሁን አግኝታችሁ ሙቱ። ከዚህ ክብር በላይ ሌላ ክብር ስሌለ። መነኮሰ ደግሞ ሞተም ስለሆነ ወደ ባዕት ለመሄድ ከተወሰነ ቀን መቀጥሩ ቂም መቋጠር ካልሆነ በረከት አያስገኝም። በፍጹም። በረከታችሁን፤ ብፃአታችሁን፤ መቀደሳችሁን ለጸላዬ ሰናይ አሳልፋችሁ ባትሰጡ ምኞቴ ነው። ክፍት ነገር ካለ ነገር እዬተሰነጠቅ የታጠበው ህሊና ቁርሾ ያበቅላል። አዋኪ መንፈሶች ምን ሥራ አላቸው፤ አንዱን አሰናክለው ሲሳካላቸው፤ ሌላው ሲያቅደው ደግሞ በ አዲስ ገበር ከች ይላሉ። ይህቺን የክብር ቀን ጥላሸት ለመቀባት አሁን በሩን ከፈታችሁ። በዛቸው ቅጽበት የአብዩ መንፈስ ተጎድቷል። ቅደስት ተዋህዶ ይህን ቅን ልጇን ማስከፋት አለባትን? ትዘዘኝ የሚላትን? ግፍ አይሆንምን?፡ 

  • ·       ወርቅ ከቀለጠ ይፈሳል… ዕድል ቅፅበት ናት?


የለማ ቡድን አመናቶ ቢሆን ኑሮ ዶር አብይ አህመድን ወደፊት ለማምጣት ይህ የዛሬ ሐሤት አይታይም ነበር። አፍሪካን እንዴት ደስ እንዳላት ሚስጢር ነው። ዕድል አንዲት ጊዜ ናት። ወርቅ ከቀለጠ ይፈሳል …. ብዙ ሰው በትዳር ዓለም ፈጣሪ የፈቀደለትን ይጋፋ እና ሌላ ሲያስብ ባልሆነ ሁኔታ ህይወቱ ባክኖ ይቀራል። ብዙ ሰው ከእናትም በላይ፤ ከአባትም በላይ እጅግ ንጹህ ፍጥርት ጓደኛ ፈጣሪ ይሰጠው እና ቁሳዊ ሆኖ ያን ያጣል። በመንፈስ የሚሞግትለትን፤ የሚመርመጠመጥለትን ጉዳዬ ሳይለው ይቀርና ያ ሞገድ ካመለጠው በሆዋላ ደግሞ ሌላ አዲስ ምልምል ልመና ይገባል። ያኛው ግን ነፃ መንፈሱን ነበር የሸለመው። የተሰጠውን አለማወቅ መበደል ነው። ከዚህ በላይ ክብር ተዋህዶ በዘመኗ አግኝታ አታውቅም። ይህ ለ ዓለም ህዝብም አዲስ ክስተት ነው። ከፈጸማችሁት፤ አብራችሁ ለመሄድ ማቄን ጨርቄን ከሌላ።   

እድል ቅጽበት ናት። ካለፈች አትመለስም። ለዚህች ሰከንድ እንኳን ፈጣሪ ተከፍቷል ብዬ አስባለሁኝ። ሰውኛውን ተውት።

ቅን መሪ ኢትዮጵያ ኑሯት አያውቅም በፍጹም። ቅን ሊሂቅ በሙሴ ደረጃ አልነበረነም። ከቅንነት በላይ የችግር መፍቻ መሳሪያ የለም። ብዙ ሰው ፍቅር ይላል ፍቅር ሰጥቶ ቅንነት ከሌላ አይሆንም። የ ኢትዮጵውያን ችግር ቅንነት መንጠፉ ነው።  

አብዩ ቅን ነው። እንደ ሰው ሰዎች ይጠራጠሩታል፤ እኔ ከእነዛ ወገኖቼ በእጅጉ ማህብርተኛ አይደለሁም። ለዚህ ነው አትንኩት እያልኩኝ ፊት ለፊት ስማገድ የኖርኩት። ምክንያቱም አብይ ከእግዚአብሄር ነው። ምርቃቱን ካለወቅንበት ይወሰዳል። ወደ ለመድነው ጉድጓዳዊ የመቃብር ኑሮ እንከትማለን። ለዬዘመኑ አጀንዳ መሆን የሚሹ ሰዎች አሉ። ያ የአጀንዳነት ሚዲያዊ ትኩረት ስንቃቸው ነው። ካለዛ መኖር የደም ሥራቸው አይንቀሳቀስም ነዳጃቸው ነው ... 

እነሱ የሥጋ ሰዎች ናቸው። የጋህዱ ዓለም ሰዎች ናቸው። መንፈሳዊ አባቶች ግን ከዚህ ሃሳብ በላይ መሄድ አለባቸው። የንስርን ያህል በከፍታ ሁሉንም ነገር ከፍ ባለ ዕሴት ማስተዋል፤ መመርምር ይገባል።

ይህ የተባረከ ሰሞን  ለቅዱሳን አባቶቼ  የተሰጠ በመሆኑ እወቁበት። አሜሪካ መኖርን ለምትፈቅዱ መመለሱን ማን ይከለክላችኋዋል? ይሄው ዶር ካሳ ከበደ እኮ ተመሰሉ። እኔ እንደ ተዋህዶ ልጅ የሚሰማኝ ከገደሏችሁም የመንግሥስት ሽፍቶች  ይግደሏችሁ። ጥሪያችሁ ይህ ከሆነ። ፍርሃት ለእኛ ሥጋ ለበስ ለሆነው የገሃዱ ዓለም  ዬዘመኑ ሸቀጦኞች እንጂ ለእናንተ ሊሆን አይገባም። የፖለቲካ ሊሂቃን በአደብ ሊዩት የሚገባ ሊኖር ይገባል። አብሶ በጥርስ የተያዙት።

ነገር ግን መነኮሳት ሞተን የተሸከሙ ሰማዕት ግን እግዚአብሄር ልጅ ሰጥቷቸው ከኢትዮጵያ ድረስ መጥቶ ይዣችሁ ልሂድ እያለ ስለምን ይገፋል? ስለምን  የአብይ መንፈስ ይዘንባችሁ? ቀድሞ ነገር እኮ የአብይ ጉዞ ቀድሜም ጽፌዋለሁኝ ለዚህ ተልዕኮ ነው እኮ፤ ጥሪው የመንፈስ ቅዱስ ነው። እናንተን ይዞ ለመሄድ ነው ሌላው ትርፍ ነው። … 

ትዮጵያም፤ አፍሪካም፤ ዓለምም ያጡት ነገር አለ። ያ መልክ ካልያዘ ይህ መከራ ቀጣይ ነው። ማን ያውቃል ቅዱሳን ሰማዕት አባቶቻችን ባዕታቸውን በረገጧት ዕለት ልብ ለነሳቸው ሁሉ ልባቸው ይመለስላቸው ይሆናል? ልብ የሚታደል ቢሆን ልቤን ሳልስት ለሁሉም ባደልኩኝ ነበር። 

የፈጣሪን ጥበብ መመርመር አይቻልም? ፈጽሞ? ማን አቅም አለውና? ወርሃ ክርምት ትንሳኤ የታወጀበትን አምክንዮ ፍሬ ነገር ማን ያውቀዋል ሚስጢሩን፤ ተደሞውን ዕድምታውን? 

ፍልሰቲትን ሱባኤዋን የዘንድሮን በወል እንዲሆን ልዑል እግዚአብሄር የወሰነበትንም አናውቀውም? ቀጣዩ ዓመት 2011 ሁሉም አባቶች በአንድ ሱባኤ የማሳለፍ ዕድል ይኖራቸዋል ብላችሁ አትሰቡት? ከማህል እምናጣው ቅዱስ ሊኖር ይችላል? ፈጣሪ ያሰበውን አናውቀውም። እዚህ ሲዊዘርላንድ በቀደመው ጊዜ የአሁኑን አላውቀውም ጋብቻ በቅዱስ ቁርባን ብቻ ነበር የሚፈጸውም።

እናም ሁልጊዜ የሥርዬት ሰሞናትን፤ የንስሃ ሰሞናትን ሙሽሮቹ የሚፈቅዱት ፆመ ፍልሰቲትን ነው። የተለዬ ጸጋ አለው። የህፃናትም ፆም ነው። „ህፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው“ አይደለም የሚለው ወንጌሉ፤ ወደ ቅዱሳን የህጻናት የሱባኤ ቀን በባዕት ለመታደም ማምራት በራሱ ለተዋህዶ ትውፊትም መሰረት ነው። ካለ ትውልድ ሃይማኖት ምንም ነውና፤ 
ሌላው የቀደመውን ሁሉ እርሱት። ለዚህም ነው አብይነት የተሰጣችሁ። በፈተና መኖር ደግሞ የክርስትና ሥጦታ ነው። „ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረች“ እንዳይሆንብኝ እንጂ ፈተናን ለምናችሁ አይደለምን የምታገኙት። ፀሎታችሁ ፈተናውን ምነው አዘገዬኸው አይደለምን? ይህ አልነበረምን የቤተክርስትያናችን ትውፊት?  ለፈተና ስለምን ዳታ ታበዛላችሁ? አይደለም እናንተ የኤርትራ ቅድስት ተዋህዶም በነፃነት ዕለት በታቀደው የሚሊዬነም አዳራሽ ታዳሚ እንድትሆን እኔ አሻለሁኝ።

እኔ እኮ በኤርትራ መንግሥት በጣም ተጠራጣሪ ነበርኩኝ። አሁን ግን ቅንጣት ታክል ያ ጥርጣሬ የለብኝ። ተኗል በኗል። ገና ልዑኩ ቦሌ ሲገባ ፈጣሪዬ የነገረኝ ነበር። ከኢትዮጵያ መንግሥት በላይ እኔ ለፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ልዑክ እጨነቅ ነበር። ስለምን? የሆነው ሁሉ ከእግዚአብሄር ስለሆነ። ሰሞኑን ከአቶ ነአምን ዘለቀ አንድ ጹሁፍ አንብቤያለሁ። አዝናለሁኝ።

ወደ ኋዋላ ሊመለስን የሚጋባ ታሪክ ሊኖር አይገባም። ያማ የጦርነት፤ የቁርሾ፤ የቂም፤ የደም፤ የነገር፤ የጭቅጭቅ ነበር። "ካሳ" እሱን እርግፍ አድርገን ትተን ያን ሳቅ እንዲቀጥል መታተር ያስፈልጋል።  እኔ ስለቀደመው ነገር ትዝ ብሎኝም አያውቅም። በሙሉ ልቤ ነው የተቀበልኩት።

ቀድመን ተናግረናል ለሚሉት ፖለቲካኞች ያን ከጋህዱ ዓለም ፍላጎታችሁ ጋር ተማክሩ። የሆነ ሆኖ ከገሃዱ ዓለም የፖለቲካ ትርፍ እና ኪሳራ ሳይሆን መንፈሳዊ በሆነ የመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን የሚገዛው መንፈስ ነው ሚሊዮኑን የሚገዛው። ያሸነፈውም፤ ለድል የበቃውም ይህ ቅናዊ ጉዞ ነው። መንፈስ ሲገዛ በተለያዬ ዘመን እኮ አይተናል። 

እኔ ደስታ ወደኛ ሲመጣ ለምን መገፍተር እንዲመያስፈልግ አያገባኝም? እጅግ ነው የማዝነው። „ማሰተዋል“ ብዬ ስላሳቸው ስለ አቶ ነአምን ዘለቀ  ቤተሰባዊ ተጋድሎ ጥብቅና ቆሜ ጽፌ ነበር። ያ ልዩ የሆነ መታመን ነበር። ግን ያ መታመን በዬጊዜው ሲዝግ እዘናለሁኝ። ከስሜት ወጥቶ የ ኢትዮጵያን የምሥራች፤  አፍሪካን ዜና ማደመጥም ቅንነትን ይሻል። ቅብዕ የፈጣሪ ነው።  

ቅድስት ቤተክርስትያናችንም ማድረግ የሚገባት ሰናይን መግፋት የለባትም።  ዲያቢሉስ ትናንትም ነበር፤ ዛሬም አለ፤ ወዲፊትም ይኖራል። እግዚአብሄር አምላክ ሥራውን የሚሠራው በሰዎች ዘንድ ሲሆን፤ ዲያቢሎስም በሰው ነው ሰይጣናዊ የጥፋት እና የተንኮል ተግባሩን የሚከወነው። "ህልም ተፈርቶ መተኛት" እንደማይቀረው ሁሉ ክፉዎች ተፈርተው የሚሊዮኖች ክብር በዚህ ሰው ሰራሽ ቀመር ሊተጓጎል፤ ሊራዘም አይገባም።

የኤርትራ እና የኢትዮጵያን ጉዳይ ታች ወርደው አፈጻጸም ላይ ዓለም ዐቀፉ የህግ ባለሙያ ዶር ያዕቆብ እንዲያ ሲያስታምሙት ጭንቅን ሲያውጁ ፈጣሪ የሠራው ታምራት ግን ሌላ ነው። ወደፊትም እንዲህ ነው። ከእግዚአብሄር የሆነ እና ከሰው የሆነውንም መለዬት ተስኖን ነው የምንታመሰው። በፖለቲካውም፤ በሚዲያውም መንደር የሆነው የተባጀው ይሄው ነው። መስቀሉ ከአንገት አላለፈም፤ ቁራዕኑም እንዲሁ።

ለዚህም ነበር እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ፈጣሪያዋን ስለምን አትታረቅም ከዲያቢሎስ ጋር፤ ይህን ያህል ነፍስ በእሱ  ምክንያት በገሃነም ከሚቀቀል ብላ የሞገተችው። ይሄን አሸንፎ መውጣት ደግሞ የራስ በእጅ ያለ ነፃነት ነው። ክፉ ማሰብን መተው። ቅን መሆን ብቻ ነው ሚሊዮን አብይ የእኛ ያለው። 

ክፉዎች ላይተዉት ይቻላሉ ዲያቢሎስ ስላለ፤ ግን ክፉነትን ሳንተው ክፉዎች አልተውም ብለን መወቀስ አንችልም። ፈተናው ይሄው ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ የክፉነት ምንጭ ነው፤ ግን እሱን የሚታገሉት ሚደያዎች ሆኑ የፖለቲካ ሊሂቃን እና ተከታዮቻቸው ግን ያንኑ ይፈጽማሉ።

ወያኔም ተሰድን ያሳድደናል፤ እነሱም ተሰደን ያሳድዱናል። ልዩነት የለውም ሁለቱንም የሚያገናኛው ሃዲድ የክፉነት ማህበርተኝነት ነው። አሁን ሰሞኑን ስለሚዲያ ነፃነት እና ሰለመሰሉ አብይ ሲሞገት ሰምቻለሁኝ፤ መቼ ለእኛ ከዚህ ነፃነት ዴሞክራሲ፤ ፍትህ ተሰጠንና። 

"የሽግግር መንግሥት" ቀድሞ ነገር የዜግነት እኩልነት መቼ ተሰጠንና ነው አሁን ሦስት ወር ያልሞላው እሸት ለዛውም ከማህበረ ደራጎን ጋር ፊት ለፊት የተረመጠ መንፈስን፤ ህውከትን አደራጅተን እራሳችን እዬአመስነው ሰላሙን ነስተን ከዛ መቆጠብ ሲሳነን ነው እኮ ያን ህዝብ ጥሶ ማገዶ የሆነው ስለ አብይ ፍቅር። አሜሪካም የታዬው ይሄው ነው። ህዝብ ጥሶ እዬወጣ ነው የሴራውን መረብ፤ የሸሩን መረብ። ቢያንስ ለዚህ ክብር ሊነርን ይገባል። እራሳችን ከተከዝነብት የማለት ብቻ  ድርድር ሳንሻገር ወቃሽስ፤ ከሳሽስ ጠያቂስ የሚኮነው እንዴት ነው? መደርከኑን ማይኩን እምንመኘው ያው አጅንዳ ለመሆን ነው። ይህም ተሰጥቶ ታይቷል እድሜ ልክ ታቱ ... 

 ይሄው ታዬ እኮ ፍስሃውን ሲያገኝ እኮ መንገድ ላይ አድሮ ነበር ደጋፊው ወረፋ የያዘው። መጀመሪያ ያሰራችሁን መንፈስ ፈቶ አብይን መሞገት መብት ነው። „ሽግግር መንግሥት“ የጸላዬ ሰናይ መንፈስ ነው። አንፈልግም! አብይ ሁሉም አለው ለሁሉም ችግር መፍትሄያችን ነው። ቁልፍ!

እራስህ እንኳን ሳትፈታ በል የተባልከውን እንደ ዳዊት ስትደግም እዬዋልክ ሞገትኩት፤ አፋጠጥኩት ወዘተ … መለናቆጥ …  ራስን ያላሸነፈ መንፈስ ወዘተረፈውን  የኢትዮጵያን ችግር ሊያሸንፍ ከቶውንም አይችልም። ንፁህ ቅን መንፈስ ሲያገኝ ቸሩ ህዝብ ነፃነቱ ይሄ ነው። የሰማይ ላይ መና ለማግኘት ወገብን ታጥቆ ሞግቶ እና መሬት ላይ አፈር ድሜ ግጦ ሰርቶ መንበርን ማደላደል ነው …

  • ·       መስቀል ፈተናን ከልተጋፈጠ ማን ፈተናን ይድፈረው?
ወደ ቀደመው እንደ አቦው ፈተናን ያላሸነፈ፤ ፈተናን ፈርቶ የተሸሸገ የሃይማኖት መሪ እንዴት መስቀለን ይይዛል? መስቀል እኮ በትንፋችን ልክ ፈተናን መሸከም እኮ ነው። ፈተናን ታግሶ ጽናትን መቀለብ፤ በጽናት ውስጥ በረከትን ማፈስ። ፈተናን የፈራ የሃይማኖት አባት መስቀልን መተው አለበት ማለት ነው። 

ስንት ዲያቢሎስን አፈር የሚያስግጥ መስቀል ይዛችሁ ሰማዕት አባቶቼ ዛሬ ለተፈቀደችላችሁ ቅደስት ቀን ስለምን ወደ ኋዋላ ለማለት ፈለጋችሁት? መስቀልን ይዛችሁ? የስለት ልጅ ሰጥቷችሁ አማኑኤል? "አታምስግኑኝ የፈጣሪን ምስጋና ክብር ለእኔ አትስጡ እኔ ፍጥረት ነኝ" የሚል ዝቅ ያለ ትህትና ያለው ልጅ ሰጥቷችሁ ስለምንስ ታመናታላችሁ?

ኢትዮጵያ እኮ እስረኛ ናት። እስረኛዋን አገራችሁን ለማስፈታት እናንተ ከእስረኛው የቆዬ የቂም እርሾ መጽዳት ግድ ይላል። የዕውነት። ታስሮ እስረኛን ለማስፈታት መትጋትም ሌላው ድርብ ሰማዕትነት ነው። ከሁሉ በላይ የልዑል እግዚአብሄር ሐሤት ሲባል እዮራዊ እልልታ ሲባል እኔ እንደ ተዋህዶ ጽኑ ልጅነቴ ከአሜኑ ጋር በአንድ አውሮፕላን እንድትሄዱ ነው ምኞቴ። ያለገልግልኳችሁ ሊመስል ይችላል።

አባቶቼን ሲያገለግል የኖረ ልጅ ባልወልደውም ፍዳዬን ከፍዬ አሳድጌ ሰጥቻችሁአለሁኝ። ታውቁታላችሁ ኮሎንቦስ ኦሃዩ ያለው ታናሽ ወንድሜ የእናቴ ልጅ፤ ልጅነቱ ለእናቴ እና እጅግ ለምሳሳላቸው አባቴ ለአባባ ነው። ግን እንደ ዓይኔ ብሌን በተለዬ ፍቅር በስስት ያሳደኩት ነው። 

ለእኔ ምንም አያደርግም፤ ለእናንተ ግን ሁለማናችሁ እንደሆነ አውቃለሁኝ። ለእኔ ጊዜ የለውም ለእናንተ ግን ጊዜው ብቻ ሳትሆኑ ነፍሱ ናችሁ፤ እሱን የሰጠቻችሁ፤ ያሳደገችላችሁ ይህቺው ጠያቂም አቋጣሪም የሌላት ሥርጉተ ሥላሴ ናት። ስለዚህ ልታደምጡኝ ይገባል።  

ሌላው በህይወቴ ሙሉ እንደ ብላቴው ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን የምወደው፤ የምሳሳለት፤ ላዬው የምፈቅደው ቢኖር ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ርቅረዮስ ነው። መንፈሴ ናቸው። እሳላቸው አለሁኝ ግን እኔም ሳላያቸው ነው የሚሄዱት። እዬሩሳሌም ከምሄድ ቅዱስነታቸውን ባዬ እምርጥ ነበር። ለ እኔ እየሩሳሌሜ እሳቸው ናቸው።  

ግን ካለሱ ፈቃድ የሚሆን አንዳችም ነገር የለም። ቅዱስ አባታችን አቡነ መልከጻዲቅም ልዩ የሆነ የሚስጢር ማህደር ስለሆኑ እሳቸውንም ባገኝ መንፈሴ ሐሤት ያገኝ ነበር። ስለዚህ ጨክኜ አገር ይግቡ ስል እያለቀስኩኝ ነው። እኔ ልቀደም እችላለሁኝ ለዓይነ ሥጋ ሳልበቃ ላልፍ፤ ግን ለዛ መንፈሳዊ አባት ላጣ ለነጣ ምህበረ እልፍ ነፍስ ምዕመናን ሲሉ መሄድ ይኖርባችዋለ ብዬ አስባለሁኝ። 

ቤተ ክርስትያናችን ከፈተና ወጥታ አታወቅም፤ ፈተና ከሌለባት ስለምንስ ተፈጠረች? የቤተክርሰትያን መፈጠረ ፈተናን ታግሳ ማሸንፍ አይደለምን? ስታሸነፍ ካለ ዕንባ ነውን?

ትልቁ ነገር አብሮ የሚሄደው መንፈስ ቅዱስ እዛ የታሠረውን ዲያቢሎስ ሊያሸነፈው ይችላል። አውሮፕላኑም ይቀደሳል። አየር መንገዳችን እራሱ እኮ የህውከት ምንጭም ነው። እዛም ውስጥ ዲያቢሎስ ታሥሮ አለ፤ ፍቅረ ንዋይ አድሎ፤ ጭቆና፤ ዘማዊነት አለበት።

ይልቅ መሬቷን ስተረግጧት ጎንበስ ብላችሁ አፈሯን ስማችሁ ዓወዱን ጸበል እርጩት በትህትና የማሳስበው። አትርሱ ጸበል ይዛችሁ ሂዱ በመንፈስም ቢሆን። አስተርዮ በደረሰበት ድፍረታዊ እርምጃም ቅዱስ ሚኬኤል ሰይፉን ይዞ ይጠበቃል፤ ቅዱስ ሚኬኤል እንደ ተቆጣ ነው፤ እሱም ፍጥነቱን ሰላም ላኪውን የወሎውን ሰማዕትነት አስታውሱት፤  ቃና ዘገሊላን እሰቡት „ጣና ኬኛ፤ ግዮን ኬኛምን“ እስቡት የሆነው ሁሉ ከእግዚአብሄር ስለመሆኑ አትጠራጠሩት አትፍሩትም። ፍቀዱት ተቀበሉት። ትእዛዝ ግን አይደለም ትቢያ ላይ ሆኜ ግን ንገሪ የሚለኝን መንገር ግዴታዬ ነው። የድርሳን አንቀጻት ተቀርፀውለት ለአብንት ት/ ቤት ሊሆን የሚችል እድለ ገድል ነው መዳፋችሁ ላይ ያለው። 

ጽዮን ማርያም አባቶቿን በእቅፏ እንደምትቀበል ለቅንጣት አልጠራጠርም። ዶር ደብረጽዮን እና ማህበራቸው ይፈርሳል፤ ያልፋል፤ አፈር ይሆናል፤ ግን ቅደስት ተዋህዶ ለዘለዓለም ትኖራለች። ምድራዊ መንግሥት ፈራሽ እና ተሰሪ ነው። ሰማያዊ መንግሥት ግን ዘለዓለማዊ ነው፤  

ለቅድስት ቤትክርስትያን ሲሉ በክብር አገር ገብቶ ባሩድን፤ ፈንጅን፤ ሽጉጥን፤ ቀልሃን ለማስተናገድ መቁረጥ ሰማያዊ ጸጋ ነው። እናንተ የሥጋ ሰዎች ሳትሆኑ የመንፈስ ስለሆናችሁ … መንፈስ ቅዱስም አብሯችሁ ስላለ ሞትን መፍቀድ „ይበቃኛልን“ ከወንጌላዊው፤ ከሐዋርያዊው፤ ከሰማዕቱ፤ ከመምህሩ  ቅዱስ ጳውሎስ ህይወት መቅዳት ለአሁኑ ጊዜ እጅግ ያስፈልጋል።

በአማላክ መታመን ከሌለ አሜሪካን አገርስ ምን ዋስትና አለውና? ከሦስት ዓመት በፊት እኮ አውሮፓ ቀውጢ ነበረች? ወጥተን መግባት ህልም ነበር። ከዚህ በተጨማሪ በሰማይ ቁጣ በመሬት ራድ፤ በውሃ ሙላት፤ በዓውሎ በወጀብ የሚሆነው አይታወቅም በዚህች ቅጽበትም፤ ነፍሳችን ቋጥረን አልያዝናትም …  
ለሞት ቀነ ቀጠሮ የለውም። 

አገር ሄዳችሁ ልትሞቱ ከፈቀደው፤ ለዛ ከሆነ የተፈጠራችሁት ሰማዕትነቱን በሐሤት ተቀበሉት። የምትታዘዙት ሳይሆን እዘዙኝ የሚል ልጅ ሲሰጣችሁ ከዚህ በላይ ታላቅ የሰማይ ስጦታ ምን አለና ነው ወደ ፊት እና ወደ ኋዋላ የምትሉት? አልገባኝም፤ እንዲገባኝም አልፈቅድም። ሰማዕታትም አጽመ ፍልስታቸውን እሰቡት።

እኛ ምድራውያን ይጨንቀን መኖርን እንመኛው አርቲፊሻሎች ስለሆን። እናንተማ ስትመነኩሱ አይደለምን የሞታችሁት? ስትመነኩሱ አይደለምን ቹቻ የተራሰላችሁ? ስትመነኩሱ አይደለምን ሰኔል የተሰፋላችሁ? ስለምን ሞትን ትፈሩታላችሁ?

ህዝባችሁን ነጻ አውጡ። ተጋድሏችሁ ሙሉ ይሆን ዘንድ በአፈራችሁት የተጋደሎ ጸጋ ላይም ቀጣይ መከራን ለመቀበል ትጉ። ካለፈተና እኮ አብይነት ከዚህ አልደረሰም። ቂምን ረቶ መሞትም ሰማዕትነት ነው። የነበረው ነገር እኮ ሃይማኖት አለኝ ለማለት እጅግ ያሳፍራል።

እኔ አፍራለሁኝ ከዚህ ያሉ ወዳጆቼ ነጮቹ ትንሳኤ ልደት ሲመጣ ሲጠይቁኝ መልስ አልነበረኝም። አንዲት ነጭ ወዳጄ በ2016 ከአርመን የቅድስት ማርያምን አድህኖ ስዕል አስመጣችልኝ። ተስፋችን እኮ ነው ያሳጣችሁን። ለዚህ ነው እኔ በቅድስና ቤቴን ዘግቼ እምኖረው።

እኔ አንድ ልብ እንጂ ሦስት ልብ ስሌለኝ፤ አንድ ማተብ እንጂ ሦስት ማተብ ስሌለኝ። ዶር አብይ አህመድ ሁልጊዜ ተዋህዶ ከሁለት ተከፍላ ሲሉ አዳምጣለሁኝ። አይደለም፤ ከሦስት ነው የተከፈለችው። ከዚህ በርን የሚባል ቦታ አለ ርዕሰ መዲናዋ ነው ለሲዊዝ እና ከዛ ሦስት የአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስትያን አለ።

አንዱ በውጪው፤ ሌላው በአገር ቤቱ፤ ሦስተኛው ደግሞ የማህከል ነው። መባውም መንፈሱም እንደዛ የተከፈለ ነው። እና እኔ ቤቴ ቁጭ አልኩኝ። እንደ እውነቱ ከሆነ ለእኔ ከዙሪክ ቅድስተ ማርያም በጽኑ ካገለገልኳት በላይ ሌላ ምንም ትዝ የሚለኝ አለነበረም።

ግን አልሆነም። ባለመሆኑ ደግሞ የስደቱን ዘመን እጅግ ገርጃፋ የፈተና ወቅት አድርጎታል። ስለምን? ስለቃማችሁት ሰናያችን። አገር ቤትም እንደዛ ዕድሉ ቢኖር ሦስት ይሆን ነበር። በመንፈስ ግን ውጪ ካለው ጋር ነው የነበሩ ብዛት ምዕመናን ነበሩ ትግራይንም ይጨምራል … አሁን አንድ ሲሆን ገነትን ማግኘት ማለት ነው። በቃ … ለዚህ ቅድመ ሁኔታ አያስፈልገውም። ፈቀደ እኮ ልዑል እግዚአብሄር። አገልጋይነቱ ለእሱ ከሆነ ይሄ ዕድል ሊያመልጥ አይገባም።

  • ·       ይኔ።
ሌላው ድንጋጤዬ ሰማዕቱ አባቴ ዓይኔ መንፈሴ ነፍሴ ሰብዕናቸው ነው እኔን እንደዛ የሚያሰኜኝ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቀርዮስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ቁመው የሚሄዱ ይመሰለኝ ነበር። በጋሬ እዬተገፉ ሲመጡ ውስጤ አዘነ። ዕንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩኝም።

በሌላ በኩል በፎቶ ሳያቸው እና እዚህ በቴሌቪዥን ቅርብ እድርጌ ሳያቸው ጸጋቸው፤ ማህባቸው፤ ግርማቸው፤ መንፈሳቸው፤ ረድኤታቸው እጅግ ከጠበቅኩት በላይ ወዙ መንፈሱ አንዳለ ነው። ማህባቸው ፍጹም ልዩ ግርማ አለው።

ይብረኩ ይህን የመሰለ አገልግሎት ሲያበረክቱ ለነበሩ የተዋህዶ ልጆች። ይህ ረድኤት ይህ ማህባ ይህ ፍጹም የሆነ በረከት ኢትዮጵያ ማግኘት አለባት  በአስቸኳይ፤ ነገ የእኛ አይደለምና። ነገ ስለሚሆነው አናውቅም።

ከአብዩ ልዩ ትህትናዊ እንክብካቤ ጋር አብረው ጎን ለጎን ተቀምጠው መሄድ አለባቸው። አብዩም ይባረካል። ለምርቃት እኮ ነው የተፈጠረው። ይህ ለዓለም ሰላም ወዳድ ህዝብም ታላቅ ጸጋ፤ ታላቅ በረከት፤ ታላቅ የህይወት የምሥራች ዜና ነው። 

ደስታችን ፍሰሃችን ሰናያችን ሐሤታችን እባካችሁን አትቀሙን። ሐሤት የመንፈስ ነው። ከአብዩ ጋር አብሮ መሄድ በራሱ ትልቅ ልዕልናዊ ክብር ነው። ስለምን እግዚአብሄር ስላከበረው።  የአሮን በትር ስለሆነ። በኢሜል እዬመጡ ሰውን ወደ ተሳሳተ መንገድ እዬመራሽው ነው አቁሚ ሲሉኝ የነበሩ ነበሩ።
ግን ለእኔ የታዬኝን ማንም አልታዬውም ነበር። 

ለእኔ መንፈሱ የቀረበኝን ያህል ማንም አልቀረበውም ነበር እና። አሁንም ተስፋዬ ሙሉ ነው ዲያቢሎስ ተሸንፎ አፍሪካ በመሪዋ ከበለጸጉት አገሮች ተርትራ በመንፈስ እኩል የምትሰለፍበት ጊዜ ይመጣል። በመንፈስ በሥነ - ልቦና ነው ያልኩት።  በዲታነት አይደለም። ኢትዮጵያም የሰው መፈጠሪያነቷ ይበልጽጋል ዕውንም ይሆናል።

 መንፈስ ነው የሚበልጠው ከሁሉ። የመንፈስ ልዕልና አፍሪካ ይኖራታል። ለዚህ ደግሞ ቅድስት ተዋህዶ ግዴታ አለባት ይህን ተልዕኮ የማሳካት፤ የታሪኩም ባለድርሻ የመሆን። አሁን ምርጫዋ አንድ እና አንድ ነው ጸጋዋን አሳልፋ ለዲያቢሎስ መሸለም ወይንም ዴያቢሎስን ድል ነስታ ማቄን ጨርቄን ሳትል ወደ ባዕቷ መትመም …

  • ·       ርዓት ለድርድር?
ሌላው ሥርዓት ነው። ስለምን እንደ ምድራዊ እንሆናልን? ስለምን? የዲሲው የሰሞናቱ ህውከት ሲገርመኝ ነበር? ምንድን ናት ይህቺ የከንቱ መናህሪያ ዓለም? ምንድ ናት ይህቺ ፍርስ ዓለም? 100 ሚሊዮን ህዝብ ጠግቦ ሳያድር እኛ ለቀጨር መጨሬው እንታመሳለን? 

አሁን የተዋህዶ ሴሪሞኒ ሰማያዊ እዬራዊ እንጂ ምድራዊ አይደለም፤ ሊሆንም አይገባም። የአዲስ አበባን ህዝብ ማን ቀሰቀሰው 5ሚሊዮን ህዝብ ሞትን ፈቅዶ ሰኔ 16 ቀን ሲተም። ትናንት ሀምሌ 19 ነጠላቸውን ዘቅዝቀው አብዬት አደባባይ ላይ ሲያለቅሱ እናቶች ሳይወለዳቸው ለኢንጂነር ስመኘው ነበር።

ከዚህ በላይ የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ትልቁ ጸጋ አታውቁትም እንጂ በመንፈስም፤ በአካልም ማደራጅት እና ማደራጀት ነው። ማህንዲስም ናቸው። ብዙ ጸጋ ነው ያላቸው። ከመምጣታቸው በፊት ይህን የቤት ሥራ  ቀድመው ሰርተው ነው አደላድለው ነው የሚመጡት። አትጠራጠሩት። ይህን ደግሞ  የኤርትራን ጉዳይ ቀድመው ያለቁ መሰናዶዎች አሉ ብዬ ነበር የባድመ ዕድምታ በሥርጉተ ዕይታ ስጽፍ። 

እሳቸው ሲረከቡ የነበረው የጠ/ ሚር ቢሮ እና ዛሬ በተለዬ በረከት ተለውጧል። እውነት ነው የምላችሁ ብብዙ ተቀይሯል ብዬ አስባለሁኝ። መንፈሱ እራሱ። አቶ ደመቀ መኮነን እኮ የህዝብ ሃብት ለመሆን አፍታ አልፈጀባቸውም።  ይህ ታላቅ ማስረጃ አይሆንም?

አሁን ቤተሰቦቼ ፎቷቸውን ፌስ ቡካቸው ላይ እንደለጠፉት ሲነግሩኝ ገረመኝ  የአቶ ደመቀ መኮነን እኮ ነው … ለጠፍን የሚሉን።  ሰው የመቀዬር፤ ሰው የማብቃት፤ ብቃትን የማካፈል፤ ህሊናን የማሰናደት ብቻ ብዙ መክሊት ነው ያላቸው … አትቸገሩ ለዛ … እኛም ከዚህ ሻማ እናበራለን … ያን ቀን እኔ በፃዕዳ ልብስ ልክ ቤተክርስትያን ስሄድ እንደምለብሰው ሁለመናዬን አጽድቼ የማከብረው ዕለቴ ነው። ግን ጉዞው ከአብዩ ከአሜኑ ጋር ከሆነ ብቻ። አታቀዝቅዙት፤ የነፈሰበትም አታድርጉት መንሳዊ ሃብቱን። 

ዕውነት ለመናገር ህዝባችን ብሩክ ነው። እማናምሰው እኛው ነን። መንግሥስት ብቻ ሳይሆን በግልም በጋራም አጀንዳ ካልሆን እያልን የምንበጠብጠው ሰዎች የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ መጠዬቅ አለብን። የትም ምድር አልተፈጠረም እንደ እኛ ያለ ቅዱስ ህዝብ። አንዲት አናት ነጠላቸውን ዘቅዝቀው ያለቅሳሉ? „ይዛመድወታል“ የጋዜጠኛው ጥያቄ ነው።  „ወደ ገብሬኤል ቤተክርስትያን አዬሄድኩኝ ሰምቼ ነው ወደዚህ የመጣሁት አይዘመደኝም“ ብለው ነጠላቸውን ዘቅዝቀው ሀዘንተኛ ሆነዋል።“

ጎንደርም አንድ ሾፌር ከአዲስ አባባ መጥቶ ሲሞት ሃዘንተኛው ሁሉ ነበር። እስከዛሬ ያሰከፋነው ይበቃል ህዝባችነን፤ ከእንግዲህ ባናስከፋው ምን አለ ያን ንዑድ ህዝብ?

ባይታደሉ ነው የትግራይ ሊሂቃንም እንዲህ የሞት ፎቶ ይዞ ወጥቶ ሌላ ጠብ፤ ቁርሾ ቂም የሚናፈቀው፤ እንጂ ይህ ዘመን የተፈቀደው ለእኛ ለይቅርታ ነበር … ከኖረው በላይ ነው እኔ ያዘንኩት፤ የሰሞናቱ የመርዶ ትዕይንት በትግራይ አደባባይ … ለእነሱም እንጸልይ ወደ ልቦናቸው እንዲመልሳቸው።

የምህረት ዘመንን ስምረታዊ ለማድረግ ጸሎት ያስፈልገናል፤ የእነሱ እንደዚህ መሆን ነው አሁን አባቶች የተፈቀደላቸውን ጸጋ እንዳይደፍሩት ያደረጋቸው። እንደ ሰው ሲታሰብ ትክክል ነው ግን መንፈስ ቅዱስን ማመን እና የመጣ ቢመጣም መድፈር ይጋባል። ሞት በጉንፋንም በጊንጥ ነካሳም ይሞታል። ነፍሳችን በጨርቅ ቋጥረን አይዛትም። መጠንቀቅ የተገባ ነው። ያተርፋል።  የአሁኑ ዕድል በተለይ አብሮ የመሄድ ግን አንድ ድርሳና ገድል ነው። አንድ የጸሎት መጸሐፍ ነው። ቤተክርስትያናችን ይህን ዕድል ማጠፍ የለባትም። በፍጹም።

  • ·       ሰከንድ ብልሃት አላት።
 … ቀን ሰዓት ደቂቃ ሰከንድ የተሰጣቸው የራሱ ጸጋም፤ ምክንያትም አለው። ብዙ ነገር አላት አንዲት ሰከንድ። ይህን ሊቃውንተ ምህዋር የቤተክርስትያናችን ቀመሩን አያጡትም … አብረው የሚሄዱ ከሆነ አደራውን አብዩ ልጀቻው ይረከባል። እንመነው እምነቱን ሲያጥፍ ደግሞ በረከቱ የተሰጠው ይነሳበታል።
ግን የምህርት መሪ ስለሆነ ሙሴነቱ ይዘልቃል። 

እግዚአብሄርን እንመን ለእሱም እንታመን። በበረከቱ እንመን ለበረከቱም እንታመን፤ ተስፋውን እንመነው ለተስፋውም እንታምን፤ ምርቃቱን እንመነው ለምርቃቱም እንታመን። ሥጦታውን እንመነው ለሥጦታው እንታምን፤ መክሊቱን እንመነው ለመክሊቱም እንታመን።

መታመን መቻልን መቀበል ከተሳነ የሚከፋው የምታገልግሉትም ልዑል እንግዚአብሄር ነው። ድንግልዬ በጣም ትከፋባችሁአለች። አብይ ውሳኔው ጠፈፍ ያለ ቁርጥ ያለ ነው። ደፋር ርምጃ ነው የሚወስደው። ልቡም ሙሉ ነው። ሲከፋውን ያኑ ያህል ስስ ነው። ነገር ግን የሚያደርገውን ያውቃል። የሚያገሉትን ይወዳል። ለሁሉም መጠን እና ልክ አለው። አሳዳጊውን ይባርከው። አሜን!

አብይነት ቆፍጣና ነው። እኔም የቅድስት ቤተክርስትያን የጉዞ ውሳኔውን ሳዳምጥ ከፍቶኛል። እልልታ ይቀጠራል ወይ? ቅዱሳን ሰማዕታት ሊቀ ሊቃውንታት አባቶቼ ሆይ! በመንፈስ እንግዚአብሄርን ጠይቁ - በአክብሮት። እሱ መልስ ይሰጣል። ግማድም ይሆን ሐሤት ቀጠሮ አያስፈልገውም። ለፈተናም ይሁን ለዘላቂ ሳቅ አዶናይን እመኑት። መታመን የሚሰጠውን ዬትኛውም የ ዕውቀት ማዕከል አያጎናጽፍም። 

የፈቀደውን እንደ ፈቀደው መቀብል ነው። እንደ ፈቃዱ ብትሆኑ እኛንም እንደ ፈቃዱ ሁኑ ብላችሁ መስበክን ትደፍሩታላችሁ፤ እናንት ግን ይህ ከተሳናችሁ ምዕመኑ እረኛ አልባ ነው። ማህበረ ምዕመናን የናፋቃቸውን ሰናይ ዘመን እባካችሁን አትንፈጉት? እባካችሁን?

ቅኖቹ ደጎቹ የቻላችሁትን ያህል ፌስ ቡክ ላይ አሰራጩልኝ አደራ! የቀንበጥ ማህበርተኞች ተልዕኳችን ለዚህ ነው። ሳቃችን ዘላቂ ስለማድረግ መትጋት። ኑሩልኝ።

„ፍቅርን ተከተሉ፤ መንፈሳዊ ስጦታንም ይልቁንም
       ትንቢት መናገርን በብርቱ ፈልጉ።“

(የሐዋርያው የቅዱስ ጰውሎስ መልዕክት
   ወደ ቆርንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፲፬ ቁጥር ፩ )

የራስ ባለደራ ሥነ - ግጥም። (29.04.2018)

https://www.youtube.com/watch?v=znuGHNacib0

Ethiopia - ዶ/ር ዐብይ አህመድ ፓትሬያሪክ አቡነ ሞርቆርዮስን ሲያናግሯቸው

ወስብሃት ለእግዚአብሄር።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።