ልጥፎች

ከጁን 23, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አቅል።

ምስል
አቅል። ከሥርጉተ © ሥላሴ  23.06.2018  (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)     „ከፊቱ ብርሃን የተነሳ ደመናት እና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ።“             (መጽሐፈ መዝሙር ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፲፪)              በቅድሚያ አባ ቅንዬ እንኳን ከሞት ተረፉ። ከብዶኝ ስለነበረ እንቅልፍ አልተኛሁም። እንዲያውም ዛሬ ሰውነቴ ስለዛለ ማረፍ ነበር የፈለግኩት፤ የፈሩት ይደርሳል ስለሆነ የምለው ይኖረኛል። ቁጭ ብዬ አፍጥጬ ስለደርኩኝ ዛሬ በቀጥታ ከሚተለላፈው የለጠፍኩት ተመስገን የምለው ሰልፉ በሰላም ተጠናቆ ቅኑ ህዝብ በሰላም ሲገባ ብቻ ነው ብዬ ጽፌ ነበር። ከዚህ ቀደመም የድጋፍ ሰልፉን ጦስ እና ወቅቱን ያልጠበቀ ስለመሆኑ አበክሬ ጽፌ ነበር። ይህም ብቻ ሳይሆን ከብራና ሳተናው ላይ ትናንት የጎንደር የድጋፍ ሰልፍን አቶ ተቀባ ተባባል አገዱት ሲባልም ብራቦ ብዬ ጽፌ ነበር የተባባል አርምሞ በሚል እርእስ ትናንት። ስከንት ያስፈልጋል። እርጋታ ያስፈልጋል። አሁን የአደባባይ ሰልፍ በመፍጹም አስፈላጊ አልነበረም። የመቆጣጠር አቅም ፈጽሞ የለንም። አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የሚፈለግም ሃይል አለ።  ትናንት በደቡብ የተፈጠረው ችግር ሳይረጋጋ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ባልተረጋጋ ሁኔተ ሰልፍ ማድረጉ አግባብ አልነበረም። ከጅምሩ „ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ“ የሚል ሁሉ ነበር። ያልተገቡ ፖስተሮች ሁሉ ነበሩ። ፍቅርን፤ አክብሮትን፤ መቻቻልን፤ መታገስን፤ መቀበልን፤ መስጠትን፤ ትህትናን፤ ይቅርባይነትን፤ ሁሉም እኩል መሆኑን የሚሰብኩ እንጂ ሌላ የፖለቲካ ትርፍ ማፈሻ እና መቸ...