አቅል።

አቅል።
ከሥርጉተ © ሥላሴ 
23.06.2018 
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)

    „ከፊቱ ብርሃን የተነሳ ደመናት እና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ።“
            (መጽሐፈ መዝሙር ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፲፪)



             በቅድሚያ አባ ቅንዬ እንኳን ከሞት ተረፉ።
ከብዶኝ ስለነበረ እንቅልፍ አልተኛሁም። እንዲያውም ዛሬ ሰውነቴ ስለዛለ ማረፍ ነበር የፈለግኩት፤ የፈሩት ይደርሳል ስለሆነ የምለው ይኖረኛል።
ቁጭ ብዬ አፍጥጬ ስለደርኩኝ ዛሬ በቀጥታ ከሚተለላፈው የለጠፍኩት ተመስገን የምለው ሰልፉ በሰላም ተጠናቆ ቅኑ ህዝብ በሰላም ሲገባ ብቻ ነው ብዬ ጽፌ ነበር። ከዚህ ቀደመም የድጋፍ ሰልፉን ጦስ እና ወቅቱን ያልጠበቀ ስለመሆኑ አበክሬ ጽፌ ነበር። ይህም ብቻ ሳይሆን ከብራና ሳተናው ላይ ትናንት የጎንደር የድጋፍ ሰልፍን አቶ ተቀባ ተባባል አገዱት ሲባልም ብራቦ ብዬ ጽፌ ነበር የተባባል አርምሞ በሚል እርእስ ትናንት።

ስከንት ያስፈልጋል። እርጋታ ያስፈልጋል። አሁን የአደባባይ ሰልፍ በመፍጹም አስፈላጊ አልነበረም። የመቆጣጠር አቅም ፈጽሞ የለንም። አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የሚፈለግም ሃይል አለ።  ትናንት በደቡብ የተፈጠረው ችግር ሳይረጋጋ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ባልተረጋጋ ሁኔተ ሰልፍ ማድረጉ አግባብ አልነበረም። ከጅምሩ „ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ“ የሚል ሁሉ ነበር። ያልተገቡ ፖስተሮች ሁሉ ነበሩ።

ፍቅርን፤ አክብሮትን፤ መቻቻልን፤ መታገስን፤ መቀበልን፤ መስጠትን፤ ትህትናን፤ ይቅርባይነትን፤ ሁሉም እኩል መሆኑን የሚሰብኩ እንጂ ሌላ የፖለቲካ ትርፍ ማፈሻ እና መቸርፈሻ መሆን  አልነበረበትም። የተጋ ካለ ልብ ይመርቅ፤ በፋውልነቱ ጀግና ነኝ ብሎ የሚፏልል ካለም ዛሬ መሪ ማለት ምን ማለት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ አያዬው ስለሆነ ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገውም። ለሰነፉ ፖለቲከኛ፤ ለሃሳብ የለሹ ተራራ ብቻ ነው ፕሮፖጋንዲስት የሚያስፍልገው። ለለማ፤ ለገዱ፤ ለ አብይ፤ ለአንቤ ግን ተግባር ብቻ ነው የሚራዳቸው የሚያራምዳቸውም።  

ሌላው እርጋታ የነሳው የግንቦት 7 መግለጫ እና የግንቦት 7 ቃለ ምልልስ ተጣብቆ ይህን ስልፍ መዳፉ ውስጥ መንፈሱን ለማያዝ የሄደበት መንገድ በዚህ ህዝባዊ ሰልፍ ማህል መለጠፍ ሌለው ጦስ ነበር። ይሄው ነው የግንቦት 7 መለያው። ልክ የ አማራ ታገድሎን የ እኔ ነው ብሎ እንደወጣው፤ ቄሮምን ለማድመጥ አርበኛ አትሌት ሊሊሳን ፈይሳን፤ ኦፌኮን የ አውሮፓ ህብረት ተጋባዥ ማድረጉ፤ ከዚህም ባለፈ የቢሸፍቱ ተወልጀነት እና ዕድምታው በመሰሉ ነበር የተከናወነው። የፖለቲካ ብልህነት ማለት ብልጥነት ነው። መሬት ላይ በፖለቲካ ድርጅት በቃሚነት መደበኛ ሆነ አለመሥራት ትርፉ ይሄው ነው። ንፋስ በተወዛወዛ ቁጥር ቁጭ ብድግ።

የኖረ ኑሮ፤ የከረመ ከርሞ ካድሬዎቹን ፕሮ ሚዲያዎችን፤ ፕሮ ጸሐፊዎችን፤ ፕሮ ጋዜጠኞችን፤ ፕሮ ተንታኞቹን የራሱን አካላቱን ጨምሮ አሰልፎ የአብይን ካቢኔ በብራና እና በማይክ ሲያስከተክት ከርሞ አሁን በመሃል ሰላም ፈላጊ ነኝ ብሎ ከች አለ። በቃ መሬት ከሌላ የት ነኝ ብሎ መፎከር ይችላል። ይህን ኤርትራ ላይ ያሉ ሌሎች ሃይሎች እንዲህ በጥድፊያ እና በሽሚያ ተክለፈልፈው አለደረጉትም።

እኔ ምን ቢደረጉ እንደሚሻላቸው አላውቅም ግንቦት 7። ያው ሽሚያ ነው በተሄደበት ሁሉ። ፎቶ ነገርም አይቻለሁኝ። በድል እንደገባ ጀግና ሁሉ ውለቅልቅህ ወጥቶ አዩኝ አላዩኝ ብሎ አንገትን ደፍቶ እንደ ሁሉ ተሳታፊ መሆን ሲጋባ በሌለ አቅም ጎልቶ ጎልብቶ ታይቶ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር፤ መንፈስንም ለማሻቀል ነው ይህ ሁሉ የ100 ሜትር ሩጫ። ምርጫ የለም አሁን። የተሸነፈ ፖለቲካ ይዘህ፤ የተሸነፈ ሃሳብ ይዘህ አብረን እንሰራለን ማለት እንኳን አይቻለም። ፖሊሲ መች አለህ እና። ውጪ ያለውን አንድ ማድረግ ተስኖህ ነገን አደራጃለሁ ማለትም ማለት ብቻ ነው።
 
የሆነ ሆኖ የግንቦት 7 እንደ ተለመደው አደብ ነስቶት እንደ ተለመደው ከማሀል መሰነቅሩ ይሄ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ መንፈስ ሰላም አይሰጥም። ምን አለ እነሱም እሰኪረጋጉ ድረስስ ጊዜ ብንሰጣቸው። ቀላል እኮ አይደለም ለ100 ዓመት፤ ለልጅል የታሰበ የሥርዎዖ መንግሥት የውርስ የቅርስ የመኖር፤ የመግዛት፤ የመንዳት፤ ሥልጣን በመተካካት ታሪክ እንዲህ ተቋርጦ ሲቀር እንደ ሰው ቢታሰብ እኮ ከባድ ነው።  

ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ መሥራቾች፤ አባለት፤ ደጋፊዎች እኪ ሰው ናቸው። ጊዜ አያስፈልጋቸውም። እንኳንስ ለ እነሱ ይህ አብዮት እኮ አንዱንም ሳሰብስበው አዬተደራረበ ውጦናል እኮ። የወያኔ ሃርነት መሪዎች፤ አባለት፤ ደጋፊዎቻቸው፤ የትግራይ ህዝብ ራሱ እንደ እኛም ስሜት አላቸው። እልህና እልህ ምን ትርፍ አለው። አቀዝቅዞ፣ አለዝቦ አለስልሶ መያዝ ያለበት ጉዳይ በቃ አሁኑ ተለወጥህ ምሰል ከባድ ነው። የ43 ዓመቱ አይዲዎሊጂን አሸንፎ ለመውጣት እጅግ በጣም ብዙ ሰው ተቸግሯል። እስኪ SBS የሚደመጡ ቃለ ምልለሶችን፤ ኢትዮ ሚዲያ የሚለጠፉ ጹሑፎችን መርምሯቸው። በጣም እኮ ሰው ከብዶታል። እነሱም ከዛ ትወልድ ውስጥ ናቸው።

በእነሱ ሲሆን ማክረር አይገባም። ሰው ሲደነግጥ የሚይዘውን የሚጨብጠውን ነው የሚያጠው። አሁን እነሱ ብታስቡት ከጎንደር፤ ከወሎ ጋር መጣላት ነበረባቸውን? ምን አላቸው ቀድሞ ነገር። ግን አፈጣራቸው የተለዬ ነው … ክፉ ነገር ደግሞ ፈተና ነው። እንኳንስ ክፉ ነገር ፍቅር ከብዶን የለንም? ይቅርታ አድርግልኝ ምን ያህል ከባድ ነው? ይቅርታ አድርጌልሃለሁ ማለትም ምን ያህል ከባድ ነው። እራሱ አዘጋጆች በነበራቸው ቃለ ምልልስ ከራራ ነው የነበረው። በዛ ባለፈበት የጥላቻ መንፈስ የዚህን ዘመን ዛሬ ማስተናገድ ራስን ከተጠያቂነት አያድንም። ፍቅርን ጠርተህ ድንበር ሰርተህ አይሆንም። 

ኑልኝ ብለህ የተወሰነውን አግደህ አይሆንም። በፍቅር ውስጥ በዳይም ተባዳይም እኩል መስተናገድ አለባቸው። ይህን ስታደርግ ህሊና ላይ ሌላ ቦንብ ቀብርሃል ማለት ነው። ሰው አገርም፤ ቤትም ሥራም፤ ትዳርም፤ ቤተሰብም ባይስማማው ይተዋዋል ግን ህሊናህን የት ትሸሻዋለህ? የት። እነሱ እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው እኛም እሳት ለብሰን እሳት ጎርሰን እሳት አጥፊው ጠ/ ሚር ውሃ ይዘው እንዴት ይሁኑ ከዬቱ ይሁኑ ወዴትስ ይሂዱልን።

እሳቸውን አክብረህ ስትጠራ ከእከሌ ጋር ጥል ነኝ ከእከሌ ጋር ወዳጅ ነኝ ብለህ መሆን አልነበረበትም። እሳቸውም የዛ ድርጅት የግንባር አባል ናቸው። አሁን ግንቦት 7 ይወገዛል ይከተከታል ሁሉ ግን አንድ በሆነ ከረጢት የሚከተት ከሆነ ስህተት ነው። ኢሳት አለ በፈለገው መሥፈርት እንደ ሰው እንደ ማንኛችንም ግድፈት ሊኖርበት ቢችልም እንደ እኔ እንደ አንቺ እንደ እርሰዎ እሱ አለ የመንለው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌናም አለ። ስንውቅሰውም እንደዛው ግን አሉ የምንላቸው ሰዎች በዬቦታው አሉ። 

የሰው ልጅ ሬድ ሜድ ተፈጥሮ የለውም። የምነወቅሳቸው እራሱ የራሳቸው መክሊት እና ጸጋ አላቸው። እንደ ሁለችንም።

ቢያንስ የታላቅ ሙያ ሊሂቅ ናቸው። ትዳር ቤት ጎጆ ልጆች አሏቸው። ቢያነስ እናት አላቸው። ስለዚህ የወያኔ ሃርነት ትግራይንም እንዲህ ለማዬት ማሰቡ ቢያንስ ሰልፍቅር ዝክረ ነገር ምስጋና ለማቅረብ ከዚህ አስተሳሰብ መራቅ ነበረብን። ምህረት መንግሥት ሲያደርግ፤ ይቅርታ ሲያደርግ፤ በድያለሁ ሲል እንደ መንግሥት እኛም ይቅር ማለት አለብን። እነሱ አሁንም በዛው መንገዳቸው ሊቀጥሉ ቢችሉም ግን ደጋፊዎቻቸው መልካም ነገር እያሸነፋቸው እንዲመጡ ብናደርግ ክፉ ነገር ይደርቃል።

ሁላችንም ከሽሚያ የፖለቲካ ትርፍ ወጥተን በክፉ ነገር ላይ ለመዝመት በውስጣችን ያለውን ክፉ ነገር ለማውጣት ቆርጦ መወስን ይጠይቃል። ዛሬ ማምሻ ራሱ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አይታወቅም። ዶር አንባቸው መኮነን የኮራሁባቸው መሪ ናቸው። ሲናገሩ ባልረጋ መሠረት ላይ ነው ያለነው ብለው ነበር። ልብ ያለው ሰው የለም። በዬደቂቃው በ አንድም በሌላም ህሊናን የሚበሳ ቦንብ አለ ትግል ማለት ይሄው ነው። በምቾት በሙሽርነት እንደ ሰማያዊ ፓርቲ የማይታሰብ።

ያገኘኸውን ስታከብረው ያጣኽውን ስለማግኘትህ አንድ ርምጃ ተራምደሃል፤ ፈጻሚው ፈጣሪ ነውና … ሁሉን እዬተቃወምክ ግን የሚገኝ በረከት የለም … አሁን ተመስገን የሚባለው የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ እና የጠ/ሚር ዶር አብይ አህመድ ሰላማዊ መንግድ ብዙ ነገሮችን መልክ ያስይዛል። ብዙ ነገሮች ክፉ መንፈሶች በዛ ውስጥ ተጠልለው ስለነበር። ሰላም ሲኖር ተረጋግቶ ማሰብ እና መኖር ይቻላል። ድህነታቸን ላይ በጋራ ሆ ሲባል ክፋትን ቅናትን ምቀኝነት ማሰወገድ ስልንችል ነው። ለዚህ ደግሞ መንገድ ተጀመሯል መሪም ሙሴም እረኛም አለው። ግን በዓዋጅ አይሆንም። ሁሉም ቤተሰቡን መግራት እና በዛ ላይ መትጋት ሲቻል ብቻ ነው።

ፕሮ ግንቦት 7 ሲነሰቱ፤ ሲበጠብጡ፤ ሲያውኩ የከራረሙት እኮ መሪያችን ያሉት ድርጅታቸው፤ አውራነቱን ማጣቱን ስላወቁ መቀበል ከበዳቸው። የፈለገው ይጨቁን ቢመረንም እነሱ ታቱ እስኪሉ ድረስ አገራዊ ንቅናቂውን ማለት ነው ወያኔ ይዞት ይቆይ ከሚል ሁሉ ተደርሶ ነበር። ሌላም ከዚህ የባሰ የሚያሰጋ ከሚይዘው ነው ነገርዬው። ግን እኔ ይህን ሃሳብ አልሸምተውም።  

ለግንቦት 7 ሳይለፋም ሳይደክም ቤተ መንግሥቱን ቢሰጠው አቅሙ አይችለውም። በፍጹም። ከተፈጠርክ ጀምሮ ተጽዕኖ ፈጣሪ ለቅመህ አገር አይመራም። አሁን ለ አዲሱ ዓመት የ ዓመቱ ምርጥ ሰው ዶር አብይ አህመድ ታጭተዋል። በቃ ግንቦት 7 ማለት እንዲህ ነው። የሌለህን ነገር እንዳለህ እራስህ ዋሽተህው አገር አይመራም። ሰው ባቀደው ሃሳብ ላይ እንዲህ ጥልቆ እዬሆንክ አገር አይመራም። ዛሬ ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ የእኛ ሰዎች ነበረቡት ፉከራ ነበረበት። በቃ ከሞቀው መጣድ። ስለዚህ ለሁሉም አዲስ የሆነው ለውጥ ጊዜም ሁኔታም ቦታም ያስፈልገዋል። የወያኔ ሃርነት ትግራይም ባላሰቡት ሁኔታ ዱብ ዕዳ ነው የወረደባቸው።

ስለዚህ ቢደናገጡ የተገባ ነው። ቢከብዳቸው የተገባ ነው ኢትዮጵያ ስትባል እኛስ ተደናብረን የለንም? ለማን ነው የምታሞኙት። የሆነ ሆኖ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የማናፌስቶው ካድሪዎች ግን ባያውቁት ነው እንጂ ለትግራይ ህዝብ ከምንም እና ከማንም በላይ ተጠቃሚ የሚያደርግ የሰማይ ምርቃት ነው የአብይ የለማ የገዱ የአንባቸው መንፈስ። በዬተገኙበት ክፉ መርዝን እንዲወጣ ነው እዬተጉ ያሉት። አዳምጡት። አንዲትም ቅንጣት ነገር ዝንፍ አይሉም። ህዝባቸው ቁጣውን ቁጭቱን እልሁን እያረጋጉት ነው።

 እኔ ለግንቦት 7 የምለው ራሱን ይወቅ። በራሱ ውስጥ የሚመካበት፤ እርግጠኛ የሚሆንበት አቅሙን ይፍጠር። አዘውትሮ የትውስት አቅም ተጠማኝ አይሁን። የብድር ዱቄት ጥገኛ አይሁን። ዕለታዊ አይሁን። የወንድሜ ዶር መሆን ለእሱ ብቻ ነው። ለትዳር አካሉ እንኳን አይሁንም። እኔ ከአንድ ልባም የፖለቲካ ድርጅትም በላይ እጅግም በላይ የሆኑ ኮ/ ደመቀ ዘውዱ እኮ ፕሮፌስር ሆኖ ትልቅ ዓለምአቀፍ ድርጅት ከሚመሩት ሆነ ከዓለምአቀፍ ሽልማት ሻምንፕዮኖች ጋዜጠኝነት ባለሙያዎች፤ ወይንም የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ዕውቅና ከሰጠው አንድ ኢትዮጵያዊ በላይ በላይ ህይወታቸው ያስተምራል። ማወከብ የለ፤ መጣደፍ የለ፤ ስክነቱ፤ እርጋታው ጭምትነቱ ወደር የለሽ ነው። እዩኝ እዩኝ የለም። ምን ዓይነት ማህጸን እና ምንስ ዓይነት ቤተሰብ ይሆን ያሳዳጋቸው? የእውነት ቅርስ ናቸው። የእውነት ትውፊትም ትሩፋትም ናቸው። የጎንደር ህዝብ፤ የአማራ ህዝብ ከእኒህ ብቁ የተደሞ ሰው ትዕግስትን አደበን እዮባዊነትን ዝቅ ብሎ መማር አለበት። ኮሚቴውን እስኪ እዩት … ስክን ያለ ነው።

 አይጽፍ፤ በዬሚዲያው ተገኝቶ ቃሉን አይሰጥ ለቀሪወም ጊዜም ቢሆን እዛ ጎንደር ውስጥ ይሁን አማራ መሬት ላይ የሚኖረው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ  ዜጋ በራሱ ቀዬ፤ በራሱ ባድማ፤ በራሱ ባዕት መኖሩ ድርጊት ላይ በመገኘት መትባት አለበት። በማስተዋል ውስጥነትን በማዬት ዘመን ካሸከመን ክፉነት ተወጥቶ በተመለደው የመረጋጋት ህይወቱ መቀጠል አለበት በሰላም። ዛሬ ያልፋል ሃፈረት እና ውርዴት ግን የዘላለም ቅርስ እና ውርስ ነው። ሃፍረት፤ ውርዴት ሊናፈቅን አይገባም። …  ለዚህ ደግሞ ኮ/ ደመቀ ዘውዱ አብነትም ናሙና ናቸው።

እኔ የክብሩ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ አማካሪ ብሆን የስልፉን አዘጋጆች በቢሮ በክብር አስጠርቼ በጠ/ ሚሩ ፊት ለፊት እንዲገናኙ አድርግ እና በቅንነታቸው ተመስግነው ግን አሁን ወቅቱ አለመሆኑን አስገልጽ ነበር። ሌላው በዚህ ማህል ከኢትዮጵያ ሚዲያ ጋር ከግንቦት 7 ጋር የነበረን መግለጫምችንም እንዲቋረጥ አስደርግ ነበር። ስንት ቀን ወደፊታችን እያለ ምን ያጣድፋል። ለቅዳሜ ሰልፍ ሃሙስ እና አርብ የአንግሊዝ ጨው እንደጠጣ ሰው ትቅማጥ እንሚያጥደፈው እንደያዘው የሚያጣድፍ ነገር በፍጹም እለነበረም። በወለቃ በር የገባ አርበኛ እኮ አለ መሬት ላይ ድፍረቱ ሚደያው ከኖረው …
  
ግንቦት 7 እኮ ትልቅ የቴሌቪዥን ፕሮግራም፤ ሁለት የራዲዮ ጣቢያ፤ የአሜሪካውም አማርኛ ፕሮግራምም VOA ቃል አቀባይ እስኪመሰል ድረስ ብረት መዝጊያ የሚሆን ጠንከር ያለ ሰው አላቸው ትስስሩን እናውቀዋለን፤ አውሮፓው ህብርት የማይደፈር ሁነኛ ሰው አላቸው፤ ሁሉም ሚዲያ፤ ሁሉም የኮሚኒቲ ራዲዮን ማለቴ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የሆኑት ብዙ አድማጭ ያላቸው፤ ብልሆቹ የማህበራዊ ሚዲያ ጀግኖች በነፍስ ወከፍ፤ ርቱ አንደበት ያላቸው ትንታጎች፤ የሙያ የጥበብ የእስፖርት ሊሂቆች፤ የትም የማያውቃቸው ጸሐፍት ሁሉ ሰሞኑን ራሱ የት ነበሩ እስኪያሰኝ የራሱ ንብረት የሚያደርግ ድርጅት ነው። ልሳኑ አልተዘጋም። ሁሉ ልሳኑ ነው። የሚሞግተውን መንፈስም በ እንድ ቃል ማስቆም ማሳገድ የሚያስችል ሙሉ ቁመና አለው። ሃሳብ ፈሪ ስለሆነ። 

ስለዚህ ምን ያጣድፋል? በቤተ ዘመዱ ድልድይነት ነገስ ማን ይከለክለዋል … ቤተ መንግሥቱን መስጠት ይቻላል … ግን አሁም መሆን አልነበረበትም። ሌላው ይቆስላል … የተጎዳ ማህበረሰብም ቤተሰብም አለ። ግብር የከፈለ …
ውጥረት ብቻ፤ ጥድፊያ ብቻ … ግንቦት 7 ጣምራ ተልዕኮ ይዞ ነው የሚነሳው፤ ሲሳካ የእኔ ነበር፤ ሲወድቅ የወያኔ ሃርነት ትግራይ እና የአብይ ግድፈት ተጨምሮበት የውጩ ማህበረሰብ አሁንም አልተረጋጋም እንዲል … አማራጭ መፍትሄ ሆኖ መቅረብ አለበት፤ ይሄው ነው … አገር አድን ንቅናቄውም ውስጥ የሲዳማው የአፋሩ አሉ እነሱስ ኢትዮጵያዊ አይደሉንም? አፍ ያለው ያግባሽ የሆነ ነገር … ማሽሎክ መሽሎክ … ውስጡን ሳስበው ከጓድ ገብረመድህን በርጋ ጋር ስለደኩኝ ኮሾ ይሆንብኝል አካሄዱ፤ ስልቱ ስትራቴጁ ብልጡት ይከረፈኛል … በዛ ውስጥ ቅኖች እንዳሉ ባውቅም፤ ሌት እና ቀን የሚጥሩ እንዳሉ ባውቅም እሱን ተጠግቶ ረጅም ጉዞ ማሳብ ቀርቶ ለጉርብትናም ከባድ ነው … አሁን ለቀማ ላይ ነው የግንቦት 7 መንፈስ፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ የኦቦ ለማ መግርሳ እና የዶር አብይ ኮቴ ፍለጋ ላይ ነው በቃ የደህነት ተግባሩ ሥራ ይሄው ነው፤ … የዕምሮ ለውጥ ያስፈልገዋል። ኢህአፓ እንዲህ አልነበረም።

ድርጅታዊ አቅምህን ገንብተህ ተዋዳዳሪ ሆኖ ለመውጣት አቅም መልቀም አያስፈልግውም … አሁን አኮ በዚህም በዚያም ተብሎ የሽግግር መንግሥትን መመኘት ነው። መሬት ላይ ወገብን ታጥቆ ሥራንማ ማን ይደፍራታል። ኤርትራ ላይ ያለው ሠራዊት ቢሆን ስንት ጀግኖች እነ አርበኛ አበጀ በለው፤ እና ጄ/ ሃይሌ መለስ፤ እና መስከረም አታላይ፤ እነ ማዕዛው የኢትዮጵያ የጎንደር አርበኞች ደሙን ከፍሎ ያደራጀው ነው … ሁልጊዜ የሰነፍ መንገድ። 

ከዚህ ስንፍናው መውጣት አለበት ግንቦት 7፤ ግን ዘመን አያስተምረውም አሁን በዛው በለመደው መንገድ አስፓልት ላይ ነው … አሁንም። እርሱን ሳዬው እራሱ ይገርመኛል። የማደራጀት ት. ቤት ያስፈልገዋል። ተወዳድሮም አያሸንፍም አቅሙን አምጦ ማምጣት ካልቻለ።

የሆነ ሆኖ አሁንም እደግመዋለሁኝ ወቅቱን የጠበቀ አልነበረም የድጋፍ ሰልፉ። ቅንነቱ ቢኖርም ቅኖች ቅንታቸውን ጥቅም ላይ ለማውል፤ ሁኔታ፤ ጊዜ፤ ቦታ ያስፈልጋቸዋል። አሁን ጊዜው አልነበረም። ሁል ጊዜ ምን አለ የ ኢትዮጵያ እናት አትታክት የሰው ብርንዶ ታቅርብ። የደቡቡ ግጭት ሰማዕታት እያሉበን። ሁሉ ነገር ተጣደፈ። ሰከን በሉ! አንድም ሰው ለምን ይጎዳ? ክብሩነታቸውስ በዬደቂቃው በዛ ርህርህና አንጀታቸው ስለምን ይቁሰሉ። 

ሳምንት ሳይሞላ የደቡብ ሰቆቃ። ሁሉ ነገር ጥድፊያ በጥድፊያ ነው። አሁን የኤርትራ መንግሥት ተሎ መልስ አልሰጠም ብዬ እኔ አልተረበሽኩም ነበር እኔ። ጥቅሙን እንደማይጸረር ነበር የገለጽኩት። አደበኛ መሆናቸውንም ገልጫለሁኝ በተደጋጋሚ የሚዲያ ራህብተኛ አይደሉም ሰዎቻቸውን በዬተራ ይህም አለን፤ ሌላም አለኝ እያሉ አያሰልፉም ለቀጣይ የሹመት መደብ። ሁኔታውን አዬ ካቢነው። ቁጭ ብሎ አስተዋለ ሰማዕታትን ቀን ጠብቆ መቀበሉን ገለጸ፤ ግንቦት 7 እኮ የተጠራው በትናንቱ የፓርላማ ንግግር አይደለም። 

ይፋዊ ጥሪው መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ነበር። ምን ሌላ ጥሪ ያስፈልጋዋል። ነው ወይንስ ግንቦት 7 ሌላ ጆሮ ይገዛለትን? ከእነ አቦ ሌነጮ ለታ በምን ይለያል። ያው የቴሌፎን ቢሮ ነው ያለው እሱም እንደ ሌሎቹ፤ እንድ ስለፓርቲ ደንብ ቆሞ መናገር ተራ አባል የሌለው ድርጅት … ገና ብዙ ሥራ አለበት ራሱ … አቅሙ ከኖረው። በግራ በቀኝ ይጣደፋል አሁን የነጻ ሚዲያ ዘመን ነው፤ ቀልዶ እና ተቀልዶ ቁብ ኮረቻ ላይ የለም …
  
እዘናለሁኝ ለእኒህ ጠ/ ሚር በደቡብ የሆነ በጣምራ የህሊና ምክክሮሽ ችግር ተፈጠረ በማግስቱ መከረኛ ጠ/ ሚር ብር ብለው ሄዱ፤ በማህል ደግሞ ሰላማዊ ስልፍ የድጋፍ ተጠራ፤ የአዲስ አበባው ሰላማዊ ስልፍ እዳያመልጥ ተንደፋደፈ ግንቦት 7። ይህ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ሌላው ራስ ምታት ነው። የሰው ልጅ ያገኘውን በረከት በቀስታ፤ በርጋታ፤ በስክነት መያዝ አለበት። አሁን አኮ የሱባኤ ቀን ነው። የሚያቅለሸልሽ አደረግነው … እራሳችን …

የሆነ ሆኖ መከራ ያጠነክራል ያበረታል። ዛሬ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በሰኔ 23 ቀን 2018 የፍቅር ቀን በኢትዮጵያ ታወጀ። እኔ የፍቅር ቀን ዓለምአቀፍ ይኑርን ብቻ ሳይሆን እንደ አንድ የቀለም ትምህርት ካሪክለም ይዘጋጅለት ብዬ ብዬ ከ2015 ጀምሮ ዓለምአቀፉን ማህበረሰብ ስሟገት፤ ከ2017 ጀምሮ የቃላት ፖስተራዊ ቻናል ጀምሬ እየሠራሁ ባለሁት ወቅት በኢትዮጵያ ህልሜ ተወጠነ ደምም ተገበረበት። ሃዘን ተፍስሃ ቢሆንም ባለቅኔው ጠ/ ሚር ይህን ቃል አበክረው ገልጸውታል። „ዛሬ የፍቅር ቀን“ ነው ብለው።

በመከራ በስተጀርባ ክብር አለ። ህይወታቸው መትረፉ በእግዚአብሄር ቸርነት እንጂ በሳቸው ጥንቃቄ አይደለም። እሳቸውማ ቅን ስለሆኑ የሚሰጣቸውን ውሃ ሁሉ እንዳገኙ ሲጠጡ አይቻቸዋለሁኝ። አሁንም በሰው ጥበቃ፤ በሰው ጥንቃቄ የሚድን ሰው ስሌለ ድንግልዬ ትጠብቃቸው። „አሜን“

የሰው ልጅ አቧራ ላይ ስላለ፤ ታዋቂ ስላልሆነ፤ ብረት መዝጊያ የሆነ ዘመድ ወገን ስሌለው የሚናገረው ነገር ፍሬ የለውም ብሎ መተው አይገባም ነበር። እኔ ተናግሬያለሁኝ። አሁንም ሁሉም ሰው ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ማን ምን እንደሆነ አይታወቅም። ሌሊቱ፤ ቀጣይ ሳምንታት ምን ሊፈጠር እንደሚችል አይታወቅም። ጋብቻ እራሱ ሥር የሰደደ ነው። 

አሁን ደግሞ አዘንኩ ብሎ መግለጫ ያውጣ ወይንም ጸሐፊዎቹ ደስታችን ወደር አልነበረውም ግን ይህ በመከሱቱ ፍርሃት ገባን ይበሉን፤ ኤርትራ ላይ ተጣመርን ሲሉ አቶ ሞላ አስገዶም አስቀምጧቸው ኢትዮጵያ ገቡ፤ ትንሳኤ እና ህይወት እኛ ነን ስንባልም የ አቦ ሌንጮ ለታ ድርጅት በቀይ ምንጣፍ ጥሏቸው ገባ፤ አሁን ደግሞ ኤርትራ ልዕክ ልልክ ነው ስትል መንገዳችን ቀዬርን .. ለዛውም ነገ ለመድረስ ዛሬ ማህል ላይ መሰንቀር … ዘመድ ይሁን፤ መካሪ ይሁን የለውም ያሰኛል … የሰከከነውን የ ኦህዴድ መንፈስ እራሱ አወከው … በዬተደረሰበት መፍትሄ መሆን ሲቻል … እሱ ይሁነው …
   
  •               ዛሬ ጥዋት አስተያዬቴ ምርኩዝ

ዛሬ ጥዋት ላይ የጻፍኩት አስተያዬት ነበር። ቁጭ ብዬ ነው ያደርኩት። ፊቴ ሙሉው አብጧል። ዓይኔ ቀልቷል። በጭንቀት ነው ያደርኩት።
የጠ/ አብይ ድጋፍ ሰልፍ አጀማመሩ Ethiopians Rally For PM Abiy Ahmed

  • አስቀድሜ ደግሞ ያልሰከነ ውሳኔ መሆኑን አበክሬ ገልጫለሁኝ።

    18.06.2018 የተጻፈ የቀደመ ስጋቴ እና የሰልፉ ፍላጎት ስክነት ማነሱን የጻፍኩበት። https://sergute.blogspot.com/2018/06/blog-post_63.html
የድጋፍ ሰልፍ አዲስ አበባ ላይ ጦሱ መከራ ነው

  •     ትናንት ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን የጻፍኩበት።

አቶ ተቀባ ተባባል የጎንደርን ስልፍ አገዱ ሲባል ብራቦ በዬ የጻፍኩት ነበር። 
https://sergute.blogspot.com/2018/06/blog-post_63.html
  • ድምጽ

Ethiopia: / አብይ በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ የሰው ህይወት በመጥፋቱ የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ


ጌታ ሆይ ሚዛን ስጠን!



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።