ልጥፎች

ከኦገስት 10, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ይድረስ ለአቶ አዲሱ ረጋሳ ካሉበት፤ ቤተ መንግሥትም ከተሆነ?

ምስል
የእጩ ጠ/ ሚር ኦቦ አዲሱ ረጋሳ ዘመናይነት። „ሥጋቸውን መከራ ያስቻሉ በፈጣሪያቸውም አምነው መከራ የተቀበሉ በክፉ ሰዎችም የተነሳ የጎሰቆሉ፤ ፈጣሪያቸውንም የወደዱ፤ ሰዎች ብርና ወርቅን አይወዱም።“ ይሄ በሴረኞች እገታ ውስጥ ላለው ለአብይ ቅዱስ መንፈስ የተጋባው ነው።  መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፵፪ ቁጥር  ፱ ከሥርጉተ© ሥላሴ 10.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አዝናለሁኝ የተለዬ ምልከታ ከቲም ለማ ቡድን እንዳላቸው ባውቅም ግን የሃሳብ ልዩነትን እንደ ወንጀል ስላማላዬው እማከብራቸው ወጣት ሊሂቅ ናቸው አቶ አዲሱ ረጋሳ። እንዲያውም እኔ በአትላንተው ጉባኤ ላይ ሁሉ ቀና ምልክታ ነው የነበረኝ ተሟግቻለሁም። ሰው ሃሳቡን ያውጣ የሚል ዕምነት ነው ያለኝ። እኒህ ወጣት የፖለቲካ ሊሂቅ ያው በአቶ ጆዋር መሃመድ እንደ ሮል ሞዴል የሚታዩም ናቸው። እኔ እውነት ለመናገር ኢትዮጵያን እንደ ጣዕንት ለሚያ መንፈስ ቆራጣ ጊዜ ማጥፋት አልፈልግም ነበር። ነገር ግን እንዲህ እዬገፋ ከመጣ ግድ ይላል። በአቶ ጃዋር መሃመድ ጠ/ ሚር እንዲሆኑ ይፈለግ የነበረውም እሳቸውን ነው። ከሳቸው ቀጣይ ደግሞ አቶ ንጉሡ ጥላሁን። የሆነ ሆኖ ሳልፈልግ ተገድጄ ለዚህ ጹሁፋቸው መልስ መስጠት ግድ ይለኛል ለአቶ አዲሱ ረጋሳ። ሰሞኑን ብቅ እያሉ መሪነታቸው እያሳዩን ነው። እራሱ ስለ አዲስ አባባ ስለ ንጉሦች ንጉስ አጤ ሚኒልክ፤ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ስቀደሙት የፖለቲካ ድርጅቶች ወዘተ እምታቀብባቸው ጉዳዮች አሉ። አስፈላጊ በሆነው ሁኔታ ብቻ እንጂ እራሱን አስችዬ የሙግት አውራ አድርጌ አልታገልበትም፤ ስለምን? ባለሙያዎች የታሪክም የሃይማኖትም ሊቀ ሊቃውናታት ስላሉበት። የሆነ ሆኖ „ምርቱን ከግርዱ እንለይ“ በሚል ከአቶ  እዲሱ አረጋ የጻፉትን አነበብኩ