ልጥፎች

ጥሎብን መልካምነትን መጋፋት ነውና።

ምስል
… ሰው ማበርከት አናውቅበትም፤ አልተሰጠነም፤ ጸጋችንም አይደለም። „ሰባት ሳምንት ትቆጥራለህ፤ መከሩን ማጨድ ከምትጀምርበት ቀን ጀምሮ  ሰባት ሳምንት መቁጠር ትጀምራለህ።“ ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ  ፲፮ ቊጥር ፱ ሥርጉተ ©ሥላሴ 09.08.2018 ውዶቼ ያልተጠናቀቀው ጉዞ በሚመለከት ሊንክ እና አስተያዬታችሁን ለላካችሁልኝ የእኔ ጌጦች እጅግ አድርጌ አመሰግናችሁ አለሁኝ።   ወጣ ያለም ሰለሆነ እንደ እናንተ ሌሎቹም ሊኖሩ ስለሚችሉ ትንሽ ልባል።   የበጎ ፈቃደኝነት ወጣቶችን ገለጻ እንዳደረጉ ይህን እማ ሳተናው ላይ አግኝቼው አዳምጫዋለሁኝ። አገላለጹም ተሳታፊዎችም አዲስ ናቸው። ንግግራቸውም እጅግ ቀስሰተኛ የደከመው ነው። የውስጥ ደስታ በፍጹም ሁኔታ የራቀው ነው።   እውን ያ አንበሳ ዶር አብይ አህመድ ናቸውን ያሰኛል? የተለዬ ነገር እኮ አላቸው? ይህ እርግጠኝነታቸው፤ ልበ ሙሉነታቸው፤ ድፍረታቸው፤ በራስ የመተማመን አቅማቸው፤ በመንፈሳቸው ውስጥ ታዳሚውን የማቀፍ የመሳብ ሃይላቸው ማግኔታዊ ነው እኮ። በእያንዳንዱ ቃል ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች እንዲሁ የሚታለፉ አይደሉም። የንግግር ክህሎታቸው እና ጸጋቸው ከተለመደው ውጪ ነው ግርማው። እንዲያውም ካነሳችሁትማ በዚህ ንግግር ውስጥ የሆነ የተቀሙት ነገር እንዳለ ይገልጻል አስተውላችሁ እዩት፤   የእኔ ግን ሌላ ነው ጭንቀቴ። አንደኛው ህልሜ ነው። ባዶ ወንበር እና የሌላ ፓርቲ ሊቀመንበር ግማሽ አካል ምን ማለት ነው ይሄ?   ሌላው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሴራ እና የኖርንበት መከራ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ እና የተስፋው ዘላቂነት ሁልጊዜ እክል ይገጥመዋል። ለግለግ ብሎ ወጥቶ እንዲታይ ተስፋ አይፈለግም። ትንሽ ደስታ ሲፈነጥቅ ያን ለማጠልሸት ወዲያው

ያልተጠናቀቀው ጉዞ

ምስል
ጉዞው ተዘጋ ወይንስ ተከፈተ? ተስፋ አለን ወይንስ ተሰደደ?  „የከበረ ስሜን የወደዱትን ሰዎችንም በበራ ብርሃን ከጋሃነም አወጣቸዋለሁ። አንዱንም አንዱንም በከበረ በክብር ዙፋን አኖረዋለሁ፤ የፈጣሪ ፍርዱ ዕውነት ነውና፤ ቁጥር በሌላቸውም ዘመኖችም ያበራሉ። በቀኑ ሥራዎች በሚገኝ በመንግሥተ ሰማይ ለታመኑ ሰዎች የሃይማኖታቸው ዋጋ ይሰጣቸዋልና።“ አቤቱ ጌታ ሆይ! አሜን! እንደ ቃልህ ይደረግልን።   መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፵፪ ከቁጥር ፲፫ እስከ ፲፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ 09.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። „ምን ያህል እንተጓዝኩ አላውቀውም። ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቀውም። አለማወቄን ስጠይቀው እሱም አያውቀውም። ተስፋን እጠብቃለሁ።“ ይህ በተስፋ መጸሐፌ ላይ የዛሬ 8 ዓመት ሳሳትመው መጨረሻ ሽፋኑ ላይ የጻፍኩት ነው። ዛሬም የሆነው ይሄው ነው። ምን ያህል ጉዞ እንደቀረን አናውቀውም? ተስፋን ግን እንጠብቃለን። የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ?  ባለቅኔው ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ ቤንሻንጉል ላይ ዝምን ያለ ጥያቄ ሲቀርብላቸው „እኔ ከእናንተ ጋር የማደርገውን ግንኙነት የማይማቻቸው እንዳሉ እወቁ“ ብለዋቸው ነበር እጅግ ባዘነ ስሜት። አዋሳ ላይም „ቡና ታመመ፤ በርበሬ ታመመ“ ሲሏቸው „ አዬ እናንተ ምን ያለተመመ አለና እኛስ ታመን የለም“ ነበር ያሏቸው።  በተለያዬ ጊዜም ስለ ፕ/ ኬኔዲ ደግነት ሲገለጽም ፤ ኬኒዲን ስለተካው ብልህ ሰው እስቡ ይላሉም፤ ይህን አዘውትረው ነው የሚናገሩት። እኔ ባልፍም ራዕዬን የሚያሰቀጥል ትውልድ ይኖራልና ያን የእኔን ሌጋሲ የሚያስፈጽውን ሰው ላይ ትኩረት አድርጉ ማለታቸው ነው። ምስጋናውን ለተኪዬ አቆዩት ማለታቸው ነበር። ከቅደስት ተዋህዶ ጋር በነ

ዴሞክራሲ ቃሉ ሳይሆን የህሊና ማሳው ነው ዕውነትነት።

ምስል
ቁልፍ። „እንሆ አፌን ከፍቻለሁ አንደቤተም በትናጋዬ ተናግሯል።“  መጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ ፴፫ ቁጥር ፪ ከሥርጉተ ሥላሴ 08.08.2018 ከጭምቷ እናትዬ ሲዊዝዬ። v   መክፋቻ። የእኔዎቹ እንዴት ናችሁ ዛሬ የሰነባባቱን ቃለ ምልለሶች ጹሑፎች ቅኝት ላይ ነበርኩኝ እና ይህን ደግሜ በአዲስ እርእስ ማቅርብ ፈልግሁኝ። ስለምን? ዋናው ቁልፍ ጉዳይ ስለተዘነጋ፤ በዛ ላይ የተስተዋሎት አትኩሮት ስሌለ ነው። አቤቱታዬ ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ የነበረ ሲሆን በግልባጭ ለዶር ለማ መግርሳም ነበር፤ የጻፍኩት በ01.06.2018 ከሁለት ወር በፊት ነበር። እርእሱ አብይ ሆይ !  ኢትዮጵያዊ ዜጋ   ከሆንኩኝማ እኔም ዘለግ ያለ ህላዊ   አቤቱታ አለኝ፤ የሚል የነበረ ሲሆን ረጅሙን አቤቱታ ለእርገት ያልኩበት ቁልፍ ጉዳይ ይህን ይመስል ነበር። መጪው የምርጫ ዘመን ብቻ ሳይሆን ዘላቂ ከብክነት የጸዳ ትውልድን ለመገንባት ወሳኙ ቦታ ወሳኙ ቢሮ ላይ ነበር አትኩሮቴ። እውነት ለመናገር አሁን ያሉት የለውጥ መንፈስ የእኔ ብዬ ከዬትኛውም ተቋም ሆነ ግለሰብ ቀድሜ ብቀበለውም ይህን ለውጥ ወደ ዘላቂ አሳታፊ ሥርዓት ለመለወጥ ግን ዋነኛው አንኳር ጉዳይ ለዴሞክራ ግንባታ መሠረት የሆነው የቢሮ አደረጃጃት፤ አወቃቀር አሰራር የሰብዕና አገነባብ ከሁሉም ድርጅት በላይ በዚህ ድርጅት ውስጥ ሥርነቀል መሆን ካልቻለ ዛሬ ያዬናቸው ወይንም የምናያቸው ሐሤቶች በፍጹም ሁኔታ ቀጣይም አይሆኑም፤ ትውልዳዊም አይሆኑም። መንፈሱ ይቀለበሳል። ዴሞክራሲ ምርጫ በራሱ እንኳን ግብ አይደለም። መዋቅራዊ ህሊናዊ መርሃዊ ለውጥ ካልኖረ በስተቀር። እንኳንስ የሁሉም ነገር ጭንቅላት እንዲህ ተዘሎ ቀርቶ። እስከ አቤቱታ 17 ያሉትን ለምትፈልጉ እዚኸው ብሎ