ያልተጠናቀቀው ጉዞ

ጉዞው ተዘጋ ወይንስ ተከፈተ? ተስፋ አለን ወይንስ ተሰደደ?
 „የከበረ ስሜን የወደዱትን ሰዎችንም በበራ ብርሃን ከጋሃነም አወጣቸዋለሁ። አንዱንም አንዱንም በከበረ በክብር ዙፋን አኖረዋለሁ፤ የፈጣሪ ፍርዱ ዕውነት ነውና፤ ቁጥር በሌላቸውም ዘመኖችም ያበራሉ። በቀኑ ሥራዎች በሚገኝ በመንግሥተ ሰማይ ለታመኑ ሰዎች የሃይማኖታቸው ዋጋ ይሰጣቸዋልና።“ አቤቱ ጌታ ሆይ! አሜን! እንደ ቃልህ ይደረግልን።  

መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፵፪ ከቁጥር ፲፫ እስከ ፲፬
ከሥርጉተ©ሥላሴ 09.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።



„ምን ያህል እንተጓዝኩ አላውቀውም።
ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቀውም።
አለማወቄን ስጠይቀው እሱም አያውቀውም።
ተስፋን እጠብቃለሁ።“

ይህ በተስፋ መጸሐፌ ላይ የዛሬ 8 ዓመት ሳሳትመው መጨረሻ ሽፋኑ ላይ የጻፍኩት ነው። ዛሬም የሆነው ይሄው ነው። ምን ያህል ጉዞ እንደቀረን አናውቀውም? ተስፋን ግን እንጠብቃለን።

የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ? 

ባለቅኔው ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ ቤንሻንጉል ላይ ዝምን ያለ ጥያቄ ሲቀርብላቸው „እኔ ከእናንተ ጋር የማደርገውን ግንኙነት የማይማቻቸው እንዳሉ እወቁ“ ብለዋቸው ነበር እጅግ ባዘነ ስሜት።

አዋሳ ላይም „ቡና ታመመ፤ በርበሬ ታመመ“ ሲሏቸው „ አዬ እናንተ ምን ያለተመመ አለና እኛስ ታመን የለም“ ነበር ያሏቸው።  በተለያዬ ጊዜም ስለ ፕ/ ኬኔዲ ደግነት ሲገለጽም ፤ ኬኒዲን ስለተካው ብልህ ሰው እስቡ ይላሉም፤ ይህን አዘውትረው ነው የሚናገሩት። እኔ ባልፍም ራዕዬን የሚያሰቀጥል ትውልድ ይኖራልና ያን የእኔን ሌጋሲ የሚያስፈጽውን ሰው ላይ ትኩረት አድርጉ ማለታቸው ነው። ምስጋናውን ለተኪዬ አቆዩት ማለታቸው ነበር።

ከቅደስት ተዋህዶ ጋር በነበራቸው የመጨረሻ ስብሰባም „እኔ ሳይሆን ፈጣሪን አምስግኑ“ ብለዋል። የታያቸው፤ የታዘቡት፤ ወስጣቸው የሚላቸው፤ ጠረኑ የሚነግራቸው ንጹህ ነገር ነበር። ከራሳቸውም ይልቅ ሌሎች ጎልተው እንዲጡ እግጅ በሚሰጥ አኳሆን ነበር የሚገልጹት፤ አሜሪካ ላይ እንዲያውም ጠ/ ሚሩ ዶር ለማ መግርሳ እንደሆኑ ነበር የገለጡት። ፍሬውም ውጤቱም የሳቸው እንደሆነ። ሁሉን ነገር አዬሩን ሁሉ ፈሩት።

 በሌላ በኩል ብጹዕኑ ለመሰከረም 8 ቀን ሲወስኑም „ጽዋው የዛሬ ነው“ እሰቡበት ብለዋል። ነገ እኔ ላልኖርም ብኖርም ለመሳፈጸም ያለኝን አቅም በእጄ አልቋጠርኩትም አይነት ነገር ነበር።  እኔም በተደጋጋሚ ጊዜም የራስ ተሰማ ናዳው ዘማናይ የአድማ ነገር አነሳስቻለሁኝ የቤተ መንግሥቱ ጠረኑ አላማረኝም እያልኩኝ።

ትናንት አንድ አንብብልኝ የተባለ ጹሁፍ ከአዋዜ አዳመጥኩኝ። ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ አቶ አለምነህ ዋሴ እሱ ያመነበትን ያለመነበት በ% ደረጃ እዬሰጠ አቅርቦታል። 

የሀምሌ 16 አጣዳፊ የድጋፍ ሰልፍ ብዙም አልተመቸኝም ነበር። ይቅርም ብዬ ጽፌ ነበር። ባይካሄድ ምርጫዬ ነበር። የሆነው ሆነ። እንኳንስ የሰኔ 16ቱ ከዛ ቀጥሎ የጎንደር የድጋፍ ሰልፍ እንዲቀር ሁሉ ጽፌ ነበር አስፈላጊ አልነበረም። በብዙ ምክንያት። የተከደኑ ነገሮች ለራስ ጥበቃ ዋስትና ናቸው። ደስታንም በልክ መያዝ ሃዘንም እንዲሁ ስለሚገባ።

ከከደንከው ምን ይታያል? ማን ምን እንደሚያሰብ ይታወቃል?  እንዲያውም ሰርቆ መውደድ እንጂ እንዲህ አደባባይ ማወጣት አደጋው ሰፊ ነው። የቀንጣ ነፍስ ሳይሆን ሳር ቅጠሉ አብይ ሆነ እናም የሆነውም ሆነ። ከ ዓይን ያውጣህ ያለ ወጣት ጋዜጠኛም ነበር የሳይንስና ቴክኖጂ ሚ/ር በነበሩበት ጊዜ።

የስሜን አሜሪካ የስፖርት ፌስቲባል ላግኛቸሁ ምኞትም ግብዣውን የመቀበል ጉዳይንም መጋበዝ የላባቸውም የሚል ጥያቄ ሲነሳ ከጠቀመ ይሆን ካልጠቀመ ይቀር፤ እግዚብሄር የወደደው ይሁን ብዬ ነበር። እርግጥ ነው ጉግሱ ሲጠና አውሮፕላኗ በሰላም ስለመግባቷ እስኪ እንሰብ ሁሉ ብዬ ነበር።  

የሆነ ሆኖ ሁለተኛ ታቅዶ ሲከወን ግን ዝማታን ነበር የመረጥኩት። እንዲያውም ፈቃደ እግዚአብሄር የአባቶቻችን አማላክ የሠራው መልካም ተግባር ነው፤ የሰላም ፋውንዴሽን ስብሰባ ላይ መገኘታቸው ሁሉ ፈቃደ እግዚአብሄር አለበት ብዬ አስቤ ነበር። በተደጋጋሚ የኑዛዜ ያህል እስኪመሰል ድርስ ያገዟቸውን ብቻ ሳይሆን ቁልፉን ሚስጢርም አውጥተውታል። ምስጋነውን ለእኔ ሳይሆን ለዶር ለማ መግርሳ አድርጉልኝ በማለት። ምስጋናውን ለዶር ወርቅነህ ገበዬሁ አደርጉልኝ በማለት። በመሃል ደግሞ እኔ ህልም አይቼ ነበር።

ባዶ ወንበር አንድ ሰው ከላይ እስከታች የተገመሰ ግማሽ ሰው ወንበሩን እዬተመለከተ አዬሁኝ፤ እኒያ ወገኔም የፖለቲካ ድርጅት መሪ ናቸው።
እንደ ዓለምአቀፉ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ አንብብልኝ የተባለውን ጹሁፍ ሲቀርበው አውሮፕላን ውስጥ የተፈጠረ ነገር ነበር ይላል። በሌላ በኩል ደግሞ  በአንተኖብ የተጫኑ የታጠቁ ሃይሎች መቀሌ ገቡ የሚል ሌላ ዜናም ነበር በተመሳሳይ ቀን።

እነኝህን ሁሉ በማያያዝ እንደገና ወደ ራስ ተሰማ ናደው አድማ እና ወደ ውጤቱ አያመራን ይሆን እያልኩኝ ነው። ባዶ ወንበሩስ? ፍቹ እና ሚስጢሩስ? ሌላው ከተጠቀሰው ውጪ አቶ ዳውድ ኢብሳም ኤርትራ እንዳገኟቸው እና በቅርቡ ኤርትራ ሄደው እንደሚያናግሯቸውም ገልጸው ነበር። የሄዱት ግን ዶር ለማ መግርሳ እና ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ ናቸው።

እርግጥ ነው ቅኑ ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ ቦሌ እንደ ደረሱ አዲስ መግለጫ ሰጥተዋል። ይህ መግለጫ እና እድምታው ግን ብዙ ነገር ይናገራል። ምን ያህል ተጉዘን ምን ያህል ላይ እንደ ቀረን? ተስፋ አያልቅም ተስፋን ማለም እንቀጠል ግን ከእንግዲህ ቅኑን ቸሩን ደጉን ግልጹን ንጹሁን ጠ/ ሚር ባሰበው ልክ፤ ባቀደው መጠን፤ በወጠነው ልክ እናገኛዋለን ብዬ አላስብም። ያው ሁልጊዜ እንደምጽፈው እኔ ፈሪ ነኝ።

ስለሆነም ከእንግዲህ ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድን ብዙ ባናስጨንቃቸው እመርጣለሁኝ ጤና ከሆኑ።  ከሳቸው ራስ ወረድ በማለት መጪውን ድቅድቅ የጨለማ ጊዜ እንዴት መሻገር ይቻላል ቢሆን ይመረጣል።

ጥጥቁን የፈታው የነፃነት ትግል አቅምን አደራጅቶ ህሊናን ማሰናዳት ይገባል። ምርቃኑ ተነስቷል። ድሮም ያልጣማቸው ያልፈቀዱት ያሻቸውን ያህል ታግለውታል። ግን እሳቸው ፍጹም ንጹህ ሰው ነበሩ።  

መንፈሳቸውን የፈቀደነውን ግን ቢያንስ ለመንፈሳቸው አቅም መቅኖ አይዞህን ስንልክ ጸሎትም እንዳረሳለን። ስለዚህ የሚጸጽተን አንዳችም ነገር የለም። ቅንነትን እንኳን መጣህልን ብለን ከጅምሩ ጀምሮ በሃሳብ ደግፈናዋል።

ታመኑም አልታመኑም ከእንግዲህ እንኳንስ የሌላውን ግዴታ የሳቸውን በህግ የተሠጣቸውን ግዴታም ለመወጣት አንዲት ጋት ፈቀቅ አይሉም ለዛውም በጤናቸው ከኖሩ። በዚህ ዙሪያም ፍንጭ አትወጣም። የወንጀሎች መበራከት እና ምንጫቸው ያልተወቀ አደጋዎች ደግሞ ቀጣይ ናቸው።

ይልቅ ከዚህ አቅጣጫው ካልተወቀው ጉዞ ራስን ማውጣት ራስን ማዳን ይገባል። ለአዲስ ዓመት አዲስ አባባ እንሄዳለን የምትሉም ወገኖቼ ማለቴ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ማለቴ ነው አደብ ይኑራችሁ፤ ልክ ወያኔ እንደገባ እንደ የእርቀ ሰላም ጉባኤ አባል ወገኖች ቀልጣችሁ ትቀራለችሁ። ምዕራፍ አንድ ተጠናቋል። በምዕራፍ አንድ ንጹህ መንፈስ ፍጹም በሆነ በፍቅራዊነት የተመራ ሁሉንም እኩል ያስተናገደ እግዜራዊ ትህትናዊ ጊዜ ነበር።

ያ ጠቀምም አልጠቀምም አልፏል። አሁን ምዕርፍ ሁለት ተጀምሯል … ምዕራፍ ሁለት ጉሽ ነው። ምዕራፍ ጉለት ጎማማ ነው። ለራሱ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌሰቶ ማህበርተኞችም የከፋ ነው። በነበረው ቅን መንፈስ ላይም አድማ ላይ የባጀው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ራሱንም ሊደረምሰው ይችላል … አይታወቅም፤ ያን ቅን መንፈስ አግዞ፤ እርድቶ ነፍሳትን ማዳን ሲገባ የዳሽን ተራራ ያህል ሆኖ ሴራ ሲሸርብ ነው የከረመው።

ለወያኔ … እንደ ቀደመው ወገኖቼ ንብረት ተቃጠለባቸው ጫጫታ ወደ ህይወት ዋስትና የወልዮሽ ማቅ ይሆን አይታወቅም … በሁሉም አቅጣጫ ይምጣ ያቺ መከረኛ እናት፤ ሚስት፤ እህት ልጆች አሁንም በዬቀዬው ዋይታ እና ለቅሶ ላይ ናቸው።

ከልብ የማይጠፉት ዶር አብይ አህመድ እሳቸው ታሪካዊ ድርሻቸውን በጥድፊያ ተወጥተዋል። ከዚህ በኋዋላ የአብይ ሌጋሲን የሚመራው ሌላ ሃይል ነው። እሳቸውን ምንም ነገር ላያደርጓቸው ይችላሉ፤ ስለምን? ያ የተሰበሰበ የመንፈስ ሃብትን ጥሪት ነው፤ በዛ ድልድይ መጠቀም ይፈለጋል። ዝምታውም ለዚህ ይሆን። እራሱ ያን የወልዮሽ ቅን መንፈስ የበላው ጅብ አልጮኽ አለ? 

በሌላ በኩል የምዕራቡ ዓለምም ጉዳይ አለ፤ ይህም ሌላው ፈተናቸው ነው ለመፈንቅለ ምልዕት መንፈስ ጠላፊዎች። ህዝቡም ሊያመጣ የሚችለው ግብረ ምላሽ አይታወቅም፤ ስለዚህ የሽግግር ጊዜውን በተፈቀደላቸው ልክ ብቅ እያሉ ብቻ ያስታምማሉ ጤና ከሆኑ ማለት ነው፤ ስለሆነም እንዲያው እረድቶን ከገኘናቸው እንዲህ ብለህ ነበር ለምን አለሆነም፤ ይሄ ቀርቷል ይሄ ወርዷል የምንልበት ሁኔታ አይኖርም… … ቀድሞውንም አላወቅንበትም።   

ምን ያህል እውነተኛ፤ ምን ያህል የእግዚአብሄር ሰው፤ ምን ያህል ሰውን እንደሚያምኑ፤ ምን ያህልስ ቅን እንደሆኑ፤  ምን ያህል የምህረት ስጦታ እንደሆኑ፤ ምን ያህል ቅዱስ ሰው እንደሆኑ የበለጠ ከውስጣቸው ተገልጽዋል።
 ስናከለክልቸው የነበረነውም ተገስ ብለን በጸሎት ልንረዳቸው ይገባል። 

ሲሆን ሲሆን ቤተሰባቸው እና እሳቸው በጤና ከኖሩ በሰላም ከአገር ቢወጡ ምርጫዬ ነው፤ ከፈቀዱላቸው የመንፈስ ጠላፊዎቻቸው፤ ለነገሩ እሳቸውን ድራሻቸውን ማጥፋት አይፈልጉም፤ በሳቸው ቅንነት እና በሚያመርቱት የፍቅር ሠረገላ አቅጣጫ የለሹን ምዕራፍ ሁለት እንዲቀጥል ይፈለጋል። ሃብቱ እኮ ህልም ነው የሚመስለው የመንፈሱ ጥሪት።  

ክቡርነታቸው ግን የ10 ዓመቱን ተግባር ከውነውታል። አቅጣጫ አመለካተዋል፤ ያላቸውን ራዕይ ሳይስቱ ዘርግፈውታል፤ ተመክሯቸውን በልግስና አቅንተዋል፤ አስተምረውናል፤ ታላቅ የተግባር ሐዋርያ። ሌላም ንድፍ ካላቸው ይህን ጊዜ ቢጋሩ ተወስዷል። ቢጋሩም ጊዜ ጠብቆ በሌላ አካል ኮፒ ራይት እንዳይጠዬቅበት ተደርጎ እንደሚፈጸም ተከድኖ ይቀመጣል።

ስለሆነም ጠ/ሚር አብይ አህመድ ነባቢታቸው እንድተቀጥል ከተፈቀደ በዛ አቅም እና ጉልበት ከእንግዲህ ደግሞ ማዬት ይቻላል ብዬ አላስብም። በሰውር ከተደራጀው ሃይል ፈቃድ እና ውሳኔ ውጪ ምንም ማድረግ አይችሉም። አዲስ መሪ ተሰጥቷቸዋል ብዬ አስባለሁኝ። ቅደመ ሁኔታ ተቀምጦላቸውል፤ ፈርመዋልም ብዬ አስባለሁኝ። ይህ ምንም ባልተረጋጋበት ኢትዮጵያ ላይ መፈጸሙ አግባብ አልነበረም።

ይህን ያደረገውም ሃይል የመረጠው ጊዜ እራሱ ትክለኛ አልነበረም። ይህን ሁሉ ያደረገው ግን የድጋፍ ሰልፉ ያመጣው ጦስ ነው። እልህ እና ቁጭት ፈጥሮ ሌላ ስጋት ውስጥ ለውጡን የከተተው።

ክፉዎች ምንጊዜም ክፉ ናቸው። ክፋታቸው ደግሞ እነሱ ፈልገውት አይደለም። ይህን የሚያደርገው ዴያቢሎስ ነው። የሆነ ሆኖ ቢያንስ ለሚሊዮን እናቶች ዕንባ ቢታሰብ መልካም በሆነ ነበር። አሁንም ሌላ ስደት በገፍ … አሁን ሌላ ጭንቀት በገፍ … አትሳቁ ተብለን የተረገምን። ደስታችን ቅጽበት፤ ፈገግታችን ቅጽበት፤ ሀዛናችን ዝልቅ … መከፋታችን ዝልቅ … ያልታደልን።

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ መፈንቀል መንግስት የአፍሪካም ህብረት ዓለምም የሚቀበለው አይደለም። ያለው መፈንቅል የመንፈስ ነው። የመንፈስ መፈንቅለ መንግሥቱ በተለያዬ ሁኔታ መጠቀስ ይችላል።

የሆነ ሆኖ ወንበሩ በህልሜ እንዳዬሁት ወንበሩ ባዶ ነው፤ ይህንንም ለአንድ የኢሜል ወዳጄ ጽፌለታለሁኝ ህልሙን ባዬሁት ማግስት። አሁን መሪው ሃይል ነው። ሃይሉ ደግሙ ስውር ነው። በዚህ ውስጥ የፈጣሪ የልዑል እግዚአብሄር የድንግል ማርያም ቸርነት እና በረከት ደግሞ አለ። አሸናፊ እና ተሸናፊው የሚለዬው ሰው ሳይሆን አማኑኤል ነው። እኛ ደግሞ የተሰጠንን ለመቀበል ዝግጁ መሆን አለብን። ቢያንስ ቢሆን ብለን በመንፈስ መሰናዳት። ተሰጦንም ምርቃት አላወቅንበትም።

በዚህ ውስጥ ነው የቆሞስ እንጂነር ስመኘው ጉዳይ የሚታዬው። በዚህ ጉዳይም ላይ ለፈጣሪ ሰጥቶ መቀመጥ ነው። ምክንያቱም በዳዩም ተባዳዩም ጥርጣሬ እንጂ እውነት ቁሞ አይናገረም። ፖለቲካ ጥሩ ያለሆነ ከይሲ ነገር ነው።

በዚህ ሂደት ከአዲስ አባባው የድጋፍ ሰልፉ እስከ እንጂነር ስመኘው ህልፈት ድረስ አንድ ሀዲድ አለ፤ ይህ ሐዲድ በራሱ ሌላ የተከደነ አምክንዮ አለበት። ይህን ለባለሙያዎች መተው ይገባል። አብሶ ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በቅንነት የሚያቀርባቸው ዘጋባዎች አሉ። የእኛ ድረሻ ሀዘንኑን መጋራት ብቻ ነው፤ ከዛ ያለፈውን ግን  የገሃዱ ዓለም ባለሙያዎች አሉ፤ ደህንነትን በሚመለከት። መጸለይ ነው መፍትሄው። ውስብስቡን መከራ የሚያስታገሰው ጸሎት ብቻ ነው።

ነገረ አባይ ደግሞ የዓለም አቀፍ የፖለቲካ አጀንዳ ነው፤ እንደ መንፈሳዊ ሰው ደግሞ ይህንም ቢሆን ለእግዚአብሄር መተው። የሚሆነውን ነገር ሁሉ ለአንድዬ መስጠት። ኢትዮጵያ በ2030 ትከስማለች ይላሉ ባለሙያዎች፤ ይህን እንግዲህ መዳኛችን ሲመጣ ለመዳኛችን ደግሞ ሌላ ሳንክ ከገጠመው፤ የተገባውን የጥበቃ ተግባር መከውን ካልቻልን፤ ጉልበት ያለው ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሄር ዘንድ ስለሆነ ለእሱ መስጠት ነው።

ለሁሉም የተሻለ ጊዜ ነበር የአብይ ሌጋሲ አዋከብነው፤ ባለቀ ሰዓት ደገፍነው ደግሞም  አመለጠ። በዚህ ሂደት አሁንም እኔ እምመክረው ቅኖች ለራሳቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ብቻ ነው አብሶ የገዱ መንፈስ። ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ ውጪ አገር ነው ወደ አገር ባይመለስ ምርጫዬ ነው። አድራሻው ያላችሁ መልዕከቱን ስጥሉኝ። አለስፈላጊ መስዋዕትነት አይገባም። ነገሮችን አለዝቦ አያያቸውም። ስለተ ቢስ ነው። ግንቦት 7 እንዲሁ አርፎ ይቀመጥ። ለጊዜው ምዕራፉ ተዘግቷል። አደብ የሚከፍተው ሌላ በር ካለ በዛ ደግሞ መሞከር ነው።

አሁን እራፊ የመንፈስ ማረፊያ የለም። የድጋፋችን ፊርማው ሳይደርቅ የሆነው ሆኗል። አላዛሯ ኢትዮጵያ ዕጣዋ ይሄው ነው። እርግጥ ነው ነገሮችን ረገብ ተደርገው እንዲያዙ ይደረጋሉ፤ ነገር ግን አብይ የት ሄድክ፤ ያን ሳታደርግ ይህን ሳታደረግ ልንለው አይገባም።

በሰውሩ መንግሥት በፈለገው መልክ ትንሽ ደስታ የበዛ ሃዘን ስናስተናግድ ቆይተናል አሁን ግን የዛች ደስታ ሙሴም ራሱም ለራሱም መንፈስ ጭንቅ ነው። ሻማዋ ጭላንጭሏ የት ገባች?

የሆነ ሆኖ ጫና ልንጨመርበት አይገባም። ምን አልባት ይሄ መላመት ሊሆን ይችላል። ግን በህልሜ ያዬሁት ባዶ ወንበር ደግሞ ከሆኑት ነገሮች ጋር ሳገናዝበው እንዲህ ሊሆን ይችላል ይለኛል።

ሽግግር …. ቀደም ብሎ እስከ ቀጣዩ ምርጫ ጊዜ ነው የምታስፈልገን፤ ከዛ ለቀቅ የሚሉ ሁሉ ቃለ ምልልሶች ቀደም ባለው ጊዜ ይደመጡ ነበር … ሰው ነፍሱን በጨርቅ የቋጠረው ይመስል። እኔ እራሱ የዶር ለማ መገርሳ የኤርትራ ጉዞ ምቾት አልሰጠኝም። አንዱ ፈተና ሳይወጣ ሌላ ዳጥ እና ምጥ … ምን አለ አሁን እንኳን ስክን ቢሉ … ምን ያጣድፋል። እዬፈረሰ እዬተናደ እኮ ነው አሁን ያለው ያን ማረጋገት ሲገባ …

መቼም በዚህ መራራ ትግል ውስጥ ለመሳተፍ ልጅን አለመፍጠር መልካም ነገር ነው። ልጅ ከፈጠሩ ግን እጅግ የሚከብዱ ነገሮች ይኖራሉ። ምረጥ ነው ልጅህን ወይንስ መንገድህን? ለድንኳን ህይወት ይህ ሁሉ ፍዳ 8ኛው ሺህ በመጣ እና በገላገለን?

አቤቶ ግንቦት 7፤ አቤቶ ኢሳት ባገኛችሁ እኔ ጠበል ነው እማስጠምቃችሁ የነበረ። መሄድ የምትባለውን ነገር እንዳትሞክሯት። የተደሞ ጊዜ ይኑራችሁ። የሃይል አሰላለፉም ሁኔታውም ድፍን ነው ድንብልብል። ይልቅ ይህን የእመቤታችን ሱባኤን ሁሉንም ነጻ እንዲያወጣ እንጸልይ። ዛሬ የአብይ መንፈሰም ካቴና ላይ ነው።

እግዚኦ! ፈጣሪ ሆይ! የሆነውን ሁሉ ቻልን፤ የሆነውን በደል ሁሉ እንዳልተፈጠረ አደርርገን እረሳን፤ አቤቱ አንተ ይቻልሃል እና አብይ እና ቤተሰቡን ነፃ አውጥተህ ውጪ አገር ነፃ መሬት ላይ ደግመን እናዬው ዘንድ እርዳን። አሜን!  ካልተፈቀደልን ሳቅ፤ ካልተፈቀደልን ደስታ፤ ካልተፈቀደልን አብሮነት መቼስ ምን እናደርጋለን?

እኔ የማዝነው ለድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች፤ ሚስቶች፤ አህቶች፤ ልጆች ነው። ትናንትም፤ ነገም፤ ከነገ ወዲያም … መቼ ይሆን በአላዛሯ ኢትዮጵያ  የዕንባ እርም የሚወጣው?

ስለምን ያ ጠንቀኛ የአዲስ አባባ ሰልፍ ተካሄደ? ስለምንስ ተፈቀደ? ስለምንስ የአባይ አጀንዳ በጥያቄ በሙሁራኑ እንዲነሳ ተደረገ? ስለምንስ በችኩላ መረጃው ተለጠፈ? ነገር ሁሉ ለበጎ ወይንስ?
 
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
የኔዎቹ ቸር ወሬ ያሰማን። ጭንቀቴ መርግ ነው ግን ለድንግል መሰጠት ነው። እሷው እንደ ትሸከመው።


መልካም የጸሎት ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።