ዝም አትበሉ መንገርም ማናገረም መልካም ነው።
ግዙፉ የግንቦት 7 ፈተና። „ደሴቶች ሆይ በፊት ዝም በሉ አህዛብም ሃይላችውን ያድሱ፤ ይቅረቡም በዚያን ጊዜ ይናገሩ፤ ለፍርድ በአንድነት እንቅረብ“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፵፩ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 05.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · መራረነት ጣፋጭነትም የእግዜሩ ሰውኛ ናቸው። የዚህ ጹሑፍ ጭብጥ የሚመራቸው ይኖራሉ። ያው ሥርጉተ ሥላሴ እንደምትማራቸው ዓይነት። ግን ዘመኑ መራራን ማድመጥ አትራፊ ስለመሆኑ እዬታዬ ነው። መራራውን መናቅ ደግሞ የውድቀት መጀመሪያ ስለመሆኑም ዘመኑ ተመሰጠረበት። ከመራራዎቹ አምክንዮች ነው ዛሬ ላይ ትርፍ እዬተዛቁ የሚገኙት። ከ66 አብዮት ማግስት ነገረ አማራ በጥርስ የተያዘ ግን በመናጆነት የተቸነከረ ጉዳይ ነበር። የመፍትሄው ቁልፍ ግን ከነገረ አማራ ላይ የተነሳ መንፈስ ብቻ ነበር። ማለት አማራነት መራራነት ነበር ግን በራሱ አቅም ውስጥ ጎልቶ እንዳይወጣ ቁልጭ ያለ መድሎ ነበር። አሁንም አለ ትሉ ይሆናል ጊዜው ልጅ ነው እና የአብዩን መንፈስ በዚህ መንቀስ ብዕሬ አትደፍረውም። ላያቸውም የምፈቅዳቸው የጊዜ ሰንጠረዦች አሉና ... ነበር ስል ግን አሁን የለም ለማለት አይደለም። አልተጀመረም ቀድሞ ነገር። ነገረ አማራ በፖሊሰ ደረጃ ነው ጭቆናውም፤ ግለቱም። ስለዚህ ተንስኤው የፖሊሲው መወገድ ብቻ ሳይሆን እጭ የሰሩ ጸረ አማራ እሳቤዎች ጊዜ ብቻ ነው ነቅሎ የሚጥላቸው። ዛሬ እንኳን በ እኛ አቅም ለተገኘ መባቻ የሚታዬውም፤ የመደመጠውም ድፍረት ማጣቱም እዬታዬነው። ይህን መሰረት ለማስያዝ በራስ ውስጥ የበቀለ አቅምን በመገንባት ብቻ የሚገኝ ነው። ይህም መራራ ጉዞ ነው። አሁንም አማራነት መራ...