የወግ ገብታ ... ለመንፈስ ዝና።
ካለ ቀጠሮ
„ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤
የአምላካችን ቃል ግን ለዘላዓለም
ጸንታ ትኖራለች።“
(ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፵ ቁጥር ፩)
ከሥርጉተ©ሥላሴ 05.08.2018
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)
- · ማካሄጃ።
የኔዎቹ ክብረቶቼ እንዴት ናቸሁ? ያው ነው ይህ ዘመን እንዲህ ነው ኃዘን ተፍሰኃ፤
ትናንት የሰላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ የትፍስህት ቀን ነበር፤ የክርስትና እና የእስልምና ዕምነት ሊቃውንታት ቤታችን፤ ማዕዳችን
መነሻችን መሰረታች ሲሉ በአሃቲ ቅን ልቦና ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ወስጣቸው አድርገዋታል፤ ዲያቢሎስም ቅስሙ ተሰብሯል፤ የ27
ዓመቱ የወያኔ ሃርነት የፖሊሲ ቅስም እንኩት ብሎ እንጦርጦስ ተልኳል። ተመስገን!
የቅድስት ቤተክርስትያናችን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማህበረ ምዕምኑ በሙሉ የሌሎቹን እምነቶችን አቦን በልባቸው ፍሬ ነገር መጸሐፍ
የጻፉበት የውል የኪዳን ብፅዕት ዕለት ነበር። እንኳን ደሰል አለን!
በሌላ በኩል የሁለቱ ብፁዓን አባቶች የክብር አጠራር ወጥ አልነበረም። ዝበት ነበረው። ይሄ በቤተክርስትያን ወግ እና ሥርዓት የተገባው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ሥርዓተ አልበኝነትን አይቻለሁኝ። እንደ አባት አደሩ ሊሆን ይገባል። ቤተክርስትያናችን ለሁለመናዋ ሥርዓተ ህግጋት ቅደምት ተከተል አላት። ከማንም ከምንም ችሮታ አትጠይቅም። አባ ዝምታ ቅደስናቸው እጅግ የጠለቀ በመሆኑ ዋጋው የሚወራረደው በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ነው። መበጠስም ያመጣል።
በሌላ በኩል ደግሞ ልባችን የተሰበረበት የፍቅር ከተማዋ ደግሞ ቃጠሎ ነዲድ፤ ይህም
አልበቃ ብሎ የወገኖቻችን ተስፋ ደግሞ እንደ መባጃው ስደት ወደ ጁቡቲ
… ሆኗል። የተሰጠን ይሄው ነው፤ ወይ ተረግማናል ወይ ረግማናል ሌላውን ያለ አግባብ።
ውዶቼ አዱኛዎቼ --- የሆነ ሆኖ ይሄ ለህትም
ካልበቃው 8ኛው የወግ ገበታ መጸሐፌ ውስጥ ያለ ነው።
የአጻጻፉ ንድፍ አሽሙር፤ የስድ ንባብ ቅኔያዊ ቅኝት ነገር፤ ትንሽ እንደምርምር ቢጤ፤ በጥቂቱም ትምህርት ጠቀስ የሆኑ
ለግንዛቤ የሚረዱ „የንግግር ጥበብ“ ዓይነትን አዋዶ የተዘጋጄ ነው። 80% እጅ አጭር አጫር ስድና የሥነ ግጥም ዝንጠዎችን ያስተናገደ
ወጋ ወግ ነው፤ ቆራጣ ነገር ነው >>>>> ብዙ ነገሩ አልቋል። የተጻፈው በ2015 ላይ ነው አላሳተምኩትም
… ምን አልባት ጉልበተኞች እንደ ሰሞናቱ ተግ ካሉ ይታሰብበታል … አሁን ወደ ጭብጡ እንሆ ...
- · እኮ ስለምን?
አይወጣም ነፍስ ይላሉ። ግን ሲታሽ ይወጣል፤ ይመነጠቅ እንጂ ማን ከልካይ ሲኖርበት እልፍ ይመጣል በሠጋሩ።
ሲፈተግ በግፍ ይለያል ያንዘረዘር ማንስ ጌታ ሲኖርበት፤ እኮ ማን?
ሲሾከሾክ በበቀል ሲነተርክ ይላል ስብር እንኩት እንጂ በጉማጂ
እዬተጎማጀ ለምን ነፍስ ካለቀጠሮ አይወጣም ይላሉ? እኮ ስለምን?
ሲበዛ እኮ ሲጠነዛ፤ ሲደራረብ እኮ ሲነባበር፤ ሲተርፍ ሲሞላ ሲቸረፍስ፤ መከራው አይሎ
ሲል ሆ! በል ሲከር መበጠሱ አይቀር ታዲያ ምን ሆነው ነው ከቶ ነፍስ ካለ ቀጠሮ አይወጣም የሚሉት?
እያገለበጠ ሲለካው፤ ሲሰነዝረው ሲመነጥረው፤ ሲሰፍረው እንደ እህል ያ ወመኔ ጠኔው፤
ሲወቃው ሲሰለላልቀው እየገላበጠ ሲያጤያጢሰው በክርኒ እህል እህል እያለ ማለፉ አይቀርም፤ ዋ! የሰው ልጅ ታዲያ ለምን ይሆን ነፍስ
ያለቀጠሮ አይወጣም ያሉት?
ምነው እንጂ ይሆናል፤ ስጋት ሰቅዞት ሰንጎት፤ ፍርፋሪ ወዝ ጠምኖበት፤ ጠኖበት አኩሩፈበት
ከናፍሩን እንደ ሊማሊሞ ጠምልሎበት ወይ ሸብልሎበት፤ ወስፋት ሲንጫ --- ጫ፤
ብር ትር ልትል ነፍስ ክሯ ሊበጠስ፤ በሰላማዊ ሰልፍ ሲጎን
ኡኡታውን በዝምታ ሲያንኮራፋው፤ መጋኛ ሲመራ ሲነዳ እንደ ጉድ፤ ሲያደርግ የምር ምጥጥ ስልቅጥ ውቅጥቅጥ … ልሳን ደርቆ ንግግር
በቃኝ ሲል ሲፈላበት ሲንተከትክ በስፋት ለምን ይሆን ነፍስ ያለ ቀጠሮ አይወጣም የሚሉት? እኮ ስለምን!ይወጣ እንጂ ልይት በመለዬት ግማድዮሽ ... ህም!
ሲሰለስል እንደ ጉርሽጥ፤ እስኪ አሰቡት አስሉት ጥዋት መክለፈቱ ቢቀር ቀን እኩልም
መሻሪያው ቢያር አመሻሽ ላይ መክሰሱም ቢያኮርፍ ማሰረጊያው ቢሆን ምንም፤ ቱክ የለ ጠክ፤ እኮ እንቅልፍ እንዴት ይወሳዳል፤ እየታጨዱ ያው ህልፈት ብቻ።
የኩላሊቱ ባንድ በድርቀት ተዋዝተው አታሞውን በባዶነት ቃር ሲያጎጉኑት ታዲያ ለምን ይሆን ቀደምቱ ነፍስ ካለ ቀጠሮ አይወጣም ያሉት …? ይል እንጂ እብስ ቅልብስ ... ላይመለስ ሽው ...
ይሆናል እንጂ ትቢያ የራህብ አጭዳው ሆታው ሲደራ፤ የወስፋት ፉከራው አይሎ ሲያላገበት፤ ፋፍሪካው ጥሪ ዕቃ አጥቶ ሲንገጫገጭ ሲጮህ በኡኡታ ተደሞ ...
የጠኔ ሙላቱ ሲገነፍል አስለቃሹን አሰልፎ ከች ይላል እንጂ ጥቁሩ ቀጠሮ ሳይጠብቅ በዬምድጃው በነፈስ ወከፍ እያሳለ ይሰለስለዋል
ወገኔን እራበኝ እንዳለ …. የራህብ ዓይነቱ በመጠኑ ላይመጠኑ፤ በወርዱ ላይወራረዱ፤ በቁመቱ ላይለካኩ በልቅ ዓለም ሊሰለቅጥ …
አይቀር መሆን እንደ ልንቁጥ…
አልቦሽ በበነገታ።
ለሞት ቀጠሮ የለውም
ለጉሮሮ ማርጠቢያ ከሌለው
እፍ ነው ያለተኩስ
በትክዝ እብስ …
ለይመለሱ ለሽ ቅልብስ …. ፍስስ …. ሽልብ
ድብን እንዳሉ ብንንንንን
የአፈር ሲሳይ ገላው …. ፍርክስ
መጪ ነው … ሰኔል ተንተርሶ ፍስስ
ቹቻን ጎርሶ ፍልስ ….
አልቦሽ በበነገታ
ሲጋታ የማታማታ ተስፋ ሲመታ!
አይበሉ ቀጠሮ የለውም ለሞትይቀነጥስ የለም ወይ ለጋ - ሀገር ምድሩ በራህብ ሲፈታ አልቦሽ በበነገታ።
መኖርን ማኖር ካቃተው መኖር ባለመኖር ይላል ኩልልልልልልልልል እስቲ ልበል ገለል …
ግልግል።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
የኔዎቹ ኑሩልኝ። እናንተን አያሳጣኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ