አለማወቅን በዕውቀት መቀበል መቻል።
ጥሞና ስለህሊና።
„ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ ሰማይንም በስንዝር የለካ፣
የምድርንም አፈረ በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፤
ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም
በሚዛኖች
የመዘነ ማን ነው?“
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፵ ቁጥር ፲፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ።
05.08.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።
- · መቅድመ ሃሳብ።
የኔዎቹ ቅኖቹ ውዶቹ እንዴት ናችሁ?
በዬወቅቱ አዳዲስ ፓርቲዎች፤ ውህደቶች፤ ህብረቶች ይፈጠራሉ። አዲስ ሁኔታ በተፈጠረ ቁጥር በመገላበጥ
ወይንም በመመሰጥ አዳዲስ ሁነቶችን የተከተሉ በዬዘመኑ አዳዲስ ሊሂቃን፤ ታታሪዎች፤ ጋዜጠኞች፤ ተንተናኞች ይወጣሉ።
አብሶ ፓለቲካ ድርጅት መሠራቾች ሊሂቃን ከወጡ በኋዋላ በመቀደም ይሁን በመሰበር የጀመሩትን ሳይጨርሱ
ሲከሽፍባቸው በሌላ ሁኔታ ደግሞ አዲስ ዓላማ በአዲስ ሥያሜ ሌላ ውጥን ይዘው ይነሳሉ፤ ይህ የማያቋራጥ በዙር ተመለስ የታዬ ጉዳይ
ነው ነገም ቀጣይ ነው። አብን እማዬውም ከዚህ አንጻር ነው።
ከታጋድሎው መንፈስ ጋር አብሮ እንኳን መፈጠር አልተቻለውም አብን። እጅግ ዘግይቶ ለዛውም አስቸኳይ ጊኤዜ አዋጅን ተንትርሶ እና አዲስ ጠ/ ሚር መንፈስ ሲፈጠር ነው ከች ያለው። የነገ ቀጣይነት
ለሚለው ዋቢ የሚሆነው የድርጅቱ አመሰራረት ሁኔታ ወሳኝ ነው። ሞረሽ በቀደመው ፍልስፍና ቀጥሎ ቢሆን ኖሮ ዘላቂ ስኬቱ
አንቱ በሆነ ነበር። ምክንያቱም አመሠራረቱ መርህ እንጂ ወጀብ ስላልነበር።
ነገር ግን እሱም አንዛላለጠው እና ወደ ፖለቲካ ድርጅትነት የተለወጠበት አሰገዳጅ ሁኔታ የአማራ
ተጋድሎ መምጣት ነበር። የተጋድሎውን መንፈስ ሳያጣጥም ነበር በሽሚያ ወደ ፖለቲካ ድርጅትነት የተለወጠው።
ዘላቂ ዓላማ ቢኖር ቀድሞውንም
ሞረሽን በተረጋጋ ሁኔታ የፈጠረው መንፈስ ሲብክስ ሳይሆን ፖለቲካዊ መንፈስ ሰጥቶ ይመሰርተው ነበር። አማራ ተጋድሎ ሲመጣም ሽሚያ
የሚያስኬደው አንዳችም ነገር ባልነበረበትም። ዘላቂ ድሉም ያለጥርጥር እርግጥ ይሆን ነበር።
የሞረሽ ሚደያውም ቢሆን እዛው ባለበት
የኮሚኒቲ ራዲዮ መጀመር ይቻል ነበር። አብሮ አህዱ ቢል። የአማራ ድምጽም የሞረሽን ቀዳሚ ስኩን መንፈስ ይዞ ተነስቶ ከድርጅቱ
ጋር ቢሆን ኖሮ ለማግስታዊነት ታላቅ የታሪክ በር ከፋች በሆነ ነበር። ግን አልሆነም …
ሞረሽ ወደ ፖለቲካ ድርጅትነት የተቀዬረበትም፤
የአማራ ድምጽ የተፈጠረበትም አመክንዮ ያው በተለመደው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች አፈጣጣር ላይ የከተመ ነው። በ አማራ ተጋድሎ መፈጠር ምክንያት ነው። ለዛውም አቶ
ተክሌ የሻው ብድር የሚያስኬድ የተመክሮ ችግር አልነበረባቸውም። ከዬትኛውም የፖለቲካ ሊሂቅ የበለጠ በዘርፉ የሠሩ ናቸው መሬት ላይ። መሬት ላይ መሥራት እና ወረቀት ላይ መሥራት አራባ እና ቆቦ ናቸው። ለዚህ ነው ተጨባጩ እና ህልሙ እንቦጭ አና እንባጮ የሆነው።
- · የመሰባሰብ ሁኔታ የሳሙና አረፋነት ነው - ለእኔ።
የፖለቲካ ድርጅቶች ሲዋህዱ ወይንም ሲቀላቀሉ፤ ወይንም ሲጣመሩ፤ ወይንም ሲገነበሩ ፈቃድ አይጠይቁም።
ተመሥርተናል እርዱን ነው። አይደለም ማህበረ ታዳሚውን የራሳቸውን አባላት እንኳን አያመከሩም። ሁልጊዜ ከላይ ወደታች። በዴሞክራሲያዊ ማክላዊነት አወቃቀሩ ካላይ ወደ ታች፤ የሃሳብ ፍሰቱም ከላይ ወደ ታች ነው።
ራሳቸውን
መርጠው ነው የሚያስቀምጡት። ስለዚህም ገዢውን ፓርቲ ኢህአዴግን ለመውቀስ ካራሳቸው ባልጀመሩት አመክንዮ ስለሚሆን የፋክት ጥሪት
አልቦሽ ነው የሚሆነው ሙግታቸው። ሁሉም ነገር ከራስ መጀመር አለበት። አመንዝራነትን ስኮንን እኔ ከዛ የጸዳሁ መሆኑን በእርግጠኝነት ማወቅ አለበኝ።
- የንፋስ ፓለቲካ ሙጥኝነት እና ብክነታችን።
ወጀብ ሲነሳ ደግሞ ያነን ወጀብ ተከተሎ መጪ ነው። ያ ወጀብ ተግ ሲል ደግሞ ያ ህብረት፤ ያ
ውህደት፤ ያ ትብበር፤ ያ ቅንጀት ይፈርሳል ለዘር ሳይበቃ መራራ ስንብት ይሆናል። የህይወት ጥፋቱን ማንም አያነሳውም፤ እንዲወሳባቸውም
አይፈልጉትም። ስለምን ወደቅን ተብለው እንደጠዬቁ ፈቃደኞች አይደሉም። ስለትናንት መውደቅ ፍርጥር አድርጎ መወያዬት አቅማችን ያኮስሰዋል የሚል ያልተገባ ስንኩል እሳቤ አላቸው ሊሂቃኖቻችን። ይህ ደግሞ የዙር ተመለስ የሽፈት አውራ ተገደው እንዲጨልጡ አደርጓቸዋል። አሳዛኙ ያ ምስኪን ህዝብ ብቻ ነው ...
ሌላው የሚያሳዝነው ቅኖች አብረው ሲፈርሱ እና ሲሠሩ መባጀታቸው ነው። አንድ ቀን ስለሚደግፉት ወይንም
ስለሚቃወሙት አምክንዮ አስበውት አያውቁም። ሰዎችን እንደ ፈጣሪያቸው ነው የሚያመልኳቸው። ፓርቲያቸው ተዋህድኩ ሲል ሲዋህዱ ፈርስኩ ሲል ሲፈርሱ ባጁ። በዚህ ውስጥ የሚደቀው ኢትዮጵያዊነት
ነው።
ኢትዮጵያዊነት ባህሉ፤ ትውፊቱ፤ ታሪኩ ሁሉም ምስቅልቅል ነው የሚለው። አብሮነት ትውፊታችን ነው። ሊሂቃኑ ለራሳቸው ፍላጎት
እና ዓላማ በቀጠሉት ወይንም በተውት፤ ወይንም እንደ ጨርቅ በመቀስ በሸነሸኑት ሃስብ ቁጥር ትውልዱ ባከነ፤ ትወልዱ ታመሰ።
ይህ የሚሆነው ስለምን ነው ቢባል ዘላቂ ዓላማ ያለመኖር፤ በፓርቲ አደረጃጀት፤ አማራር፤ አካሄድ፤
አመሠራረት ላይ የእውቀት ድህነት ነው። በባህላችንም „ወትሮም ባልዘፈንሽ ከዘፈንሽም ባለሰፈርሽ“ የሚለው ብሂል ከዚህ የመነጨ ነው።
ስክንት ሳይሆን፤ እልህ፤ ቁጭት እንዴት ተሸነፍኩ በሚሉ የግል ሰብዕናዎች ዙሪያ በታጠሩ ወጀቦች የኢትዮጵያ እናት እድሜ ልኳን ስታለቅስ
ኖራለች። ከሁሉ የሚከፋው እና የሚከረፋው ከሴራ ፖለቲካ ለመፋተት ቁርጠኝነት አልመኖሩ ብቻ ሳይሆን በመርህ ደረጃ የተያዘ መሆኑ ነው።
የኢትዮጵያ ፓርቲዎች የሚፈለፈሉት ወይ በምርጫ ሰሞን ወይ ደግሞ ህዝብ በቃኝ ብሎ ሲያምጽ ያን
ተንተርሰው ነው። ስለዚህም ሥረ መሰረታቸው የሚያዘልቅ ዓላማን ተንተርሶ አይደለም።
ከዚህ በኋዋላ ህዝባዊ አመጹ አቅጣጫውን ከቀዬረ
እነሱም ተገልብጠው የተነሱበትን ዓላማ እርግፍ አድርገው ትተው ወደ አዲሱ ዘመን ደግሞ በለበጣም ይሁን በመላጣ ይቀላቀሉታል። ምርጫው ሲያበቃ ደግሞ አሁንም ወደ
ተለመደው የፉክክር ወይንም የፍርሰት ወይንም የክፍለት ሁኔታቸው ይጓዛሉ ለዛውም በጥሎ ማለፍ የሴራ ዘመቻ ነው።
አሁን ለቀጣዩ ምርጫ ተሰባሰቡ እያላቸው ነው መሪያቸው ኢህአዴግ። አሁን ከዚህ ላይ መሪያቸው
ኢህአዴግ እንጂ የእነሱ ዓላማ ብለው ያ ሁሉ ህዝብ ከኑሮ እና ከመንፈሱ የተፈናቀለበት፤ አካሉን በሌለበት በሥማቸው ያጠበት እልፍ
ጉዳይ አይደለም። የተነሱበት ታላቁ ተልዕኮ አስተዋሽ አላገኝም። ለዚህ ነው የተጽዕኖ ፈጣሪዎች አንድነት ፓርቲ እንመሠርት አዲስ የሮሮ ጎራ ደግሞ የተከፈተው።
ስለሆነም ለቀጣዩ ምርጫ ሲባል ብቻ ይሰባሰባሉ ወይ ይዋህዳሉ፤ ወይ ይጣመራሉ፤ ወይ ይገነበራሉ።
ከምርጫ በኋላ ደግሞ ሥርጉተ ምን አለች በሉኝ ይበተናሉ። በቃ ቲያትሩ ይሄው ነው።
ስለምን በወስጣችን ያለው ራስን
የማሸነፍ መርህ በውስጥ የበቀለ ሳይሆን በንፋስ ሃይል ስለሚመራ ነው። ለዚህ ነው እኔ አሁን የተፈጠረው መንፈስ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች በላይ የላቀ ሃሰብ ያለው እና ሊደገፍ ሊበረታት ይገባውል ብዬ በጥዋቱ ስተጋበት የባጀሁት። ሁሉም ዕጣ ነፍሴን ስተገባት ወደ ነበረው ሃሳብ እዬተመመ ነው ... ከጥቂቶች በስተቀር ጥቂቶችም ቢሆኑ በ እጅ ያለን ሃብት ብቃቱን አግንነው በማዬታቸው ነው። የለንም አቅም። እውነቱ ይሄው ነው።
የኢትዮጵያ ፓርቲዎች የአመሠራረት ችግር ነው በዚህ ዘመን በሃሳብ ፍሰት ብቻ ተሸናፊ ሆነው
የሚይዙትን የሚጨብጡትን አጥተው የወለሌ ገበታ ላይ የሆኑት። ስለሆነም እንሱ እራሳች ኮርስ ያስፈልጋቸዋል። ተከታታይ ትምህርት ያስፈልጋቸዋል። አባሎቻቸውንም በሞራል የማነጽ ተግባር ሊከውኑ ይገባል።
ደጋፊዎቻቸውም ባለፈው ነገር ተቆጭተው ይሄ ማህበራዊ ኑሯቸውን ትውፊታቸውን ተጋፍተው ሊሂቃኑን አምነው የሚከፍቱትን ጦርነት ልብ
ገዝተው ማቆም አለባቸው። ቋሚ መንፈስ ያልፈጠረላቸውን ሊሂቃን ነው መሪ በማለት በ =እምነት ሁለመናቸውን የገበሩላቸው እና።
ዬትኛውም ፓርቲ ደጋፊዎች በቅን ግለሰቦች ላይ የሚያውጁትን ጦርነት እና እልፊ ሂደው ሰብናን፤ ነፃነት የሚገፉበትን መንገድ
መተው አለባቸው - እርግፍ አድርገው። ከዚህ ዘመን በላይ አሰተማሪ እና መርማሪ ስሌለ።
ሊሂቃኑ እነሱ ሲሳማሙ፤ ሊሂቃኑ እነሱ ሲከበሩ እነሱን ደጋፊዎችን ማለቴ ነው የሚያቋጥራቸው ቀርቶ እግዚአብሄር ይስጥልን
የሚል አንድም ነፍስ እንደማያገኙ ብቻ ሳይሆና ሃላፊነትም፤ ተጠያቂነትም ሳይኖራቸው ግን ስለነሱ ስንማገድ ለኖርነው ታላቅ ተቋም
እነሆ ተከፍቷል ዘንድሮ። "ልብ ያለው ሸብ።"
ሚዲያዎችም ቢሆኑ መሠረታቸው እንደ ዘሃበሻ እና እንደ ሳተናው ዕውነት እንጂ ሰው እንዳይሆን
ከዚህ ዘመን በብርቱ ሊማሩ ይገባል።
- · የሰሞናቱ ፍጥጫ።
እንድም በአቋሙ ጸንቶ ያዬሁት ብቁ የፖለቲካ ድርጅት የለም ካዳመጥኩት ማለት ነው ከስሜን አሜሪካኑ ጉባኤ። ሳላዳምጠው
ከቀረው ሊኖር ይችል ይሆናል። ግን ብዙውን አብሬ ስለኖርኩ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የንፋስ ሃይል እንደሚመራው አሳምሬ ስገልጠው ስለኖርኩ
ከዚህ ውጪ ይሆናሉ ብዬ አላስብም እድሉን አግኝቼ ሁሉንም ባልከታተለው ማለት ነው።
የኢትዮጵያ ፓለቲካ የዓላማ ጽናት፤ የተልኮ ጥራት፤ የግብ ግብዕት
መሠረቱ አይደለም። አንዱ ሌሊት ያስባል፤ ጥዋት ተነስቶ ማንፌስቶ፤ ሥም፤ ዓርማ እና ፕሮግራም
ያወጣል። በቃ በዛ ብቻ እንበናለን። አውነት ለመናገር ሊሂቃኑ ጥሩ አድርገው ሥነ - ልቦናችን
አንበርክከው ገዝተውታል። እንዴት ወደ አሻቸው እንደሚገሩት ተጠብበውበታል። ያላቸው አቅም ይሄ ብቻ ነው። መሬት ላይማ ቀበቶውንም
መዳፉንም አዬነው፤ ተፈታተሽን። ሳይበር ሆነ ጀግንነት።
- · ድንብልብሉ ገመና።
ሌላው ድፍን ያለ እና ድብልብል ጉድ ደግሞ ከቀድሞው ሰማያዊ ፓርቲ ሊቀምንበር ከኢንጂነር ይልቃል
ጌትነት ሰሞኑን አንድ ቃለ ምልልስ አዳምጫለሁኝ። ውስጣቸውን ፍንትው አድርጎ አሳይቶኛል።
በዛ በሳጅን በረከት መንፈስ ተጠምኖ በበረዶ ክምር ለውጥ ይገኛል ብሎ ለድርድር በተማህጽኖ ኤሉሄ ሲል የባጀ፤ ራሱን በአሃቲ መንፈስ ማስቀጠል፤ መምራት፤ ማስታረቅ አቅቶች
በደመነፈስ የተከፈለ ፓርቲ፤ ዛሬ ደግሞ ለውጥ የሚባል የለም ተነሳሽነት
ታይቶል በማለት እጅግ በመታበዬ አገላለጽ ሲናገር ላዳመጠው እውን ኢትዮጵያን ልጆች አሳቢ አሏትን የሚያሰኝ ነው።
ሰማያዊ ፓርቲ ተከፋዩም የአቶ የሺዋስም ቢሆን ያው ኢትዮጵያ እርቅ የሚፈጥር መንፈስ የላትም
የነጭ አደራዳሪ እስከ አልመጣ ድረስ በጅ አልልም ብሎ ሞግዶ መክረሙን አዳምጠናል። ካሉት ይሻላል ከአቶ ደመቀ መኮነን እና ከአቶ
ሽፈራው ሽጉጤ ዶክተር አብይ አህመድ ይሻላል ብሎንም ነበር። ሌላ ተፎካከሪ ሰው ስላልቀረበ ነው እንጂ አለን እኛ እንበልጣለን ነው ነገረ ሚስጢሩ።
የዓለሙ ፖለቲካ ሊሂቃን 20 ዓመት ሙሉ ታክተው እርግፍ አድርገው የተውትን የአፍሪካን መከራ ባሊህ ያለውን
የኤርትራ እና የኢትዮጵያ የግንኙነት ጥበብ አፈጣጠር ጋር ያ መታበይ
ከፎቅ ወድቆ ሲፈጠፈጥ ለዚህ ፓርቲ የተከፈለው መስዋዕትነት ምን ያህል አላስፈላጊ እንደነበር ብቻ ሳይሆን ወደፊትም ቅንጣት አቅም
ማባከን እንደማይገባ ታላቅ አስተምህሮት ነው።
ገራሚው ነገር በዛው በወያኔ ሃርነት ትግራይ መንፈስ በተቀረጸው በኢህአድግ ፕሮግራም፤ ፓሊሲ፤
በህገ መንግሥት ነው ተፎካክረን እናሸንፋለን ተብሎ ለምርጫ ውድድር የተካሄደው። ተው እያልን።
አሁን ደግሞ በተሻለ አዬር ብቻ
ሳይሆን የዓለም የፖለቲካ ሊሂቃን አጀብ ያሉት በ4ወራት ውስጥ ድንቅ
ብሄራዊ፤ አህጉራዊ፤ ሉላዊ ክንውኖች እዬታዩ ዓይኔን ግንባር ያድርገውም ሌላው የአንባርጭቃ ተረብ ነው። ርግጥ ነው የወያኔ ማንፌስቶ
አልተለወጠም ግን ያን የሚዳፈሩ እርምጃዎች ደግሞ አሉ።
ይህ ሁሉ የሆነው ፓርቲ መሥራቾች ገፊ ሃይል ስሜት እንጂ
ዕውቀት አልነበረም። ዕውቀት ስል የሙያ ዕውቀት አይደለም የነፃነት ጥማት ዕውቅት ማለቴ ነው። ነፃነት የመኖር
ነፍስ ፍልስፍና ነው። ነፃነትም የነባቢት ሥነ - ሳይንስ ነው። ብዙ ያንሳናል ስለዚህም ከሀ ጀምሮ በጽኑ ፍላጎት
ላይ የተመሰረቱ ብቃቶችን አምጦ መውለድ ይጠይቃል። ለዛም አለማወቅን በዕውቅት መቀበል ሲቻል ብቻ ነው።
- · ደጋፊው እና አሳሩ። መፍትሄ ያልተበጀለትም ቀጣይ መከራ።
ደጋፊውም እንደ አለፈው ጊዜ በወጀብ፤ በስሜት፤ በአውሎ ሳይሆን ከልብ በዘለቀ የህሊና ብቃት በመርመር፤ በመፈተሽ፤ አገላብጦ በማዬት ነው መደገፍም መቃወምም የሚገባው።
ከዚህ በኋዋላ ወቀሳውንም፤ ናዳውንም፤ ነቀሳውንም ተግ አድርጎ የፈረሰውን ማህበራዊ ሰብዕናን
በመገንባት ላይ ማተኮር የተገባ ይመስለኛል። ማህበራዊ
ሰብዕናችን ፈርሷል። እያዘንኩም እዬሳኩም ነበር የነበረውን የዲሲ ዝግጅት ዘገባ የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የተከታተልኩት። እኔ ቀደም ብዬ ጽፌዋለሁኝ። የሎሳንጅለሱ ግጥሜ እንደነበር ከዛ የተረፈው የሁለቱ ሃይማኖች እድምታም ጣ =ዕሜ ነበር።
አብሶ ሥሜ ላይ ይጻፍልኝ ቀድሞ የፖለቲካ አስተሳሰበችን ብቃታችን ትቢያ ላይ እንዳለ ያሰዬናል። ቁም
ነገሩ ግን ይህን ሁሉ መከራ አይቶ ልዑል እግዚአብሄር መሪ ሰጥቶናል። መሪው ሁሉንም ላያረካ ይችላል፤ መታዬት ያለበት አብዛኛው
መንፈስ በአንድ የሃሳብ ማዕከል ለማሰባሰብ የሚደረገው ጥርት እና ከውጤቱ የፍሬያማነት ወቄት ላይ መሆኑን አይተናል። ሞጋች ሃሳቦችም ጉልበት እንጂ ጣውነት ተደርገው ሊታዩ አይገባቸውም። እንደ ኢንጂነር ይልቃል ድንብልብል ካልሆነ በስተቀር። መንፈስ ሐሴት አብዛኛው አግኝቷል። ያሳካው ግን የሰው ሥራ ሳይሆን ፈቃደ እግዚአብሄር ነው።
- · እርገተ ሃሳብ።
ማስተዋልን ስናውቅ የምናባክነውን ማናቸውንም ነገር በልብ በተቀመረ ተግባቢ ክነውን ይጸደያል።
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።፡
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ