ልዕልት ርዕዮት አለሙን እስኪ እንዴት ባጀሽ ልበላት።
ትናንትን ዛሬ በምልስት እስኪ ይቀፈው? ወርዱ ከቻለው? „በሰዎችና፡ በመላእክት፡ ልሳን፡ ብናገር፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ እንደሚጮኽ፡ ናስ፡ ወይንም፡ እንደሚንሽዋሽ ው ፡ ጽናጽል፡ ሆኜአለሁ። ትንቢትም፡ ቢኖረኝ ፥ ምሥጢርን፡ ሁሉና፡ እውቀትን፡ ሁሉ፡ ባውቅ፡ ተራሮችንም፡ እስካፈልስ፡ ድረስ፡ እምነት፡ ሁሉ፡ ቢኖረኝ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ከንቱ፡ ነኝ። ድሆችንም፡ ልመግብ፡ ያለኝን፡ ሁሉ፡ ባካፍል፥ ሥጋዬንም፡ ለእሳት፡ መቃጠል፡ አሳልፌ፡ ብሰጥ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ምንም፡ አይጠቅመኝም።“ ( ዬሐዋርያው ዬቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆረንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፫ ቁጥር ከ፩ እስከ ፫ ) ከሥርጉተ© ሥላሴ 21.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · ማሰብ እና ማግኘት ጋዳ ናቸው። ልዕልት ርዕዮት አለሙን ዓይኔን በዓይኔ የማዬት ያህል ነበር የማስባት። እጅግም እሳሳላት ነበር የዛሬውን አያድርገው እና። ከእስር መፈታቷን ብቻ ሳይሆን የብርታትን እኩልነት ብርሃን ትሆናለች ብዬም በጽኑ አስባት ነበር። መመኘት ከልካይ ስሌለበት የውስጤ ሐሴት ትሆናለች የሚል ብሩህ ተስፋ ሰንቄ ነበር መፈታቷን የጠበቅኩት። የሚገርመው የእሷም የእህቷም መጠሪያ ሥም የእኔም የእህቶቼም ነው። ሥምም ትርጉም ይሰጣል የውስጥ ሲሆን። እናም እጅግ አቅርቤ አያትም ነበር። በመጨረሻ ግን አሜሪካ ከገባች በኋ ዋላ ለእነዛ ካቴና ላይ ላሉ ነፍሶች ብጣቂ አዘኔታ ስታጣ ነፍሴን ጨነቃት፤ እጅግ ካዘንኩባቸው ጥቂት ነፍሶች አንዷ እሷው ሆነች። አሁን በቅርቡ በጀግኒት እማዋይሽ አለሙ ጉዳይ ታታሪ አቶ ተሎ...