የአቶ ወንድም የ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ተረብ...
የጋዜጠኛ ፋሲል ተረብ
ማለዘቤያ ቁራሽ መላሾ ነው።
„አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል?“
መዝሙር ፲፬ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
21.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
እንዴት ናችሁ የኔዎቹ። ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ዳውን ሎድ ማድረግ ተቸግሬ ጹሑፌን ሳላወጣ ቀረሁኝ። የትናንቱ በሌላ ዙሪያ ነበር። ዛሬ እሺ ካለ ይሞከራል። ስለዚህም ትናንት ቀጥዬ ልጽፍ የነበረኝ ፍላጎት ከፈጣሪ ፈቃድ ጋር ነው ብዬ በሌሎች የንባብ ፕሮግራሞች ላይ አተኮርኩኝ። ዛሬ በአዲስ አጀንዳ ብቅ አልኩኝ።
የአዴፓ መሪዎች ምን ይላሉ? – ፋሲል የኔዓለም
እንድምን አለህ ወንድም አለም ልጅ ፋሲል የኔአለም። ደህና ነህ ወይ?
ውዶቼ፣---- ዛሬ ከአቶ ወንድም ከጋዜጠኛ ፋሲል የእኔ ዓለም ጉዳይ ጋር አብረን እንዘናከት ዘንድ ወደድኩኝ። ጥሩ ነገሩ እንደ ድርጅቱ እንደ ግንቦት 7 አይደለም እሱ። ወቃሰው ሆነ ሙግቱ ቂም አብቅሎ ዘመቻ ግለት ጫና የሚያስከትል አይደለም። እንዲያውም እኔ እስኪ በቃው ሞግቼው ወጣቶች እንደ ነገሩኝ ከሆነ አንድ ጹሑፌን በቤተ መንግሥቱ ሚዲያ በአምስተርዳሙ ኢሳት እንደ አቀረበው ነግረውኛል። እስኪ ገርመኝ ድረስ።
በሌላ በኩል አንድ ጊዜም አንድ ሃሳብ ኖሮኝ ስጽፍለት በጎ መልስ አክብሮ ሰጥቶኛል። ይህን በራሴ ደርሶ ስላዬሁት በአንድ ወቅት በዝርዝር ጽፌያለሁኝ። ሌላው ትልቁ ጸጋው የፈለገ አስተያየት ይጻፍ አክብሮ መልስ ይሰጣል። ትህትናው እንዲያውም እናቴን እብዬን ይመስለኛል። እናቴ የባዛ እጅግም የበዛ ደግ ቅን እና ትሁት ናት። ትህትናዋ ስለሚበዛ ልጆቿኝ እንደ ትዳሯ ታከብራለች፤ ትፈራናለችም። አዘዦቿ እኛ እንጂ እሷ አይደለችም። ለትህትና ተቋም ናት።
ወደ ቀደመው ምልስት ሲሆን እንዲህ ይለናል አቶ ወንድም ፋሲል የኔአለም
„ሰሞኑን ከሚኒስትሮች ሹመት እና ከዶ/ር አምባቸው መኮንን ጋር በተያያዘ አዴፓ ( ብአዴን) ከፍተኛ ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል። በእነዚህ ሁለት ጉዳዮች ዙሪያ በቅርብ ከማውቀው የድርጅቱ ቁልፍ ሰው ጋር ውይይት አድርጌ ነበር። የነገረኝን እንደወረደ አቀርበዋለሁ። (ልብ በሉ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የእኔ አስተያየት አልተካተተበትም።)“
አሃ!
„ከማውቀው የድርጅቱ ቁልፍ ሰው“ የተለመደ ነው እኛም አለን በሁሉም ቦታ መባልን። ባጅተንበታል ከርመንበታል። የሆነ ሆኖ ለሁሉም ምቹው ሊንክ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው። ቁልፍ ሰው የተባሉት እሳቸውን ነው። የአዴፓ ብቻ ሳይሆን ዛሬ ላይ የፌድራል መንግሥቱም ቁልፍ ሰው መሆናቸውን እናውቃለን። ከዚህም የሚያልፉ ነገሮችም ይኖራሉ ባይም ነኝ። የሆነ ሆኖ ግንኙነቱም በምን አግባብ እንደ ሆነ ይታወቃል። አቶ ንጉሡ ጥላሁን የብዙ መንፈሶች አፈ ጉባኤ ሊንክ ናቸው።
እሳቸው መታወቅን ያገኙት በብሮድ ካስት ሙግት ላይ በነበራቸው ኮስታራ አቋም ነው። ከዛ በኋዋላ አንዣባቢው በረከት። ከዚህም ባለፈ እዮር የሚያውቀውም ሌላም ግንንኙነት እንዳላቸው እኔ እገነዘባለሁኝ። አቅም አላቸው፤ ደፋር ናቸው፤ ራሳቸውን መግለጽ ይችላሉ ሲያስፈልግም በፈለገው ጉዳይ ጋር ማሳደም ይችላሉ። ላመኑበት ዓላማ የሁሉም መተንፈሻ ቧንቧ ናቸው።
ለአማራ ደግሞ ከሳጅን በረከት ያልተለዬ መከራ እንደለበት ይሰማኛል።
እንደዚህ ዓይነት ሰዎች አሉታዊ ከሆኑ ብቻ ነው ጠቃሚነታው። አስተሳሰባቸው ሆነ አቋማቸው አጋጣሚውን ሲያገኙ ጥፋቱ አሉታዊ ከሆነ እጅግ መራር ነው። ለነገሩ የፌድራል መንግሥቱ የክልሉ ፕሬዝዳንት ዶር ገዱ አንዳርጋቸውን እሳቸውን ማመን ተስኖት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ነው ኤርትራ የላከው። ለፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂም የሚመች ሰብዕና ነው ያላቸው። እጅግም ተፈላጊ ሰው ናቸው የአማራን ነፍስ ተረጋጭ ለማድረግ።
ሌላው የአቶ ወንድም የጋዜጠኛ ፋሲል ተረብ ዶር አንባቸው መኮነን ራሳቸው ለፌድራል ፕሬዚዳንትነት ጠዬቁ ነው የሚለን። ማለዘቢያውንም ባጅተንበታል። አቶ ታዬ ደንዳአ እና አቶ አዲሱ አረጋ ሲግቱን ባጅተዋል። በራሳችን ፍላጎት የደገፍነው የቀድሞውን ኦህዴድ/ የዛሬዎን ኦዴፓ ጥዝጠዘው መሰረት እስኪይዝ ድረስ ተኙልን ሲሉን ባጁ እኮ። አሁን እንኳን እስከ አንገት ማሰሪያችን ድረስ ነግረውናል።
የልጅ ፋሲል ትርክት ...
„ዶ/ር አምባቸው ፕሬዚዳንት ለመሆን ጥያቄውን ያቀረቡት ራሳቸው ናቸው። ጥያቄውን እንዳቀረቡ አቶ ገዱና አቶ ደመቀ በጽኑ ተቃውመዋቸዋል። አንተም ልትከዳን ነው በሚል ማንገራገሪያ ሳይቀር ውሳኔያቸውን እንዲያጤኑት ለምነዋቸዋል። ዶ/ር አምባቸው፣ ‘በዚሁ ቦታ ብሆን፣ ትንሽ ጊዜ ወስጄ ለማንበብና ለሌሎች የሃላፊነት ቦታዎች ራሴን ለማዘጋጀት ይጠቅመኛል’ የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል። ይህም ተቀባይነት ባለማግኘቱ ‘ እንደሱ ከሆነ የፕሬዚዳንቱ ስልጣን በአዋጅ ትንሽ ከፍ ይደረግና ኢንቨስትመንትን በመሳብ እና በዲፕሎማሲው ስራ በስፋት የምሳተፍበት ሁኔታዎች ይመቻቹልኝ’ ብለው ሃሳብ በማቅረባቸው በዚህ መሰረት ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቷል። ምናልባትም ሰኞ ፕሬዚዳንት ሆነው በይፋ ሊሾሙ ይችላሉ። በአቶ ገዱና አቶ ደመቀ ላይ ሲዘንብ የነበረው ትችት ተገቢ ያልሆነና በመረጃ ላይ ያልተደገፈ ነው።”
አይደለም። በፍጹም አይደለም። ተገደው ድርጅታዊ ማዕከላዊነት በሚባለው ፈሊጥ ወይንም ሾጥ በምታደርግ የቅድመ ሁኔታ ስውር ድርድር ሊሆን ይቻላል። በማስፈራራት። ከተቀበሉት ይህን ልጥፍ ቅርድድ ሙልሙል ሹመት።
ከሳቸው በፊት አቶ ደመቀ መኮነን ለማድረግ ነበር የታሰበው። አቶ ደመቀ መኮንን ከም/ጠ/ሚር የማንሳት የኦዴፓ ምህንድስና ነበር። በሁለት ምክንያት። በዝርዝር ስቸከችክ ባጅቻለሁኝ። ያን የአማራ ጉባኤ ፉርሽ አደረገው።
አሁን የት ይገባ የአዋሳው ጉባኤ በዛ ድንገተኛ እርምጃ። የአዋሳው ጉባኤ ድርጅታዊ ሥራ አፈር ድሜ ያስጋጠው የባህርዳሩ ጉባኤ ቀድሞ ነበር። የቲም ለማ ምህንድስና በሽምቅ ሽንፈትን የተቀበለበት የመጀመሪያውም ምዕራፍ ጎህ የቀደደበት ነበር።
ቲም ለማ የመጣበት ዘመን ወያኔ ከመጣበት ዘመን በእጅጉ ይለያል። እሱ ግን በዛ መስመር መሄድን መርጧል። መጠቅለል። ያን ጊዜ የአማራ ብሄርተኛነት እንደ ዛሬው ስላልሆነ ይቻል ነበር። ዛሬ ግን መሬት ላይ ያለው ነገር ብቻ ሳይሆን የእኔን መንፈስ ሳጠናው አማራነትን መግፋት የማይሞከር ሴንሲቢል ጉዳይ እዬሆነ ነው።
እኔ እራሴ ለራሴ ዘብ መቆም ግድ ይለኛል። በራሴም የደረሱ ጫናዎችን ስጋፈጥ በዝምታ ባጅቻለሁ እና። የሆነ ሆኖ የኦዴፓን ዲዛይን አዴፓ ጉድ ሲያፈላበት የአዋሳው ጉባኤ እንደ ገና መዋቅር መስራት ነበረበት። የሚገረመው አስደንጋጭ ጉዳይ የነበረው ግን ቲም ለማ ምህንድስናው ፉርሽ ሲሆን ሌላ ያላሰበው አደጋ ላይ ወድቆ ነበር። ቀደም ብዬም ይህን ገልጬው ነበር። ወ/ሮ ሙፍርያት ካሚል ለጠ/ሚር ቢወዳደሩ ለኦዴፓ „የቆጡን አውርድ ብላ የብብቷን ጣለች“ የሚለውን አደጋ ይገጥመው ነበር።
ክብርት ሙፍርያት ካሜል ጠ/ሚር የመሆን ሰፊ ዕድል ነባራቸው። ድምጽ ነው እኮ ጠ/ሚር የሚያደርገው። ፕ/ ትራንፕን የአሜሪካ ጠ/ሚር ያደረገው ድምጽ ነው። ክብርት ወ/ሮ ሄለሪ ክሊንተንን ትቶ ክቡር አቶ ባራክ ኦባምን ሥልጣን የሰጠው ድምጽ ነው። ቁጥር። ለወደፊትም ስላሰጉ ነው አሁን የሰላም ሚ/ር እንዲሆኑ የተደረጉት የሚል የግልም ጠንከር ያለ ዕይታ አለኝ።
ምክንያቱም ክብርቷ በዝምታቸው ውስጥ ያለው ዕምቅ እልህ ሙቀቱን ጠብቆ ከቀጠለ ነገም ማስጋቱ ግድ ይላልና። እርግጥ ነው አሁንም የተሰጣቸው ቦታ ቁልፍ ነው እጅግም ቡዙ ነው፤ እጅግም ውስብስብ ነው። በተገባው ልክ ክብር ካልተሰጣቸው እና ልብ እንግጠምልሽ ቢባሉ እኒህ አንበሳ ሴት እሺ ባይ የሚሆኑ አይመስለኝም።
አንድ ጹሁፍ አንብቤያለሁኝ ሴቶች እሺ ስለሚሏቸው ነው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሴት ሚ/ሮችን ያበዙት የሚል። ሌላው ይቅር እስኪ የስሜን አሜሪካ ኮሚሽን ፌድሬሽን ስብሰባ ተመልክቼው ነበር ከውስጤ አንዲት ሴት የለችበትም። እኔ እንዲያውም ለውጭ አገር ሊሂቃን ማመልከቻ ሲኖረኝ የወንዶች ማህብር ብዬ ነው እምጸፈው። ይህ ደግሞ አሁን እዬተዬ ነው። ተፎካካሪ የሚባለው ሁሉ ራሱን ይዞ ነው የገባው።
የዶር መራራ ጉዲና፤ የፕ/ በዬነ ጵጥሮስ፤ የአቶ መርሻ ዮሴፍ፤ የዶር ነገደ ጎበዜ፤ የዶር አረጋይ በርሄ፤ የአቶ እያሱ አለማዬሁ፤ የአቶ ዳውድ ኢብሳ፤ የአቶ ሌንጮ ለታ፤ የዶር ሙሳ ኮንቴ፤ የፕ/ ብርሃኑ ነጋ ፓርቲዎችን ተመልከቱ እንዴት በሴት በድርቅ እንደ ተመታ።
ዶር አብይ አህመድ ዛሬ አይደለም ስለ ሴቶች ያስተማሩት የተለዬም ምልከታም ልዩ የሆነ አሜነታ በእኛ ላይ ያላቸው ሊሂቅ ናቸው። ወይይቱን ድርድሩን ሙግቱ እስኪ እዩት ብራና ላይ እንኳን እዩት። የፈለሰ እና የፈሰሰ ነገር ነው ያለው። 50 ዓመት ሙሉ ለጠ/ሚር የምትወዳደር ሴት የላትም ኢትዮጵያ።፡
ውዶቼ ይህን አዳምጡት። እኔም አንዲህ ዶር አብይ አህመድ በፖለቲካው ዘርፍ የዓለም መነጋጋሪያ ከመሆናቸው በፊት በስፋት ጽፌበታለሁኝ።
ዶር አብይ አህመድ መጋቢት 24 ቀን የ2010 የሹመት ንግግርም በሴቶች ላይ የተለዬ ምልከታቸውን አሳይተዋል። ለዚህም ነው የኢትዮጵያ እናቶች ከልባችን ቀጥ ብሎ የገባ ብቸኛው መሪ የሚሏቸው። በአንባሳደርም ሹመት ይህ ቀጣይ ይሆናል እሳቸው በህይወት እስከ ኖሩ ድረስ።
ገና በሹመቱ ላጋ ላይ የፌድሬሽኑ ምክር ቤት እና የፓርላማው አፊ ጉባኤም ሴቶችን ነበር ያደረጉት፤ ኤርትራ ሲሄዱ ሁለቱን አፈ ጉባኤዎች እንኳን ይዘዋቸው የሄዱበት ምክንያት ማንም አላስተዋለውም ነበር። ሴቶች የሰላም ምልክት ስለመሆናቸው ለማስተማር ነበር። የጎንደር እናቶች እንደ ሰማሁት ከሆነ መላዕክ ነው የሚሏቸው ጠ/ሚሩን።
ይህም ብቻ አይደለም በግንቦት 20ቸው መታሰቢያ ላይ ያደረጉት ንግግር ለሴቶች ክብር ስለመስጠት በአጽህኖት ተናገረዋል። እኔ ከተወሰኑት የፖለቲካ ሊሂቅ በስተቀር ብዙዎችን በአካል አውቃለሁኝ። ሴቶችን በሚመለከት ሞግቻቸዋለሁኝም። ይህን ዶር መራራ ጉዲና አሳምረው ያውቁታል።
ዛሬ እነሱ የማያደርጉት፤ አጀንዳቸው ያልሆነውን የሚስጢር አናትን ጠ/ሚር ሲያደርጉም ይህም መተቻ ሆነ። አንድ ጊዜ ሴቶችን ወደ ፊት አምጥቶ ሴት ጠ/ሚር ብትገኝ ኢትዮጵያ ችግሯ ያባቀል በሚል የጻፍኩት ጹሑፍ ወንድሜ እያነበበው ነበር የተነሳው። አስነሱት ጉልበተኞች። ይህችን መስማት አይሹም።
በሌላ ጊዜ ደግሞ ሴቶች ብልህ አቅም አላቸው ጊዜ እስኪሰጣቸው ድረስ ጠብቀው ይይዙት ዘንድ እምክራለሁ የሚል ጹሑፍ አወጣሁኝ።
አሁን እዬሆነ ያለው ይህ ነው የወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስንም፤ የወ/ሮ አይሻ መሐመድ፤ የወ/ሮ ፍጹም አሰፋን ቃለ ምልልስ የሦስቱን አዲስ ሚኒስተሮች ራዕይ አዳምጫለሁኝ። ልቤ ቅቤ ጥጥት ነው ያለው። ካለፍቀዴ ኮለል እያለ ነው ለብ ያለው የተፈጥሮ ቅባት ሳዳምጠው - ያዳምጥኩት። እራህቤ ነበር። ብዙ ጊዜ ሴት ሃላፊዎች ተዳራቢ ሃላፊነት እንዳለባቸው ዋናውን እንብርት ጉዳይ ይዘነጉታል። ለሴቶች ዕውቅና ለማሰጠት በሴቶች አቅም ግንባታ ተግባር ላይ አለማተኮር ነው የዚህ የጨለማው ዘመን መከራ ሆኖ የተኖረበት።
ይህን ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሚል ደፍረውታል ለህውሃት፤ ለብዴን፤ ለኦህዴድ ጉባኤ ደቡብን ወክለው ንግግር ያደረጉ ሴት ሊሂቃንን ነበር ለሦስቱም ጉባኤ የላኩት። አሁን አብሶ ወ/ሮ አንሻ ግልጽ አቋም ነው ያላቸው ሴቶችን በሚመለከት። ውስጣችን በሚገባ ገብቷቸዋል። መከራውን ግለቱን ውግዘቱን ያውቁታል እና።
Ethiopia: ዶ/ር ዓብይ አህመድ እና ወ/ሮ ፍፁም አሰፋ | Dr Abiy Ahmed | Fistum Assefa
https://ethiopianregistrar.com/amharic/archives/58692
“ኢትዮጵያ ለሁሉም እኩል የሆነች አገር ናት”- ወ/ሮ አይሻ መሐመድ (የመከላከያ ሚኒስትር)
https://www.ethiopianregistrar.com/dagmawit-moges-ethiopian-woman-politics-sbs-amharic/
Dagmawit Moges: Ethiopian Woman in Politics – SBS Amharic
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቃን ሴቶችን ስለምን የፖለቲካ ሊሂቃን ያገላሉ ሲባሉ ስስታም ስለሆኑ እና ሙግቱን ስለማይችሉት ነው። ወንድ ፖለቲካኞች በሞቀው መጣድ እንጂ ማሞቅ አይችሉበትም። ሴቶች ግን ሁሉንም አይነት ፈተና የመድፈር ሙሉ አቅም አላቸው። ስለዚህ ዶር አብይ አህመድ ይህን ደፈሩት።
እናም እንደ እኔ ፈተና በራሳቸው ላይ ጥለዋል። ቀድሞ ነገር እዚህ የሚደርሱ ሴቶች አልጋ ባልጋም ሆኖላቸው አይደለም በስንት ውጣ ውረድ፤ በግልጽ ቋንቋ በጦርነት ውስጥ ነው ከዚህ የሚደረሰው። የብዕር ተሳትፎን የሚፈሩ ጉዶች እኮ ናቸው የእኛ የፖለቲካ ሊሂቃኑ እንኳንስ የወንበር ፉክክር። እኔን በዬፌርማታው አይደለም ወይ የሚያሳግዱኝ? እኔን ድምጥማጤን ለማጥፋት ስንት ተተግቶበታል። ስለምን ቢባል ሰነፎች ናቸው? ሃቅን ፈሪዎች ናቸው።
ወደ ቀደመው ነገር አዴፓ ምልስት ሲሆን ድልድሉን የሠራው ቲም ለማ ነው። ቲም ለማ ባይሆን አዴፓ የሚለውን ሥያሜ ብአዴን አይቀበልም ነበር። በራሱ ተፈጥሮ ውስጥ የራሱን ሥያሜ ያወጣ ነበር። እጥያነትን ምን አስፈለገው?
ለውጭ ጉዳይ ሚ/ር የታጩት ዶር ለማ መገርሳ ነበሩ። ይህም ዳብል ተልዕኮ ነበረው ያ ቢሆን ኖሮ። ዛሬ አልናገረውም። በሌላ በኩል ዶር አንባቸው መኮነን ከሆኑ የመረጃው ቅርበት ከቲም ለማ ይልቅ ለአዴፓ ይሆናል ተብሎ ተሰጋ።
በዛ ላይ ለአማራ ይህን ቁልፍ ቦታ መስጠት የማታሰብ የማይታለም ነገር ነው። ኦሮምያ ዶር ለማ መገርሳን አለቅም ሲል፤ ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ ውጭ ጉዳይን ለቀው ሊይዙት የነበረው ቦታ ለሌላ ለሚታመን አካል ተሰጠ።
ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ አረረም መረረም የሁለቱን ጥምር ፍላጎት በማሳካት ማለትም የወያኔ ሃርነት ትግራይን እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን ስለሚያሟሉ ቲም ለማ ከመረጃ ምንጭነት ቲም ደብረጽዮን ከመረጃ ምንጭነት እንዳይወጡ ተደርጎ በዛው ቦታቸው እንዲቀጥሉ ተደረገ። ስለሆነም ዶር አንባቸው መኮነን ተንሳፋፊ ሆኑ። ድፍን የአማራ ህዝብ ታማኝ አይደለም ነው አመክንዮው በትርጉም ሲቃና!
ዋናው ከታሪክ የአማራን የህልውና ተጋድሎ ያስገኘውን የለውጥ አጋርነት እና ጉልህ ድርሻ የመሰረዝ ሲሆን ሁለተኛው ከታሪክ ሐዋርያነት ከሚባሉት የአማራ ሊሂቃንን በስልት መፋቅ ነው። ልቅናቸው ዕውቅናቸው ቀጣይ እንዳይሆን ማጨንገፍ ነው የታዬው።
ከኢትዮጵያውን ልብ ውስጥም ማስወጣት ነው ተልዕኮው። ምን ይሸፋፈናል አቶ ጌታቸው ተስፋዬ ያለፉት በተፈጥሮ ህመም ነውን? ኢንጂነር ስመኛው በቀለ የተገደሉት ለዬትኛው ፓለቲካ ማራመጃ እረፍት ሲባል ነው? ስለምን ነው በግራ በቀኝ በአማራ ላይ በአዲስ አቅም በአዲስ ሃይል የተዘመተው?
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ራሱ የግድ በኦሮሞዎች ብቻ ጥግ እንዲጠለጠሉም ያስፈልጋል። በዛ ላይ ብቻ ጥገኛ እንዲሆኑ። የደገፋቸው፤ የተቀበላቸው ባላቸው ደግሞ አማራ ነው።
እሳቸው ለአማራ ጥያቄ ምን ያህል ቅርብ ናቸው ስለምን ራቁት ያቀረባቸውን መንፈስ ሌላ ጉዳይ ነው። ለአማራ ዋ! እና ወዮ! እንዲደመሩ ነው ፈቃዱ! ለሳቸው ለራሱ ለጠ/ሚር አብይ አህመድ መሰሏቸው ነው እንጂ ታማኝነት የት ላይ እንዳለ እዮር ያውቀዋል። ይህን ሁሉ ትርምስ አደራጅተው የሚመሩት የራሳቸው የድርጅት ሰዎች ታማኞቻቸው ናቸው።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንግዲህ የዛሬ ሳይሆን የቀደመ ግንኙነት እንዳላቸው ነው የሚታወቀው ከዶር አንባቸው መኮነን። ከዚህ ሊንክ ወስጥ ስማቸውን ሲጠሩ ሰምቻለሁኝ። ለዚህም ነው አቶ ጀዋር በጥርሱ ዬያዛቸው።
Gonder Vs Kigali, Dr Abey explains why Gonder remained poor. ዶ/ር አቢያ ኪጋሊንናጎንደርን ያወዳደሩበት።“
በጥገናዊ የለውጡ ሂደትም ሰፊ የሆነ የሎቢ ተግባራትን ከውነዋል ዶር አንባቸው መኮነን። ለኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ውለታ መዋልም ይመሰልለኛል ዶር አብይ አህመድን ደግፎ ለሥልጣን ማብቃት። ጉልሁን ተግባርም ተወጥተዋል። ኦዴፓ ይህን አሳምረው ስለሚያውቁ ከአማራ ክልል ለጃውርውያን ሆነ ለመሰል ድርጅቶች ተመራጭ የሆኑት አቶ ንጉሡ ጥላሁን እንጂ ዶር አንባቸው መኮንን አልነበሩም።
ቀደም ሲል የነበረው ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ሐዋርያነት በሦስተኛንት ሲጠቀስ ነበር። አሁን አቶ ደመቀ ታከሉ፤ አሁን ዶር አንባቸው ታከሉ፤ አሁን ከአዋሳው ጉባኤ ደግሞ ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል ታከሉ፤ አቶ ሚሊዮን ታከሉ። ለነገሩ ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል የውለታ ፊርማቸው ሳይደርቅ ነው የተነሱት።
ይህ ለኦሮሞ ሥነ - ልቦናን አፍሪካዊ ለማድረግ አቅም እና ታሪክ አልተመቸም። አሁን እኮ የታሪክ መጸሐፍም መጻፍ ተጀምሯል። እንደ ዛሬ እነ አቶ ሌንጮ ለታ አዲስ አባባን በወታደር ነው የለቀቀነው ታሪክ „ሀ“ እዬተባለ ነው። ልክ ግንቦት 7 በሌለበት ባልዋለበት ብራስልስ ላይ ሆኖ የአማራ የህልውና ተጋድሎን „የነፃነት ሃይል“ እንዳለው ሁሉ ማለት ነው። ጊዜ መልካሙ መልስ ሰጠበት።
በታሪክ ሲመጣ ያለተደፈረውን አምክንዮ መድፈር ያቅት እና ውሸት ዕድሜ ጠገብ ሲሆን ታሪክ ሆነ እንደ አሁን አዲስ አባባ፤ ወልቃይትና ጠገዴ፤ ራያ እና መተክል አዲስ ልብጥ ቁሮ ታሪክ ሆኖ ቀውስ አምራች ይሆናል - ለማግሥት። አሁን እኔ እማዬው የ16 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ምልሰትን ነው። አዳራ እና ኪዳን ውሃ የበላው ቅል እዬሆኑ ነው።፡
በዚህ በአዴፓ ላይ የባጀው ጫና ታሪኩ የአማራ ታሪክ እንዳይባል ከዲያስፖራ ጀምሮ በትጋት የከወነ ተግባር ነው። የለውጥ ሐዋርያት፤ ለውጥ አስገኝ ሃይል ኦሮሞ ብቻ እንደሆነ አድርጎ ታሪክን የመሥራት የፊደል ገበታ ነው። ይህን ፕ/ መስፍን ወ/ልደማርያም ተሳስተው አቶ ገዱን ጨምረው ተደምጠው አያውቁም፤ ሌሎችም እንዲሁ። በዚህ አግባብ ነው አሁን የምናያቸው የሹመት ጉዳዮች። ይህ አካሄድ ደግሞ የዘሩትን እዬፈሱት ነው ነጣዮቹ ሊሂቃን ... ማበጠን መታበይን ከብክበው እያሳደጉት ነው። ስለምን? ሚዛን አስጠባቂውን እውነት ፈቅደው ስለዳጡት። የሚታዬው መታበይ እኮ ቃላት አይችለውም።፡
አቶ ንጉሡ ጥላሁን በግልጽ ቋንቋ የኦዴፓ የጽ/ቤት ሃላፊ በባህርዳር ሲሆኑ ቀደመው ባለው ጊዜም ከአቶ ሹፈራው ሽጉጤ ጋር የወንድም ያህል የሚተያዩ ስለመሆኑ አስተያዬት ሲሰጡ ታዝቤያለሁ፤ አንተ እያልህ አይነት ነበር አስተያዬቱ። ሊንክነታቸው ባህር ማዶም ጭምር ነው። በጥንቃቄ ሊያዙም የሚጋባቸው ሰው ናቸው እምለውም ለዚህም ነው። ለዚህም ነው እኔ ዳግሚያ አባ ኮስተር ያልኳቸው። የጥገናዊ ለውጡ አካል ናቸው ብዬ ግን አላስብም። የአብይን መንፈስ እንዲጠጋቸው የማይፈልጉ ሰው ናቸው። ይህን እኔ በተለያዬ ጊዜ ገልጫዋለሁኝ።
እና አቶ ወንድም ፋሲል የአኔ ዓለም እይታ መጣጠፍ ሲተረጎም „ዶሮን ሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት“ ነው የሆነው። ዶር አንባቸው መኮነን ፈቅዶ ይህን የህንጻ ጠባቂነት ሃላፊነት ከተቀበለ መይሳው ካሳ፤ በላይ ዘለቀ 10 ጊዜ እንደተሰዉ እቆጥራዋለሁኝ። ለህንፃ ጠባቂነት እሱን የመሰለ በተመክሮ የሰከነ ሊሂቅ እዛ ቁጭ ብሎ ቤት ጠባቂ መሆን ለጠላቴም አልመኘውም። የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቢሆን እንጂ እንግዳ በመቀበል እና በመሸኘት የቦሌ ትኬት ቆራጭ እና ሊጋባ በመሆን አይደለም ወሳኝ ቁልፍ አካልነት።
ዶር አንባቸው መኮነን ተወርውሮ መጣሉን አሜን ካለም ቀበቶውን እጠራጠራለሁኝ። ምን አለው ክልሉ? በዲሞሽን እዛው ከቤተሰቦቹ ጋር ሆኖ መኖርን መምረጥ ነው። ምን አቶ ታዬ ዳንደአ ወደ ፊት ሲመጡ የዜግነት ፖለቲካ የሚያራምዱት አቶ ውብሸት ሙላቱ ነበሩ፤ ረ/ፕ/ አበባው አያሌውም አንቱ ናቸው።
ወቅታዊ-በአማራ ቴሌቪዥን ብቻ
https://www.youtube.com/watch?v=BPukWO0J7gw&t=1161s
የምናዬውን ንጹህ የማግለል ጉዳይ እያየን ነው እዮባዊነትን ሰንቀን። ልጅ ፋሲል የሚለን ግን እነሱ የሚፈለጉት ለኦሮሞ ኢንፓዬር አማራ ትክሻውን ዝቅ አድርጎ መደላድል እንዲሆን ነው። ሲጀመርም ሥሙን አይቼ ግርባነት ብዬዋለሁኝ። ለዚህ ነው እኔ በመንግሥት ይወሰን አይወሰን ኦሮምኛ ሁለተኛ ቋንቋነት ከዚህ ዓመት ጀምሮ አማራ የሚስጢር ውቅያኖስነቱን ለማውቅ ግዕዝ ማጥናት አለበት የምለው። ግዕዝ የራሳችን ውስጥ ነው። ወደ ውስጥ ተምልሶ ራስን መሆን ግድ ይላል።
አሁን እኮ ምልክት አይደለም እያዬን ያለነው የኦሮሞ ኢንፓዬርን የአፍሪካ መሪ እናድርጋለን ተጫባጭ ጉዳዮችን ነው፤ ለዛውም በሃይል በመግደል፤ በማሰር፤ በማሳደድ። ለዚህም አማራ ተኝትህ በለኝ ማለት አለበትም ነው የሚለን ልጅ ፋሲል። ይህን ነው እዬመከረ ያለው ልጅ ፋሲል የእኔ አለም። ልክ አቶ ታዬ ደንዳ እና አቶ አዲሱ አረጋም ይህን መሰል የአደንዝዘኝ ትርክት ነው የነበራቻው። እያዛሉ የልብን ማድረስ። ከዚህ በላይ ምንም አይመጣም።
የጋሞ ልጆች የተጨፈጨፉት አማራኛ ቋንቋ ተናገራችሁ ተብለው ነው። ተዚህ ላይ አንድ ነገር ልከልበት እና ከሰሞናቱ አማሮ ላይ የደረሰው ሰቆቃ የኢትዮጵያን ብሄራዊ የዜግነት ልሙጡን ሰንደቅዓለማ ይዘው ጠ/ሚር አብይን ደግፈው ስለወጡ ቂም ተቋጥሮባቸው ነው ዛሬ ሞታቸውን የምንሰማው። ይህን ቡራዩ ላይ የጋሞ ተዋላጆች አማርኛ ቋንቋ ተናገራችሁ ተብለው ነው ያ ሁሉ መከራ የታዬው።
የአዲስ አባባ ከተማም ጭፍጨፋም ይህው ነው። የታሰሩት ሁሉ ከዜግነት መለያ ምልክት ጋር ነው። እንደ ለውጡ ተጋድሎ ይወሰድ ብለዋል ጠ/ሚር አብይ አህመድ ለሳቸውማ ሰኔ 16 ራሱን ገበረ የ አዲስ አባባ ህዝብ አሁን ለ አቶ ታከለ ኡማ ደግሞ ግበር ራስህን፤ ዜግነትህ መድረሻ አልባ ስለመሆኑ ፈርመበት እዬሉን ነው።
ነገ ይህን ሃሞት አማራ እንዳይቀበል ትጥቁን ጠበቅ ማድረግ ያስፈልገዋል። ማናቸውንም ዜና ከልብ መከታታል ይገባል። ቋንቋ ምርጫው ላይ ግዕዝን በአቋም ደረጃ ማድረግ ግድ ይላል።
የአብይን መንፈስ ብንወደውም፤ ለእሱ ሌጋሲ ቀጣይነት ብንተጋም ሙሉ ለሙሉ ዜግነትነት ለማስከበር ያለው አቅሙ ግን ስስ ነው። ሌላው ቀርቶ የአቶ ደመቀ መኮነን፤ የዶር ገዱ አንዳርጋቸው እና የዶር አንባቸው መኮነን ተገለው አረጊ ፈጣሪ አቶ ንጉሡ ጥላሁን መሆን የሚነግረን ያልተፈታ ቁልፍ አመክንዮ እንዳለ ያሳያናል። እሳቸው ጃዋርውያን ናቸው።
ከሁለቱ ለሚወለዱት ችግር ላይሆን ይቻላል ከአማራ ለተወለዱ ልጆች ግን አዳጋው ጀምሯል። መስካሪ እኮ አያስፈልግም እያዬን ነው። ሌላው ቀርቶ „የገዳ ሥርዓት“ የሚባለው በ21ኛው ምዕተ ዓመት ጋር ያለውን ሥልጣኔ ሰው ተግድሎ ተዝቅዝቆ ተሰቅሎ አዬን ሻሸመኔ ላይ በፌስታ፤ በእልልታ በሳቅ በጭፈራ። እግዚኦ ነው። ቡራዩ ላይ የሆነውን ሁሉ መረጃ ማግኘት አልተቻለም። ፈፃሚው ድብዛውን አጥፍቶታል። አይፍርም የመንግሥት ሚዲያ ከአዲስ አባባ የሄዱ ሲል ትናንት ዘግቦታል። ግርባ።
ይህም ብቻ አይደለም ሰሞኑን ከልዕልት ቤተልሔም ታፈስ ጋር አቶ በቀለ ገርባ ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ሳዳምጥ በኦዴፓ ጉባኤ ላይ ንግግር ሲያደርጉ ገዳ የአክብሮት አስተምህሮቱን አሳይተውናል። ጠ/ሚሩን ዶር አብይ አህመድ እና የክልሉን ፕሬዚዳንት ዶር ለማ መገርሳን አድሬስ ሳያደርጉ ራሳቸውን የጠ/ሚር ጠ/ሚር/ የፕሬዚዳንት ፕሬዚዳንት አደርገው ሾመው ነበር ያቀረቡት። ገዳ ይህ ከሆነ እኔ በአፍንጫዬ ይውጣ፤ ይህን ለህግ እና ለሥርዓት ተገዢ አለመሆናቸውን ቀደም ብሎም አይተናል እስር ቤት እያሉ ለዳኞች ከመቀመጫ አለመነሳትን አስተውለናል። የፈለጉ አይነት ዳኞች ይሁኑ ኢትዮጵያ መከበር አለባት፤ እነሱ ኢትዮጵያ ማለትን አለመቀበላቸው ውስጣቸው አሳይቶናል። ገዳ ህግ ጣሽነቱን ነው በዘመነ ገዳ መራሂነት እያዬን ያለነው።
አቶ በቀለ ገርባ እና ዶር መራራ ጉዲናም ሁለተኛውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ጥሰው ሄደው ነቀምት የፈጸሙትን በተደሞ ውስጣችን ቁስል እያለ ተመልከተናል፤ የመጀመሪያውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም መሰሉን ፈጽመዋል ዶር መራራ ጉዲና። ሰው ከህግ በላይ አይደለም። ቢያንስ ያልተጻፈው ህግ መከበር አለበት። በኢትዮጵያ እዬኖሩ ህግ ሳያከብሩ መኖርን ነው እያዬን ያለነው። ገዳ ይህ ነው እንግዲህ ለዓለም አሰተማርን የሚባለው። ዓለምን እኛም እዬኖርንበት ነው። ዓለም ከፈጣሪ በታች ያሉ ዓለም አቀፍ እና ብሄራዊ ህጎች ተከበረው ነው የምናዬው ስለዚህም የተወረሰ ነገር የለም ገዳይነት ወይንም ህግ ተላላፊነት ተወራሽ አታደርግም ሥልጡኗ ዓለም - ለዛውም አጀንዳዋ ሰው በሆነበት ዘመን።
ስለሆነም በቸለልታ ሳይሆን መሆን ያለበት ሁሉም በራሱ ውስጥ ሆኖ ህግ የሚጥሱ፤ ከህግ በላይ የሆኑ ሰዎችን፤ ይህን ያካል መታበይን ስለምን እጬጌው አይሆኑም በህግ ሊጠዬቁ ሲገባ በቸለልታ እያተለፈ ነው። ህግ መጣስ ህጋዊነት ህግ ማከብር ህግ ጣሽነት ዛሬ ኢትዮጵያን የገጠማት ፈተና ይህ ነው በዘመነ ኦዴፓ። ለዚህም ነው የአዲስ አባባ ወጣቶች ለእስር የተዳረጉት። ህግ ጣሾች ህግ አክባሪዎችን በዘመናቸው እዬተበቀሉ እዬተመለከትን ነው። ልባቸውን ነፍተው ደረታቸውን ገልብጠው የልባቸውን ይናገራሉ ማን ከልካይ ሲኖርባቸው ዘመኑ የእነሱ ነው። "ዘመን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል" እንዲሉ ...
ይህን ሸፍናችሁ ተቀመጡ ነው የአሁኑ ስብከተ - አምስርዳም። ከጠንካራ የአማራ ሊሂቃን ግልት ዘመቻ ተከታዩ ደግሞ ምን ሊሆን እንደሚችል የምንመለከተው ይሆናል። ሊያስገድሉትም ይችላሉ ዶር አንባቸው መኮነን።
አቶ ጌታቸው ተስፋዬ በጥዋቱ እንዲለቅ ተደርገዋል። ምን ሲቸግር በጠራራ ጸሐይ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞተዋል። የአቶ ጃዋር መሃመድን እና የቲሙን አቀባባል ደግሞ በፌስታ አይተናል። የእነ አቶ ዳውድ ይብሳ፤ የእነ አቶ በቀለ ገርባ ህግ ጣሽነት ደግሞ አሜን ብለው ተቀብለዋል አውራው ፓርቲ ኦዴፓዎች። ስለምን? ዘመኑ የኦሮሞ ኢንፓዬር ነውና። የሚገርመው አስቂኙ ነገር ኤርትራ ተረስታ ጫጉላ ላይ ስላለች የፍልስጤም ተረት ደግሞ መሳጭ ቧልት ነው። ለውጡን የማይፍልገው ሃይል ማን ስለመሆኑም ድፍረቱ የለም። ስንጥቅ ወጭት። ቅራኔ ደፍሮ መግባት ተስኖታል ኦዴፓ፤ የሃይል አሰላለፉም ያልጠራ ነው። ይህን ሥርጉትሻ ሳትሆን ሃቅ ነው የሚሞግታቸው።፡
ስለ የህግ ባሙያው አቶ ውብሸት ሙላት ከላይ ስላነሳሁኝ በዚህ ሊንክ አቅማቸውን ማዬት ይቻላል። ሌላም አቶ ሙሉጌታ ማዕረጉ የህግ ባለሙያም አቶ ታደስ ታግሎ የፖለቲካል ሳይንስ ሊሂቅ ናቸው። አማራነት እንዲህ ይገለጻል። ስለምንለው ሳይሆን የትንፋሽ አቅሙ ራሱን ያብራራል። ተመስገን! እንኳንም ድምጣቸውን በነፃነት እንዲህ ለመስማት አበቃን። በስውር ደግሞ አንድ ነገር እስኪያስደርጓቸው ድረስ።
ሊደመጥ ብቻ ሳይሆን የህሊና ቤተኛ እንዲሆን የሚፈቀድለት አቅም ስለሚፈራ ነው አማራ ሲነሳ ሁሉም ጸጉሩ የሚቆመው። የውሃ ልክነት የአባቶቻችን ሌጋሲም እንዲህ ነው …
https://www.youtube.com/watch?v=lH4Av3TTpYg
- · መከወኛ።
አቶ ወንድም ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ምንጩን ለመግለጽ ቢቆጠብም ለእኔ ግልጥ ነው። የራስ ተሰማ ናደው ሌጋሲ ቀጣይነት አስፈጻሚ የሆኑትን አግኝቶ ሚስጢርን ከምንጩ ቀዳሁት ይለናል። ጅል የለም። ከእሱ በፊት በመደበኛ ሰልጥነንም ሰርተንበታል ድርጅታዊ ሥራውን። ገና በሩቁ በጠረኑ እናውቀዋለን። የሆነው የምንለውን ነው የሆነው። ዛሬ አይደለም መከራው በ176 ድምጽ ይህ ከመጣ ነገ ደግሞ በኢትዮጵያ ሙሉ ድምጽ ዕድሉ ሲገኝ ማግስት እንዴት ይሆናል ነው ጉዳዩ። ጉድጓድ ስለሆነ በጥዋቱ ሊቀጣ እና ሊገራ ይገባዋል። መኖር ሲሞት እውነት ዝም አይልም።
ኢትዮጵያም አፍሪካም ርዕሰ መዲና አልቦሽ ይሆናሉ ከዛልን። አሁን የአዲስ አባባ ነፍሰጡር እናቶች ለጽንሳቸው ስጋትን እንዲቀልቡ መገደዱ በእርግዝናቸው ላይ ሁሉ ከፍ ያለ ጫና ፈጣሪ ነው። እዛ ተውልደው ያደጉት ታዳጊ ወጣቶችም ባለቤት አልባ ናቸው። አዲስ አበባ ብሄር አልባ ናት። ብሄር አልባነቷ ባለቤት አልባ አድርጓታል። ይህ ባለቤት አልባነቷ ደግሞ የጡንቻ መሞከሪያ ጣቢያ አደርጓታል። ይህ ነዋሪዎቿ እያሉ ስደት ተፈርዶባቸዋል። መከራም ተጭኗቸዋል። እንዳይተንፍሱም አዲስ የፍልስጤም ካባ ተደርቦላቸዋል። አዲስ የወሮበላነት፤ የሃሽሽ ሱሰኛነት፤ የጫት ማህበርተኝነት፤ የደረቅ ወንጀል ሰብዕና መለያ ተስጥቷቸዋል።
አሁን አማራ መሬት ላይ በርዕሰ መዲናዋ ጉባኤ እና ዕድምታ እዬታዬ ያለውም ይህንኑ ነው፤ የአማራን የዜግነት ስረዛ የሚሞግቱትን ከምድር ማስወገድም ይኖራል።
አማራ የሚፈራበት ሚስጥር ደግሞ ይህ ነው። አማራነት እንዲህ ይገለጻል። ስለምንለው ሳይሆን የትንፋሽ አቅሙ ራሱን ያብራራል። እንኳንም የሊሂቃኑን ድምጣቸውን ለመስማት አበቃን። ለመኖር ከተፈቀደላቸው - ካሰነበቷቸውስ?ያኮራሉ።
https://www.youtube.com/watch?v=4qK0SRhyU5E
የአዴፓ ለውጥ በምሁራን አንደበት
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ማዕልት።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ