ልዕልት ርዕዮት አለሙን እስኪ እንዴት ባጀሽ ልበላት።

ትናንትን ዛሬ በምልስት እስኪ ይቀፈው? ወርዱ ከቻለው?
 „በሰዎችና፡ በመላእክት፡ ልሳን፡ ብናገር፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ እንደሚጮኽ፡ ናስ፡ ወይንም፡ እንደሚንሽዋሽ ጽናጽል፡ ሆኜአለሁ። ትንቢትም፡ ቢኖረኝ ምሥጢርን፡ ሁሉና፡ እውቀትን፡ ሁሉ፡ ባውቅ፡ ተራሮችንም፡ እስካፈልስ፡ ድረስ፡ እምነት፡ ሁሉ፡ ቢኖረኝ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ከንቱ፡ ነኝ። ድሆችንም፡ ልመግብ፡ ያለኝን፡ ሁሉ፡ ባካፍል፥ ሥጋዬንም፡ ለእሳት፡ መቃጠል፡ አሳልፌ፡ ብሰጥ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ምንም፡ አይጠቅመኝም።“ (ዬሐዋርያው ዬቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆረንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ቁጥር ከ፩ እስከ
ከሥርጉተ© ሥላሴ
21.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


·       ማሰብ እና ማግኘት ጋዳ ናቸው።
ልዕልት ርዕዮት አለሙን ዓይኔን በዓይኔ የማዬት ያህል ነበር የማስባት። እጅግም እሳሳላት ነበር የዛሬውን አያድርገው እና። ከእስር መፈታቷን ብቻ ሳይሆን የብርታትን እኩልነት ብርሃን ትሆናለች ብዬም በጽኑ አስባት ነበር። መመኘት ከልካይ ስሌለበት የውስጤ ሐሴት ትሆናለች የሚል ብሩህ ተስፋ ሰንቄ ነበር መፈታቷን የጠበቅኩት። የሚገርመው የእሷም የእህቷም መጠሪያ ሥም የእኔም  የእህቶቼም ነው። ሥምም ትርጉም ይሰጣል የውስጥ ሲሆን።
እናም እጅግ አቅርቤ አያትም ነበር። በመጨረሻ ግን አሜሪካ ከገባች በኋዋላ ለእነዛ ካቴና ላይ ላሉ ነፍሶች ብጣቂ አዘኔታ ስታጣ ነፍሴን ጨነቃት፤ እጅግ ካዘንኩባቸው ጥቂት ነፍሶች አንዷ እሷው ሆነች። አሁን በቅርቡ በጀግኒት እማዋይሽ አለሙ ጉዳይ ታታሪ አቶ ተሎሳ ቃለ ምልልስ ያደረገላት እህት ስትናገር በስደተኛ እህቶቿ ላይ ፊርማዋን አለመፍቀድን ስሰማ የስደትን መከራ አውሮፓን ብታያት አልኩኝ።
እሷ እሰከ እህቷ ሁሉ ነገር አልቆላት አልጋ ባልጋ ነው ከአገር የወጣቸው። ሥራም አንቱ የተባለ ተደራጅቶ ነው የጠበቃት። የ40 ቀን እድል እንዲህ ነው። ስለዚህም ለስደተኛ አንዲት ቀን ለተደፋበት እህት አጋር ፊርማ ማሰረፍ ውድ ሆነ ከእሷ ቤት። ቅድመ ሁኔታ አስፈለገው። እነ ከርታቴን አላዬችም፤ ሲንከራተቱ አራዊትም ውቅያኖስም በልቷቸው የቀሩትም ለእሷ የነፃነት ታጋይ የዓለም አቀፍ ተሸላሚዋ ምንም እና ምን እንደሆኑ ህሊናዋ ብይን ይስጠው።
  • ማረፊያ

የሆነ ሆኖ በስንት ጊዜዬ ትናንት አንዲት የተቆረጠች ንግግር ከልዕልት ርዕዮት አለሙ ፈቅጄ አዳመጥኩኝ። እሷን ፍለጋ ለባጀው ነፍሴ ብርቱ ድልዳል ማረፊያ ነበር። እሷ ስትታሰር እና ስትፈታ ልዩነት ነበረው ለእኔ። አሁን እውነት ነው ላለችው ላመነችበት ጉዳይ ፍለጋ የሰጠችው አስተያዬት አስደስቶኛል። እጅግ አድርጌም ወድጀዋለሁኝ።  የእኔ ከእሷ በተቃራኔ ቢሆንም። ሙሉውን አላደመጥኩትኝም በእሷ እጅግ ስለተከፋሁኝ አዳምጫት አላውቅም። የሆነ ሆኖ ሙሉውን ማዳመጥ ለሚፈቅዱ ታሪኳም ስለሆነ ተወራራሽ ይሆን ዘንድ ከሥር ለጥፌዋለሁኝ።  
ሙሉውን ላመድመጥ አቅም አጣሁኝ። የመከፋት ዓይነቱን ለመግለጽ ራሱ ቃላት አጣሁለት። እንዲህ ከተገኘች ዘንዳ ይህን እውነት ፍለጋ የቀደመ ሰብዕናውን፤ አቅሟን ዛሬ ካገኘቸው ራሷንም፤ ከዝግጅቷ ጀምሮ ድርጅቷንም ግንቦት 7ን፤ መሪያዋንም በዕውነት ኢንዶስኮፒ መመርመር ግድ ይላታል። የዛሬው ጹሑፌ ዕድምታ ይኸው ነው። 

እግሬ መንገዴን እኔ ይህን ስጽፈው ትእግስት አልቆ ፍቅር እንዴት እንደ ተሰደደ ነበር። በ2016 የተጻፈ ጹሑፍ ነበር። ሊሂቃኑ ሁሉ ቢያነቡት ምኞቴ ነው። ብልጥናት እና ብልህነት ለፖለቲካ ትርፍ ያለውን ትርፍ እና ኪሳራ። ማህበራዊ ንቃተ ህሊናን የመምራት አቅም እና የመሳት ጉዞን ... 

ቁሞ ዬሚጠብቅ (Stagnant) ዬሆነ ዬአመክንዮ ድንጋጌዓለም አስተናግዳ አታውቅም!

የግል ሰብዕናን መገንበት የጠ/ሚር አብይ አህመድ ብቻ ሳይሆን የግራ ርዕዮት መከራ ነው። ግራ የተፎካካሪ አቅምን የሚሸበሽበብት ወነኛ የአይዲኦሎጂው መግለጫ ነው። መጨፍለቅ ነው፤ መጠቅለል ነው። ማጥፋት ማምከን ነው። ቡቃያን መንቀል ነው። በውስጡ ሳላለች አልታወቃትም መሰል፤ ለዛውም ጠ/ሚር አብይ አህመድ ቡድን አደራጀተው አቅም ለቅመው፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰብሰበው አይደለም ውደዱኝ ያሉት።
በራሱ ጊዜ መንፈሳቸው ቅርብ ውስጥ ስለመሆኑ ካለ አንዳንች ፕሮፖጋንዲስት፤ ካለ አንዳች የሚዲያ፤ የሙሉ ድጋፍ ችሮታ ባጡበት ሰዓት ሁሉም የአገር ውስጡም የውጩም ጥቃቅን ነገሮች እዬተቀነጫቡ ባገለሏቸው ወቅት በዝምታ ውስጥ የነበረው አብዛኛው ባለቤት አልቦሹ ውጭ እና አገር ወስጥ የሚገኘው ወገናቸው ያን ሁሉ በሳቸው ላይ የሚወርደውን ውርጅብኝ፤ ንቀት፤ እና ነቀፋ ጥሶ በጥዋቱ ነበር ሙሉ ድጋፍ በመስጠት አቅማቸውን ያጎለበተው።
በታሪክ እንዲህ አይንት የፍቅር ማዕበል ሞገድ በኢትዮጵውያን ዘንድ ሲፈጠር አገርም ዓለምም አይታ አታውቅም። ሲዊዞችን ራሱ ያስገረመ ያሰደመመ ነበር ተቀባይነቱ ሆነ ተስፋማነቱ። አንድ ልዩ ፕሮግራም ሰርተው እንዲያውም ለጥፌውም ነበር።
ይልቅ አሁን ይህን ዲካ የለሽ ተቀባይነት እና ፍቅር ፉርሽ ለማድረግ ድርጅታቸው ተግቶ የሚሰራበትም ያ የፍቅር እና የተቀባይነት ሞገድ አስደንግጦት ይመስላል እና ያ የፍቅር ስጦታ ቀውስ እስተናጋጅነቱ ዕለታዊ ሆኗል እጬጌው ተቀባይነታቸው።
አሁን ታሪካቸውን በማክሰል ላይ የሚገኘው ከራሳቸው ማህበረስ ያሉት ወገኖች ናቸው። ራሱን በራሱ በአዎንታዊና በአሉታዊ ወጅብ እዬናጠው የሚገኘው እራሱ የኦዴፓ ወሳኝ አመራሩ ነው። ደስታን በቅጡ መመራት ተስኖት። በተዛነፈ አቋም እና ፍላጎት እሱ ተነጦ ደጋፊዎቻቸውንም እዬበተነው ነው ያለው። አቶ ጀዋር ይብልጥብኛል ብሎ።
እነ አቶ ጃዋር አህምድ ከጉዳይ ባልጣፉት ጊዜ ስንት የተደከመበትን ሰብል እያጠወለገው ነው አቤቶ ኦዴፓ። ወጥ ፍላጎት እና ራዕይ ማጣት ራሱን እያዳጠው ይገኛል ድርጅታቸውን። 5 ዓመት ሙሉ በቀድሞው ጠ/ሚር አቶ ሃይለማርያም ደስ አለኝ ኮሽታን ያላስደመጠው ኦህዴድ /አዴፓ አሁን ባለመንበር፤ ባለ የወርቅ ካባ ተሸላሚ ሲሆን እራሱን በራሱ እዬፈተነው እና እዬፈተገው ይገኛል። ቸኮለ። ትእግስት አጣ። በአንድ ማዕልት ኦሮምያ እንፓዬር ካልጫንኩባችሁ ብሎ ደጋፊዎችን በጠራራ ጠሃይ ሞገተን። 
ወደ ክብርት ርዕዮት አለሙ ስመጣ የራስ ሰብዕና ግንባታን እመቤት ርዕዮት አለሙ ያነሳቸው የሌለ አይደለም ያለ ነው። እሷም እኮ መሸለሟን ትወደዋለች። ታከብረዋለች። ራሷን አስባ ነው የምትተጋው፤ የምትኖረውም ለራሷ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ነው። ስለዚህ ይህ ሰዋዊ ተፈጥሯዊም ነው። ነውር የለበትም ልላት ነው።
"አዲስ ነገር አላዬሁም የተለመደ ነው" ለምትለው ህልም እንደ ፈቹ ነው። 10 ዓመት ከግንቦት 7 ያዬነው አመርቂ አዲስ ሃሳብ አንድ ተብሎ ወደ ሁለት የሚሻገር የለም ለምንላትስ ምን ትል ይሆን? ይህ ቢሆን መብትም ነውና።
ጭራሽ እኮ የጠ/ሚር አብይ መንፈሰን የማያቀርቧቸው ወገኖችም አሉ። ይህም መብት ነው። ለነገሩ ግን አዲስ ነገር ከጠ/ሚር አብይ አህመድ ወዲያ ታይቶም ተስምቶም አያውቅም። እንዲያውም በዛብን። ተዋጥን። ፋታም አጣን። መቼ አንዱን አጀንዳ በሥርዓት መርመረነው አውቀን ነውና? አጣደፉን በአዲስ ደራሽ ነገር ቢባል የተሻለ ነው። ከሰበር ዜና ውጭ የዋልንበት ቀን ጥቂት ነው። አንዳንድ ጊዜ ድርብም ነው። የ100 ቀኑን  ይተንተን ይበተን ሙዙዬም ይሰራለት ቢባል አንድ አመት ይወስዳል። እኔ የአፋሩን ልቤን ስለመሰጠው አቅጣጫ ቀያሽም ስለነበረ ከሁለት ሳምንት በላይ ፈጅቶብኛል፤ ለዛውም ገረፍ ገረፍ ለማድረግ።   
በሌላ በኩል በዛ ገለጣ ውስጥ አንኳር ጉዳይ ተነስቷል። ከልቡ ላዳመጠው። የሐምሌ ዝምታ ወጀብንም ፍንጭ ሰጥተውበታል ስለ ቡና የስንብት ቅርቃር ፖለቲካ።
ወደ ቀደመው ነገር ስመለስ ሰራዊት ሲያምጽ ከሰራዊቱ ውጭ ካለው ይልቅ ቤተኛው በሚያውቀው ዲስፒሊን የመግራት ልዩ አቅም፤ ልዩ ተደማጭነትም አለው። ሜቶሎጂውን ያውቀዋል። ሥነ -ልቦናውን የራሱን ያህል ይረዳዋል። እሳቸው ደግሞ ከታች ጀምሮ እያደጉ በሠራዊቱ ውስጥ የመጡ  እንጂ ከላይ ቁብ ያሉ መኮነን አይደሉም። በሥራ አለም ደግሞ ቤተሰባዊ አቀራረባቸውን አብረዋቸው የሠሩት እንዲህ ይመሰክሩታል።
ከዶር አብይ አህመድ ጋር ስሰራ የማልወዳቸው 5 ነገሮች።፡

የኦህዴድ ሞተር ~ ዶክተር አቢይ ማን ናቸው?


ከመሬት ተንስቶ የተዋጊ አዛዥ መሆን እና ሰልጥኖም ኑሮበትም መሆን በፍጹም ሁኔታ የተለዬ ነው። ሌላው ቀርቶ ሲቢል ጋዜጠኛ መኮንኖችን ቃለ ምልልስ ሲያደርግ ብዙ ፈተናዎች አሉበት። አያውቀውም አልሰራበትም እና ሳይንሱን። የሠራዊቱ ቤት በመደዴ አይኬድበትም። የሠራዊቱን አካላትን ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ የማዬው በሲቢሉ ቋንቋ ነው። አይመጣጠንም ያ። መግባባትምን አይፈጥርም። 
እንደገናም እነሱን ለመሞገት አቅም ያጥራል። የሠራዊቱ ቋንቋው ራሱ የተለዬ ነው። አንድ ጊዜ ግንቦት 7 ለኢትዮጵያ ሠራዊት የበቃኝ ጥሪ ሲያቀርብ ከቋንቋ አጠቃቃም ጀምሮ ክህሎቱ ስስ ስለመሆኑ አብክሬ ጽፌዋለሁኝ። የወታደር ሰዓት አቆጣጠሩ እራሱ የተለዬ ነው። ቃላቶቹም የተለዩ ናቸው - የሠራዊቱ። አኗኗሩም እንዲሁ ፍጹም የተለዬ ነው። ቆቅ ነው።
ውትድራና ጥበብም ሳይንስም ነው። ውትድርና የሂሳብ ትምህርትም ነው። ውትድርና ምህንድስናም ነው። ውትድራና በገዢ መሬት እና በሙት መሬት ፍልስፍና፤ በመረጃ መቅደም እና መሳት ማሃል ቀውስን አርቆ የ አገርን ልዑላዊነት የሚጠበቅ ትልቅ ጥልቅ የጥበብ አውድ ነው። ይህ ደግሞ ኑረውበታል ጠ/ሚር አብይ አህመድ። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ብቸኛው የፖለቲካ ሊሂቅ ናቸው በዛ ጦርነት ላይ የተሳተፉ፤ ይህም ብቻ አይደለም ኢትዮጵያ በወታደራዊ ዘርፍ የደህንነት ሰው ወደ ሙሴነት ሲመጣ የመጀመሪያው ናቸው፤ ይህም ብቻ አይደለም በውትድርና ዓለም የተባባሩት መንግሥታት የሰላም ህግ ያስከበሩ የተባባሩት መንግሥታት ጥሪ የፈቀዱ፤ የተገበሩ አባልተኛም ናቸው። 
ይህን ኪጋሊ ላይ በርዋንዳ ፈጽመወታል። ይህም ብቻ አይደለም በኢንሳ ምስረታ ላይ ሰፊ ድርሻ የነበራቸው ሰው ናቸው። በመሪነት ደረጃ ለዲጅታሉ ዓለም ሙያተኛና ቅርብም ናቸው። ለሰላም እና ደህንነት ተቃርኖዎችን በመፍታት ሙያተኛ ናቸው ሠርተውበት ለስኬትም በቅተዋል፤ ለአስተዳደራዊ አማራርም ሙያተኛ ናቸው ሰርተውበታልም።
በፖለቲካ ሊሂቅነት ደግሞ አዬር ላይ ሳይሆን መሬት ላይ ከህዝብ ጋር አገልግሎት በመሰጠት ሠርተዋል። በትህትና፤ በርህርህና ደግሞ አይተናቸዋል። ስለዚህ ሰብዕናቸው ፕሮፖጋንዲስትም አያስፈልገውም ራሱ ይናገራልና።
ወታደር መሆናቸውን መናገራቸው ትክክል ነው። ምን ያሳፍራቸዋል? ለዛውም ባለ ማዕረግ ከፍተኛ መኮነን ናቸው። የእኔን ችግር ሴት እህቴ እንጅ ወንድሜ አይደለም የሚያውቀው። የወታደርን ችግር ደግሞ በቤቱ የኖረ ብቻ ነው የሚያውቀው።
የወታደር ኩዴታ እንዲህ በሙሉ የሥነ - ልቦና ትጥቅ እና ስንቅ ቤተ መንግሥት ድረስ ፊት ለፊት ሲመጣ ወታዳራዊ ቤት ላልኖረ ሰብዕና እጅግ ከባድ ነው ርደትም ነው። ስላለፈ፤ መከራው ስላላዬነው፤ ስልተኖረበት፤ አደጋው ደርሶ ስላልገጠመ አይደለም። ጥበቡ ሙያዊ፤ ጥበቡ ሰብዕናዊ፤ ጥበቡ ደህንነታዊ፤ ስልቱ ሰዋዊ የሆነ የ16ኛውን መቶ ክ/ዘመን የአጤ ፋሲልን ትህትና፤ የ19ኛውን መከራ የእቴጌ ጣህይቱን ብልህነት የ21ኛው ምዕተ ዓመት ሰውን ማዕከል ያደረገው የሉላዊ ስሜት እጅግ በሚደንቅ ክህሎት አዋደውታል።
ሊቀ ሊቃውንቱ የሙያው ባለክህሎት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በሩቅ ነው እንግዲህ ስሰማ ደነገጥኵኝ ነው ያሉት። እሳቸው የደነገጡ ሲቢል መሪ ቢሆኑ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ምን ይመጣ ነበር ብሎ አርቆ ማሰብ ነው። ይህን ብርጋዴር ጄኒራል ተፈራ ማሞ አጣነክረው መግለጣቸውን የዘሃበሻ ዜና ዛሬ ጥዋት በትኩሱ አዳምጫለሁኝ።
Ethiopia: -ሐበሻ የዕለቱ ዜና | Zehabesha Daily News

ሙያ እኮ ሙያ እንጂ ፕሮፖጋንዳ አይደለም። መፈለግ እና መሆንም አይገናኝም። ይህን እኔ አንድ ከፍተኛ የወታደር መኮነን እና እና የሲቢል የፖለቲካ ሊሂቅ በአንድ ኮሜቴ ውስጥ ሲኖር ህይወቱን ኑሬበት አይቻዋለሁኝ። በፍጹም ልዩ ነው። ማቀራረብም አይቻልም።
·       መወቀስ ግን አይገባትም።
በሌላ በኩል ልዕልት ርዕዮት ስሜቷን ደፍራ መግለጧ ደግሞ ተወቃሽ አድርጓታል። እኔ እንዲህ ዓይነቷን ርዕዮትን ነበር ስፈልግ ሳፈላልግ የባጀሁት። እናም ወደ እራሷ ተፈጥሮ ተመልሳ እንዲህ ሞግታ መውጣቷ ለእኔ ጎሽ እመቤቴ እንዲህ ሁኝልኝ ለሁልጊዜም እላታለሁኝ። 
ሌላው የእሷ ድርጅት አላት ግንቦት 7 የሚባል። ልትታገል፤ ልትሰዋ እምትፈቅድለት፤ ስለዚህ ሙግቷን ስታቀርብ የእሷ መሪ የውትድርና ባለሙያ ስላልሆኑ አቅሙ የላቸውም ከሚል ምልከታ ደጋፊያቸው እንዳይናወጽ የማረጋጋት መልዕክትም ነው ዕድምታው። ይህን መሰል ወታደራዊ ኩዴታ ንቅናቄያቸው አውራ ሆኖ አገር ቢመራ ቢገጥም አይችለውም የሚል የሥነ - ልቦናዊ ሽንፈት እንዳይኖር መከላከሏም ነው። ይህ ደግሞ የተገባ ነው። ድርጅቷን መከላከል አለባት። ከራስ በላይ ንፋስ የለምና።
ይህም ብቻ አይደለም ነገ የእሷ መሪ ፕሬዚዳንት// እና ጠ/ሚሩ ፉክክር ሲያደርጉ ፊት ለፊት ወጥታ ሞግታ ማሸነፍ ግድ የሚላት በአባልነቷ ነው። ይህ ደግሞ ትክክል፤ ይህ ደግሞ መሆን ያለበት፤ ይህ ደግሞ መሆን ያለበት ውሰኔ ነው። ለልዕልት ርዕዮት አለሙ መንፈስ መሪ አለው። መሪዋ ፕሬዚዳንት ፕ/ ብርሃኑ ነጋ ብቻ ናቸው። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ፊት ሲመጡ የነበረው ጉግስ እኮ ይህው ነው።
የጠ/ሚር አብይ አህመድ ደጋፊዎችም ሰከን ማለት ይኖርባቸዋል። ምክንያቱም ሲያጠፉም፤ ግድፈት ሲሰሩም፤ ሲያዳሉም ጠ/ሚሩ ሊወቀሱ፤ ሊተቹ ግድ ይላል። ለደጋፊወቻቸው ትክክል የሆነው ለደጋፊዎቻቸው ብቻ ሊሆን ይችላል፤ ያ ትክክል አይደለም ብለው የሚሞግቱ ከኖሩ እንሱንም ማድመጥ እና ሚዛንን ማስተካክል ይገባል።
እሳቸውም ቢሆኑ ይህን ከፈሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ቀድመውንም ወደ ፊት መመጣት አይገባቸውም ነበር። ደጋፊዎቻቸውም የሚመቻቸውን ብቻ ሳይሆን የማይመቻቸውን ትችትም መቀበል ግድ ይላቸዋል። ዴሞክራሲ አልጋ ባልጋ አይደለም። እዬመረረ እዬጎመዘዘም መቻልን ይጠይቃል። እንደ አቶ በቀለ ገርባ ገበርዲኔ ከረባቴ ወቀሳ አይነካው ከሆነ ሰብሰብ ብሎ መቀመጥ ነው የፖለቲካ ሊሂቁ ሁሉ። እኔ የምለው ግን እሷ ካነሳቻቸው ነጥቦች ባለነሰ ድርጅቷ ግንቦት 7 አድክሞናል እና እሱንም ትድፈረው በነካ እጇ ነው። አማራጭ ንቅናቄ ነውና። 
·       እንዴት? እንዲህ? 
የእሷ ንቅናቄም ወቀሳ ነቀሳ አይሻም። ትችትን አያስተናግድም። ሙግትን አይሻም። መታበይም አብዝቶ አለበት። ጠቅላይነቱን ደግሞ እኛው እራሳችን አሳምረን እንመሰከረዋለን። ብዕራችን እንዳይወጣ ከራሱ ሚዲያ የደረሰበት ሳይኖር በሞፈር ዘመት ተጉዞ እንዴት እንደሚያሳግደው ይታወቃል። አዳፍነው ነው መርሁ።፡አንዲትም ውጥን ማሳካት አይቻልም። ውሸትማ በገፍ ነው። እቅድ ሰክኖ ጸድቆ በቅሎ ያዬነው የድርድር የቃል የውሳኔ አይነት የለም። ስለዚህም ነው ትዕግስት እንዲህ እንጥፍጥፍ ብሎ አልቆ ፍቅር የተሰደደው።
ከላይ የለጠፍኩት ሊንክ ጹሑፍ ያን ጊዜ በድርጅቷ የተከፋሁበትን ይገልጣል። በርካታ ወጎችን ነበር የጻፍኩት። ዛሬ እሷ እንደ ልዕልት የምትታይበት ድርጅት ግንቦት 7 እሷ ሃሳቡን እራሱ ሳታውቀው ሥርጉተ ሥላሴ ተግታበታለች። 
ከሲዊዝ ጋዜጠኞች ጉባኤ ላይ ገለጣ ሰጥታበታለች፤ ለረጅም ጊዜ በጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራሟ ታግላለት አለች፤ በጸጋዬ ድህረ ገፆም አክበራዋለች። ሞጋቾቿ ጉዲት የሚል ሥም ሰጥተዋት ሌላ ሥራ አጥተው ሲያዋክቧትም ባጅተዋል። አባልም ደጋፊም ሳትሆን። 
ነገር ግን ኢትዮጵያን የማዳን ተልዕኮ ይዟል በማለት ነበር ፊት ከፊት ወጥታ እንደ እሷ ቀይ ምንጣፍ ሳይነጠፍላት ፍዳ ስትከፍል በጣምራ የኖረችው። ምላሹ ግን ኮሶ ነበር። በግል የደረሰውን መከራ አንድ ቀን ይጻፋል። በዝርዝር።
ትናንት የተናቀው የተገለለው የተረገጠው አማራ ዛሬ እክብሮ እንዴት እንደ ተቀበለ እንዴት ለማድመጥ ዝግጁ እንደሆነ ደግሞ አስተመሯል እትብት መንደሬን ጎንደርዬን አክሎ። ጥሩ ነው ያደረገው። አገር ወገኖቹን እልል ብሎ መቀበል የተገባው ነበር። ዛሬም ከማንም እና ከምንም በላይ ህይወታቸው ከስኬታቸው በላይ ያሳስበኛል። ለስኬቱ እነ ልዕልት ርዕዮት አለሙ ይትጉበት። እነሱ ወገኔ ባይሉኝ እኔ ግን ወገኖቼ ናቸው እና ክፉ እንዲደርስባቸው አልሻም።
የሆነ ሆኖ ልዕልት ርዕዮት አለሙ ሰሞኑን የጠ/ሚር አብይ አህመድ ወጣ ገብ የሆኑ አገላለጦች እሷ ስትወቅስ፤ ስትነቅስ ራሷን ማዬት መመርምር አለባት ነው የጹሑፌ መሰረታዊ ጉዳይ። አብይን አትንኩት ይላሉ የአብይ ደጋፊዎች እነሱም ብርሃኑን አትንኩ ነው የሚሉት። አብይን ብዙ ሰው አምልኳል እንሱም የብርሃኑ አምላኪዎች ናቸው።
በአጋጣሚው እኔ ብነግራት በአብይ ሌጋሲ ደጋፊ ሆኜ፤ ተሞግቼለት ግን እማያቸውን ግድፈቶች ለእህቴ ስነግራት ብርጭቆ ውሃ ከሞላ በኋዋላ አይጨምርም አብይን በሚመለከት የምፈልገውን መንፈስ አግኝቻለሁ እና አትድከሚ ብረጭቆዬ ሞልቷል ትለኛለች። እሷ ፓለቲከኛ አይደለችም ግን የማዬውን ስጋት እና ተስፋ ሳቀርብላት ተስፋውን ብቻ ነው የማደምጠው ትለኛለች።
እንደ እሷ አይነት ደግሞ ታላቅ እህቴ በፕ/ ብርሃኑ ነጋ ላይ የጸና አቋም አላት። ይህም መብት ነው። እኔ ደግሞ ፋክት ያለበት ቦታ ላይ መገኘት ምርጫዬ ነው። እኔ ለማውያን ነኝ ብያለሁኝ። ግን ሰው ተገድሎ ተዘቅዝቆ ተሰቅሎ እያዬሁኝ ዝም የምልበት ሞራል የለኝም። እማዬው ነገር እውነቱን እውነት ያልሆነው ደግሞ እንደ ለመደብኝ ወጥቼ መሞገት ነው። ህይወቴ ማጣሪያ ማንዘርዘሪያ ከሌለው ስለምን ሰው ሆኜ ተፈጠርኵኝ? 
ወዳጅ እንዲኑረኝ፤ አጃቢ እንዲኖረኝ አይደለም እምተጋው የድምጽ አልባዎቹ እናቶች የመከራ ሌሊቶች እንዲያልቁ ነው። ስለሆነም ትጋትን ለእውነት መቀለብ ግድ ይላል። ወቅት የሚሰጠውን መልካም ነገር አክብሮ መነሳት እክሉን ደግሞ መናገር ግድ ይላል። ዶሞክራሲ ሂደት ነው። ሂደቱ መታረም እና መታረቅ ይኖርበታል። 
ፖለቲካ የኩሬ ውሃ አይደለም። በዬጊዜው ሳንኩ፤ እንክርዳዱ፤ የጎሸው ነገር ሁሉ መጥራት አለበት። ጠ/ሚር አብይ አህመድ እስከ አሁን አገር እንመራለን ብለው ከተሰለፉት የሚለዩበት ቅን እና ስህተቶቻቸውን ለማድመጥም፤ ስህተታቸውም ለማረም ፈቃደኛ እና ዝግጁ ናቸው። የእሷ ድርጅት ግን ብጹዕን ነው ከሰማዬ ሰማዬት የመጣ። ግድፈትም ችግርም የማይፈጠር። በቃ ድንግል።
በጠ/ሚር አብይ አህመድ በኩል ግን ሁሉንም ጠረባ ያስተናግዳሉ። ያውም ከሳቸው ቁጥጥር ውጭ ያሉ ነገሮች አለባቸው፤ እኛ የማናውቀው ገልጠው የማይናገሩት ገፍተውም የማሄዱበት፤ የማይጋፉት ክፉ ሰቅ አለባቸው። ይህን እዮር ብቻ ነው የሚያውቀው የቡናውን ፓለቲካ የሐምሌውን የዝምታ ናዳ።   
በሌላ በኩል ግን የእሷ ፓርቲም የቅዱሳን ቅዱስ እንዳልሆነ ሁሉ፤ መሪዋም እንደሚያጠፉ እንደሚሳሳቱ ያሉትን ባሉበት ልክ እንደማይገኙ ደፍራ መተቸት አለባት። ትንሳኤን ህይወት ሲባል ሰምተን ነበር እኮ! እነሱ ያን ቢአስፈጽሙ ከ ኢህዴግ ጋር ምን ድርድር ያስፈልግ ነበር።
ራሷ በሃላፊነት ከምትመራው ፕሮግራም ጀምራ ሚዲያዋም እኩል እንደማያስታናገድ አጋ እንደሚለይ መሞገት አለባት። እንግዲህ ዕውነትን ደፍራ ሙግት ከቀጠለች ስፈልጋት የባጀሁትን ልዕልት ርዕዮትን አለሙን አገኘሁ ብዬ ሐሴት አገኛለሁኝ ማለት ነው። በውጥኑ ግን አልፈነድቅም እንደ ኦነጋውያን፤
የትናንቱ ጀግንነት የሚለው ቅጥል ማስቀጠል የሚቻለው ከራስ መነሳት ሲቻል ብቻ ነው። በምልሰት ያን ጊዜ በዚህ መሰል ተከታታይ ጹሑፍ ድርጅቷኝ ስሞግት ተወግዣለሁኝ፤ ዛሬ እሷ ጠ/ሚር አብይ አህመድን ስትሞግት ግን ጀግና ናት። እኔ ጀግና እምላት የአገር ፕሬዚዳንት ለመሆን ምኞተኛው መሪዋን ፕ/ብርሃኑ ነጋ ከድርጅታቸው ውጭ ያለውን ዜጋን እንደ ዜጋ የማዬት አቅም እንዲኖራቸው መሞገት ይኖርበታል። መሪነት በሃሳብ የሚሞግተውንም ቻል አድርጎ ማቅረብ፤ ማቀፍ፤ ማድመጥ ወገኔ ነው ብሎ ከልብ መቀበል ሲቻል ብቻ ነው። የዬትኛውንም ሚዲያ ሙግት ሲደፍሩ ነው። ሃቅ ካላቸው ስለምን ሚዲያንስ ሙግትንስ ይፈራሉ?
እስቲ በዚህ አቅሟ አቶ ልደቱም እናት አለው፤ አቶ ልደቱም እህት አለው አቶ ልደቱም ዜጋ ነው፤ ሰው ነው ካጠፋም/ ካላጠፋም በማለት የእኛ ንቅናቄ አሸንፎ ፕሬዚዳንት ስንሆን፤ መሪ ስንሆን አቶ ልደቱን እስከ ቤተሰቡ ልንሰርዘው ነው ወይ ብላ ትጠይቅ እስቲ ፕ/ብርሃኑ ነጋን? 
እኔ የፕ/ብርሃኑ እናት ሁለት ጊዜ ልጃቸው ሞት የተፈረደባቸውን ስሜት ተጋርቻለሁኝ፤ አቶ ልደቱ አያሌውም እናት አላቸው። ለሳቸውም አሳብላቸዋለሁኝ። የልጃቸው ሰላም መሆን ምኞታቸው ነውና። ለ እናቶች በዬትኛውም ዕድሜ እንሁን ሁልጊዜ እንደ ልጅ ነው የሚያዩን። 
ለእኔ የሁለቱም እናቶች ክብሮቼ ናቸው። ዕንባቸው - ሰቀቀናቸው - ስጋታቸው የእኔም ነው። ሐሴታቸው ደግሞ ውስጤ ነው። በእንሱ እናት ውስጥ የእኔም መከረኛ እናት ሞገደኛ ልጅ ወልዳ ፍዳዋን አሳሯን አስከፍያታለሁኝ። ስለሆነም ወደ አገር ሲገባ ፍቅር - ምህረት - እርቅ እኮ መጀመሪያ ከራስ ጋር መታረቅ ይመስለኛል። የዲያስፖራውን ልተዎው እና። ዴያስፖራውን ስንታመስ እንደባጀነው እንደ በተኑን ነው አገር የገቡት።
ገና ሰሞኑን ነው ርዕዮት አለሙ የተፈጠረችበትን ፍንጭ መጀመሯን ያዬሁት፤ ስለሆነም በነካ እጅሽ ንቅናቄሽንም አብጠልጥይው፤ ሞግችው፤ ጥረቢው ነው ቁም ነገሩ። ሃሰት ሲናገረም ሞግቼው፤ ቃል ሲገባም የት ደረሰ ያ ቃል በይው ነው ፍሬው ነገር። 
ይህ ለልዕልት ርዕዮት የምሰጠው ቆራጣ የቤት ሥራ ነው በንቅናቄዋ አናት ሊሂቃን ላይ መጀመር ስላለባት። አሁን እንደ አዲስ የቅንጅት ጦስ ተቀስቅሷል። መንፈሱ የቅንጀት ከተፈለገ ፍርሻውንም ደፍሮ ማጥራት ይጠይቃል። በስተቀር እያመረቀዘ ከትወልድ ወደ ትውልድ ቋሳው ይሸጋገራል። እስከ ስንት ጊዜ ነው በሁለት ጎራ ተከፍሎ ይህን የጥገና ለውጥ መንፈስ ጋር አብሮ መጓዝ የሚቻለው። አንድ ሰው ዕድለኛ ሲሆን ዕድሉን ለመጠቀም የፈተናውን ዳገት መድፈርም ይጠይቃል።
ይህ ዛሬ ቢፈራ መሬት ላይ ህዝብ ይጠይቃል። ተሸሽቶ የማይሸሹት ነገር ነው። አንድ ቦታ ላይ ዕልባት ማግኘት አለበት ለትወልድ ብከነት ሲባል። ማን አጠፋ ለማለት አንድ መረጃ ተይዞ መኬድ የለበትም። የግራ ቀኙን ማድመጥ ግድ ይላል።
ለውጥ እንደግፋለን ሲባል ከዚህ መሰል ቁርሾ መውጣትን በእጅጉ ይጠይቃል። አሁን ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ዛሬ ከአንድ አፍታ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩኝ። ከዶር ወርቅነህ ገበዬሁ ጋር የነበራቸውን ቅሬታ ገልጾ እንደሚያገኛቸው ነበር ደስ በሚል ስሜት የገለጸው።
ከፕ/ ብርሃኑ ነጋም ይህ ነው የሚፈለገው ይህንኑ ነው። በፍቅር ፍለጋ አሸናፊም ተሸናፊም የለም። ተሸናፊው በቀል፤ ቁርሾ፤ ጥላቻ፤ ቂም እና ኢጎ ብቻ ናቸው። ስንት ዘመንስ ሊኖር? ይኸው ይቅር ሳይባባሉ ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል እኮ አለፉ። በዚህ አጋጣሚ ጋዜጠኛ ክንፈ አሰፋን እጅግ አደርጌ አመሰግኜዋለሁኝ። የልጅ አዋቂ ነው። እራሱ የነገ ፕሮጀክቱ መስመር እንዴት ከልብ ይገባል። እምዬ በጎደላት ላይ ለመትጋት ነው ትልሙ። አላዛሯ ኢትዮጵያ ቀዳዳዋ፤ ነዳላዋ በርካታ ነው። ተባረክ የእኔ አባት።
በሌላ በኩል አሁን ከዚህ ላይ የአብይ ሌጋሲ ይህን ሁሉ ፍዳ የሚያው በማፈረስ ስላልጀመረ ነው። ወንጀለኛው፤ ሴረኛው፤ መልቲው ሁሉንም ከእነሸሩ ተሸክሜ ለውጥ አመጣለሁ ብሎ ፍዳውን እዬከፈለ ነው። ያ ጠላፊ የተንኮል መረቡ ሁሉ እንዳለ ነው። ሰውም እንዳለ ነው። እናም መከራው በፍጹም ሁኔታ አዬለ። ይህን መረዳት ደግሞ እኛም ተሳነን።  
ሁልጊዜም የፋክት ወገንተኝነት ነው ለማናቸውም ሰው ልብ ሊሆን የሚገባው ባይ ነኝ። ሚዛንም የሚያስጠብቀው ዕውነት ብቻ ነው። በዚህ ላይ ከመሼ ልዕልት ርዕዮት አለሙ ምን ታይቷት እንደ ሆነ ባላውቅም ቃለ ምልልስ አድርጋላቸው አለች ለኢትዮ አፍረካዊው የኢኮኖሚ ሳይንቲስት ለዶር ፈቃዱ በቀለ።
እሳቸውን በጹሐፋቸው እጅግ አድርጌ የማከብራቸው ምክንያቱ ሥርዓት ቢለወጥ ባይለወጥ፤ ተደናቂ ቢመጣ ባይመጣ፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ ኖረ አልኖረ ሁልጊዜም ፋክታቸውን ይዘው ነው ብራና ላይ የሚገኙት። እኒህን ሊቀ ሊቃውንት አብዝቶ ኢትዮ ሚዲያ ያስተናግዳቸዋል፤ አሁን ከሆነ ደግሞ ዘሃበሻ እና ሳተናውም ታክለዋል። እንደሳቸው ያሉ ሊሂቃንን ጌታ ያበራክትልን። አሜን!ከስሜት፤ ከኢጎ፤ ከፖለቲካ ድርጅት ፍላጎት የወጣ ሊሂቅ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ትንፋሽ ነውና።  
ማንም ይሁን ማንም አጠፋ፤ ግድፈት ፈጸመ፤ ህግ ተላለፈ ብለን ስናስብ ወጥተን መመጎት ብቻ ነው የዴሞክራሲን መንገድ ፍልስፍና ጉሸት የሚያጠራው እንጂ በማስታመም፤ አትንኩብኝ በማለት፤ ለእውነት ድርብ ግርዶሽ በመሥራት ከሆነ ፈጽሞ ዴሞክራሲ ህልም ነው የሚሆነው።

ስለዚህም የልዕልት ርዕዮት አለሙ የአሁኑ መስመር ከራሷ መጀመር ከቻለች ተፈላጊ መስመር ነው። በሽታው ግን የሶሻሊዝም ስለመሆኑ እና የዚያ ቅኝት ሊሂቃን ስለመሆኑ ልነግራት እሻለሁኝ።

·       መቋጫ። መቋጫዬ ከቀደመው ጹሁፌ የተቀነጨበ ነው።
ራዕይን በርስትነት ለመያዝ ማሰብ ሃቅን ያልደፈረ፣ ዬሰውን ልጅ ዬማሰብ ጸጋውን ዬሚጠቀጥቅ ህግ አልቦሽ መንፈስ ዬወለደው ዬኢጎ፤ ዬግል ሌጋሲ ዕዳ ነው።  ሰውስ ቢያንስቢያንስ ምን አለ ለወቅት ይሉኝታ ቢኖረው? ወቅት እራሱን ዬሚገልጸው ለአድማጬ ብቻ ነው። ወቅት ዕውቅና ዬሚሰጠውም ለአክባሪው ብቻ ነው። ወቅት ትርፋማ ዬሚያደርገውም ለአፍቃሪው ብቻ ነው። ወቅት ውስጡን ዬሚሸልመው እሱን ሊተረጉሙት ለፈቀዱ ቅኖች ብቻ ነው። ዬወቅት ዬማስረጃ ሰነዱ ህዝብ ብቻ ነው። ከህዝብ ውስጥነት ላለመውጣት ልዩ ጥረት ማድረግ ይገባይመስለኛል። ከወቅት ሥህነህይወት ጋር መተላለፍ ለሁሉም አይበጅም።
በመጨረሻ እኔ የልዕልት ርዕዮት አለሙን ገለጣ የተቆረጠችውን ብቻ ነው ያደማጥኩት ሙሉን አላዳመጥኩትም። ግን መነሻ ሃሳቡ ቁንጽል እንዳይሆን ከታሪክ ጋርም መያያዝ ስላለበት ሙሉውን ሊንክ ፈልጌ ስላገኘሁት ለጥፌዋለሁኝ። ከሥር በልዕልት ርዕዮት አለሙ ላይ ወቀሳ አለ ሳነበው። ይህ በፍጹም ሁኔታ የተገባ አይደለም። ነፃነቷን መጋፋት ነው። ዕውነት ያላቸውን፤ የምታምንበትን አፍልቃ መቀረቧ እኔ ስፈልገው የነበረው የቀደመ ሰብዕናዋ ስለሆነ እኔ አስደስታኛለች።
ESAT Eletawi Thu 18 Oct 2018

ዕውነት ተሸንፋ አታውቅምዬምታሸንፈው በአደባባይ በገላጣ ነው!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

ማለፊያ ሰንበት። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።