ልጥፎች

ከጃንዋሪ 4, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የራስነገር።

ምስል
የራስ ነገር ። „አንተ በህይወት ሳለህ አእምሮህም  ሳለች ግብርህን አትለወጥ።“  መጽሐፈ ሲራክ ፴፳ ቁጥር፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 04.01.2019 ከእመ ዝምታ - ከሲዊዘርላንድ። መቅድም። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? የራስነገር። የራስነገር ብዙ ነው። የራስነገር ሁለመና ነው። የራስነገር ሁለንትና ነው። የራስነገር መስታውት ነው። የራስነገር ሰውኛ ነው። የራስነገር ተፈጥሮኛ ነው። የራስነገር መ ሆን ኛ ነው። የራስነገር ቢሆንም ባይሆንም ቢያምርም ቢከፋም ብቻ የራስነገር የራስ ነው። አፍንጫው ደፍጠጥ ከንፈሩ ነፋ፤ ፊቱ ከስከሰከስ ቁመቱ አጠረ፤ ሰውነቱ ደንበል ትክሻው ጠበብ ያለው የራስነገር ከሆን ደስ ይላል ይወደዳል። የመቻል ትሁቷ እህቴ አጭር ወንድሟን እሰከ ነፍሷ ነው የምትወደው። የትዳር አጋር ግን ምርጫዋ ረጅም ነው። እሷ እራሷ አጭር ናት። በዛ ላይ ባርቾ ናት። አጠር ያለ የትዳር አጋርነት ጥያቄ ቢያቀርብ ሁለ ነገሩ ቢስማማት ግን ላትፈቅድ ትችላለች ዘለግ ያለ ስለምትሻ።  ለወንድሟ ግን ቅድመ ሁኔታ መስፈርት አይወጣለትም የራስነገር ስለሆነ ጌትዬ አባትዬ ትለዋለች። እሱን ሳታይ፤ ትንፋሹን ሳታዳምጥ ውላ ማደር ጭንቋ ነው። እህቴ ወንድሟን እንዲህ ነው  የምትጠራው አብዬ ጌታዬ አባትዬ ቁልምጫው እንክብካቤው ልክ የለውም።  ሌሎቻችን ትርፍ ነን። እሱን የመሰለ ሰው በምድር የተፈጠረ አይመስላትም። ጋብቻ ላይ ሲመጣ ደግሞ ቆንጆ ወንድ ነው ምርጫዋ። ወንድሟ ደግሞ አሜሪካዊውን ስሚዝ ነው የሚመስለው በቁመት እንዲያውም ከስሚዝ አጠር ይላል። ስለምን ወንድሟን መረጠችው ሲባል የራስነገር ስለሆነ። የራስነገር ተወዳጅ፤ ተፈቃሪ ነው። ...