የራስነገር።
የራስነገር።
„አንተ በህይወት ሳለህ አእምሮህም
ሳለች ግብርህን አትለወጥ።“
መጽሐፈ ሲራክ ፴፳ ቁጥር፱
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
04.01.2019
ከእመ ዝምታ - ከሲዊዘርላንድ።
- መቅድም።
ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? የራስነገር።
የራስነገር ብዙ ነው። የራስነገር ሁለመና ነው። የራስነገር ሁለንትና ነው። የራስነገር መስታውት ነው። የራስነገር ሰውኛ ነው። የራስነገር
ተፈጥሮኛ ነው። የራስነገር መሆንኛ ነው። የራስነገር ቢሆንም ባይሆንም ቢያምርም ቢከፋም ብቻ የራስነገር የራስ ነው። አፍንጫው ደፍጠጥ
ከንፈሩ ነፋ፤ ፊቱ ከስከሰከስ ቁመቱ አጠረ፤ ሰውነቱ ደንበል ትክሻው ጠበብ ያለው የራስነገር ከሆን ደስ ይላል ይወደዳል።
የመቻል ትሁቷ እህቴ አጭር ወንድሟን እሰከ ነፍሷ
ነው የምትወደው። የትዳር አጋር ግን ምርጫዋ ረጅም ነው። እሷ እራሷ አጭር ናት። በዛ ላይ ባርቾ ናት። አጠር ያለ የትዳር አጋርነት
ጥያቄ ቢያቀርብ ሁለ ነገሩ ቢስማማት ግን ላትፈቅድ ትችላለች ዘለግ ያለ ስለምትሻ።
ለወንድሟ ግን ቅድመ ሁኔታ መስፈርት አይወጣለትም
የራስነገር ስለሆነ ጌትዬ አባትዬ ትለዋለች። እሱን ሳታይ፤ ትንፋሹን
ሳታዳምጥ ውላ ማደር ጭንቋ ነው። እህቴ ወንድሟን እንዲህ ነው የምትጠራው አብዬ ጌታዬ አባትዬ ቁልምጫው እንክብካቤው ልክ የለውም።
ሌሎቻችን
ትርፍ ነን። እሱን የመሰለ ሰው በምድር የተፈጠረ አይመስላትም። ጋብቻ ላይ ሲመጣ ደግሞ ቆንጆ ወንድ ነው ምርጫዋ። ወንድሟ ደግሞ
አሜሪካዊውን ስሚዝ ነው የሚመስለው በቁመት እንዲያውም ከስሚዝ አጠር ይላል። ስለምን ወንድሟን መረጠችው ሲባል የራስነገር ስለሆነ። የራስነገር ተወዳጅ፤
ተፈቃሪ ነው።
· ስለራስነገር ሲሰላ።
እንደ አገር ልጅነት እኛስ የራስነገርን ለማክበር የኢትዮንየራስነገር ለማክበር ምን አቅም አለን ነው ቁምነገሩ
የዚህ ጹሑፍ አብይ ጉዳይ። የራስነገርን ዕድል የሰጠነው ቀን በሁለመና እንሸንፋለን። ኢትዮጵያነት ሱስ ነው ምን ያህል ዶር ለማ
መገርሳን አንጥሮ መንበር ላይ እንዳዋላቸው ተመልክተናል፤ ከዚህም ባለፈ „ስንኖር ኢትዮጵያ ስንሞትም ኢትዮጵያ ነን“ የሚለውም ምን
ያህል ዶር አብይ አህመድን የውስጥ ፅላት እንዳደረጋቸው ይታዋቃል። የቅድስት ተዋህዶ ነገርም ከመጣ "ኦርቶዶክስ አገር ነው" ያሉት
ነገር ጽላት ያስቀርፃል። የራስነገር እንዲህ ከውስጥ ሲሆን ውስጥን ያብራራል፤ ውስጥን ይተረጉማል፤ ውስጥን ያመሳጥራል - ውስጥንም ያነጥራል እንደ ጠራ ንጡህ ቅቤ።
ዕድሜ ልኩን በፖለቲካ ዓለም የኖረው ሁሉ "ኢትዮጵያ“
የምትለውን ውስጥነት ለመሸሽ ቀለም ሲመርጥ ውሎ ሲያድር አንበሶች መጥተው ኢትዮጵያ ባሉ ማግስት ሚሊዮኖች አበረን ተሰለፍን። እኛ ብቻ አይለም። ዓለም እራሷ እንዲዚህ ዘመን የደፈረ አወንታዊ ርዕሰ
ጉዳይ መሆንን በእኛ ዘመን አላዬንም አልሰማነም።
ሚዲያው ሁሉ ድንቅነቱን ተመሰዕጦውን እዬገለጠ ነው። አፍሪካውያን አውሮፓውያን ጋዜጠኞችም
ምስክርነቱን ደፍረውታል። የመንጌም „ኢትዮጵያ ትቅደም“ እሰከከሁን ተመስጥረው እንዲወደዱ ያደረገው ሚስጢር ነው። ናልን መንጌ የሚሉ
የዛሬ ታዳጊ ወጣቶች ሁሉ አሉ። የማያውቋቸው።
· ህዝብ እና ኢትዮጵያዊነት።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሊሂቃኑ ናቸው የሚያምሱት
እንጂ ልዩነት አያውቅም። አገር ወዳድ ስለሆነ አገርን አስቀድሞ የመጣውን ሁሉ እጁን ዘርግቶ ነው የሚቀበለው ደጉ የኢትዮጵያ ህዝብ። „ሃይማኖት የግል አገር የጋራም“ የጃንሆይ መርህ ነው። የሚገርመው ዶር ለማ
መገርሳም፤ ዶር አብይ አህመድም፤ ኮ/ መንግሥቱ ሃይለ ማርያምም፤ አጤ ሐይለሥላሴም ኦሮሞ ናቸው። በዘመኑ ኃያል፤ ተፈሪ፤ ተደማጭ ሆነው እንደ የሚከተሉት ርዕዮት
ዓለምም ሉላዊ ዓለምም ተቀብሎ አስተናግዷቸዋል።
ሁሎችም ደግሞ ፓን አፍሪካኒስት ናቸው። ጎላ ያለጥሪታም ያደረጋቸው፤ በመንፈስ ሃብት ዲታ
የሆኑትም ከዛ ጥብቆ ሳጥን ውስጥ ያመለጡ ሰለሆነ ነው ከፀረ ኢትዮጵያዊነት ፍልስፍና። ፈጣሪ አድኗቸዋል። በኢትዮጵያዊነት ፍልስፍና ራሳቸውን ለሰከንድ አታላው ሸፍጠው የማያውቁም ናቸው። የራስነገር ልባቸው ስለሆነ። የራስነገር ልባቸው ህሊናቸው
አንጎላቸው የሆነ ሁሉ ወድቀው አይወድቁም። ማለቴ በለጠፍ ማንነት በአክሮባቲስትነት
አይታወቁም እንደማለት። ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ ከሆነ ግን የህዝብ ህሊና ማንዘረፍዘሪያ ስላለው ገለባውን እዬለዬ ስንዴውን ያነግሳል።
ስንዴ ደግሞ የድንግልና የቅድስና ምልክት ነው። ከእህል ዘር ስንዴ፤ ከአዕዋፍ ዘር ርግብ እንደሚወከለው ሁሉ። ንስርም ሆነ ጥቁር ቁራ አሞራ እንዲሁ በተለያዩ አገሮች የተለያዬ የክብር ዕውቅና አላቸው። ጥቁር አሞራ ብልህ እና አዋቂ ነው ለጀርመኖች።
በነገራችን ላይ የራሰነገርን ባለማከበር፤ በመርሳት፤ ዕውቅና ለመስጠት
ባለመድፈር በዓለም ደረጃችን ከዬትኛው እንሆን ብዬ አስባለሁኝ - ዛሬ ዛሬ። ያው የቁጥር ተማሪ አለመሆኔን በአንድም በሌላም ገልጫለሁኝ።
ከዚህ በላይ በጥናት ስላልተመሰረተ ለሃሳቤ ደረጃም መስጠት አልችልም። የራስነገር ናቂዎች ስለመሆናችን በ60ቱ የሶሻሊዝም ዘመን ያዬነው
የኖርንበት ያደግንበት ገመናችን ነው።
የራስነገር አይከበርም። የራስነገር አይደነቅም። "ኢትዮጵያ“ የሚለውን ሥም ፊት ለፊት ለማምጣት ምጥ ነው። ፍዳ። መለያዋን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ምልክት ለማድረግ አይደለም ለማዬት
ፍዳ ነው። ድርጅቶች ዓርማ ሊኖራቸው ይችላል። ይህ ክፋት የለውም።
ከዜግነታችን በላይ ግን ሊሆን አይገባም። ዜግነታችን የራሱ የሆነ ዓርማ
አለው። ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነኝ ለማለት ያስቻለን ሚስጢሩ ያለው ከዚህ ስለሆነ። ሃሳብ እንዲጫነው ለማድረግ ቅጥልጥሉ ቀርቶ ንጹሁን
ተጠቀሙ ብሎ ነው ጎጃም እንጅባራ ላይ እኛ ስንታመስ ቦግ አድርጎልናል እዮር። ሐረር አካባቢም ኢትዮጵያዊነትን ለመንቀል በቅድስት ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ የተካሀደው ዘመቻ ቁጣው ከሰማይ እሳት አዝንቧል።
ዋንኛው ጸረ ኢትዮጵያ ሸጎሬ ላይ ያሉ እራሳቸውን
አብለው የሚኖሩ
ሊሂቃን ኢትዮጵያዊነት እራሱን ችሎ ነጥሮ እንዳይወጣ ተጭነውታል በአንድም በሌላም። አንዱን አቅርበህ ሌላውን ስታራቅ በዛ ወስጥ
ኢትዮጵያዊነት እንደሚታመም አይታውቅም። የራስነገር በተረሳ ሁኔታ ላይ ማዕካለዊ አመክንዮ እንደሚሾክል ልብ አይባልም።
ሲያዳልጥ ደግሞ መልሶ ከዛ ለመሸጎጥ እሩጫ ነው። ካለሱ መድመቀም፤ መክበርም እንደሌለ ሰኔ 16 ቀን 2010 ጸሐዩ በአደባባይ ስለወጣ። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ
እና ቅኖች ሳተናው ድህረ ገጽ ጨምሮ ስንናገር ግን አድማጭ አልነበረም። ሰኔ 16 ቀን ሁሉንም መልክ አስያዘልን። ሴኔ 16. 2010ን ባገኘው የወርቅ ሀብል አሳራለት ነበር። እና ሯጮቹን ረድፍ አስተካክሎ ገራልን። በዛ አደባባይ ጎልቶ ደምቆ ለመታዬ አዲስ ጥረት ተጀመረ። ከውስጥ ከሌለ ግን በዬፌርማታው መንጠባጠብ አይቀሬ ነው። ድልዝ ማሰሮ
ቀኑን ጠብቆ መወርዛቱ አይቀሬ ነውና።
· አማርኝ ቋንቋ እና ትንግርቱ።
የኢትዮጵያዊነት ደማቅ ማንነት መግለጫ የዕውቀት
አውራው አማርኛ ቋንቋ የራሱ የፊደል ገበታ ያለው መሆኑ ነው። የጎንደር ጥልቅነት የሚቀዳው ከዚህ ሚስጢር ነው። አማርኛ ቋንቋም
ተገፍቶ ተገፍቶ የትሜና ቢጣልም ዘመን በራሱ ጊዜ ከዓለም ቋንቋዎች ተርታ አውሎታል።
አማርኛ ቋንቋን የመሰለ ታላቅ የሉላዊ ቋንቋ ምን
ያህል በራስነገር አኮሻሾች ጦርነት ላይ እንደ ታወጀበት የምናወቀው ነው። ለራስነገር ሌላ ተቀናቃኝ ይፈልግለታል። አሁን የላቲን
ፊደል ሌላ የ አማርኛ ቋኝቋ ተቀናቃኝ ሆኖ እንዲወጣ 27 ዓመት ተሰርቶበታል። የመንፈስ ባንዳነት በፈቃድ። የመንፈስ ቅኝ ተገዢነት በመውደድ። የራስህን ወርውረህ የሌላን የራስነገር የ እኔ ብለህ ስትቀበል ልጥፍነት መፍቀድን ስለመሆኑ አልታዬም።
ኦሮሞኛውን በግዕዝ ወይንም በአማርኛ ቋንቋ ማኬድ ሲቻል። ስለጎንደር ሲነሳ ኦሮሞዎች መንፈሳቸውን ማሸሸት አይኖርባቸው ነበር።
ፈደል ሲባል ጎንደር ነው። ጎንደር ሲባል ደግሞ በዛ መንፈስ ውስጥ ሁሉም አለሁ ማለት ነበረበት፤ ሁሉም ባለበት ነገር ጠላት ሆኖ
መውጣት መታመም ነው።
ፊደልን የ እኔ ብሎ በዛ ሁሉንም ቋንቋ ማስኬድ ይቻል ነበር። ሃብትነቱ የሁሉም ነውና። ጎንደርም አማራም
ኢትዮጵያዊ ነውና። ከፍ ሲል አፍሪካዊ ነው። የእኛን ነገር ለማደብዘዝ የተሄደበት መንገድ ዛሬ
የፌድራሉ ሥልጣን ሲያዝ ማስሪያው ያ ነበር። ይህ እንዳይሆን ነበር ህውሃት ተግቶ የሠራበት። ትግራይ ላይ አማርኛ ቋንቋ እዬተነገረ
ኦሮምያ ብሎ በከለለው አማርኛ ቋንቋ ውግዝ ከአርዮስ ተብሎ ተለጣፊ
ማንነት ተሰጠው፤ በሌላ በኩል ህውሃት በወረራ በያዛቸው ወልቃይት፤ ጠገዴ እና ራያ ያሉ ማህበረሰቦች ደግሞ አማርኛ እንዲናገሩ አይፈቀድም።
ስለምን ፌድራል ላይ የመድረስ ዕድላቸው መታገድ ስለነበረበት ልክ እንደ ኦሮሞዎች።
በሌላ በኩል አማራ ከፖለቲካ ምደረክ ማውጣት ትልቁ ተልዕኮም ነው የህውሃታውያን እና የመሰሎቻቸው የመንፈስ ተጋቢዎቻቸው። ትግራይ ላይ የሚወለዱ ግን በሁሉም መስክ ይሳተፋሉ።
አዋራ ተወናዮች እነሱ ናቸው በጥበቡ ዓለም። በርካታ ጸሐፍትን አሏቸው። በርካታ ዬፌድራል አራጊም ፈጣሪ አላቸው።
የሌላ ብሄረ ብሄረሰብ ሊሂቃን አማራ መደራጀት የለበትም
የሚሉበት መሰረታዊ ምክንያት ሌላ ምንም ሳይሆን በፖለቲካ ተሳትፎ ላይ ማህበረሰቡን ለማስገለልም ጭምር ነው። ተጨማሪ ከአማርኛ
ቋንቋ ሌላ ቋንቋ መቻል የሚል መሥፈርት ግንቦት 7 ያወጣበትም ሚስጢሩ ይኸው ነው። በዚህ ወስጥ ተሁኖ የዜግነት ፖለቲካ ህልም እልም ነው። አውነቱን ራሳቸው መሥራቾቹ መዋጥ መሰልቀጥ ይኖርባቸዋል። ለዚህም ነው አንድ ቀን በራሳቸው ሚዲያ አቶ ሃብታሙ አያሌው ገልብጡ ያላቸው ከጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው ጋር ውይይት ሲያደርጉ።
ምክንያትም አማራን ከፖለቲካ ለማግለል የተመሰጠረ የሴራ ሸጎሬ ስለነበር። አምርኛ ቋንቋ መጫን ሲጀመር የተካበው
ተናደ እና እኩል ሁሉም ዜሮ ላይ ተቀመጠ። ዋንጫው ቂጡ ወለቀ። ቋንቋ የወል ሃብት ነው። ቋንቋ የዕውቀት የጥበብ ሥጦታ ነው። በእኛ ሲመጣ ደግሞ በጠላትንት
የተፈረጀ ነው። ከእኛነገር ጋር በምናጠፋው ጥፋት ልክ ድህነትን ማለያ አድርገን ኖርን። ድህነታችን በ ኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን በ አስተሳሰብ ልክነታችንም ያልተመጣጠነ እድገት ላይ ነን። ይህ መቼም አሊ አይባልም።
ጀርመኖች ህሊናችሁ ምንድን ነው ተብለው ቢጠዬቁ ቋንቋችን ነው
የሚሉት። የሃይማኖት አባታችን የሚሏቸው ሉተር ታላቁን ገደል የሚያጎናጽፏቸው የቋንቋችን ጥበብ አሳደገ ብለው
ነው ጀርመኖች።
እኔ በግሌም ብትውሰዱኝ የቅኔውን ሉዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ታቦቴ ያደረኩት መሰረታዊ ጉዳዬ የእኛንነገር
አንጎል አድርጎ በመነሳቱ ነው። በዓለም የሊቅነቱ ባለቅኔነቱ የተገኘበት ሚስጢርም በአማርኛ ቋንቋ የፍልስፍናው ምጥቀቱ እና ጥልቀቱ ነው። ጠ/ሚር አብይ አህመድን
የህሊና ቁንጮ ያደረጋቸው የአማርኛ ጥበብ የቋንቋ አጠቃቀማቸው ልቅና ምጡቁነት ነው።
የቃላቱ ውበት ከድምጽቸው የቃና ምት ጋር የማዋደድ ጥበባቸው
መሪነታቸውን አጎልብቶታል። አፋፍቶታል፤ አበልጽጎታል፤ መንፈስን ገንብቶበታል። ቋንቋ በራሱ የሙዚቃ ቅላፄ አለው። አሁን እኔ የሳቸውን ንግግር በምልሰት ሳላዳምጥ የቀረሁበትን
ቀን አላስታውስም። የመንፈስ ቴራፒ ነው ልክ እንደ ሜዲቴሽን።
በንግግር ጥበብ ልቅና አሁን ባለው ሁኔታ የሚደርስባቸው የለም። መሪ ደግሞ የወጣለት ዓራት
ዓይናማ ተናጋሪ ሲሆን ልብ ይሸለማል። ፖለቲካ ንግግር ነው። „ቃል“ ምንድነው የሚሉት "ቃል" ማለት ህሊናን በፍቅር የሚናዳ፤ የሚያስተዳደር
የመንፈስ ሃብት ነው።
ብላቴው ቋንቋውን በብልጽጋና አሳድጎታል ብዬ ነው
እኔ እማስበው። እሱንም የፈጠረው ያጨገዬው አማርኛ ቋንቋ ባላፊደል የመሆኑ ብልሃት ነው። ቋንቋውን በብልጽግና በማሰዳጉም ከእንግሊዞች
ሶኔት ከጃፓኖች ሃይኩ ጋር ዓለም አቀፍ ዕውቅና 8ዮሽ ከፍ ያለ ድርሻ እንዲኖረው አድርጓል። ስለሆነም ነው ታላላቅ የአገር መሪዎች
ሳይቀር ስለ እሱ የፊደል ውበት ምስባኩን በቅኔ የሚዘርፉት ።
ዛሬ በዓለም ደረጃ የትርጉም አገልግሎት ጉግል ከሚሰጥባቸው
አንዱ የአማርኛ ቋንቋ ነው። እዚህ ደረጃ ያደረሰው የጋሼ ጸጋዬ መንፈስ የሄደበት ለራስነገር የሰጠው የዕውቅና እና ሁነኛ አክብሮት ጉዳይ
ነው።
ስለምን? ጋሼ ጸጋዬ የራስነገር ላይ የፈጸማቸው ተግባራት አገር እንድንለው በሚያስችል ደረጃ የታነፀ ስለሆነ ነው። ሎሬት
ረቂቅ ሚስጢርነቱ የሚቀዳውም ከዚህ የብህልህነቱ ብትህና ሰቅ ነው። የብላቴው የማስተዋል አንጓ የራስነገር ነው። ብላቴው አገርን
ሲተረጉም ሁሉም የእኔ የእኛ የሁላችን የወላችን ብሎ ለራስነገርን ሙሉ ዕውቅና ልዕልና ሰጥቶ ነውና።
እኔም ሥርጉተ ሥላሴ ከ20 ዓመት በላይ የመጻፍ ተግባሬ
ሙሽራ ቃሎችን ፈልጎ ርዕስ በማድረግ በመጸሐፍ ለህትምት በማብቃት፤ አደባባይ ዓይን አፋር ቃላቶችን በማውጣት በድህረ ገፆች በምጽፋቸው ጹሑፎቼ ላይ በመጠቀም
አባቴን - ጌታዬን - ሉዑሌን ታቦቴን ብላቴ ሎሬት ጸጋዬን የተከተለውን መንገድ ለመከተል ብርቱ ጥረት አድርጌያለሁኝ ። እርግጥ ነው በተባባረ በደቦ ሴራ ለህዝብ ያልደረሱ የመንፈስ ሃብቶቼ መጋዘን ቢያሞቁም ግን በዚህች ባለቸው መድረክ የሚቻለውን ለማድረግ ተፋልሚያለሁኝ።
ቃ የሚል
ዕርስ በግጥም መጸሐፌም ላይ በጹሁፌ ላይ ተጠቀሜያለሁኝ። ቃ እና ዳ ብዬ አንድ ጹሑፍ ጽፌያለሁኝ። ቃ ማለት ክው ባለ ጠራራ ጸሀይ ወይንም በተንገበገበ
እሳት የደረቀ ማለት አይደለም። በዝግታ በለሆሳሳ በልስላሳ ሙቀት ራሱን እያዝነና ውበቱን እንደጠበቀ በተፈጥሮው ውስጥ የደረቀ እንደማለት ነው። ዳ ማለት ደግሞ ከመዘግዬት ያነሰ ማለት ነው።
ስለምን?
እንዲዚህ አይነት ቃሎችን እምጠቀመው የራስነገርን የወሰድኩት ከዛ አፍሪካዊ ኢትዮጵያዊ ሉላዊ ድንቅ ፍጡር ከቅኔው ሉዑል ከብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን የመንፈስ ምህንድስናውን ተከታይ በመሆኔ ነው። አጥናዋለሁኝ እሱን። በፊደሎቹ ልክ የ እሱ ተዘርዝሮ የማያልቅ ሚስጢር አለና።
ብላቴው በሁለመናው ከራሱ ነው የሚነሳው። ብላቴ ሎሬት
ጸጋዬ ገ/መድህን ለራሱ ምህረት ያደረገ በዛ ምህረት ውስጥ ምህረት ሆኖ የኖረ ስለሆነ የበታችነት ትውር ሳይልበት በወስጡ ድምቀት
ደምቆ ለዓለምም ተርፏል። የብላቴው የህይወት ዶክተሬኑ ምን ይባላል ቢባል የራስነገር ነው። የራስነገር ብቻ አይደለም
የራስነገር አዎንታዊ ዕውቅና በመስጠት ፈርጥ ነው።
ለዚህም ነው ማስተዋሉ ዝልቅ፤ ብልህነቱ ልሁቅ የሆነው።
ማስተዋሉ ዝልቅ ሲሆን ፍትህኛ መሆን ይቻላል። ፍትህኛ መሆን ሲቻል ደግሞ ዕውነትን መድፈር ይቻላል። ብላቴው ቀድሞ ነው "ፍቅርን
ፈራነው" ያለን። ፍቅርን ፈርተን እምንደፈርስበት መዳረሻችን ታይቶት። ጉዟችን ምን ሊሆን
እንደሚችል ተንብዮልኛል። ድፍርሶች ነን።
መቼም ማንኛችንም አንስተውም ዛሬ ሰውኛ ጉዳያችን ላይ እንዳልሆን። ሰው
ጠላን። እንግዳ አይምጣብኝ ከማለት ውጪ ሌላ ምን ይምጣ? አሳደን አስረን የማንችለውን በክለን መገደል ነው። ይህ ሰውኛ መቼም አያሰኝም። ሰው የሚጠፋበት
መርዝም በመንግሥት ደረጃ ሁነኛ ጉዳይ እንደሆነ እያዳመጥ ነው። ለነገሩ ሰውን ለማጥፋት መርዙን የፈበረኩት እራሳቸውም ሰውኛ ናቸው
ለማለት አያስደፍርም። ዓለም መጀመሪያ ይህን ድርጅት ለመዘጋት ይድፈረው። ስለሌ ነገር ከመታገል በፊት። መርዙ የሚደርቀው ከሥሩ ማምረቻው ፋፍሪካው ሲዘጋ ብቻ በመሆኑ። የሰው ልጅ እንደ ተባይ በማዳህኒት እንዲጠፋ የተፈላሰፈው ህሊናም ርጉም ይሁን። አሜን በሉ!
· ባለቅኔ ጠ/ሚር።
ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ከመሄዴ በፊት ኢትዮጵያ እኛ
ባለንበት ትውልድ ጥበብን አፍቅሮ የተነሳ መሪ ቢኖራት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ናቸው።
ኢትዮጵያ - ሚኒስትሩ በንባብ ለሕይወት ላይ / Ethiopian Minister about Reading and Life
የሚገረመው ድንቅ ነገር ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ
ገ/መድህን መንፈሳቸው ነው። በዬሄዱበት የእሱን ፎቶ ይዘው ነው የሚሄዱት። አሁንም ተስፋ አደርጋለሁኝ ጠ/ሚር ቢሮ የአባቴ ምስል
እንደሚኖር። የራስነገር መርኃችን ከሆነ መሰለሚያ ታቦታችን የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን እጬጌነት መሆን ይኖርበታል ባይ ነኝ።
እኔም አሳሬ የበዛው እሱን ተከታይ በመሆኔ ነው። ኢትዮጵያዊነት ለሚንዘፈዝፋቸው ከንቱዎች ግን እኔን ማሳደድ የተገባ ነበር። ታርጋው ነው ኢትዮጵያዊነት "ውስጡ ለቄስ" እንዲሉ … የኩሸት አገራዊነትነቱ።
ኢትዮጵያ ሚስጢርም ረቂቅም ናት ሲባል ለጨዋታ ሟሟያ
አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የምርምር ማዕከል የለውም እንጂ ቢኖረው ቀለሙምም ብራናውም አይበቃውም። ፕሪፌሰር አባስ /ካናዳ የሚኖሩ
የኦሮሞ ሊሂቅ ናቸው እና ፕ/ ህዝቃኤል ጋቢሳ OMN ሲሳለቁበት በራሳቸው ላይ መሰላቅ ስለመሆኑ ያ ገናናው የሙያ ፕሬፌሰርነታቸው
አልተረጎመላቸዋል።።።
እንዲያውም እንደ ሥርጉተ ሥላሴ መንፈስ ለኢትዮጵያ ካልዐይ ሳይሆን ቀዳማይ ተግባሯ ሊሆን የሚገባው ልትካስም ሲለሚገባት የኢትዮጵያዊነት የምርምር ማዕክል በመክፈት ይሆናል። ምንድነው
ኢትዮጵያዊነት መንፈሱ? ኢትዮጵያዊነት ከምን ንጥረ ነገር ተቀመመ? ኢትዮጵያዊነት ዜግነት ብቻ አይደለም ለእኔ። ኢትዮጵያዊነት
ፍለስፍናም ነው። የኢትዮጵያ ሊሂቃን ሲወድቁ ነው ጸረ አማራ አቋም አራማጆች የሆኑት። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት ከዚህም ስለሚቀዳ።
መቼም የፊደል ገበታ አልቦሽ ኢትዮጵያዊነት አይታሰብም። ዕውቀት አልባ አገር አይገነባም እና።
ይህን ብጡሊት ተዋናይ እና የፊልም ዳሪክተር
ወ/ሮ መቅደስ ጸጋዬ ሰርጓን ምክንያት በማድረግ ጀመራዋለች። ይህን ቅዱስ መንፈስ ወደ አንድ ተቋሚዊ ሁነት መለወጥ ነው። ለነገሩ
ትንቢተኛ ናት። ትንቢቷም ደርሷል። የእሷን የሙሽርነት ግርማና ሞገስ ሂደት እና የጠ/ሚር ሚር አብይ አህመድ የቤተ መንግሥት ርክክብ
የቀዳማዊት እምቤት ሁኔታ ጋር ሳስተያዬው የመቅዲ ህልም ዕውንነት አመሳጥሮልኛል። መቅዲ መከካለኛውን ዘመን እሰከ 21ኛው ክፈለዘመን
አዋዳ ነው ያዘወደችው።
ልክ ጠ/ሚር አብይ አህመድ የጥቅምቱ ወታደራዊ የኩዴታ
ግርግር ለማብረድ የደጎችን አጤ ፋሲልን፤ እቴጌ ጣይቱን፤ አጤ እያሱን በመከተል የሴራውን ባላባት ራስ ተሰማ ናደውን ውርሰ ሸር በብልህነት በጥበብ እንደ
ተቀኙት ማለት ነው። ይህ ዘመን ተነባቢ ነው፤ ዘመኑ ራሱ መጸሐፍ ነው። የራስነገር የከበረበት፤ የቆመሰበት፤ የጸደዬበት ወቅት ላይ ነን።
ቀደም ባለው ጊዜ በተማላ ነበር የራስነገር ሲባክን
ሲብከነከን የነበረው። ዛሬ ሙሴ አለው። ተመስገን።
"አታምልኳቸው ሰው ናቸው" ብለውናል በቅኔ ሊቀ ሊቃውንቱ ሻ/ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በቪዥን ኢትዮጵያ ጉባኤ ላይ። ስለምክራቸው ምስጋና አቅርቤ ዘርዘር ያለውን በምምጣበት መለክ
እመለስበታለሁኝ።
የሆነ ሆኖ ጸጋ የመንፈስ ቅዱስ ከሆነ ግን ታቦትም ያስቀርጻል። እኔ እኮ ጎንደርን ለለማ የዴሞክራሲ ተቋም ታቦት
አስቀርጹለት እያልኩ ነው ቤተሰቦቼን እምጎሰጉሰው። ለዚህ ደግሞ ጎንደር ልባም ነው፤ ወልቃይት ጠገዴ ሊቦ ከምክም ጉርጎራ ደንቢያ ጋይንት ሰማዳ እስቴ አፈርውሃናት
ጃናሞራ በያዳ አዲመረመጽ ማይጸመሪ አዳርቃይ የቀረጸውን ታቦት ልክ ያውቀዋል። ለመንገዶች፤ ለበሮች፤ ለድልድዮች ሥም - ሲያወጣ መጸሐፍ ሲደርስ
የኖረ ብልህ ህዝብ ነውና።
ታውቃላችሁ የንግሥት ማክዳ እና የንጉሥ ዳዊት ፓስተኛ
ለነበረ ሰው አንድ መንደር በሱ ወደ ሊቦ አካባቢ አለ። ሚስጢር ይቀዳል ከዛ ሠፈር እንደማለት። ህወሃቶች በጥርሳቸው የያዙት ያነን
ህዝብ በዚህ ምክንያት ነው። ስለዚህ ሚስጢራችን በራስነገር ውስጥ ለማመሳጠር እንደ አያት ቅድመያቶችን ባይሆንም እንጥፍጣፊ አይጠፋም
ና ስለ ዶር ለማ መገርሳ ፍልስፍና አንድ ይባል እንላለን አዘውትረን እኔ እና ውቢቷ ሸባላ ብዕሬ።
· ገና እና እኛ።
ገና የሚለው ጠብቆ ነው የሚነበበው። ወደ ተነሳሁበት ምልሰት ሳደርግ ሰኞ ልደት ነው የጌታችን
እና የመዳህኒታችን የእዬሱስ ክርስቶስ። የገና ባዕል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት ባህላዊ፤ ትውፊታዊ፤ ትሩፋታዊ፤ ታሪካዊ፤ ወጋዊ
ነው። የእኔ ስለሆነ ሳይሆን በተፈጥሮው እንደዛ ስለሆነ ነው። ሃይማኖታዊ ባዕላት ትውፊታዊ ባህላዊ ነገሮችን ይከተላሉ።
የጌታችን የመዳህኒታችን የእዬሱስ ክርስቶስ ትነሳኤ
ሆሆ ምሻምሾ እና ሆ! ስለ አዳምን ይይዛል፤ ጥምቀት ሎሚ ውርዋሮን ያካታል ያው የፍቅር ግኝት የቤተሰብ ምስረታን ከፍ ሲል ትውልድን
ያካታል፤ ሐምሌ አቦ አነባበሮ አለበት። ቅዱስ ዮሖንስ አድዮን አክብሮ አበባ ቆሎ ሙጌራው ኑጉ ቡሄ በሉን ያውድዳል። ፍልሰቲት አድርሽኝን ያቀስሳል፤
መስቀል ሆያ ሆዬን፤ ጅራፍ ማጮኽን ርሚጦውን፤ ምርቃትን ያስቃኛል። ገና የገናን ጨዋታን ይዞ ያስደምማል። የገና ጨዋታ የደስታ የብሥራት የፍቅር የአብሮነት
የመቻቻል የሰላም የእርቅ የምህረት ዓዋጅ ነጋሪ ነው። እንቁር እና የገና በትር ይህን የነፍስ ነገር ይዞ ይመጣል። ግን እኛ በራስነገር
ውስጥ ነን ወይ ስንል አይደለነም ነው።
ሶሻሊዝም የሚባል ነቀርሳ ሁሉንም ነገር ድራሹን ነው
ያጠፋው። እርግጥ ነው አምጪዎቼ ጀርመኖች ተላቀዋል፤ ራሺያኖቹ እና ቻይናዎችም ረግጠው ላላፏቸው ነገሮች ተጸጽተው ምልሰት እያደረጉ
ነው። አብሶ ዘመነ ህውሃት የሁሉመናችን መደረመሻ የጥቁር ቃናት አንቀፃት የተደነገገበት ነው። ለክስመት ምክንያታዊ የሆነ ድርጅት ነው።
በይፋ እና በአደባባይ ነው ኢትዮጵያዊነትን በፅኑ አግናባት ያነጸውን፤ ያቋመውን
ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንዳይነሳ አድርገን አጥፍተናዋል ብለው አቦይ ስብሃት እንደ መልካም ነገር ነው ያወጁት። አማራ
የተጠመደበትም መሰረታዊ አንጎል ጉዳይ ይኸው ነው። አማራ ጠል ሂደቶች ሁሉ መነሻቸውም መድረሻቸውም ይኸው ነው ጸረ ኢትዮጵያዊነት።
ይህ ማለት ትውፊቱ፤ ትሩፋቱ የእኛነገር ሁሉ አክሰመነዋል
ነው - ለዛውም ተፈቅዶለት። የገና ጨዋታ ዛሬ አውሮፓ ላይ ልክ እንደ መረብ፤ ባስኬት ኳስ ጨዋታ የሚወዳደሩበት፤ ዋንጫ የሚወስዱበት፤
የሚሸለሙበት፤ ዕውቅና የሚያገኙበት፤ የሚሰለጥኑበት ታዋቂ ሆነው የሚዲያ ዜና ባላባት የሚሆኑበት ነው። ሙያም ነው።
በሃይማኖት ሽፋን አገራችን ሲመኟት፤ ሲሰልሏት የኖሩት አገሮች ሁሉ የመንፈስ ሃብቶቻችን እስኪበቃቸው ጭነዋል። እኛ በፈጠረነው ውስጥ የራስነገር እኛው ስሌለንበት ሌሎች አጎልመሰው - አሳድገው -አብልጸገው - አበረታትው - አሰልጥነው፤ አዘምነው የራሳቸው አድረገው በስፖርት ኢንደስትሪ
ከፍ ብለውበታል። ትወልዱንም አንጸውበታል።
ፈረስ ግልቢያ፤ ተኩሶ አለመሳት /ኢላማ/ ለናሙና መውሰድ እንችላለን። ፈረስ ግልቢያ
ባህላዊ እስፖርት ነው ነገር ግን ከዛው ከገበሬው መንደር አለውጣም። ስለምን? ሰለየእኛነገር ያለን ግንዛቤ በዬለም ስላለ ስርዙ ስለሆነ፤ የእኛንነገር አክብረን ስለማንነሳ እንጂ የገና ጨዋታ፤ ዒላማ ተኩስ እና ፈረስ ግልቢያ
በዓለም አቅፍ ደረጃ ብንወዳደር እንደ ሩጫው ሁሉ ተወዳዳሪ ሊያደርገን የሚችል አንቱ የሆነ የስፖርት ዓይነት ነበር።
· ነገሩ ከተነሳ ዘንዳ …
አሁን ተመስገን የሚያሰኘው የራስነገር ፍጹም የሆነ
አክብሮት ያለው የአዎንታዊነት አብነት ሙሴ ኢትዮጵያ አግኝታለች። የህውሃት እና የኦነግ ጋብቻም ይኽ መሰረታዊ ጉዳይ ስለበጠበጣቸው
ነው።
ዶር ብርሃነ መሰቅል የሚባሉ ሙሁር „የኦነግ ወራሽ አብይ ነው“ ሲሉ አንድ ቃለ ምልልስ ሰሞኑን ሰጥተዋል። ራስን ማዋደድ
አመል ስለሆነ። በሳቸው አገላለጽ ኦነግ እዬመራችሁ ነው። ሎቱ ስብሃት! በህልማችንም አይምጣብን።
አንዲት ነገር ተዚህ ላይ ራስን ማዋደድ አመል የሚሆነው
የዶር ብርሃነ መስቀል ብቻ ችግር አይደለም የሁላችንም ነው። እኔ ያን ቃለ ምልልስ ስሰማ ህሊናዬ ከሁለት ነው የተተረተረው። „ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ“ ሆኖ እሳቸው የኦነግ መንፈስ አራማጅነታቸውን እናውቃለን፤ ጹሑፋቸውን
ስለምንከታተል፤ ቃለ ምልልሳቸውን ስለምንከታተል።
ለኦነግ የራስነገር ጠላቱ ነው። ስለምን? በራስነገር ውስጥ ኢትዮጵያ ከእነ ሙሉ
ክብር እና ሞገሷ ስላለች። ይህ ህውሃቶችንም ኦነጋውያንም ያርዳቸዋል። ኦነጋውያን እና ህውሃታውያን ፉክክራች ከኢትዮጵያዊነት ጋር
ነው። ኢትዮጵያዊነት ተደቁሶ እንዲቀር ነው ህልማቸው። ህልማቸው ግን ወንዝ አሻጋሪ አይደለም። ከስሞ ከስሎ በኖ ተኖ ነው የሚቀረው። ስለምን?
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ስለሆነ።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ የኦነግ ወራሽ ስለመሆናቸው
እና ስላልመሆናቸው መለያው ኢትዮጵያዊነት
ብቻ ነው። ኢትዮጵያዊ ሆኖ ኦነጋውያዊነት ስለሌለ። ኦነጋውያን
ሆኖ ኢትዮጵያዊነትም ስለሌ። በኦነጋውያውን ውስጥ ለጊዜ መግደያ ካለሆነ በስተቀር ብናኝ ኢትዮጵያዊነት የለም። ይህን በኦነጋውያን ብቻ ሳይሆን በህውሃታውያኑም እንዲሁ
ነው። ስለዚህ የጠ/ሚር አብይ አህመድ የኦነግ
ወራሽነት ኢትዮጵያም አያድርግባት እኛም አያድርግብን። ምን ሰርተነው ፈጣሪ።
አንዲት እንጥፍጣፊ ኦነጋዊነትን መንፈስ ቢኖራቸው
እኔ ከ2016 ጀምሮ ስለሆነ እመከታተላቸው አንድ ቦታ ላይ ሲያድጣቸው አይ ነበር። ነገር ግን በዛ ውስጥ አለመኖራቸውን አሳምሬ
አውቃለሁኝ።
ስለሆነም ነው የህሊናዬ ልዩ ቀለበት ያደረግኳቸው - ፈቅጄ እና ወድጄ። የኢትዮጵያ ህዝብም ሙሉ ፍቅሩን አክብሮቱን ሳይሰስት በገፍ ከሊቅ እሰከ ደቂቅ የሰጠው የኦነግን ዶክተሪን አስፈጻሚ አለመሆናቸውን ስላረጋገጠ እንጂ እንዲህ የሚቀለድበት ህዝብ አይደለም የኢትዮጵያ ህዝብ። የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ እኛም እንደ ዜጋ የሰጠነው
ሙሉ ፍቅር አክብሮት የደከምነለት መንፈስ ለኢትዮጵያዊነት እንጅ ለኦነጋዊነት ፈጽሞ አይደለም። ጨርቃችን ጥላን አላበደንም ህሊናችንም አልሳትነም!
Anteneh Part 1
Anteneh Part 2
Ethiopia - Dr Abiy Ahimed ትፈርሳለህ እንጂ ኢትዮጵያ አትፈርስም HASAB MEDA
Ethiopia - ….ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች! ትለወጣለች!
· ስለውድቀት ማህበርተኞች።
ድንቁ ነገር በኢትዮጵያዊነት የሸፈተ ሁሉ መጨረሻው
ውድቀት ነው የሚጠብቀው። እዬወደቀ መሆኑን የሚያውቀው ግን ከወደቀ በኋዋላ ነው። ማንም ኃይል፤ ምንም ኃይል በኢትዮጵያዊነት ላይ
ሸፍቶ ራሱን ሆኖ የዘለቀ የለም። ወደፊትም አይኖርም። እዬተሸማቀቀ እጁን ወደ ሆላ ጠፍሮ እዬተንዘፈዘፈ ነው ወደ እውነቱ የሚመጣው።
ኢትዮጵያዊነት በመሆን ውስጥ ነው። ኢትዮጵያዊነት በመሆን ወስጥ ሲኮን ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ድንበር ክትር ሳይሰሩ
በውስጡ ለመድመቅ ሲፈቀድ ብቻ ነው። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ይህን ገናና ጸጋ ያጎናጸፋቸው ምንም ታምር ሠርተው አይደለም።
በውስጣቸው
ያላቸውን የተቃኙላትን ኢትዮጵያን በመሆን ውስጥ ፈቅደው ስላሳዩን ነው።
ለሳቸው ለባለቅኔው ጠ/ሚር ሁላችንም እኩል ነን። ተማርን አልተማርን፤ ሃብታም ሆን ዲታ ሆን፤
አማኝ ሆን ኢ- ማኝ ሆን፤ ሴት ሆን ወንድ፤ ስደተኛ ሆን አልሆን፤ የማንፌሰቶ አባል ሆን አልሆን፤ ጤና ያለን ሆን አልሆን፤ ገበሬ
ሆን ሰራተኛ፤ አካል ኖረን አልኖረን ብቻ ለሳቸው ሰው መሆናች ይበቃቸዋል።
Ethiopia - Dr Abiy እንዴት ሰዉ በ1% ልዩነት ይሰቃያል?!
ለሳቸው የራስነገርም ውስጣቸው ምርጫቸውም ነው። ባለቤታቸው ደልዳላዋ
ቀዳማይ እመቤት „የኢትዮጰያ ልጆች እናት ነኝ“ ሲሉ አዳምጠናል። ማዳመጥ ብቻ ሳይሆን በ9 ወራቱ የቀዳማዊት እመቤት ተግባራቸውን
ለክተናል ትጋታቸውንም አይተናል። „የሚያድግ ጥጃ ከገመዱ“ እንዲሉ አለፍ ብለውም በአለምዓቀፍ መድረክ ሰሞኑን አንድ ዘመን ተሻጋሪ
ራዕያቸውን አብስረውናል። ይባረኩ!
ህልሜ „የተባረከ ትውልድ
ለተባረከች አገር“ ሲሉም ገልጠዋል። አለፍ ብለውም ማሰረጊያቸው „የተባረከ የዓለም ዜጋ ለመፍጠር
አብረን እንሥራም“ ብለዋል ጉባኤተኛውን። ይህ ማለት የራስነገር አካል ተ-አምሳል መሆኑን ያሳዬናል። የእኛነገር ሚስጢር
ከቤተ መንግሥት እዬተቀዳ እዬተንፎለፈለ ነው ዛሬ።
ቤተ መንግሥቱ በራስነገር ስለተመሰጠ በጥበብ ሰዎች፤
በሠራዊቱ አባላት፤ በታዳጊ ወጣቶች ጉብኝት አህዱ ተብሏል፤ የንጉሶች ንጉሥ የአጤ ሚኒሊክ ቤተመንግሥትም የዓለም ህዝብ ቤት እንዲሆንም
እዬተሠራበት ነው።
ስለሆነም የገና ጨዋታ፤ የዒላማ ተኩስ ውድድር፤ የፈረስ ግልቢያ ነገ የዓለም አቀፍ ውደድር ቤተኛ የማይሆኑበት
ሁኔታ የለም። ዘለግ ያለ ህልም ላለው የተቀደስ ሰብዕና ሁለመናው የራስነገር መርሁ ናፍቆቱ ስስቱ ነባቢቱ ነውና። ስለዚህም ጠ/ሚር አብይ አህመድን
ከመወደድ የዘለሉ ከፍ ያሉም የመንፈስ ጥበቃ ሁሉ አለበት። እንጸልይላቸዋልን በትጋት። ተመካክረንም የግል የፈቃድ ጸሎት እንደርግላቸዋለን።
አገሬ ስል እሳቸውን ነው እማስበው።
Ethiopia - Dr Abiy ፈረንጆቹን አሸማቆ መለሳቸዉ!!
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደረግ እነኝህ ባህላዊ የስፓርት
ዓይነቶች ገና፤ የአነጣጥሮ ኢላማ ተኩስ፤ የፈረስ ግልቢያ የእኛ ሲሆኑ ግን በቅይጥ ባህል አይደለም መከወን ያለባቸው። ማልያው
የውጭ ቅጂ፤ ጨዋታው የባህል አንዲህ በቅይጥ ዲቃላ ማንነት ሳይሆን ወጥ በሆነው ማንነታችን እንደ አባት እናት አደሩ አልባሳቱም
በእኛነገር አምሮ እና ሰምሮ መሆን ይኖርበታል።
አንዲት ነገር በቀጠፍን
ቁጥር ብዙ ነገር ነውና የሚናደው፤ አንዲት ቅንጣት ነገር ባከበር ቁጥር ደግሞ የራስነገርን እንዲያፈራ እንስመቻዋለን ማለት ነው።
ጀርመኖች በቋንቋቸው ላይ ያላቸው ቀናዒነትን መርህ መከተል እንደማለት፤ ንጉስ ዳዊትም „የቤትህ ቅናት በላኝ“ እንዳለውም።
· እርገት።
ውዶቼ የዛሬ የራስነገር በዚህ ይከወን ትንሽ ሙግት
ቢጤ ከትዝበት ጋር ደግሞ ቀጣዩ ጉዳዬ ይሆናል …. ትናንት ተወዳጁ የሃሳብ ቀኔ ስለነበር ለቀጣይ ቀናቶች የተላለፈ አጀንዳ አለኝ …. የወይንዬ
ጉዳይም እንዲሁ ጉዳዬ ነው በራስነገር ውስጥ መከተብ አለበት።
… ምን እንባባል? ወዶቼ ክብረቶቼ፤ ሃብቶቼ … ውስጦቼ ደህና ቆዩልኝ … ኑሩልኝ … አብቡልኝ … ለምልሙልኝ።
ቅኖቹ ሆይ! በራስነገር ሲኮን ሁሉ ይታዬናል። የራስነገር
ነገን ለመምራት ብቻ ሳይሆን ለማሸነፍ ሴላችን ነው። ዛሬ የአንዲት ሴል ምርመራ ሁሉን ትናገራለች እና። በራስነገር ውስጥ ማሸነፍ
እንጂ መሸነፍ ከቶም ዝር አይልም። ከራስነገር ወልፍት ስንል ግን የሽንፈት ማህበርተኞች እነሆናል።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ
የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
የእኛነገር አባወራው የአብይ ሌጋሲ ዓራት
ዓይናማው መንገዳችን ነው።
መሸቢያ ጊዜ!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ