ልጥፎች

ከኤፕሪል 6, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ሐዲዱን ያልሳተው የእነ ሺመልስ ባቡር. . .|| “ከጃል መሮ ይልቅ ሺመልስ ያስፈራኛል”

ምስል

ኢትዮጵያ ዜግነት የሌለባት አገር።

ምስል

ውሸትም ዘመን ሰጥቶት ጠቅላይ ሚኒስተር አገኜ።

ምስል

ዬዘመኑ ማገዶዎች።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።   ዕለተ ማክሰኞ ማዕዶተ ይግቡ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)   ማዕዶተ ይግቡ ባለቤት የሌላቸው ሰብዕናዎች፤ ተቋማት፤ ባህርያት፤ ትውፊትወትሩፋት፤ ተቋማት የሚቃኙበት ዕለት ነው። ባለቤት የሌላቸው ቁምነገሮች አሉ። ሲፈጠሩ ሰብዕናቸው ለቁምነገር የተፈጠሩም ግን ባለቤት የሌላቸው። ማገዶዎች። ትናንትም ዛሬም አቶ እስክንድር ነጋ ካቴና ላይ ነው። ትናንትም ዛሬም አቶ ስንታዬሁ ቸኮል ካቴና ላይ ነው። ትናንትም ዛሬም ወ/ሮ ቀለብ ስዩም ካቴና ላይ ናት። የሚገርመው ካሳዶጃቸው ጋር አብረው ነው የታሠሩት። የእስኬው ህሊና አንፖል ይመስላቸዋል። የሆነ ሆኖ እንዲህ እንሱ ይመጋዳሉ የሌሎች ሰብዕና ካቴና ያልነካቸው ሰብዕናዎች መወድስ ይሆናሉ።   በእነሱ አቅም መጤ ሰብዕናዎች ይከብሩበታል፤ ይነግሡበታል፤ ይጵጵሱበታል። ግፉን ማዬት እንዲህ ከውስጥ ይገባል። እልፍኝ ሰርትህ እልፍኝህ ሲዘረፍ። ለዛውም በስልት እና በጥበብ ሳታስጠጣ። ውስጥን ይከረክራል። ሌላውን ማታለል ይችል ይሆናል። እኔን ግን አይታሰብም። ሂደቶችን ሁሉ ከውስጤ ነው እምከታተላቸውና።     እነሱ ዘመናቸውን፤ ወጣትነታቸውን፤ ትዳር ጎጇቸውን ገብረው ዕድሜያቸው በካቴና እንዲህ ያርጋል። አሁን ደግሞ ወ/ት አስካለ ደምሌ ተጨምራለች። ውስጥን ይመረምራል። ስለሆነም ዛሬ የገጣሚ የባለቅኔ ክቡር ደበበ ሰይፉን ግጥም እነሱን ስለገለጠልኝ አቅርቤዋለሁኝ። በትክክል ይህ ቅኔ ይገልጸዋል። ደጉ እጬጌው ሂደት የሚገርሙ፤ እራስን የሚፈታትሽ ስርንቅ...