ብራቮ ፕሬዚዳንት ሩቶ በዓለም ቁልፍ የሰላም ጉባኤ በልቅና መመረጥ መታደል! ተስማምቶኛልም።
ብራቮ ፕሬዚዳንት ሩቶ በዓለም ቁልፍ የሰላም ጉባኤ በልቅና መመረጥ መታደል! ተስማምቶኛልም። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ዬአቤቾ ሃቅ እና ሳቅ ሚዲያ ሳዳምጥ "የኬንያን ውክልና በዓለም ሰላም ላይ አቅሎ አቅርቦታል። ደሬ ዜናውን እንደሠራውም አደመጥኩ። ደሬ ዜናውን ሲሰራው የኢትዮጵያ ደረጃ መወሰድ "የቤትህ ቅናት በላኝ" ብሎ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ። ኬንያም የእኛ ብትሆን ግን እንደ ፓን አፍሪካኒስት አንከር አገር ግን ኢትዮጵያ ደረጃዋን ማጣቷ የደሬን የዜናውን ትክክለኝነት ለእኔ ይገልፅልኛል። አቤቾ ሃቅና ሳቅ ለምን የጠሚር አብይ አህመድን ዜና አትዘግቡም ዓይነት ሃሳብ አቅርቧል። የመንግሥት ሚዲያ እነ ሉዓላዊ፤ እነ ሃቅ እና ሳቅ ወዘተ ምን ይሥሩ። ሌላ ሥራ ምን አላቸው? አሸበረቅን ነው። በሚቀጥለው ዓመት ተመንድገን የታንኪው ዘመን ይሆናል ነው። ያድርገው። የሆነ ሆኖ አይደለም የኢትዮጵያ ዜና ዘጋቢወች ዓለም አጀንዳቸው እኮ ኢትዮጵያ ነበረች። #በአወንታዊነት ። የፕሬዚዳንት ኦባማ ወደ ሥልጣን የመጡበትን ዘመን የሚመጥን ብቁ አትኩሮት ነበር። ለምን አሁን ለሚለው #ችግሩን ማጥናት #ለመፍትሄው #መቁረጥ ይገባል። በውነቱ የዓለም የአገር ውስጥ ተፈናቃይ ሻንፕዮን ለሆነች አገር፤ ሁለት ቤተ - መንግሥት ላላት አገር አዲስ እና ጎንደር ሌላ ቤተ - መንግሥት መሥራት ያስፈልጋታልን? #አሁን #ዛሬ ? የዓለም የሰላም ሎሬት ለዛውም አፍሪካ ላይ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ እያሉ #ሦስተኛው ዓለም ጦርነትን ያሰጋውን አርማጌዶን የራሽያ እና የዩክሬን፤ የኔቶ እና የራሺያ ጦርነትን ለመክላት በሚካሄደው ግሎባል ጉባኤ ለዛውም በቅድስት አገር ሲዊዘርላንድ #የኢትዮጵያ #አሻራ #ነጥፎ ተንኩሳን የማታውቀው የአክባሪያ...