#ፋኖ የአማራ ህዝብ የተፈጥሮ #የቀይ ደም #ሴሉ ነው።
ፋኖ ያበራል። ተሽሎክሉከን ሳይሆን ገጥ ለገጥ ወጥተን። ተጠማኝ ጥገኛ ሳንሆን እኔም ፋኖ ነኝ እንለዋለን። ውጠነዋል። ስንፈጠር ሳይሆን ስንጠነሰስ ከፋኖ መንፈስ ጋር ነው። መለያችን አርማችን ፋኖነት ነው።
እኔ እራሴን ችዬ ፋኖ ነኝ። አንገቴን አልደፋበትም። በብእሬ እሞግታለሁ። ብዕሬ ሃቅን ታበራለች። እኔ አቶ እከሌ ወይንም ወሮ/ እከሊት አይደለሁም። እኔነት በብድር አይሆንም።
እኔ እኔ ነኝ። እኔ እራሴም ፋኖ ነኝ። ብዕሬም የቀለም ባሩድ አላት። ይህን ለሁለም እጽፋለሁኝ። ፋኖነት የጊዜ ኩርፍርፍ አይደለም። የቤተሰብ ውርስ እንጂ። አወን እኔ ሥርጉተ ሥላሴ፤ ሰብለ ህይወት ፋኖ ነኝ። መሳሪዬ ሃሳቤ ነው። ድልድዬ ብዕርና ብራናዬ።
ፋኖ የፖለቲካ ድርጅት #መጂ አይመራውም። ሲፈጠር በባህሉ፤ በወግ በልማዱ በህግ አምላክን ጠጥቶ የተፈጠረ ነው። በተፈጥሮው ልክ የኖረ ለወደፊትም የሚኖር አልፋ - ኦሜጋ። የአማራ ህዝብ ቀይ የደም ሴል ፋኖነት።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
15/06/2023
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ