ኢትዮጵያን የማበጀት አቅም የነበራቸው የአገር ብራንድ ናቸው ያሳደጉኝ

 

የሲዊዝጀማሪ ጋዜጠኞች፤ ጀማሪ ፖለቲከኞች ይገርሙኝ ነበር። ሥነ ፁሁፍም፤ መምራትም፤ ሚዲያም፤ ፖለቲካም እዚህ ሀ ሁ ያልኩ ይመስላቸዋል። እንደ እኔ ዕድለኛ የለም። በሁሉም ኮርስ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የማበጀት አቅም የነበራቸው የአገር ብራንድ ናቸው ያሳደጉኝ። እናም ምን እንዳለኝ አውቃለሁ።
ምን እንደለለኝም። ምን እንደሚፈቀድልኝም፤ ምን እንደማይፈቀድልኝም የመብቴን ጣሪያ እና ግድግዳ አውቃለሁ። እኔ በእኔ ውስጥ መኖርከተሳነው፦ እኔ እኔን ማሰናበት አለበት። ይህ ደግሞ በሥርጉትሻ የማይታሰብ ነው። የእኔ የምለው ራዕይ፤ ፍልስፍና፤ ዓላማ አለኝ። ዛሬ ፖዘቲብ ኢነርጂ ስለሚባለው እኔ የተከበሩ የተመድን ዋና ፀሐፊ ደጉን አቶ ኪም፤ የአውሮፓ ህብረትን ፕሬዚዳንት የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ዓለም አስፈራችኝ ክፋነትን ሊቋቋም የሚችል ተቋም ይፈጠር። የፍቅር ተፈጥሮ፤ የህግ ተፈጥሮ ካሪክለም ተነድፎለት ሁሉም ይማረው ብዬ ሞግቻለሁ። መልስም ተልኮልኛል።
እና ሞገደኛውን ሥርጉትሻ ህሊና ላይ ቁብ ብሎ መሾፈር አይፈቀድም፤ አልተፈቀደምም ወደፊትም። በንፁህ ህሊና በነፃ ህዝቤን አገልግያለሁ። ወደፊትም። ላይ ላዮዋን ነው። ብዙ እጅግ የተከደኑ ዕንቁ ተግባራትን ለአገሬ ዕጣ ነፍሴን ፈጽሜላታለሁ። ቀረ ጎድሎባታል የምለው የለም።ፈጽሞ። ለዚህም ነው በቁጥብነት ገድሜ እምኖረው።
ሥርጉ// ሰብለ ሕይወት ውቦቼ እረገት ይሁን። ደህና ሁኑልኝ። አሜን።
"የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
(ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።