አክብሬ አመሰግናችኋለሁ
በዬሰከንዱ እናት አገሬ ከውስጤ ናት። ዛሬም ቢኖረኝ ባደርግላት አልጠግብም። ለሲዊዚሻ ውለታ ሳልከፍል በመቅረቴ ግን እጅግ አዝናለሁ። የሰው ልጅ ሲመረቅ ሲዊዝ ይመጣል። ቅዱስ በዓት። የሰላም አንባ። የህይወት መድህን። ጭምት ሥልጡን። ጨዋ ብቁ። ሰባዕዊ ባለማተብ ውድ ዕንቁ በዓት።
በህይወቴ የገጠመኝን የማይገኝ ዕድል ገፍቼ ነው የተገኜሁት። ግን ንጽህናን በይበቃኛል ቃሉ እንደ ቃሉ ገድሞ መኖር። የበሞቴ ልዕልቴ አንድ ጊዜ ፀሎት ያስፈልገኛል አልኳት። "ሱባኤ" ላለ አለችኝ። አወን የሙሉ ዕድሜ የቁጥብነት ህይወት በብዕር ጠብታ ፍቅር ተነድፎ። በታቦቴ በብላቴ ፀጋዬ ገብረ መድህን ፃዕዳ ሩቅ በጣም ርቅ መንፈስን ተጠግቶ። ደፋሮች ይገርሙኛል። መረገምም ይመስለኛል። ታቦቴን ሲዳፈሩት።
የሆነ ሆኖ ተመስገን ሲያንስ ነው። ከሰሞኑ በምለጥፋቸው ፎቶወች የተደመሙ ንፁኃን የሚልኩልኝ መልዕክት ፈውሶኛል። በውነቱ ጽናቱን አፍልቆታል። አክብሬ አመሰግናችኋለሁ ውዶቼ ክብረቶቼ። ቀሪው ጊዜ ታምቀው የተቀመጡ ልምዶቼ ምክሮቼ ፀጋወቼን ሁሉ አስረክባችኋለሁ።
ኑሩልኝ።
ሥርጉ14/06/024
ጥበብ ትጠራለች። ታከብርማለች። ታስከብርማለች። ውደዟት። አትግጿት። ምን አደረገች????
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ