በእኛነት ላይ ያለው ተፃራሪ መንፈስ ቀድሞ #የተረታ ነው።

 

በእኛነት ላይ ያለው ተፃራሪ መንፈስ ቀድሞ #የተረታ ነው።
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።"
 May be an image of textNo photo description available.May be an image of frisbee, button and textMay be an image of 1 person and smiling
አማርኛ ቋንቋን እና የአማራ ሥልጣኔ ኢትዮጵያን በማበጀት ረገድ ያለውን ሚና ለማደብዘዝ ብዙ ተለፍቷል። መንፈስ ቅዱስን የረታ ጥቁር መንፈስ ሆነ ጥቁር ቀን ግን የለም። የትም ቦታ፤ በማንኛውም ሁኔትታ ጠባቂ ሠራዊት አለው በቅንነት ለተከወነ ማናቸውም ጌጥማ፤ ፈርጣማ አሻራ።
ትናንት የመጡት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ የሺህ ዘመናትን ሥልጣኔ ደርምሼ እራሴን ቁብ አደርጋለሁ ብለው ቢታክቱም በአንድዬ ኃይል ቀድመው የተተገበሩ መሠረትም የያዙ መልካም ነገሮች አሉ። ሲዊዝ እጅግ ጭምት ገለልተኛ ቅድስት አገር ናት። በእሷ መሬት እንኳን ይህ ተሠርቷል በአንድ ክንድ።
የያዝኩት መፀሐፍ "ፊደል" የልጆች የሥነ ግጥም መጸሐፍ ነው። ልጆቻችን እኛ ባለፍነው ትርምስ ማለፍ ስሌለባቸው እንካ ሥላንትያን እና ፊደልን ከመፃፌ በፊት በሱባኤ ነው። ቅንጣት ክፋ ነገር ሙግት ፖለቲካ የለበትም። የዝናብ ውሃ ጠበል ነው አይደል እንደዛ። ፊደል ሽፋኑ የአማርኛ ቋንቋ አልፋቤት ነው። በእኔ ዕውቀት ልክ ያሉ ነገሮች አሉበት። ሁለቱም የልጆች መፃህፍት መፍቻ አላቸው። ከኦስትርያ የመጣች የጓደኞቼ ቤተሰብ የወለጋ ልጅ ናት ለእኛም ስለሚሆን ለልጆች ለምን አልሽው ብላ ሞግታኛለች። ቅኒት ናት። ባህላችን፤ ወጋችን፤ ልማዳችን ተቀመርበታል።
ብዙ የሲዊዝ የኢንተግሬሽን ቤተ መፃህፍቶች አማርኛ ቋንቋ ዲፓርትመንት አላቸው። ታግለናል አሳክተናልም። ለምን? አገራችን በክብሯ ልክ፤ በዊዝደሟ ልክ መቀጠል ስላለባት። ለዛውም ቸነፈሩን ተቋቁመን። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፍልስፍናው ክፋት ነው። ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚታመሱት ለክፋት አጤነት ነው። ግን ሲተኑ እንጂ ሲበቅሉ አላዬሁም። በአማራ ላይ ተመስጥሮ የተያዘው ስምምነትም በሰው ኃይል ሳይሆን በፈጣሪ አቅም ይመክናል።
ኃያሉ ኃይሉን እፍ ይልበታል።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች ይጥራሉ። ይተጋሉ። ግን አፍሰው በመልቀም። ለቅመው በማፍሰስ። ምን መደረግ አለበት? መከወኛዬን አቀርባለሁ። በቀጣይ።
ሥርጉ 14/06/024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።