ብራቮ ፕሬዚዳንት ሩቶ በዓለም ቁልፍ የሰላም ጉባኤ በልቅና መመረጥ መታደል! ተስማምቶኛልም።
ብራቮ ፕሬዚዳንት ሩቶ በዓለም ቁልፍ የሰላም ጉባኤ በልቅና መመረጥ መታደል! ተስማምቶኛልም።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ዬአቤቾ ሃቅ እና ሳቅ ሚዲያ ሳዳምጥ "የኬንያን ውክልና በዓለም ሰላም ላይ አቅሎ አቅርቦታል። ደሬ ዜናውን እንደሠራውም አደመጥኩ። ደሬ ዜናውን ሲሰራው የኢትዮጵያ ደረጃ መወሰድ "የቤትህ ቅናት በላኝ" ብሎ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ። ኬንያም የእኛ ብትሆን ግን እንደ ፓን አፍሪካኒስት አንከር አገር ግን ኢትዮጵያ ደረጃዋን ማጣቷ የደሬን የዜናውን ትክክለኝነት ለእኔ ይገልፅልኛል።
አቤቾ ሃቅና ሳቅ ለምን የጠሚር አብይ አህመድን ዜና አትዘግቡም ዓይነት ሃሳብ አቅርቧል። የመንግሥት ሚዲያ እነ ሉዓላዊ፤ እነ ሃቅ እና ሳቅ ወዘተ ምን ይሥሩ። ሌላ ሥራ ምን አላቸው? አሸበረቅን ነው። በሚቀጥለው ዓመት ተመንድገን የታንኪው ዘመን ይሆናል ነው። ያድርገው።
የሆነ ሆኖ አይደለም የኢትዮጵያ ዜና ዘጋቢወች ዓለም አጀንዳቸው እኮ ኢትዮጵያ ነበረች። #በአወንታዊነት። የፕሬዚዳንት ኦባማ ወደ ሥልጣን የመጡበትን ዘመን የሚመጥን ብቁ አትኩሮት ነበር።
የዓለም የሰላም ሎሬት ለዛውም አፍሪካ ላይ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ እያሉ #ሦስተኛው ዓለም ጦርነትን ያሰጋውን አርማጌዶን የራሽያ እና የዩክሬን፤ የኔቶ እና የራሺያ ጦርነትን ለመክላት በሚካሄደው ግሎባል ጉባኤ ለዛውም በቅድስት አገር ሲዊዘርላንድ #የኢትዮጵያ #አሻራ #ነጥፎ ተንኩሳን የማታውቀው የአክባሪያችን #የእህት #አገር #ኬኒያ አሻራ ሲተከል እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሊሰማ ይገባል። ደሬም መሥራቱ ዜናውን ትክክል ነው። አቀራረቡን አላዳመጥኩትም። ግን #ደወሉ ትክክል ነው። አቤቾ አቃሎ ማቅረቡ ግን ገርሞኛል።
የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት በዬቤታችን ገብቷል። ስጋቱም ድቀቱም። አዲሱ የአውሮፓ ትውልድም ክልል እዬተበጀለት ነው። ሩሲያ በኢሮ - ቪዥን - ሶንግ - ኮንቴስት፤ በእግር ኳስ፤ በዓለም የኢኮኖሚ ትስስር ስትገለል። የትውልድ የመኖር ዕድልስ የሚል ግሎባል ጥያቄ ሊነሳ ይገባል። ሁለት ተፎካካሪወች ቢታረቁ ቢቀራረቡ ያተርፋሉ። ትውልዱም ሰላም ያገኛል።
ሌላው ደግሞ ዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪወችን ወደ #መሪነት ስታመጣ ልታስብበት ይገባል። መሪነት ተፅዕኖ ፈጣሪነት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በሆነ ክስተት ተጽዕኖ ፈጣሪነት የመሪነትን #ሁልአቀፍ #ብቃትን ሊያጎናጽፍ ፈፅሞ አይችልም። በፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ዘመን ዓለማችን ብዙ ልትማርበት የሚገባ ጉዳይም አለ። የኔቶን ፍላጎት መምራት ማለትስ ምን ማለት ይሆን ዓለማችን በአንድ ኮመዲያን ተጽዕኖ ፈጣሪ ይሁንታ ስትሰጥ? የሁለቱ አገር ህዝቦች እንግልትም ሆነ ሐሤትስ በምን ሊታይ ይገባል በግሎባላይዜሽን ዕድል አፈፃፀም።
በ2023 ነጥቡን አንስቼ በግንቦት መባቻ ላይ ሞግቻቸዋለሁኝ። የሆነ ሆኖ ዓለማችን በዕውነተኛ ሰላም ዙሪያ ልትሠራ ይገባታል። ካለዚያ የቻሪቲ ተቋሞቿ ያቋቋመችበት ንፁህ ዓላማ ፈተና ይበዛበታል። እኔ እግዚአብሄር እንዲያሳካው ምኞቴ ነው። አሜሪካ እና ራሽያም ውጥረቱን እንዲያረግቡትም እሻለሁኝ። የዓለም ሰላም መታወክ ለትውልዱ ብቻ ሳይሆን ለፍጥረታት ሁሉ ሳንክ ስለሆነ። ለእንሰሳት፦ ለምድሪቱም። ምድሪቱ ነደደች። ያ ኬሚካል ለቀጣዩ ትውልድስ???
የሳቸው ኃላፊነትን ትተው ትጋታቸው ኢትዮጵያ እና ትናንት የተመሠረቱ የአረብ አገሮች ኮንስትራክሽን ኮርስፖንዳንስ ሠራተኛ ሆነዋል እኮ። ዝም እምለው ስለማይሰሙን ነው ዶር አብይ ከሥልጣናቸው በፊት ማንም ባላሰባቸው ጊዜ በጣም ብዙ ወሳኝ ሃሳቦችን አንስቼ ጽፌያለሁ። ሥልጣን ሲይዙም እኔም ዜጋ ከሆንኩማ ብዬ ዘለግ ያለ ዕይታዬን አጋርቻለሁ። ጥበብ ላም እረኛ ምን አለ ማዳምጥ ነበር። ምስክርነታችን ሁሉ አፈር ድሜ አስግጠው አንገታችን አስደፋን በኦነግ ፖለቲካ ተነክረው።
#ልከውነው። ግን ዘለግ ይላል።
ይህ ዕንቁ ዕድል ልዩ አትኩሮት ልዩ ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል። ይህ ከተለመደው የመሪወች ጉባኤ ጋር በአቻነት ሊቀርብ ፈፅሞ አይችልም። #ልዩ #ተልዕኮ #የላቀ ግብ ያለው፤ #መመረጥን መሰጠትንም ይጠይቃል። ብቃት እና ክህሎትን ፍፁም ያፈራ ታማኝነ
ያገናዘበ ምነው። ስለቀረብን ባናኮርፍም ልናስብበት ግን ይገባል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አሜሪካ በኬኒያ ላይ ልታመጣ ቀጣይ ተፅዕኖም ጫሪ ሃሳብ ተነስቷል። "ሲያጣ የጦመውን" ይላሉ ባለ ቅኔወች ጎንደሮች።
የዓለምን እግር ኳስ ሳሚት ላይ ጠቅላይ ሚር አብይ ከፕሬዚዳንት ጆባይደን እኩል ተቀምጠው አዩ ምን ያህል ፍንደቃ በፕሮ አብይዝም እንደነበር ታዛቢወች እኮ አይተናል። ምንም ማንም ቢሆን ከአሜሪካ ፍላጎት ውጪ መሆን የሚቻልበት አቅሙም ክህሎቱም ዘመኑም አይደለም። ዓለም ዓቀፍ ፖለቲካ የሚባል ፖርሽን እኮ አለ። የዘመናችን የፖለቲካ ባህሬ የሚል ዲፓርትመንትም አለው።
ኢትዮጵያ ባለመመረጧ ከሄሮ ወደ ዜሮ የገባው ተስፋችን ሁሉ አብረን ልናፍርበት የሚገባ ጉዳይ እንጂ የሚያስመካ ሆኖ ከተለመዱ ጉብኝቶች ጋር ተነፃፅሮ አልይህ ሊባል አይገባም። ብራቦ ፕሬዚዳንት ሩቶ እና ቲማቸው። ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ሚስጢሯን ያከበሩ ክቡር መሪ ስለሆኑ ጎዳናቸው የተቃና ሆኗል።
ውዶቼ ቅንጣቢ ጊዜ ስላለችኝ እስቲ ዜና እንኳን ብዬ ሳይ ወሳኝ ጉዳይ ገጠመኝ። በመንፈስ እኔም አለሁበት ሞግቻለሁም። ስለሚገለሉ አገሮች ትውልድ እና ስለግሎባላይዜሽን እርቀሰላም። ለዚህም ነው የፃፍኩበት።
እረገቱ ኢትዮጵያ አብዝታ ልትጠነቀቅበት የሚገባው መሪነት እና ተፅዕኖ ፈጣሪነት፤ መስዋዕትነት እና የአገር መሪነትን ብልህ ፖለቲከኛ ያስፈልገዋል ባይ ነኝ። ለቀጣይ የተስፋ ጎዳና። "ነጮቹ ነጮቹ" የሚል አዌርነስ እሰማለሁ። ምን እዬተዶለተ እንደሆን ባላውቅም።
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ውድድር ያልገቡበት መስክ የለም።
ከመቅድመ፤ ከመካከለኛው ዘመን፤ ከአሁነኛዋ የኢትዮጵያ ዘመን ጋር፤ በተለይ ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፤ ከዓድዋ ድል እና ከአጤ ሚኒሊክ ጋር፤ ከኢትዮጵያ ጦርነቶች እና ድሎች እና ከወቅቱ መሪወች ጋር፦ ከኢትዮጵያ ተፅዕኖ ፈጣሪወች ጋር፤ ከካቢኔ ሚኒስተሮቻቸው ጋር፤ ከኢትዮጵያ ባልሃብቶች ጋር፤ ከኢትዮጵያ ፀሐፍት ጋር፤ ከኢትዮጵያ አንጋፋ ጋዜጠኞች የኢቤንት መሪወች ጋር፤ ከዓለም ሎሬቶች ጋር ……… ከሻለቃ ኃይሌ ጋር፤ ጎርጎራ የቀደመ የመዝናኛ ማዕከል ነው አሻሽለዋለሁ ብሎ ሲነሳ ነጠቁት። ከዲሻታ ጊና ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት ጋር። ወደፊትም ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ከኖሩም ይቀጥላል። ከየዘመኑ የኢትዮጵያ መሪወች ጋር የሠርክ ተርቲማቸው ነው። አስራ ሦስተኛ ፕላኔት ቢባሉም፤ ኢትዮጵያ በሳቸው ሥምም ብትጠራ አትላስ ቢፍቃት ይሻሉ። ይህን አደብ ገዝቶ መመርመር ይገባል።
የኢትዮጵያ ቀደምትነት እዬተፈተነም ነው። ኢትዮጵያን ውስጣቸው ያደረጉ ኢትዮጵውያን አቅል ያላቸው ጥናት ምርምር ሊሠሩበት ይገባል በቅንነት። እኔ የአባይ ድልድይ ብቻ አይቻለሁ። የእናቶች ቀን ስለነበር። ሌላ ዜናውን እርዕስ ብቻ ነው እማዳምጠው። እማስተውለው። ፈልጌው አይደለም። ተስፋዬን ስላጣሁ የህሊናዬ ትዕዛዝ ነው። አይስበኝም። ቤተ መፃህፍት ላይ ምረቃ? ፋና ሲመረቅ አልነበሩም። ቀድመው ግን ሄደዋል። ስስታምነቱ የታሪክ ሽሚያው ልክም ደንበርም የለውም። እስቲ አሁን ፕሬዚዳንት ሩቶን ተወዳድረው ያሳዩን። አሸንፈውም።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
1/06/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ