የፀጋዬ ራዲዮ፤ የፀጋዬ ድህረ ገጽ ግብዣ።
የፀጋዬ ራዲዮ፤ የፀጋዬ ድህረ ገጽ ለሲዊዝ የጀርመንኛ ተናጋሪ ክፍላተ አገራት የልምድ ልውውጥ ግብዣ።
"አድርገኽልኛል እና አመሰገንኃለሁ።"
ስደተኛ ካንፕ ነበርኩ። ካንፔ ክላይነአንደልፊንገንባድ የሚባል ትንሽዬ ገጠር ከተማ ውስጥ ነበር። ቤቱ የ300 ዓመት ዕድሜ ያለው ይመስላል። ምዕራፍ በሚል ትንሽ ፁሁፍ አለችኝ። ለትረካ የምትሆን። ሲቻል ስዕላዊ ድርሰቱ ሲቀርብ የቤቱ ገፀ ባህሬ ይገለጥላችኋል። አደራጅነት ጥሩ ነው። ሙያውን ማለቴ ነው። እና ቀዝቃዛው ኤክሲሞ፤ ምድረ በዳው ሳህራም ቢሆን ማደራጀት ሸካራውን ልጎ ሐሴት ያስኮመኩማል። እንገዶች ሲመጡ ከተረክሽው ታሪክ ጋር ቤትሽ ግን ይላሉ። ይህ ቤት ግን ከዚህ ህንፃ ውስጥ ነውን ይላሉ። ቀለም መቀባት እወዳለሁ። በዲዛይን። የዛሬን አያድርገውና ቤቴ ሙሽራ ነው እማደርጋት። እረፍት እማልሻውም ቤቴን ቤተ - መቅደስ አድርጌ መኖር ስለምችል ነው።
እና በዚህ ህንፃ ኢንተርኔት የለኝም፦ ኢሜል የለኝም። የገዘፈ ስምንት መምሪያ ያለው ድህረ ገጽ፤ ሦስት መምሪያ ያለው ራዲዮ መሰናዶ ግን እመራለሁ በብላቴ ሎሬት ለውለታው ክብር በሥሙ በመሠረትኳቸው ሚዲያወች።
። ለእግዚአብሄሩ ጠረጴዛ እንኳን የለኝም። በቀን ሆም ፔጁ ላይ ዘጠኝ አውዲዮ ያከለ ቴክስት ይለጠፋል። ኮንፒተር እኮ የለኝም። እና ይህ ፕሮጀክቴ ነው "ሚዲያ ሚዲያን ይሠራል" በሚል ሮሜሮ ሃውስ ከቆንጂት ሉዘርን ከተማ በተዘጋጀው ዓውደ ጥናት ልምዴን እንዳካፍል የተጋበዝኩት። ወጩ ተችሎ። ሆቴሉ ተከፈሎ ነው ታዲያ።
በጋራ አንድ ዝግጅት ነበር። ከዛ በተመደብልን የመግለጫ ሩም በስላይድ የተደገፈ መግለጫ ነበር። ብዙ እንግዶች ወደ እኔ ክፍል መጡ። የተመድ የዩኒሴፍ መሥራች ቤተሰቦች፤ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ዘጋቢ ጋዜጠኛ ቤተሰቦች ነበሩ።
አንድ ጋዜጠኛ የጠዬቀኝ። ካንፕ እዬተኖረ እንዴት? እንደ ወፍ ፍሬ፤ እንደ ጥገት እሳር አትበይ በ400 የሲዊዝ ደሞዝ እንዴት አቀድሽው የሚል ፈታኝ ጥያቄ ጠዬቀኝ። ድፍረት ነው። በራስ መተማመን ነው። በልምድ፤ በተመክሮ በፁሁፍ እምበደረው ስላልነበር ያን ጥሪት አድርጌ ነበር የጀመርኩት።
ሲዊዝ እምትኖሩ ታውቁታላችሁ ብሊክ መጋዚን ዋና አዘጋጁ መግለጫ ይሰጡ ነበር። እኔም። የፈጣሪ ሥራ ይገርማል። ያን ጊዜ ማዕከላዊ ስደተኛ ቢሮ፤ ብዙ ኢንባሲወች ይጋብዙኝም ነበር። ቤት መውጣት ጭንቁ የእኔ ባህል ነው። ቤቴ ቤተ- መቅደሴ ናትና። የሲዊዝ ጓዶቼ ብዙ ይረዱኝ ነበር። በሃሳብ። እራሳቸው ለአምንስቲ፤ ለተመድም ይጽፋ ነበር።
የሆነ ሆኖ በተግባር ውስጥ ፈተና ጠጥቼው ስለአደኩ ምንም አይመስለኝም ነበር። ቤተ እግዚአብሄር አገለግል ነበር። አራሽ ያጡ ስደተኞችን አርስ ነበር። በሚዲያም እስተዚህ የደረሰ ተሳትፎ ነበረኝ።
ሆም ፔጄ ላይ የሎሬት ተስፋ የሚል የልጆች መሰናዶ ነበረኝ። ህልሜ ዘለግ ያለ ነበር። ራዲዮ ላይም የልጆች ክፍለ ጊዜ ነበረኝ። አሁን እዬደከመኝ ነው ።………
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/06/2024
ጥበብ ጥሪዋ ንዑድነው። ተመስገን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ