ለቅኖች፣
ለቅኖች፣ ለዓይነ፣ ልቦና፣ ዕዝነ ህሊና ሰፊወች እንጂ ለዓይነ ጠባቦች ለቅንጣቷ እንኳን ለሚጠዘጥዛቸው ኩርኩዶች አይደለም።
ትንሽ ስለ ደጋግ የሲዊዝ ልጆች። ቤተ እግዚአብሄር በህብረት፣ ሰላማዊ ሰልፍ እና ህዝባዊ ጉባኤ በህብረት አውቶብስ ተከራይተው አገልግሎት የሚሰጡ ቅኖችም አሉን።
በጉዞ ወቅት ፈቅጄ ከሄድኩ አንድም ቀን ከፍዬ አላውቅም። በወረፋ ነው የሚከፈልልኝ። የውነት ነው። ለሽያጭ ዕቃ የሚያቀርቡትም በነፃ ነው የሚሰጡኝ።
እየሩሳሌም የሚሄዱ በረከቱን ይዘውልኝ ይመጣሉ። ጥፍት ስል ቤቴ ድረስ መጥተው ደህና መሆኔን ጠይቀው የሚሄዱም ቅዱሳን አሉን።
የእኛ ፖለቲካችን ነው ያልታረመው። ሰብዕናችን በክፋነት ተክል ኮትኩቶ የሚያሳድገውም ይሄው ነው። ፖለቲካ የውቀት ዘርፍ መሆኑን ባለመረዳት ይመስለኛል።
ለማንኛውም የእኔ አቋጣሪ ደጎቼ ሁሉ ኑሩልኝ። አንድ ቀን እንገናኛልን። እሺ። ኑሩልኝ እመ እና አበው። አሜን።
ዓለም ዓቀፋ የፎቶ ኤግዚቢሽን በዙሪክ የኢትዮጵያ ውክልና ይህን ይመስል ነበር። ኑሩልኝ።
ሥርጉትሻወሰብሊ።
13/06/024
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ