ካሜራ ለምን ተሰራ?
እንዴት ናችሁ ማህበረ ቅንነት? ይህ እዚህ ሲዊዝ ዙሪክ ውስጥ ሳኡ የሚባል የስደተኛ መጋዚን ነበር። ሚዲያ ግሩፕ የሚባል ቲም ነበር። እዛም ለሶስት ዓመት ያህል ተሳትፌያለሁ።
ግን የሠራሁት በነገረ ኢትዮጵያ ነበር። ዛሬ ያሉት የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን የተከበሩ ዶር ዳንኤል በቀለን ሥም ታገኛላችሁ ለአቶ እስክንድርም ከዛን ጊዜ ጀምሮ ታግያለሁ። ለማድመጥ ባይፈቅድም።
ዕውነት ልንገራችሁ ደክሞኛል። እና አንዳንድ ጊዜ መተራረፊያ የሚሆን ነገር ስሰራ በሰጨኝ የሚሉ ጓደኞች ገጥመውኛል። ግሉባሉ ከፎቶ ውጪ ምን እዬሠራ ነው?
ካሜራ ለምን ተሰራ? በዬዓመቱ አድባንስድ የሚሆኑ ቴሌፎኖች ለምን ተግባር ተሰሩ? ኢኒስተግራም ሆነ ሌላው ሚዲያ ሥራው ምንድን ነው?
ቪዲዮ ለምን ተፈጠረ? ፎቶ እኮ አርት ነው። የሚሰለጥኑበት ሙያ። ሞድ ኢንደስትሪ ምንድን ነው?
ህሊናቸውም፣ መንፈሳቸውም ጥብብ ያሉ ሰብዕናወች ይገርሙኛል። ለዛውም ፕሮፋይላቸው ፎቶ ሆኖ።
ምንስ እንደ ቅቤ ያንጨረጭራል? በዘጠኝ ወር አንድ ቀን ቀርቶ በዬለቱ ያሻኝን ብለጥፍ በቤቴ ምን ይጨንቃል። ኦ !ኢትዮጵያ መጥኒ ላንች። እኔስ ዘመኔ እያለቀ ነው። ኖሪቱ አንቺ ግን ታሳዝኚኛለች።
ዓይነ ጠባቦች ቤታቸው ቢኬድ ምን ሊሆኑ ይሆን።? ለኦክስጅን ቢያመለክቱ ይሻላቸዋል። አጤ ኦክስጅን ሆይ ለሁሉ ፀጋ የሆነውን ስጦታህን እባክህ ለሥርጉትሻ ንፈጋት ብለው ያመልክቱ። ተረበኞች።
በፌቡ በዩቱብ ቻናል ቀደም ባለው ጊዜ በድህረ ገፄ እስካሁን በፀጋዬ ራዲዮ ታገሉ። ፀጋ ሰጩ ተቋቁሞ የበለጠ ዕድል እዬሠጠኝ ኖርኩኝ። በዚህም ተቀጥል።
እኔ ፌቡ እኮ እጅግ ዘግይቼ እናቴ ነው ያስጀመረችኝ። ቲኪክቶክ ገብቼ አላውቅም። ሰሞኑን ነው ያስጀመሩኝ። ሳዬው ብዙ አማራጭ አለው።
ጥበብ ገፊዋ ብዛቱ። ጠሚር አብይ ጥበብን አሰሩ ብዬ አዝን ነበር። የፌቡ ተጠቃሚ ፎቶ ማዬት አይሻም። ትልቅ ኢንደስትሪ ነው። እኔ ደግሞ እጅግ በጣም ነው እምወደው።
ስለ እናቴም ምን እንደሆነ የሚያውቁ ተመድን ጨምሮ የዓለም መንግሥታት ያውቃሉ። ሌላው የሚሸለምበት፦ የሚወደስበት፦ እንክህ እንክህ የሚባልበት የማን የእጅ ሥራ እንደሆን አንድዬ እና አማካሪዬ የውጭ አገር ሰወች ያውቁታል።
ከአቅሜ በላይ ሠርቻለሁ። ቀረ እምለው ነገር የለም። ሲዊዝ ውስጥ ብሄራዊ ኢንተግሬሽን ቤተ መፃህፍት ለስድስት ጊዜ ያህል ጉባኤው ተወያይቶበታል በመፃህፍቶቼ ላይ። ተዳፍኖ በእኛው ወገኖች እንጂ ብታዩት አዲስ አርት ነው።
ቲያትር እዬሰለጠንኩ በአማርኛ ቋንቋ ትረካ እንዳቀርብ ተፈቅዶልኝ ነበር። እኔ ስለ አገሬ? የገደምኩት ስለእሷ ነው። መጠንቀቅ ስላለብኝ።
እና ፎቶ ይለጠፋል። የታሪኬ አካል ነው። ከማለፌ በፊት ታሪኬን እራሴን እሰራዋለሁ።
ለመሆኑ ሥርጉትሻ ሰብዕናውን ያልገነባችለት፣ ታስሮ ያልጮኽችለት፣ ጥሩ ሰርቶ ፊት ለፊት ወጥታ ያልመሰከረችለት፦ ያልተማገደችለት አለን? በራሷ ወጪ በራሷ ጊዜ። የቤተሰቦቿን የማትገኜውን የናቷን ፈቃድ ጥሳ ለኢትዮጵያ ኑራለች።
እና ፌቡ ፎቶ ለጠፈች ነው ጉዳዩ????? ይለጠፋል። እንዲያውም በሙሉ አቅሜ ልሠራ የምችልበትን ሁኔታ እያደራጀሁ ነው። ትናንት በቀደመው ቀን ጥሩ ቀን ስለነበረ ለፈጣሪ ምስጋና ነበር የፎቶ ቀን የነበረው። በቃ ጥሩ ሰሞናት ነበሩ። ወደፊትም ተስፋችን አምላካችን ነው።
በዚህ ወር ብሎጌ ከ20500 በላይ ታዳሚ ነበር። የሚያነብም አለ ማለት ነው። ራዲዮኑም እዬሠራ ነው። እንዲቀመጥ የምሻቸው በድምጽ በተጨማሪነት በጥራት ዩቱቤ ላይ ይፖሰታል።
ሁለተኛ ዩቱብ ቻናል በፍቅር ተፈጥሮ እሱም ይሠራበታል። ምክንያቱም የውስጤን ሃዘን በገለጽኩ ቁጥር አድማጮቼን እንደጎዳሁ ተሰምቶኛል። ክፋ ነገርን፣ ጭካኔን አብረን እንዋጋበታለን። መኖር እረፍት ማግኜት ስላለበት።
ፎቶው ይቀጥላል። ቡናው በረደ ይጠጣ።
ቅኖች፦ ዓዕሞሮ ሰፊወች፦ ለጥሩነት፦ ለአድማጭነት፦ ንፋግ ያልሆናችሁ ውዶቼ ውስጤ ንፁህ ቅን እና ግልጽ ነውና ከንፀኋ ልቤ የፈለቀ አክብሮቴን፣ ትህትሁት ምስጋናዬን እንሆ።
ስለ ፎቶ ይጣፋል። ባይገርማችሁ ዓለም ያልጀመረው መስክም አለኝ። ሌላ ጊዜ አጫውታችኋለሁ።
ለዘጠኝ ወር ኢኒስተግራም አልሰራሁም። የግል ትንተናወቼ ባህሌ በእኔ ፎቶ ነበር የሚወጡት። ከፋኖ ውጊያ ጅማሮ ጋር ቆሞ ነበር። ከእንግዲህ ፎቶዬም ለሚያንገበግባቸው ይለጠፋል። ክፋ ሰብዕናወች መድህን ይሆን ዘንድ ቀደምት ባህሉ እንደነበረው ይቀጥላል።
"አድርገኽልኛል እና አመሰግንኃለሁ። "
ፁሁፋ በጀርመንኛ ቢሆንም ሥሙን ማዬት ትችላላችሁ። አመሰግናለሁ።
ከቤታችን ከቅንጣቱ እስከ ገዘፈው የተጋድሎ ታሪኬ የሚያውቁ ክብሮቼም አሉ። ድምጣቸውን አጥፍተው ይከታተላሉ። ያደባባዩን ልቅም አድርገው ያውቃሉ። ብገድፍ የአደባባይ ሰወች ስለሆኑ ወጥተው ይናገራሉ። ሥራ ማብዛቴ፦ ቤተሰቦቼን መርሳቴ፦ አገሬ አለመግባቴ ግን ያሳዝናቸዋል። እኔ ለእኔም ለቤተሰቤም ሁኜ አላውቅም። ፎቶ ብርቅ ሆኖ ደግሞ? ኧረ ስንት አፍ ሞልቶ የሚያናግር የዝምታ ተግባር ከውኛለሁ።
ኑሩልኝ። ውድድድድድ።
ሥርጉትሻ 13/06/024
ጊዜ ራዲዮ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ