ልጥፎች

ከጁላይ 29, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ስጋቴ "የስበት ህግ" #ምልክት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ላይ #እንዳይጫን ነው።

  #ስጋቴ "የስበት ህግ" #ምልክት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ላይ #እንዳይጫን ነው።   "ቤት በጥበብ ይሠራል፤ በማስተዋል ይጸናል፤ በውቀት ከከበረውና ካማረው ሃብት ሁሉ ጓዳወች ይሞላሉ።" አሜን። ይደረግልን። ይሁንልን። (ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ከቁ ፫- ፬)   ማህበረ ቅንነት እንዴት ናችሁ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።   #ምዕራፍ ፲፱።   የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ፕሮጀክት #ሎጎ በመደበኛ እከታተላለሁኝ። ለእኔ ሎጓቸው የምር ጉዳዬ ነው። የፖሊሲወቻቸው መሻቶች በሎጓቸው #ካፒትንነት የሚካሄድ በመሆኑ።    #የአብይዝም #ብልፄው ፖሊሲ የለሽ ነው የሚሉ ወገኖች እንዳሉ አውቃለሁኝ። በስሱ ብቅ ጥልቅ የሚሉ፤ በሙሉነት ግን በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ህሊና ተመስጥረው የተያዙ ፖሊሲወች አሉ። የአብይዝም መሪ ሃሳባ የሚሰክነው በሎጎወቻቸው ነው። ስለዚህም በአትኩሮት የየፕሮጆክታቸውን ሞቶ እና ሎጎ እከታተላለሁኝ።   እስከዛሬ ባየሁት የሎጎ ምርጫ ከኢትዮጵያ ኦርጋኒክ ተፈጥሮ፤ አሻራ እና ትውፊት #ሽሽት ነው እማይባቸው። እኔ እንደማስበው አብይዝም የዓለም ሎጎ #ጭማቂ የመሆን ህልም እንዳለው አስባለሁኝ።   የራስ - ነገር፤ ቀደምት ክብርና - ልዕልና፤ አዛውንት ባህልና - ቅርስ፤ የበቃ የታሪክ - መዘከርነት እና የኛነት ድምቀት ለአብይዝም አጀንዳው የሚሆን ሆኖ አላየሁም። ህዝባዊ ድጋፍን ላለማጣት ደማቅ ጉዳዮችን ተቀብሎ በውዞ፤ ወይንም አሸጋሽጎ ለማስቀጠል ጥረቱን አያለሁኝ። ዓድዋ ወደ ማዕከል መጥቷል። ሥሙ ግን የተለፋለትን ጥረቱን ገዳይ ነው።    "ዓድዋ #ዜሮ ዜሮ" አንድ ዜሮነት አልበቃም። ዜሮ ስኮዬር? የታሪክ ሙሁራንም ጭጭ ነው ያሉት...

"#ጥቃቅን ቡድን?" የምክክር ኮሚሽኑ ሥያሜ። #ሰብዕናን #ይጫናል። ሰብዕናዊ ክብርንም ይዳፈራልም።

  " #ጥቃቅን ቡድን?" የምክክር ኮሚሽኑ ሥያሜ። #ሰብዕናን #ይጫናል ። ሰብዕናዊ ክብርንም ይዳፈራልም።   "የዋሆች ብጹዓን ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና።" (የማቲወስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፭)   #ምዕራፍ ፲፱።   የምክክር ኮሚሽኑ ለሥራ እንዲያመቸው የጉባኤውን ተሳታፊ በተለያዩ ዘርፎች ማደራጀቱን አዳምጫለሁኝ። " #ጥቃቅን ቡድን" የሚለው አልተመቸኝም። ንዑስ እንዳይሉት #ንዑስ የሚባል አለ። ከንዑስ ዝቅ ያለውን ይመስለኛል " #ጥቃቅን ያሉት።    ቡድኑ የሰወች #ማህበር ነው። ቡድን ለቋሚም ለጊዚያዊም ተግባር ይደራጃል። የምክክር ኮሚሽኑ የጉባዔ አደረጃጀት #ለጊዜያዊ ተልዕኮ ነው።   ቡድኑ ለተወሰነ ጊዜ፤ በተሰጠው አጀንዳ፤ በተፈቀደለት #የጊዜ ማዕቀፍ ተለይቶ የተሰጠውን #ተግባሩን ከውኖ የሚያስረክብ። ለሰወች ጊዚያዊ ይሁን ዘላቂ ቡድን " #ጥቃቅን " ማለት ይከብዳል። #ሰብዕናን #ይጫናል ።   ጥቃቅን #ለቁስ ሊሆን ይችላል። #የነገር ሥም። ለሰው ልጅ ማህበር ግን " #ጥቃቅን " ፈጽሞ የማይመጥን ሥያሜ ነው። ከጥቂት ደቂቃወች በፊት መግለጫ ተሰጥቷል። ከዛ ስሰማው ከበደኝ።   ከጥቃቅን ይልቅ #መሠረት ቢባል የተሻለ በሆነ ነበር። #መነሻ ቢባልም እንዲሁ ለሰው ልጅ የሰብዕና ልዕልና የሚመጥን ይመስለኛል። አስኳል ይባላል በፖለቲካ አደረጃጀት። ይህንንም ከአዕውፋት ዝርያ ወይንም ከዶሮ፤ ከቆቅ፤ ከዥግራ ጋር የሚያገናኝ መንፈስ ስላለው፤ እንደ " #ጥቃቅን " ባይከብድም ………   ቡድን #በሰው ልጅ ነው የሚደራጀው። ስለዚህ ለሰው ልጅ ማህበር የሚሰጠው ሥም #መጣኝ ፤ #በክብሩ ልክም ቢሆን ጥሩ ነበር። ፈጣሪ አልቆ፤ አጽድቆም በእኔ ...

አሁን ያለው ብሄራዊ መዝሙር #ቢቀጥል ምርጫዬ ነው። #እፈርምለታለሁኝ።

ምስል
  አሁን ያለው ብሄራዊ መዝሙር #ቢቀጥል ምርጫዬ ነው። #እፈርምለታለሁኝ ።   "ልጄ ሆይ ጠቢብ ሁን ልቤንም ደስ አሰኜው።" (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፯ ቁጥር ፲፩)       #ምዕራፍ ፲፱።   የኢህአዲግ ትውልድ ያደገበትን ብሄራዊ መዝሙር ይወቀው፤ አይወቀው፤ ስሜት ይስጠው፤ ስሜት አይስጠው አላውቅም። እያንዳንዱ ክልል መለያ ዓርማ፤ መዝሙርም እንዳለ አዳምጣለሁኝ።    የቅኝ ግዛት ምኞት ያላቸው አገሮች የኢትዮጵያን የጥንካሬ ሞተር የፈተኑበትን ህልም ያሳካው ህወሃትሻ ነው። ብሄራዊ መዝሙር፤ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ የዜግነት አሻራ ነው። በቋሚነት የሚቀጥልበት የመቻል አቅም አምጠን ልንወልደው ይገባል። እራስን ማሸነፍ ያስፈልጋል።   አገር ስላለ ነው ሹመቱ ሽልማቱ፤ ምኞቱ ቅብጠቱ አና ያለው። ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ፤ ብሄራዊ መዝሙር፤ ብሄራዊ ቋንቋ አገር የፈጠሩ፤ አገራዊነትን የመገቡ። በራስ መተማመንን አፍልቀው ያጸደቁ ልዩ ስጦታወች ናቸው። ክብር ቀርቶባቸው እንግልታቸው ግን እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያቆስላል። እርሾ አልባ አየር ላይ ተንሳፎ ተጠንስሶ፤ የተወለደ፤ ያፈራ፤ ያሰበለ ምንም ነገር የለም።   የሆነ ሆኖ የኢህአዴግ ዘመን ብሄራዊ መዝሙር እንደአለ #ቢቀጥል ጥሩ ይመስለኛል። የጃንሆይ ትውልድ ነበረው፤ የደርግ ትውልድም ነበረው፤ የኢህአዴግ ትውልድም አለው። ይህን ሰርዞ እና ንዶ እንደገና "ሀ" ብለህ ጀምር ብዙ ንደት ያመጣል። የእስከዛሬው ግድፈታችን ይበቃል። የመቻል አቅማችን ፈታትሸን እራሳችነን ገስጸን ወደ ቀልባችን ልንመለስ ይገባል።   የግጥሙን ስንኝ በተደጋጋሚ አየሁት። የዜማ ቅኝቱን አዳመጥኩት። ስሜት ይሰጣል። አገራዊ ፍቅርን ይስባል። እኔ ህወሃትሻን በብዕር ሞግቸ...

ከንቲባ አዳነች አበቤ ወደ #ፌድሬሽን ምክር ቤት ጎራ ይሉ ይሆን?

ምስል
  ከንቲባ አዳነች አበቤ ወደ #ፌድሬሽን ምክር ቤት ጎራ ይሉ ይሆን?   "ቀን የሚያመጣውን ምን እንደሆነ አታውቅም እና ነገ በሚሆነው አትመካ።" (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፯ ቁጥር ፩)         ምዕራፍ ፲፱።     #በር ። በምን ቀመር አዲስ አበባ እራስ ገዝ ትሁን፤ አዲስ አበባ ክልል ትሁን ተሸንፎ አዲስ አበባ በኦሮምያ ሥር ትተዳደር የሚል የውሳኔ ሃሳብ እንዳለፈ አይታወቅም። ብልፄው ለካንስ የቁጥርም ስፔሻሊስትም ነው።   #የማይመች ።   በዘመነ አብይዝም የማይመች ገጠመኝ አንድ ሰብዕና ከአብይዝም ልቆ #ዘለግ ብሎ ማደግ ነው። ወይንም ገነን ያለ ተቀባይነት ማግኜት ፈጽሞ የማይመች ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያ እያደገ፤ ከፍ እያለ፤ እየደረጀ እንዲሄድ የሚፈቀድለት የአብይዝም መንፈስ ብቻ ነው።   ነገረ አዲስ አበባ እና የኮሪደር ልማቷ፤ ተጨማሪ የውበት ፕሮጀክቶቿ ሲጠሩ የሚጠቀሱት ከንቲባ አዳነች አበቤ ናቸው። #መጠሪያቸው ሁናለች ለከንቲባ አዳነች አበቤ አዲሷ።    ለነገሩ ሥራውን ሁለቱ ቢሠሩትም፤ ግን የአዲስ አበባ ተጠሪ ከንቲባዋ ስለሆኑ፤ መንትያው ሥያሜ ይረሳል፤ ወይንም ይዘነጋል። ይህ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አቅደው ለሚፈጽሙት፤ ለሚደክሙለት የውሃ ዳንስ ትዕይንት በሌላ ስኬቱ ሲጠራ አይፈልጉም። #የኮፒራይት © ጉዳይ ነዋ!    በዚህ ሂደት በሰጨኝ አይቀሬ ነው። መጋቢት 1/2011ዓም የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ እና የባልደራስ ምሥረታ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ እራሳቸውን ሳይደብቁ አደባባይ ላይ ብስጭታቸውን ያዬንበት ዕለት ነበር።   እኔ በወቅቱ በሰጨኝ ለጠቅላይ ሚኒስተር አይመችም ብዬ ወግ ቢጤ ጫጭሬ ነበር። አዲስ አ...