"#ጥቃቅን ቡድን?" የምክክር ኮሚሽኑ ሥያሜ። #ሰብዕናን #ይጫናል። ሰብዕናዊ ክብርንም ይዳፈራልም።
"የዋሆች ብጹዓን ናቸው፤
ምድርን ይወርሳሉና።"
(የማቲወስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፭)
#ምዕራፍ ፲፱።
የምክክር ኮሚሽኑ ለሥራ እንዲያመቸው የጉባኤውን ተሳታፊ በተለያዩ ዘርፎች ማደራጀቱን አዳምጫለሁኝ። "#ጥቃቅን ቡድን" የሚለው አልተመቸኝም። ንዑስ እንዳይሉት #ንዑስ የሚባል አለ። ከንዑስ ዝቅ ያለውን ይመስለኛል "#ጥቃቅን ያሉት።
ቡድኑ ለተወሰነ ጊዜ፤ በተሰጠው አጀንዳ፤ በተፈቀደለት #የጊዜ ማዕቀፍ ተለይቶ የተሰጠውን #ተግባሩን ከውኖ የሚያስረክብ። ለሰወች ጊዚያዊ ይሁን ዘላቂ ቡድን "#ጥቃቅን" ማለት ይከብዳል። #ሰብዕናን #ይጫናል።
ጥቃቅን #ለቁስ ሊሆን ይችላል። #የነገር ሥም። ለሰው ልጅ ማህበር ግን "#ጥቃቅን" ፈጽሞ የማይመጥን ሥያሜ ነው። ከጥቂት ደቂቃወች በፊት መግለጫ ተሰጥቷል። ከዛ ስሰማው ከበደኝ።
ከጥቃቅን ይልቅ #መሠረት ቢባል የተሻለ በሆነ ነበር። #መነሻ ቢባልም እንዲሁ ለሰው ልጅ የሰብዕና ልዕልና የሚመጥን ይመስለኛል። አስኳል ይባላል በፖለቲካ አደረጃጀት። ይህንንም ከአዕውፋት ዝርያ ወይንም ከዶሮ፤ ከቆቅ፤ ከዥግራ ጋር የሚያገናኝ መንፈስ ስላለው፤ እንደ "#ጥቃቅን" ባይከብድም ………
እርግጥ ነው የዘርፋ አባላት ተግባራቸውን በማጠናቀቅ ላይ ስለመሆናቸው አድምጫለሁኝ። ተልዕኮው ከመሠረቱ ወደ ላይኛው ክፍል ቢሄድም የቡድኑ #ሥያሜው ግን ቀጣይ ይሆናል።
ማህበረ ቅንነት እንደምን አድራችሁ፤ አረፈዳችሁ፤ ዋላችሁልኝም።
ቸር አስበን ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
28 / 07/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው አሜን።
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ