#ስጋቴ "የስበት ህግ" #ምልክት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ላይ #እንዳይጫን ነው።
"ቤት በጥበብ ይሠራል፤
በማስተዋል ይጸናል፤ በውቀት
ከከበረውና ካማረው ሃብት
ሁሉ ጓዳወች ይሞላሉ።"
አሜን። ይደረግልን። ይሁንልን።
(ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ከቁ ፫- ፬)
ማህበረ ቅንነት እንዴት ናችሁ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።
#ምዕራፍ ፲፱።
የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ፕሮጀክት #ሎጎ በመደበኛ እከታተላለሁኝ። ለእኔ ሎጓቸው የምር ጉዳዬ ነው። የፖሊሲወቻቸው መሻቶች በሎጓቸው #ካፒትንነት የሚካሄድ በመሆኑ።
#የአብይዝም #ብልፄው ፖሊሲ የለሽ ነው የሚሉ ወገኖች እንዳሉ አውቃለሁኝ። በስሱ ብቅ ጥልቅ የሚሉ፤ በሙሉነት ግን በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ህሊና ተመስጥረው የተያዙ ፖሊሲወች አሉ። የአብይዝም መሪ ሃሳባ የሚሰክነው በሎጎወቻቸው ነው። ስለዚህም በአትኩሮት የየፕሮጆክታቸውን ሞቶ እና ሎጎ እከታተላለሁኝ።
እስከዛሬ ባየሁት የሎጎ ምርጫ ከኢትዮጵያ ኦርጋኒክ ተፈጥሮ፤ አሻራ እና ትውፊት #ሽሽት ነው እማይባቸው። እኔ እንደማስበው አብይዝም የዓለም ሎጎ #ጭማቂ የመሆን ህልም እንዳለው አስባለሁኝ።
የራስ - ነገር፤ ቀደምት ክብርና - ልዕልና፤ አዛውንት ባህልና - ቅርስ፤ የበቃ የታሪክ - መዘከርነት እና የኛነት ድምቀት ለአብይዝም አጀንዳው የሚሆን ሆኖ አላየሁም። ህዝባዊ ድጋፍን ላለማጣት ደማቅ ጉዳዮችን ተቀብሎ በውዞ፤ ወይንም አሸጋሽጎ ለማስቀጠል ጥረቱን አያለሁኝ።
ዓድዋ ወደ ማዕከል መጥቷል። ሥሙ ግን የተለፋለትን ጥረቱን ገዳይ ነው።
"ዓድዋ #ዜሮ ዜሮ" አንድ ዜሮነት አልበቃም። ዜሮ ስኮዬር? የታሪክ ሙሁራንም ጭጭ ነው ያሉት። ዜሮ ሲደመር በዜሮ፤ ወይንም ሲቀነስ ከዜሮ፤ ወይንም ሲባዛ በዜሮ፤ ወይንም ሲካፈል በዜሮ ያው #ዜሮ ነው። እሳቸውም ደክመው አሰርተው፤ ቀደምቶችም የደም፤ የአጥንት ሰማዕትነትን የተቀበሉበትን ግሎባል ድል፤ የዊዝደብ ብቃት አፍሰውበት ግን በሁለት #ዜሮወች ተጠቃለለ።
የንጉሦች ንጉሥ የአጤ ሚኒሊኬ ቤተ - መንግሥቱን በአብይዝም መንፈስ #የፒኮክ ንግሥና ታውጆለታል። አንበሳ ከእነ - ግርማው፤ ከእነ - ማዕረጉ፤ ከእነ - ትሩፋተ ብቃቱ አታሻኝም ብሎ አብይዝም #ነቅሎታል። ነቀላው የመንፈስም ነው።
ጎንደር ቤተ - መንግሥቱ ታድሷል። በቀለሙ ጉዳይ እጅግ አዝኜ ነበር። ተጓዡ ካሜሬ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም በሰጠው ማብራሪያ ምክንያት የእሱን ገለጣ አምኜ እንዲያውም የፌቡ መለያ ሆኗል። አሰራሩ ብቃት እና ጥራት እንዳለው ምስክርነት ሰጥቷል። ይህ መልካም ነገር ነው። በብዙ የተጎዳ ቅርስ ስለነበር።
የጎንደር የፒያሳ ህንፃ ቀለም የኢትዮጵያ ሆቴል፤ ቴሌ ፖስታ ቤቱ፤ የአባ ተስፋማርያም ስቴሽነሪ የነበረው፤ የአባ በዬነ ግርሶሪ እስከ ጎንደር ፎቶ ቤት፤ የጋሽ ልዑል ፎቶ እስከ መድህን ድርጅት፤ ሲኒማ ባር የነበረው ቀለም ተሽሯል። #ድጠት ከምል #ግድያ ነው የተፈጸመበት።
ምንም እንዳይናፈቅ አድርገው የፈዘዘ፤ የደነዘዘ፤ ጥንታዊ ውበቱን #የተነጠቀ ነው የሆነው። ማማከርም ያባት ነው። ማን ይናገራል? አብይዝም ከአጤወች በላይ ነውና። ያለው መብት መቀበል ብቻ ነው። የጎንደር መንፈስ ተደፋሪ አልነበረም። ግን?
በዚህ መልክ ሙሉ 8 ዓመት የተለያዩ ፕሮጀክቶች ታቅደው ተፈጽመዋል። ውስጣቸውን ሄጄ ስላላየሁ በምን መንፈስ እንደሆን አደረጃጀታቸው ይሁን አወቃቀራቸው ስለማላውቅ #ዝምን አጸደቅኩት።
#ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ።
መቼም በዘመነ አብይዝም አሳሩን ካየው በኽረ ጉዳይ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ነው። ተሰቃይቷል። ነዷልም። በሌላ በኩል እራሱ ብሄራዊው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሎጎ #ቀለሙም ዲዛይኑም ግርም ይለኛል። ይህንንም ላለማወክ #በዝምታ ነው ያለፍኩት። ተቀራራቢነቱ ከምን ጋር እንደሆን ብጠረጥርም ማለት ነው።
የሆነ ሆኖ አገራዊ ምክክሩ ከሚወያይባቸው አመክንዮወች አንዱ የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ጉዳይ ነው። ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ንባቡ ከላይ ወደ ታች ነው። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ተብሎ ነው የሚነበበው።
ከዛሬ 15 ዓመት በፊት ለልጆች በፃፍኩት የጥያቄ እና የመልስ መጽሃፍ ዲዛይኑ አድዮ ነው። በውስጥም ያሰብኩትን ጽፌያለሁኝ። ማህለኛው ቀለም ሊንኩ #ከብሄራዊ አበባችን የተወሰደ ነው ብዬ ዘለግ ያለ ማብራሪያ ሰጥቸበታለሁኝ።
ከዚህ ቀደምም ከአንድ ቀን በፊት #ብራንዳችን ሊሆን የሚገባው የመነሻ ቀለማት እንዳሉ እንደ ተፈጥሯቸው ቢጸድቅ ብዙ የተበተነን መንፈስ ሊያሰባስብ የሚችል፤ አደራጅ እና መሪ የሆነ ጸጋ እንዳለው ጽፌያለሁኝ።
ብልጽግና እራሱን ለማስቀመጥ ካሰበ ብራንዱን ለመጠቀም ለሚፈልጉ ኢትዮጵውያን ሆነ አፍቅሮተ ኢትዮጵያ ያላቸው የሌላ አገር ዜጎች ጃማይካን ጨምሮ #ክልከላው እጅግ ነውር ስለሆነ ማዕቀቡ እንዲነሳ ጽፌ ነበር። ያው የኢትዮጵያ ፖለቲካ "ላም እረኛ ምናለን" አድማጭ አይደለም እና ሃሳቤን በካልቾ ሊያስሽቀነጥረው ይችላል።
ከሁሉ ስጋቴ ግን በአድዮ አበባ አንጋችነት #የስበት፤ የኢነርጂ ምልክት እንዳይለጠፍበት ነው። ከተለጠፈበት ግን፤ ከአዲስ ኪዳን በፊትም ይሁን በኋላ አምላክ፤ ፈጣሪ፤ አላህ አለኝ ብላ ለምታምን ፈላስፊት ኢትይጵያ የእምነት ፍልሰት የሚፈጸምባት አገር ትሆናለች።
"የስበት ህግ ኢነርጂ ይሰጣል። የፈለጋችሁትን ያሳካል። ዩንቨርስ ነው ባለ አቅሙ" የሚል ፍልስፍና በነፃነት ኢትዮጵያ ምድር ላይ ይነገራል። ይህ አጥፊ ዕሳቤ በብራንዳችን በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓለማችን ላይ ከተጫነ፤ የኢትዮጵያን የዘመናት ልቅና እና ልዕልና የሃይማኖት ምድርነቷን የሚፈትን ይሆናል። የኮሚሽኑ ጠቅላላ ተልዕኮ ፍፃሜ ---- ም አፋፍ ላይ ይሆናል። ጨርሼ ከመናገር መቆጠቡ ይሻላል።
ኢትዮጵያ ይህን የስበት ህግ ሎጎ እንድትቀበል ከተገደደች፤ በይፋ እና በአደባባይ ሃይማኖት የለሽ አገርነቷ ይታወጃል ማለት ይሆናል። በተለይ የአገራዊው ምክክር ኮሚሽን አካላት ከዚህ መሰል የገዘፈ #ነቃይ እርምጃ ውስጥ እንዳይገቡ በትህትና እና በአክብሮት ላሳስባቸው እፈልጋለሁኝ። ኢትዮጵያን በፈንጅ ደብድቦ የመግደል ያህል ይሆናል። መሠረቷን ነቅሎ ለሌላ ሁነት መንፈሷን እንዲገዛ የማስገደድ ድፍረት --- ም ይሆናል። ***** ስጋቴ***** ይህ ነው።
በሃሳብ፤ በምልከታ፤ በአካሄድ፤ በዝንባሌ፤ በመሻት፤ በርዕዮት ለማቀራረብ የታሰበው ተልዕኮ በድን ነው የሚሆነው ይህ "ኢነርጂ፤ የስበት ህግ፤ ዩንቨርስ አምልኮ" በኢትዮጵያ ቅዱስ መንፈስ ላይ ከተጫነ።
በዘመነ አብይዝም ብልፄው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የመንፈስ አቅም ጋር ያለው ግብግብ ማሳረጊያው "በኢነርጂ አምልኮ" ከሆነ አይደለም ነገ፤ ዛሬ አፍ ባለው መቃብር ውስጥ ይሆን ዘንድ ይገደዳል።
በዊዝደም በተበጀች አገር የተገኜ ሥልጣን፤ ጥበቡን አክብሮ ካልተነሳ ሚስጢር ይደፋል። ሚስጢር ከተደፋ {} ይኮናል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ሳይዙ እራሱ መዛባት የለበትም። አግድም ነው። ሦስቱም ቀለማት በእኩልነት የተመጠኑ ናቸው። አረንጓዴው ከቀዩ፤ ቀዩ ከቢጫው አያንስም፤ አይደጉስም፤ አይደምቅም ወይንም አይፈዝም። ቀለማቱ የጥቁር ሆነ የግራጫምነት ጫና ትውር የማይልባቸው ብሩህ እና ብርሃናማም ናቸው።
ብሄራዊው የምክክር ኮሚሽን አውታር፤ አንከር፤ ፒላር፤ የጀርባ አጥንት በሆነው ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ሳንክ የሚፈጥሩ፤ ዲቃላ ዕሳቤወችን፤ ልጥፍ - ሁነቶችን፤ ቁሮ ምልከታወችን የመቋቋም ብሄራዊ ብቻ ሳይሆን አህጉራዊም ኃላፊነት እና ግዴታ አለበት። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እንጂ እስያ አይደለችም። በብዙ ሁነት የእስያ መንፈስ ኢትዮጵያን ሲጫናት አስተውላለሁኝ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
29/07/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ወጌሻ ወይንም ጋራጅ አያስፈልገውም።
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ