ባለ #ትንቢቱ #እጬጌ! አባ #እዮብ ጥናት መቀነቱን ቅድስት ድንግል ማርያም ትስጠወት። አሜን።
ባለ #ትንቢቱ #እጬጌ ! አባ #እዮብ ጥናት መቀነቱን ቅድስት ድንግል ማርያም ትስጠወት። አሜን። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" አባት ሆይ! #የፋመው ተጋድሎ የሚጀምረው አሁን ነው። የማቱሳላን ዕድሜ አጋይስትዓለሙ ሥላሴ ይስጠወት። አሜን። ስንቱን #መከራ ተሸከሙ? ስንቱንስ ፈተና በጥበብ #ታገሡ ? ሰው ምን አቅም አለው ይህንን #ምርቅ የፈተና ሂደት የማንበብ ሆነስ #የመተርጎም ? ከባድ ነው መጪው የአገልግሎት ዘመን። ይመስለኛል። እንደ ሰው ሳስበው። ጥንካሬወ፣ ብርታትወ፣ ትዕግሥተወት #ብልህነተወትንስ ማን አቅም አለው ለመተርጎም??? አይደለም ለመተርጎም የተዋህዶ ልጆች ከሊቅ እስከ ደቂቅ #ገብቶናልን ??? አይመስለኝም። የፖለቲካ ሸቀጥ በልጦናል። የዞግ ደንበር ገዝቶናል። ያማ ባይሆን ለአኃቲ ሃይማኖት #ቅጥልጥልስ ፤ #ግንጥልጥልልስ ምን ያስፈልጋት ነበር። ዕምነቱ ካለ፤ ጸጋው ከታወቀበት። ቅብዓ ከእዮር እንጂ ከሰው አይደለም። ለሃይማኖታችን ጥንካሬ የሚጠቅመው በማስተዋል #በንፁህ ልቦና በአኃቲ መንፈስ መጓዝ በነበረ። #ቅንነት ። ለእመ ቅኒት ለቅድስት ተዋህዶ ሃይሞኖት ጽናት ተምሳሌ የሆኑ እጬጌን የመቀበል እንኳን አቅሙ እየታዬ ነው። አይደለም በ፯ ዓመታት፤ ለ፯ ሰከንድ የቅዱስነታቸው ያህል በብልህነት ፈተና መሸከም ሆነ ትብትቡን የአሳር አሳር ተቋቁሞ መቀጠል ከባድ ነው። አባ እዮብ ግን ችለውበታል። ከጎናቸው መቆም የሚገባቸው ፈተና አምራች ሆኖ ከማየት በላይ ምን የሚገርም የታሪክ ድርሳን ይኖር ይሆን? በተለይ የትግራይ ብጹዓን አበው። ዝም የምለው ያላቸውን አውቃለሁ። ግን ያላቸው ለትውልድ መጠኑን #መከለል ? ፈጣሪ ደንበርም ወሰንም ዞግም የለውም። ዕድሉን...