ባለ #ትንቢቱ #እጬጌ! አባ #እዮብ ጥናት መቀነቱን ቅድስት ድንግል ማርያም ትስጠወት። አሜን።
አባት ሆይ! #የፋመው ተጋድሎ የሚጀምረው አሁን ነው። የማቱሳላን ዕድሜ አጋይስትዓለሙ ሥላሴ ይስጠወት። አሜን።
ከባድ ነው መጪው የአገልግሎት ዘመን። ይመስለኛል። እንደ ሰው ሳስበው። ጥንካሬወ፣ ብርታትወ፣ ትዕግሥተወት #ብልህነተወትንስ ማን አቅም አለው ለመተርጎም??? አይደለም ለመተርጎም የተዋህዶ ልጆች ከሊቅ እስከ ደቂቅ #ገብቶናልን??? አይመስለኝም። የፖለቲካ ሸቀጥ በልጦናል። የዞግ ደንበር ገዝቶናል። ያማ ባይሆን ለአኃቲ ሃይማኖት #ቅጥልጥልስ፤ #ግንጥልጥልልስ ምን ያስፈልጋት ነበር። ዕምነቱ ካለ፤ ጸጋው ከታወቀበት። ቅብዓ ከእዮር እንጂ ከሰው አይደለም።
ለሃይማኖታችን ጥንካሬ የሚጠቅመው በማስተዋል #በንፁህ ልቦና በአኃቲ መንፈስ መጓዝ በነበረ። #ቅንነት። ለእመ ቅኒት ለቅድስት ተዋህዶ ሃይሞኖት ጽናት ተምሳሌ የሆኑ እጬጌን የመቀበል እንኳን አቅሙ እየታዬ ነው። አይደለም በ፯ ዓመታት፤ ለ፯ ሰከንድ የቅዱስነታቸው ያህል በብልህነት ፈተና መሸከም ሆነ ትብትቡን የአሳር አሳር ተቋቁሞ መቀጠል ከባድ ነው።
አባ እዮብ ግን ችለውበታል። ከጎናቸው መቆም የሚገባቸው ፈተና አምራች ሆኖ ከማየት በላይ ምን የሚገርም የታሪክ ድርሳን ይኖር ይሆን? በተለይ የትግራይ ብጹዓን አበው። ዝም የምለው ያላቸውን አውቃለሁ። ግን ያላቸው ለትውልድ መጠኑን #መከለል? ፈጣሪ ደንበርም ወሰንም ዞግም የለውም። ዕድሉን አስመልጠውታል። ጸሎት በህብረት፤ ሱባኤ በአህቲ ልቦና ማሸነፍ በመዳፍ በሆነ። በሌላ በኩል ምንም ቢሆን በፈተና ጊዜ ከአባት ጋር ከጎን የቆመ፤ ያገዘ፤ አይዞወት ያለ ብፁዑም ሊመረቅ በተገባ። የሥጋን ለሥጋውያን ትቶ መንፈሳውያን ነገረ መንፈስ ቅዱስን ቢከተሉ……… አባት ላይ በር #መዝጋት??? ሆድ እንዲብሳቸው ማድረግ። ጥግ፤ መጠለያ እንደሌላቸው ማሳጣት ማንን ጠቀመ???
ሌላው ለብፁወቅዱስ አባታችን የሚሰጠው የውስጥ አክብሮት ልዕልና ሁሉንም የመከፋት ዓይነት ንዶ በአንድ የሚያቆም ነበር። ካለምንም ቅድመ ሁኔታ። የዘመኑን ባህሬ አለመረዳት ያሳዝናል። በተለይ ኢትዮፎሮም ቁስል እየቀራረፈ ካለ ተሰጥዖው፤ ካለልኩ፤ ትልቅ እዮራዊ #ዩንቨርሳል አቅም ያላትን ተዋህዶ ልዕልና ጋር እየተዳፈረ መፋለሙ ውስጤን ያሳዝነዋል።
ግን አዘጋጆች የተዋህዶ ልጅነት ትርታ የለባቸውምን ብያለሁ። ዶሮ በጋን ነው የሚሆንብኝ። የሚገርመኝ እስር ቤት እያሉ የተከወነውን ወቅታዊ አጀንዳ ይሰጡታል። ስታዳምጡት የደከመ ሙት ባህር ላይ የከተመ ጉዳይ ነው። ፀጋው አላቸው። ምን ያደርጋል ጥሪ ካለቦታው ከሆነ። አድማጫቸው ደግሙ በርካታ ነው። ትውልድን በዚህ መልክ ማነጽ ነገን #ያጎፍረዋል።
የሆኖ ሆኖ በጥርስ የተያዘችው ያቺ #ብርክታዊት በዕት፣ ያቺ የሊቀ - ሊቃውንታት ዓውደ ምህረት #ጎንደር ቅዱስነታቸው ለትምህርት ወደ ጎንደር ከተማ ባቀኑበት ወቅት #ትንቢት ተነግሮላቸው ነበር ከሊቀ ሊቃውኑቱ መምህራቸው። "#እጬጌው #ይቅደም ተብሎ።" ያን ጊዜ ማንም ይህ ይሆናል ብሎ አላሰበውም ነበር። ትንቢቱ ተፈጸመ። የትንቢቱ #እጬጌም ትንቢቱን በክብሩ ልክ #ጠበቁት። ተመስገን። "#መንበሬን ለቅቄ የትም አልሄድም።"
ግልጡንም - ስውሩንም፣ ረቂቁንም - #ምርቁንም የፈተና ክምር ቅዱስነታቸው የሚያበርዱበት አቅም፤ የቅባው ልክ በልኩ ስለሆነ ነው ብዬ አምናለሁኝ። ስለዚህ አልናወጽም፣ አልወዛወዝም በጽናቴ እቀጥላለሁኝ። እግዚአብሄር አምላክ #በድንበር #በወሰን አይለካም እና።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
24/05/2025
ወስብኃት ለእግዚአብሄር። አሜን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ