ልጥፎች

ከኖቬምበር 4, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#አሜን። ዓለም የሰላም አንባ ትሆን ዘንድ የአሜሪካን ግሎባል ምርጫ እግዚአብሄር በሰላም ያስፈጽመው። አሜን።

ምስል
  #አሜን ። ዓለም የሰላም አንባ ትሆን ዘንድ የአሜሪካን ግሎባል ምርጫ እግዚአብሄር በሰላም ያስፈጽመው። አሜን።   "አድርገህልኛል እና ለዘላለም አመሰግንኃለሁ፦ በቅዱሳንህም ዘንድ፦ መልካም ነውና ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ " (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፶፩ ቁጥር፱ )   1) እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መልዕክት ይዞ ይወለዳል። 2) እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ ጥሪ ይዞ ይወለዳል። 3) እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት ወይንም ስጦታ ይዞ ይወለዳል። የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ ሮ ካሚላ ሃሪስ ( ኮሞላ ሃሪስም) ይህን አጣምረው ተወልደዋል ብዬ አምናለሁኝ። በእኛ አገር አባባል "ልጅ እና ጢስ መውጫው አይታወቅም" እንዲሉ።    ጤና ይስጥልኝ የማከብራችሁ ውድ ቤተሰቦቼ? እንዴት ሰነበታችሁልኝ? በበዛ #አርምሞ እና በሰከነ #ጥሞና ልንከታተለው የሚገባው ለእኔ ዓለም ዓቀፋ የኢትዮጵያ፤ የአፍሪካ ቀንድ፤ የመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ፤ የእስያ፥ የቻይና እና የታይዋን፤ የአህጉራችን የአፍሪካ፤ የእስራኤል- የጋዛ፤ የሊባኖስ - የኢራን፤ የራሽያ - የዩክሬን፤ የአውሮፓ ህብረት፤ የአፍሪካ ህብረት ጉዳይ፦ የአሜሪካዊው የ2024 የምርጫ ሂደት ጋር ህሊና ላለው የሰው ልጅ ሁሉ መንፈስን አንቅቶ ሊከታተለው የሚገባ ጉልላታዊ #ፒላር ጉዳይ ይመስለኛል። የአሜሪካ ጠቅላላ የታች እስከ ላይ የሚካሄደው ሥልጡን፤ የተደራጀ፤ በቅጡ ኮኦርድኔት የተደረገው የምርጫ ሂደት ጉዳዩ ለእኔ #ቅንጦት አይደለም። ብዙ ግሎባል የህይወት፤ የተፈጥሮ መስኮች ላይ ተጽዕኖም አሳዳሪ ነው።    ጉዳዩ #የጫጉላ የሙሽርነት ሽርሽር አይደለም። ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ እጦት ሙሉ 50 ዓመታት እንደምን ትውልዷ እዬታጨደ እንዳለ፤ ምን ያህል የኢትዮጵያ እናቶች ...