ልጥፎች

ከኖቬምበር 4, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ከብርት ፕሬዚዳንት ሳሀለ ወርቅ ዘወዴ ትውፊት ናቸው!

ምስል
መልካምነት ይበጃል። „ወደ ደጋግ ሰዎች የሚላኩ ሪቂቃን የሆኑ መላዕከት ብርሃን ናቸው።“ መጽሐፈ መቃብያ ከልዕ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፲ ከሥርጉተ©ሥላሴ 04.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                       ዋው! የኮ/ ጎሹ ወልዴ ክብር አከበርኩት። ምኞቴም ተሳካ ተመስገን! የጭብጤ መነሻ አሉታዊ ነገሮች አቅም ማግኘት አይገባቸውም ነው። ክፉ ነገር ይወረናል። ክፉ ነገር ይገዛናል። ክፉ ነገር ያሰተዳድረናል - ፈቅደንለት። ቀና በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንኳን ስምምነቱ ያን ያህል ነው። ታዲያ በዬት ታልፎ መልካም ነገሮች ሥር ይኑራቸው። ፍሬስ እንዴት ያፈሩ? መልካሞችን መልካም ለማለት ካልተደፈረ፤ መልካም ያልሆኑት መልካም አይደለም ማለት ካልቻልን ታዲያ እኛ ሰው መሆናችን ከምኑ ላይ ነው? እውነት ለመናገር አሉታዊ ነገር ወረራው መልካሞችን እንዳናይ ሸብቦናል። መለዬት አልቻልንም። በጣም ጥሩ የሆኑ መልካም ነገሮች ይታያል ኢትዮጵያ ውስጥ። እጅግ የሚመስጡ ጥሩ ነገሮች አሉ ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ፤ አሁን ሴቶችን የፖለቲካ ዕውቅና በመስጠት እረግድ ሉላዊ አብዮት በአብነት እዬተካሄደ ነው ልብ ላለው ልበ ህሊና ብርሃን ላለው፤ እነዚህ አቅም እንዲያገኙ፤ እንዲራቡ፤ እንዲበራከቱ መትጋት ቀርቶ ደግመን ደጋግመን ከክፉ ነገሮች ጋር ልውስውስ አድርገን ግርዶሽ ሰርተን፤ ዝንቅንቅ አድርገን መልካምነትን የተፈጠረበትን ቀን እንዲረግም እናደርገዋለን። ግን ስለምን? የሰው መለያው እኮ ክፉ እና ደጉን የሚለይበት ህሊና ስላለው ነው። ያ ህሊናው እንኳንስ መልካም ነገሮች እያሉ ወደ መልካም ነገር የሚወስዱ ጥሩ ዜናዎች፤ ውጥኖች፤ ጅምሮች፤ ፈሎች፤ ቀንበጥ ሃሳቦች እንኳን ሲኖሩ እነዛ ሃይል ብርታት አግኝተው የመልካም ነገሮች ቤተኛ