ልጥፎች

የአማራ ተጋድሎ ቀዳሚ ተግባር ለሰላም ዘብ መቆም ነው!

ምስል
የአማራ ተጋድሎ ቀዳሚ ተግባር ለክልሉ ህዝብ ሰላም ዘብ መቆም ነው። „አግዚአብሄርን የሚፈለግ ልብ ደስ ይበለው።“ መጽሐፈ መዋዕል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፲ 03.11.2-18 ከሥርጉተ©ሥላሴ ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አማራ ከዚህ መሪው ጎን መቆም ግድ ይለዋል።  ጦርነት አውዳሚ ነው። ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ ቢኖር አመድ እና ቂም በቀል  ብቻ   ነው። ቂም እና በቀል ደግሞ ለቀጣዩ ትውልድ ጸር ነው። ጥቂት ሰዎች  ለውጥ  አልመጣም ይላሉ። በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በቀና የሚዩት አንዳችም ነገር  አለመኖሩ ሰው ከምን ተሠራ እስከማለት እደርሳለሁኝ። ፍጹምነት ከሰው  መጠበቅ ዓይነት ነው። ግድፈት የለም ማለቴ አይደለም። ግድፈት ራሱ ሰውኛ   እንጂ ሮበትኛ አይደለም። ብቻ ሁሉንም ድፍጥጥ ሲያደርጉት የትኛው  ፕላኔት እንዳሉ ይገርመኛል።  እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ግን የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ ለውጤት የበቃ ነው  ባይ  ነኝ። ኮሽታ የማያሳማ፤ ዕወጁልኝ የማይል ለውጥ አለ። ቀውስ የለም ማለቴ  ግን አይደለም። የግርግር ሙሽሮች በእጃቸው የሰሩት ቀውስ አለ። ያው ሁሉ  የሥልጣን ጥመኛ አይደለ።  ያ ያው ሁሉ የቤተመንግሥት ቀይ ምንጣፍ ምኞተኛ አይደለምን? የአማራ የማንነት ህልውና ተጋድሎው መሰረታዊ ጥያቄዎች መፈታት ለመቻል  የሥርዓቱ አዋራሪሶች ከሥልጣነ ገብታቸው በስልት ማስነሳት ነበር የመጀመሪያው  ረድፈኛ ተግባር። ይህ በሚደንቅ ሁኔታ ተከናውኗል። ርዕዮቱም ቢሆን ሞራው  ነው ያለው። ይህ ስለተከናወነም በሁለቱ የአገር መሰረት ሃይማኖቶች ተፈጥሮ  የነበረው የ27 ዓመት ስንጥቅ ተገጥሟል። ተቋም ለሚበላው ከኦርቶዶክስ  ተዋህዶ እና ከእስልምና በላይ የሚኖሩት ለገሃድዋ ዓለም

ለመሆኑ አማራ እንደ ኢትዮጵያዊ ሙሉ ዜጋ ይታያልን?

ምስል
ዕውቅና ያልተሰጠው ችግር መፍትሄ ያገኛል  ብዬ አላስብም። „አቤቱ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፤ ችግረኛና ምስኪን ነኝና።“ መዝሙረ ዳዊት ፹፭ ፩ ከሥርጉተ© ሥላሴ ለመሆኑ አማራ እንደ ኢትዮጵያዊ ሙሉ ዜጋ ይታያልን?  ከጭምቷ ሲወዘርላንድ። ·        መነሻ። በመጀመሪያ ነገር በአማራ ፍልስፍና ላይ ጠ/ሚር አብይ አህመድ እምነቱም ፍላጎቱም የላቸውም። አማራ የሚለው መጠሪያ መስማትም አይፈልጉትም። ይህን ባህርዳር ላይ በቅኔ ተናግረውታል። እኛ አጠቃላዩን ስለምናይ ብቻ ነው ውስጣችን፤ ፍቅራችን፤ አክብሮታችን የምንሰጣቸው እንጂ በነገረ አማራ ያላቸው አቋም እጅግ ከረር ያለ ስለመሆኑ በተለያዬ ጊዜ በሚያደርጉት ንግግር ይገልጡታል። የሚገርመው በቀደመው ጊዜ እንዲያውም ተቆርቋሪነታቸው አመዝኖ ነበር የማዳምጣቸው። እጅግም የሚያሳሳ አቅም ነበራቸው። በአዲሱ ማንነታቸው ውስጥ ግን ልዩ ተልዕኮ የተሰጣቸው ያህል ፊት ሲነሱት ነው እኔ የምመለከታቸው።  ከውስጤ አላዝንም። ይህም ለበጎ ስለመሆኑ ስለማምንበት። አንድ ቀን እንደሚጸጽታቸውም ልብ ልክ ነው። የመጀመሪያ 6 ወር ሥራቸው ላይ በጫን ተደል የቤት ሥራ ክልሉን ሲያጣድፉት ነበር የባጁት። መተንፈሻ እስኪታጣ ድረስ። ሌላ ቦታ የማይሞክሩትን ሁሉ የለማ አብይ አካቢኔ የመሞከሪያ ጣቢያው ለሁሉም ነገር አማራ ክልል ላይ ብቻ ነበር። ይህም ሆኖ እንደ ሰውም አይተው ዕንባውን ለማድመጥ መፍቀድም የአባት። እኔ እንደማስበው እራሱ አዴፓ የሚበላውን ድርጅት ሥሙ ራሱ አሁን ከሆነ የሚመቻቸው አይመስለኝም። እነሱ እራሳቸው ከዞግ ድርጅት ወጥተው ያን ያህል የተንጠራሩ የኦሮሞ ሊሂቃንን ተሸከመው፤ እያባበሉ፤ እያቆላመጡ ሠርግና መልስ እያስደረጉ የራሳቸውን ወገኖች አማራ ግን አ