ልጥፎች

ከዲሴምበር 8, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

በተደራጀ ህሊና ታቅዶ እዬተከወነ ያለው መሳጭ ጥሞና።

ምስል
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ህሊና የታደመበት የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ተከበረ! „በሕይወትም እንድትኖር እንድትበዛም፣ አምላክህም  እግዚአብሄር ልትወርሳት በምትገባበት ምድር እንዲባርክህ አምላክህን እግዚአብሄርን ትወድድ ዘንድ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ ትእዛዙን ፍርዱን  ትፈጸም ዘንድ ዛሬ እኔ አዝዝሃለሁ።“ ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፴ ቁጥር ከ፲፮ እስከ ፲፯ ከሥርጉተቐ@ሥላሴ (Seregute@Selassie) 08.12.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዝ የ27 ዓመቱ የእርግጫ እና የልግጫ ዘመን እነሆ አፈሩን ፈጭቶ ሰኔሉን አዘጋጅቶ ቹቻውን ታጥቆ ዛሬ ወደ ቀብር ተላከ - ዛሬ። የዛሬ ዓመት የብሄረ ብሄረሰቦች ቀን በሰመራ ሲከበር „ስብስቆ“ በሚል ዕርእስ ጽፌ ነበር። ቃል በቃል እያዳመጥኩኝ ነበር የጻፍኩት ፈቃዱ ካላችሁ ይኸውና ኢትዮ ሬጅሰተር ላይ ታገኙታላችሁ። https://www.ethiopianregistrar.com/amharic/archives/42674 የጠቅላይ   ሚ / ር   ሀይለማርያም   ደሳለኝ   ስብስቆ December 9, 2017 ዛሬ ዕለቱ ደግሞ የወያኔ ልብ ተገጥሞለት የኖረው የአፋር ክልል የሊሂቃኑን ጉባኤ እያከሄደ አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ይገኛል። አሮጌን አውልቆ አዲስ መንፈስ ሊያጠልቅ መንገድ ጀምሯል። እንደ እኔ የመጀመሪያውን ሴት ሊሂቁን ወ/ሮ አይሻ መሀመድን ያደርጋል ብዬ አስባለሁኝ። ያለፈው ዓመት ሰመራ ላይ ሲከበር መከራው ጭነት ነበር … ዛሬ ደግሞ ጧፍ ሰማራ ላይ። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወፍ አላወጣውም፤ በለስ አልቀናውም በመውደቅ ላይ መውደቅ ተነባበረበት። ለነገሩ የየእጁም ነው የሰጠው። መሸነፍን እያቃተው ገርገጭ እያደረገው ነው። ዛሬ ወርቅ ቀን ነው ለነፃነት ፈላጊው። የ