በተደራጀ ህሊና ታቅዶ እዬተከወነ ያለው መሳጭ ጥሞና።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ
ህሊና የታደመበት የብሄር
ብሄረሰቦች ቀን ተከበረ!

„በሕይወትም እንድትኖር እንድትበዛም፣ አምላክህም
 እግዚአብሄር ልትወርሳት በምትገባበት ምድር
እንዲባርክህ አምላክህን እግዚአብሄርን ትወድድ
ዘንድ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ ትእዛዙን ፍርዱን
 ትፈጸም ዘንድ ዛሬ እኔ አዝዝሃለሁ።“

ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፴ ቁጥር ከ፲፮ እስከ ፲፯
ከሥርጉተቐ@ሥላሴ (Seregute@Selassie)
08.12.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዝ



የ27 ዓመቱ የእርግጫ እና የልግጫ ዘመን እነሆ አፈሩን ፈጭቶ ሰኔሉን አዘጋጅቶ ቹቻውን ታጥቆ ዛሬ ወደ ቀብር ተላከ - ዛሬ። የዛሬ ዓመት የብሄረ ብሄረሰቦች ቀን በሰመራ ሲከበር „ስብስቆ“ በሚል ዕርእስ ጽፌ ነበር። ቃል በቃል እያዳመጥኩኝ ነበር የጻፍኩት ፈቃዱ ካላችሁ ይኸውና ኢትዮ ሬጅሰተር ላይ ታገኙታላችሁ።

የጠቅላይ / ሀይለማርያም ደሳለኝ ስብስቆ
December 9, 2017

ዛሬ ዕለቱ ደግሞ የወያኔ ልብ ተገጥሞለት የኖረው የአፋር ክልል የሊሂቃኑን ጉባኤ እያከሄደ አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ይገኛል። አሮጌን አውልቆ አዲስ መንፈስ ሊያጠልቅ መንገድ ጀምሯል። እንደ እኔ የመጀመሪያውን ሴት ሊሂቁን ወ/ሮ አይሻ መሀመድን ያደርጋል ብዬ አስባለሁኝ። ያለፈው ዓመት ሰመራ ላይ ሲከበር መከራው ጭነት ነበር … ዛሬ ደግሞ ጧፍ ሰማራ ላይ። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወፍ አላወጣውም፤ በለስ አልቀናውም በመውደቅ ላይ መውደቅ ተነባበረበት። ለነገሩ የየእጁም ነው የሰጠው። መሸነፍን እያቃተው ገርገጭ እያደረገው ነው። ዛሬ ወርቅ ቀን ነው ለነፃነት ፈላጊው።


የዛሬ ዓመቱ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ተብዬውን ንግግሩን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሶፍት ዌር ሳጅን በረከት ስምዖን ነበር የጻፉት። እናላችሁ ተጽፎ ተሰጥቶ ማንበብ እንኳን አልቻል ብሎ ያን ያክል ጭንቅ በጭንቅ ላብ በላብ ነበር። ያ ውሃ ያዘለ የተራራ ሸከም ዘመን አልፎ እንሆ ትናንት ታዳጊዎች ከመሪያቸው ጋር በቤተ መንግሥት ዘና ብለው መከሩ። 

አዋቂዎች ደግሞ አዲስ አባባ ላይ እንደ አባት አደሩ ቡና ጠጡልኝ ሥርዓት ሲፈጸም ዛሬ ጥዋት አይቻለሁኝ በኢቲቢ፤ ኢቲቪም እንኳን ለዚህ አበቃህ ማለትን ፈለግሁኝ። ባትሪውን እንዲሁ በስብስቆ ለሚጨርስ።

አሁን ደግሞ የዕለቱን ጹሑፌን ለጥፌ እስኪ እጬጌው ዩቱብዬ የእኔ ሸበላ ምን አለ ከእጅህ ስልላችሁ ታላቅ የምሥራቸው ታየ። እነዛ በበጎ ፈቃድ ባህርዳር የዘመቱ የትግራይ ወጣቶች አንጀቴን በልተውኝ ነበር። አንድ ጡሁፍም ጥፌ ነበር። ዛሬም በአፈና ወጀብ በምትናጠው ትግራይ ያሉ ለዚህ ዕድል የበቁ የዚህ ደስታም ታጋሪ ናቸው። ምን እዬሆነ እንዳለ ካለማዕቀብ ያያሉ። „ነገር በዓይን ይገባል“ እንደሚሉት ጎንደሬዎች። በሙት መንፈስ ሽምጥ ላይ ያለው መንፈስ ሁሉ የዛሬን የወጣቶችን አብረው እንዲህ ፍልቅልቅ ብሎ ሲያ ከቶ ምን ይሰማው ይሆን?

የትግራይ ልጆች በዚህ ሥርዓት ላይ የታደሙት ማለቴ ነው በ27 ዓመት የቆዩበትን እስር ሰንሰለት፤ እግር በረት ማዖኢዝምን ዶግማ ቀብረው ከወንድም እህቶቻቸው ጋር እንንሆ በፍሰሃ በሐሴት ላይ ይገኛሉ።

ትንታጉ የአብይ መንፈስ ንድፉን በጥበብ እያስኬደው ነው። በተደራጀ፤ በቅጡ በታሰበብት፤ በውጉ በተሰናዳ ሁኔታ ልቅናው እንዲህ አጎመራ። ወጣቶች ደስ አላቸው። ተመስገን። አትራፊ ዝግጅትም ነው።

እንዴት ነፍሴን እንደ ገዛው ሁለመናቸው። በዚህ ውስጥ እናት አገር ኢትዮጵያ አለች። ሳትዛነፍ ተባደግ ሳትሆን ከእነ ሙሉ ክብሯ እና ማዕረጓ በሞገስ። እማ ኢትዮጵያም እንዲህ ልጆቿ ፈክተው ስታይ የእናት አንጀት ነውና ተመስገን ወደ እዮር ትልካለች። ወጣቶች ደስ አላቸው። ወጣቶች ሐሴት አደረጉ። ተመስገን!

Ethiopia: በአብይ ጊዜ የለም ትካዜ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ

https://www.youtube.com/watch?v=SlJPUz1dPRg



ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ዐህመድ ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የ1ኛ ደረጃ ተማሪዎች ጋር ቆይታ አድርገዋል

ኢትዮጵአዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።

ኑረሉልኝ! መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።