ከቢቢሲ BBC አሁን ያገኜሁት መረጃ ነው። ረሃብን ማሰር?
ከቢቢሲ አሁን ያገኜሁት መረጃ ነው። ረሃብን ማሰር? • ከቢቢሲ አሁን ያገኜሁት መረጃ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cn8zxd33d0xo «አንድ ሱዳናዊ ሐኪምን ጨምሮ ከ80 በላይ የጤና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ» «ከሰሞነኛው የጤና ባለሙያዎች ከፊል የሥራ ማቆም አድማ ጋር በተያያዘ በመላው አገሪቱ ከ80 በላይ የጤና ባለሙያዎች መታሰራቸውን የንቅናቄው አስተባባሪዎች አመለከቱ። የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተለይም በትላልቅ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የሚያገለግሉ በርካታ የጤና ባለሙያዎችን እያሰሩ እና እያወከቡ መሆኑን አንድ የንቅናቄው አስተባባሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከጎንደር ዩኒቨርስቲ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ከተወሰዱት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል አንድ ሱዳናዊ ሐኪም መኖሩን ባልደረቦቹ ለቢቢሲ ገልጸዋል። "ሐኪሞች፣ ነርሶች፣ ላብራቶሪ ባለሙያዎችን" ጨምሮ በርካታ የጤና ባለሙያዎች ለወከባ፣ ለድብደባ እና ለእስራት እንደተዳረጉ ገልፀዋል። የንቅናቄው አስተባባሪዎች ባሰባሰቡት መረጃ መሠረት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ባለሙያዎች መካከል ዘጠኙ ሴት የጤና ባለሙያዎች ናቸው። 'የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ' በሚል ስያሜ የደሞዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄን ጨምሮ የጤና ሥርዓቱን ያስተካክላሉ ያሏቸው 12 ጥያቄዎችን ያነሱ ባለሙያዎች፤ ከግንቦት 5/2017 ዓ.ም. ጀምሮ የከፊል የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸውን ገልፀዋል። ከዚሁ አድማ ጋር በተያያዘ አዲስ አበባ የሚገኙትን ጥቁር አንበሳ እና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎችን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በርካታ የጤና ባለሙያዎች ከሆስፒታል እና ከቤታቸው በፀጥታ ኃይሎች እየተወ...