ከቢቢሲ BBC አሁን ያገኜሁት መረጃ ነው። ረሃብን ማሰር?

 

ከቢቢሲ አሁን ያገኜሁት መረጃ ነው። ረሃብን ማሰር?
 
• ከቢቢሲ አሁን ያገኜሁት መረጃ ነው።
 
 
 
«አንድ ሱዳናዊ ሐኪምን ጨምሮ ከ80 በላይ የጤና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ»
«ከሰሞነኛው የጤና ባለሙያዎች ከፊል የሥራ ማቆም አድማ ጋር በተያያዘ በመላው አገሪቱ ከ80 በላይ የጤና ባለሙያዎች መታሰራቸውን የንቅናቄው አስተባባሪዎች አመለከቱ።
 
የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተለይም በትላልቅ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የሚያገለግሉ በርካታ የጤና ባለሙያዎችን እያሰሩ እና እያወከቡ መሆኑን አንድ የንቅናቄው አስተባባሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
 
ከጎንደር ዩኒቨርስቲ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ከተወሰዱት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል አንድ ሱዳናዊ ሐኪም መኖሩን ባልደረቦቹ ለቢቢሲ ገልጸዋል። 
 
"ሐኪሞች፣ ነርሶች፣ ላብራቶሪ ባለሙያዎችን" ጨምሮ በርካታ የጤና ባለሙያዎች ለወከባ፣ ለድብደባ እና ለእስራት እንደተዳረጉ ገልፀዋል።
የንቅናቄው አስተባባሪዎች ባሰባሰቡት መረጃ መሠረት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ባለሙያዎች መካከል ዘጠኙ ሴት የጤና ባለሙያዎች ናቸው።
'የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ' በሚል ስያሜ የደሞዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄን ጨምሮ የጤና ሥርዓቱን ያስተካክላሉ ያሏቸው 12 ጥያቄዎችን ያነሱ ባለሙያዎች፤ ከግንቦት 5/2017 ዓ.ም. ጀምሮ የከፊል የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸውን ገልፀዋል።
 
ከዚሁ አድማ ጋር በተያያዘ አዲስ አበባ የሚገኙትን ጥቁር አንበሳ እና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎችን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በርካታ የጤና ባለሙያዎች ከሆስፒታል እና ከቤታቸው በፀጥታ ኃይሎች እየተወሰዱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።
 
ከእነዚህም ውስጥ ለስፔሻላይዜሽን ትምህርት ወደ ዩኒቨርስቲው የመጣ ዶ/ር አብርሃም አፖኬ የተባለ ሱዳናዊ የማህፀን እና ፅንስ ሬዝደንት ሐኪም እንደሚገኝበትም ተናግረዋል።
 
"[ሆስፒታሉ] ግቢ ውስጥ በቅርብ አገልግሎት እንዲሰጡ በተሠሩ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ሐኪሞችን ነው ጠራርገው ያሰሯቸው" ብለዋል ከእስር የተረፉ የሕክምና ባለሙያዎች።
 
አንድ የጎንደር ሆስፒታል ዶክተር ለቢቢሲ እንደተናገሩት የፀጥታ ኃይሎቹ በምሽት ወደ ሐኪሞች መኖሪያ በመግባት በኃይል እና በማንገላታት ባልደረቦቻቸውን በተሽከርካሪ ጭነው መውሰዳቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
 
እስሮች የባለሙያዎችን 'ክብር እና ሰብዓዊነት' በሚነካ መልኩ መፈፀሙን የተናገሩት አስተባባሪው፤ የጤና ባለሙያዎችን "ለማሸማቀቅ" ሆስፒታሎች በፀጥታ ኃይሎች ተከበዋል ብለዋል።
 
በሆስፒታሎች ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የጤና ባለሙያዎችም መታሰራቸውን የጠቆሙት አስተባባሪው፤ አገልግሎቶች መቋረጣቸውን በመጠቆም "ከዚህ በኋላ ሊመጣ የሚችለው ቀውስ ግልፅ ነው" በማለት አስጠንቅቀዋል።
 
"በዚህ ሁኔታ ችግሮች ይባባሰሉ" ሲሉ የመንግሥትን እርምጃ የተቹት የንቅናቄው አስተባባሪ፤ ከመንግሥት የተሰጣቸውን ምላሽ "የንቀት" እና "መንግሥት ነኝ ከሚል የማይጠበቅ" ሲሉ ገልፀውታል።
 
"በይፋ እየደበደበ፣ ክብራቸውን የሚነኩ ንግግሮችን እየተናገረ ከፍተኛ ዛቻ እና ኃይልተከለበት ማስፈራሪያ እየፈጸመ ያለው መንግሥት ነው" ብለዋል።
 
ቢቢሲ የተመለከተው እና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ የሕክምና ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ የጤና ባለሙያዎች ስም ዝርዝር አስከ አርብ ከሰዓት በኋላ ድረስ 81 መድረሱን ያመለክታል።
 
ዝርዝሩ የታሰሩ የሕክምና ባለሙያዎችን ሙሉ ስም፣ የሚሠሩባቸውን የጤና ተቋማት፣ የሙያ ዘርፋቸውን፣ የተያዙበትን ዕለት እንዲሁም ያሉበትን ክልል ይዟል።
 
ከፊል የሥራ ማቆም አድማው ከተጀመተበት ከማክሰኞ ግንቦት 5/2017 ዓ.ም. ጀምሮ የጤና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ቢሆንም ከመንግሥት በኩል ይህንን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም። 
 
ትናንት ሐሙስ ምሽት መግለጫ ያወጣው ጤና ሚኒስቴር የከፊል ሥራ ማቆም አድማውን "ተቀባይነት የሌለው" ብሎታል።
ሚኒስቴሩ እንቅስቃሴውን "በሆደ ሰፊነት" ሲያየው መቆየቱን በመጠቆም፤ በሥራ ገበታቸው ላይ በማይገኙ እና "ሁከት እና ብጥብጥ በሚፈጥሩት" የጤና ባለሙያዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል።
 
ይህን ሚኒስቴሩን መግለጫ የንቅናቄው አስተባባሪዎች "ያልጠበቅነው" እና "ፖለቲካዊ መልክ የያዘ" ብለውታል።
ባፉት ቀናት በርካታ ሆስፒታሎች በሥራ ላይ የማይገኙ ባለሙያዎች ላይ "አስተዳዳራዊ እርምጃ" እንደሚወስዱ ማስጠንቀቂያዎችን ያወጡ ሲሆን፤ ሬዝደንት ሐኪሞች ደግሞ የሕክምና ኮሌጆች ከሚያቀርቡት "መኖሪያ ቤት" ለቀው እንዲወጡ አሳውቃል።
 
'የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ' አስተባባሪዎች ከመንግሥት አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘታቸው ሙሉ ለሙሉ የሥራ ማቆም አድማ ከሰኞ ጀምሮ ለመምታት የያዙትን አቅድ እንደሚገፉበት ለቢቢሲ ተናግረዋል።»
 
«ባለፉት ቀናት 15 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች መታሰራቸውን የንቅናቄው አስተባባሪዎች ተናገሩ»
 
«ከጤና ባለሙያዎች የከፊል የሥራ ማቆም አድማ መምታት ጋር በተያያዘ 15 የሚሆኑ ባለሙያዎች በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የንቅናቄው አስተባባሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
 
የደሞዝ እና የጥቅማ ጥቅምን ጨምሮ የጤና ሥርዓቱ እንዲስተካከል ጥያቄ ያቀረቡት የጤና ባለሙያዎች፤ የንቅናቄው "መሪዎች" ናችሁ የተባሉ በርካታ ባለሙያዎች "በመላው አገሪቱ" እየታሰሩ እና ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው እንደሆነ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አስተባባሪዎች ገልፀዋል።
 
ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንትን ጨምሮ በርካታ ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ መንግሥት የጤና ባለሙያዎችን "የዳቦ ጥያቄ" ከመመለስ ይልቅ "አፈና እና ወከባ" እያደረገ ነው ብለዋል።
 
እየታሰሩ ያሉት ባለሙያዎች በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች ድንገተኛ ክፍልን ጨምሮ አገልግሎት እየሰጡ የነበሩ "ጋዎን የለበሱ" ባለሙያዎች መሆናቸውን አንድ አስተባባሪ ተናግረዋል።
 
የጥቁር አንበሳ እና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ባለሙያዎችን ጨምሮ፣ የፈለገ ሕይወት፣ የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል፣ የለኩ ሆስፒታል (ሲዳማ ክልል)፣ የጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ አዲስ ዓለም፣ ነፋስ መውጫ ሆስፒታሎች ባለሙያዎች መታሰራቸውን ገልፀዋል።»

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?