ልጥፎች

ከኦክቶበር 16, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አይበገሬው! የቁም ነገር አባት።

  አይበገሬው! የቁም ነገር አባት።    «አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።» አሜን።   "Kenya Mourns as Trailblazing Leader Raila Odinga Dies at 80 – LCCTV Uganda" https://lcctvuganda.com/kenya-mourns-as-trailblazing.../   አይበገሬው! አፍሪካዊ ፖለቲከኛ የጽናት መሠረትን ጥለው ታግለው የማያሸንፋት ሞት ወሰዳቸው። ይህን የመሰለ የሰላማዊ ትግል አብነት ለኬንያ ቀጣይ ትውልድ ተቋሙ ይሆን ዘንድ እመኝለታለሁኝ። ለእማማ አፍሪካም። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊቃናት ይህን ከመሰለ የአይበገሬነት ተምሳሌት ምን ይማሩ ይሆን?   ጥንካሬ፤ ብርታት፤ የተዛባ ሥርአትን በፍርድ ሂደት ውስጥ አስገብቶ መርታት እጹብ ድንቅ ትንግርት ነው። ይህ አርያነት ለመላ አፍሪካ ትምህርት ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው። የማይታየው ረቂቅ አይበገሬው መንፈስ የኬንያ ወጣቶች ስለመብታቸው በሚያደርጉት ደፋር ሰላማዊ ተጋድሎ በዘመናችን ተመልክተናል።    የኬኒያ ወጣቶች አብነታቸውን መራራ ሞት ቢቀማቸውም መሠረቱ ስለተገነባ ሃዘናቸውን ማመጣጠን ይችላሉ። በመጨረሻም ለመላ የኬኒያ ህዝብ፤ ለዲሞክራሲ ለሚታገሉ የነፃነት ፋናወች፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እመኛለሁኝ። ክቡር ሆይ ያባከኑት ቅንጣት ጊዜ የለም። ዕድለኛም ነወት የድካመወን ሰብል አይተዋል። በሰላም ይረፋ። አሜን።   ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 16.10.2025 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።   “Nairobi, Kenya — October 15, 2025 — A subdued yet searing sorrow has spread across Kenya and beyond today with the news that Raila...