ገዱ ደጉ ፈሪህ ተበራከተ ስለምን ይሆን?
እንኳን ደህና መጡልኝ። ገዱ ደጉ ፈሪህ ተበራከተ ስለምን ይሆን? „በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሳ ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ።“ መዝሙር ፲፯ ቁጥር ፲፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ፈጣሪ አለ! ፍርድና ዳኝነቱን ይሰጣል! · በጣም ልክ ያጡ ነገሮች ነው ያሉት በስክነት ይፈተሹ። የዶር ገዱ አንዳርጋቸው ድንገተኛ ከሥልጣን መነሳት ከሰበር ዜናው ቀጥሎ ፍተሻ ይደረግለት። ብልቱ ሆነ ብሎኖ ተፈታቶ። የዶር ገዱ አንርጋቸው ከሥልጣን መነሳት የኦዴፓ የዛሬ ዕቅዱ አልነበረም። የአቶ ደመቀ መኮነንም ከሥልጣን ለማንሳትም ሰፊ ጥረት አድርጎ ነበር በመሰከረሙ የብአዴን ጉባኤ። ብዙም ጽፌበታለሁኝ። የብአዴን ጉባኤተኛው ሞግዶ አሻም ብሎ ሁሉም በወገን ወገኑ ተመካክሮ ተጠናክሮ ስለመጎተ ተግ አለ። ዋነኛው የኦዴፓ ተግባር እነሱን ሁለቱን ማስወገድ ነበር ትልሙ። እንዳሻው አማራ ክልልን ሰጥ ለጥ አድርጎ በጃዋርውያን ቅኝ ለማድረግ። ለዚህ ደግሞ አባ ገዳ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ታጥቀው የተነሱበት ጉዳይ ነበር። ያን ጊዜ ሳይሳካ ሲቀር በሌላ ስበሰባ እሳቸው በምክትል መስተዳድር ማዕረግ የምንትሶ የቢሮ ሃላፊ ሆኑ። አሁን ሄደው ከቁንጪ ላይ ወጥተዋል ጃዋርውያኑ አቶ ንጉሱ ጥላሁን። ለለውጡ በሉት ለኢትዮጵያ ትልቁ ደራጎን እሳቸው ናቸው። ሌላው ዶር አንባቸው ነበሩ ከፖለቲካ ውሳኔ ገለል ለማድረግ የተፈለገው በመስከረም ወር። እሳቸውን ፕሬዚዳንት ለማድረግ ኦዴፓ ያቀረበው ጥያቄም ውድቅ ሆነበት። እናም ተነሳፋፊ አድርጎ አጃቢ አድርጎ ባጀ። አሁን አገር ሰላም ሲሆን የብአዴን ጉባኤተ...