ሁለተኛው የአቶ ጃዋር ቦንብ አዋሳ ላይ የደህዴን ዓርማ አቃጠለ።



እንኳን ደህና መጡልኝ።
ሁለተኛው የአቶ ጃዋር ቦንብ
አዋሳ ላይ የደህዴን ዓርማ ተቃጠለ።
„አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል?
በተቀደሰው ተራራህስ ማን ይኖራል?“
መዝሙር ፲፬ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።



Ethiopian info || አሳፋሪ ድርጊት || ኤጄቶ ባለስልጣን ደበደበ || ባለስልጣናቱ ሸሽተው አመለጡ ||



አሁን ደግሞ አዲስ ዜና አለ። የ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በ እጅጉ የሚያስለፈልግ ይመስለኛል። የአቶ ሌንጮ ለታ የሲዳማ ምክክር እርገት ይኸው ነው። ኤጄቶ የሚባለው የሲዳማ ወጣት ማህበር የደህዲን መለያ ዓርማ አውርዶ ማቀጠሉን እና ድብደባም በአመራሩ ላይ እንደተፈጸመ ትኩስ የትኩስ መረጃ ኢትዩብ አሁን ገልጧል።  

ሲዳማ የተሄደው ጅጅጋ ላይ ያሰቡት ስላልተሳካላቸው ነው። በጫና አቶ ሙስጡፋ ኡመርን ለማወርድ ታስቦ ነበር። ግን አልተሰካም። ትልቁ ኢላማቸው ያ ቦታ ነበር … የጠ/ሚሩ የስሜን አሜሪካ ጉዞ መልስ እንዳሳኩት በዛው ለመቀጠል ሰፊ ድርጅታዊ ተግባር ነበር … የሆነ ሆኖ ያ ለከፍተኛ ንደት የተሳካው ቦታ አልሳካ ሲል ወደ ሲዳማ ተዛወሩ።

በሌላ በኩል ጎንደርን 100 ሺህ ወገንን በማፈናቀል ሲያሳምስ የባጀው በጃዋርውያን የንስሃ አባት በቅማንት ስም የተደራጀው አሸባሪ ቡድን ጎንደር ከተማ ላይ መሰሉን እንዳይፈጽም ብርቱ ጥንቃቄ ቢደርግም መልካም ነው። መፈንቅለ መንፈሱን በስውር ሲቆጣጠር የባጀው ቡድን አይሁን ይፋ የሆነው የጥቃት ዘመቻውን በሁሉም አቅጣጫ ጀምሯል።

አብሶ የአማራ ወጣቶች ይህን ጉዳይ በጥንቃቄ መከታተል ሲኖርባቸው አካባቢያቸውን እና ክልላቸውን እንደ ነፍሳቸው የመጠበቅ ግዴታ ይኖርባቸዋል። ነገረ ሲዳማ መርዝ ለመነስነስ ከዚህ ቀደም አቶ ሌንጮ ለታ ወደዛ ሲሄዱ ማስታወሴ ይታወቃል።

አሁን በቀጥታ የማጥቃት እርምጃ እዬተወሰደ ነው አዋሳ ላይ። በሌላ በኩል በጠ/ሚር አብይ አህመድ ላይ ማዕትና ምህረት የምታፈሱ አክቲቢስቶች ተግ ብትሉ መልካም ነው። እሳቸው እራሳቸውን በህይወት እንዳይቀጥሉ በስፋት እዬተሠራበት ነው ያለው። እሳቸውን ከስልጣን ማውረድ ነው የዚህ ቡድን ተልዕኮ። ሊሞቱላቸው ስላልቻሉ። ለዚህ እኮ ነው ጃዋርውያኑ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የፕሬስ ሰክሬታሪ ሆነው የተመረጡት።

 ለአክቲቢስቶች ማስገንዘብ በትህትና የምፈልገው በምንም መስፈርት አቶ ጃዋርን እና ጠ/ሚር አብይ አህመድ የሚያገናኛቸው አንዳችም መስመር የለም ኦሮሞ ከመሆናቸው ውጪ።  በሰብዕና እራሱ ምን እና ምን ይገናኛሉ። ለደቂቃ ቁጭ ብለው በቋንቋም መግባባት አይችሉም። የሚያሳብደውም እኮ ይሄ ነው የጠበቀው ክብር እና ተደማጭነት በሳቸው ዘንድ አለማግኘቱ።

ስለሆነም ቅኖቹ … እስኪ አደብ ግዙ እና ፍዳቸውን በወቃሳ እምታጣድፏቸው ጠ/ሚር አብይን በሚመለከት አቶ ጃዋር ምን ምልከታ እንዳለው ይህን ቃለ ምልልስ አዳምጡት ….ሰብ አድርጎ እንኳን አይቀርጻቸውም። ከሰው ተራ ነው የሚያወርዳቸው ... 

ሕወሓት ለማ መገርሳን ለጠቅላይ ሚኒስተርነት ለምን አልፈለገችውም?– ጀዋር መሐመድ ያብራራል | ከሳዲቅ አህመድ ጋር ተወያይቷል


እነሱ ጠባቸው ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ጋር ነው። ስለዚህ በምንም መስፈርት ኦነጋውያን ከጠ/ሚር አብይ መንፈስ ጋር የሚያገናኛቸው አንዳችም ነገር የለም ኦሮሞ ከመሆናቸው በስተቀር። እስካሁን ችለው ያቆዩት ስንት የታመቀ ነገር አለ። ግድያው በመርዝ እኮ ትክክል ነው የነበረው „አክ“ ወሬ ተብሎ የተስተባበለው። እገታውም ትክክል ነው። በመቻል የያዙት ብዙ ነገር አለ።

እና ሲጀመርም የጠ/ሚር አብይ አህመድን አቅም የፈሩ ሃይሎች አሁን በሁሉም መስክ እዬተፈታተኗቸው ነው ያለው። ስለምን? ኦህዴድ እዬተዝረከረከ ስለሆነ። ኦህዴድ ራሱን ችሎ መቆም ተስኖታል። እጁን ለፌስ ቡክ አርበኞች እዬሰጠ ነው። 

እንግዲህ እምንጠብቀው የክልሉ መስተዳደር አቶ ጃዋር ሲሆን ማዬት ነው። ዶር ለማ መገርሳ ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር። አሁን ትናንት ኦዴፓ ባሳናዳው ሰልፍ እራሱን ገለጻ በመግለጫው። የራሱ ተወካይ አዲስ አባባ ላይ የፈጸመውን አውግዞ ተነሳ - ኦዴፓ።

ምክትል ከንቲባው እኮ የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ናቸው። በሌላ በኩል ብትኩ ጉዳይ መግላጫው አዲስ አባባ የኔ ናት እያለ ወሰን ይከለልኝ ደግሞ ይላል፤ በነገራችን ላይ ከ5 የኦሮሞ ድርጅቶች መግለጫ ውስጥም ኦዴፓ ነበረበት። 

በሁሉም ቀውሶች ላይ እጁ ድርጅቱ ስለተነከረ ነው ፍትህ ዘብጣ እምትታዬው። እሱ ራሱ ያሳናዳቸው ናቸው በሁሉም መስክ ግድያውንም፤ ቀውሱንም የሚያደራጁለት። ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን የጠ/ሚሩ ቅቡልነት ቅናት ነው እንዲህ የሚያሳብዳቸው።   

አሁን በሁሉም መስክ ወጥረው ኢትዮጵያን የማፈረስ ተልዕኮ ነው እዬተራመደ ያለው። የታፈነው ወንጀል ታፍኖ፤ የታመቀው ሴራ ታምቆ የራስ ነገር ስለነበር። አሁን ለይቶለታል፤ ለነገሩ ካልጎሼ አይጠራም። 

ነገር ግን በመደናገጥ፤ በመርበትበት፤ በመዘናጋት ሳይሆን እንክርዳድ እና ስንዴን ለይቶ ከስንዴ ጎን አብሮ በጽናት በመቆም መጪውን መከራ መጋፈጥ ይገባል።

ይህ በማጥቃት ላይ ያለው ሽበርተኛ ቡድን በቀጥታ በሽብር የተሸረበ እሬት እና ኮሶ ነው ይዞ የተነሳው ሲፈጠርም። ስለዚህ የኤርትራ መንግሥትም ሌሎች የአፍሪካ አገራትም ቢሆንም ሁሎችም በንቃት ሊከታተሉት ይገባል። 

አብሶ የጠ/ሚር ቢሮ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ እጅግ የሚያሰጋ ነገር ነው ያለው። ይፋዊ ኩዴታ ሁሉ አደራጅተዋል ብዬ ነው እኔ እማስበው። ስውሩ መንግሥት እራሱን ጠ/ሚር አድርጎ የሚሾምበት ሂደት ነው የሚጠበቀው። በልክ አላደረጉትም አጣዳፋቸው?

 መጥፊያቸው ሊሆን ይሆን? ልቅምቅም አድርጎ እስር ቤት ቢያስገቧቸው ምን ሊሆኑ ነው?
የሆነ ሆኖ አገር ከጠፋ በሆዋላ ሳይሆን ከመጥፋቱ በፊት ነው ባሊህ ሊባል የሚገባው። አቅምን አሰባስቦ ጠ/ሚር አብይን ማገዝ ግድ ይላል። 

ይሻላቸዋል ተብሎ ያሉት ሁሉ ተደርጎላቸዋል። እነሱ ግን አይረኩም፤ አይጠግቡም። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጎረቤት ለጎረቤት አገር ሲሄዱ እነ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በለመደባቸው እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ስሜን አሜሪካ ሲሄዱ ደንብያን እና ጭልጋን ቤንዝን እና ጭድ አሰናድተው እንደጠበቁት እዛው ማዕከላዊ ላይም ቢሆን የሚፈነዳ ነገር ይኖራል ብዬ አስባለሁኝ።

ኢትዮጵያ ሸንፈቷም፤ ድህነቷም፤ መከራውም በውስጥ ባንዶች ነውና። አብሶ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅንነት መከራ አምራች ነው። ግልጽነት ፍዳን ፈልፋይ ነው። ተቆርቋሪነት ግማድ መሸከም ነው። አሁን እኔ እንደማስበው ተሸፍኖ የኖረው ነገር ሁሉ ፈንድቶ የሚለይለት ጊዜ ላይ ያለን ይመስለኛል። በህልሜ ያዬሁት ወንበር ባዶነቱ ይቀጥላል ወይ ደግሞ ሙሉ ስልጣኑ ተሟልቶለት በኮንፊደንስ ይቀጥላል።

ለነገሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፤ የደህንነት አካል፤ የፖሊስ ሠራዊት ከዬትኛው ወገን እንደሚሰለፍ ድንግል ትወቀው። ምዕራባውያን አውሮፓውያን ከአብይ መንፈስ ጎን እንደሚቆሙ እጠብቃለሁኝ። ያ ገራገር ኢትዮጵያዊ በነገርኩት ጊዜ ሐምሌ ላይ ይህን የሎቢ ተግባር በጥንቃቄ ፈጽሞ ቢሆን ይህ ሁሉ ጥቃት አይፈጸመም ነበር። ይህን ያህልም የልብ ልብ እነሱም አያገኙም ነበር።

ለነገሩ እነሱ ለቁርስ ሲያስቡ ወይ ሌላ ሃይል ያልታሰበ ዱብ ብሎ መጥቶ ሁሉንም አመድ ሊያደርግ ይችል ይሆናል። ማን ያውቃል። ጥጋበኞችንም አስተንፍሶ ጸጥ ለጥ አድርጎ ህግን ያስጠብቃል።

ታስታውሳላችሁ እኔ ሀምሌ ላይ ግንቦት 7 እራሱን ኢሳትን እንዳትሄዱ እያልኩ ስጽፍ ነበር። ያ የቆሞስ ስመኘው በቀለ ሞት ትልቅ ደወል ነበር። ግን ሰሚ አልተገኘም። አሁን እያሳበዳቸው ያለው የኢሳት አገር መግባት ነው። 

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

ማመሸቢያ ጊዜ።
ኑሩልኝ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።