ገዱ ደጉ ፈሪህ ተበራከተ ስለምን ይሆን?
እንኳን
ደህና
መጡልኝ።
ገዱ
ደጉ ፈሪህ ተበራከተ
ስለምን
ይሆን?
„በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሳ
ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ።“
መዝሙር ፲፯ ቁጥር ፲፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።
ፈጣሪ አለ! ፍርድና ዳኝነቱን ይሰጣል!
· በጣም ልክ ያጡ ነገሮች ነው ያሉት በስክነት ይፈተሹ።
የዶር ገዱ አንዳርጋቸው ድንገተኛ ከሥልጣን መነሳት ከሰበር ዜናው ቀጥሎ ፍተሻ ይደረግለት።
ብልቱ ሆነ ብሎኖ ተፈታቶ። የዶር ገዱ አንርጋቸው ከሥልጣን መነሳት የኦዴፓ የዛሬ ዕቅዱ አልነበረም።
የአቶ ደመቀ መኮነንም ከሥልጣን ለማንሳትም ሰፊ ጥረት አድርጎ ነበር በመሰከረሙ የብአዴን ጉባኤ። ብዙም ጽፌበታለሁኝ።
የብአዴን ጉባኤተኛው ሞግዶ አሻም ብሎ ሁሉም በወገን ወገኑ ተመካክሮ ተጠናክሮ ስለመጎተ
ተግ አለ። ዋነኛው የኦዴፓ ተግባር እነሱን ሁለቱን ማስወገድ ነበር ትልሙ። እንዳሻው አማራ ክልልን ሰጥ ለጥ አድርጎ በጃዋርውያን
ቅኝ ለማድረግ።
ለዚህ ደግሞ አባ ገዳ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ታጥቀው የተነሱበት ጉዳይ ነበር። ያን ጊዜ
ሳይሳካ ሲቀር በሌላ ስበሰባ እሳቸው በምክትል መስተዳድር ማዕረግ የምንትሶ የቢሮ ሃላፊ ሆኑ። አሁን ሄደው ከቁንጪ ላይ ወጥተዋል
ጃዋርውያኑ አቶ ንጉሱ ጥላሁን። ለለውጡ በሉት ለኢትዮጵያ ትልቁ ደራጎን እሳቸው ናቸው።
ሌላው ዶር አንባቸው ነበሩ ከፖለቲካ ውሳኔ ገለል ለማድረግ የተፈለገው በመስከረም ወር።
እሳቸውን ፕሬዚዳንት ለማድረግ ኦዴፓ ያቀረበው ጥያቄም ውድቅ ሆነበት። እናም ተነሳፋፊ አድርጎ አጃቢ አድርጎ ባጀ። አሁን አገር
ሰላም ሲሆን የብአዴን ጉባኤተኛው በሌለበት፤ ወሬው ተከድኖ ዶር ገዱ አንዳረጋቸው በግፍ እንዲነሱ ተደረገ። እሳቸው ጠይቀው አይደለም። በድርጅታዊ ሥራ ግዳጅ ተሰጥቷቸው ነው።
ይህ ደግሞ ለህወሃት ዝቀሽ ድል ነው።
ለጃዋርውያዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁንም ትንሳኤ። ዛሬ
የህውሃት እና የጃዋርውያኑ የአቶ ንጉሡ ጥላሁን የዋንጫ ቀን ነው። ድንጋጤው ነው ዶር አብይ አህመድን ከዛ ያስኬዳቸው። እሳቸው
መብታቸው ከጠላፊው ቡድን የሚሰጣቸውን ማናቸውንም ትእዛዝ ኮሽታ ሳያሰሙ፤ ሚስጢር
ሳያወጡ መፈጸም ማስፈጸም ነው። ይህን የውስጥ ለውስጥ ድርድር ም/ክ/ጠ/ሚር አቶ ደመቀ መኮነን በግልጥነት ያውቁታል ብዬ አላስብም።
ሌላው ተፈሪ ወጣቱ ፖለቲከኛ እርጉው አቶ ምግባሩ ከበደ
ናቸው። እሳቸውም የብአዴን
ጽ/ቤት ሃላፊ ነበሩ። አልተወደደላቸውም በተደጋጋሚ በአዲስ አባባ ጉዳይ የሰጡት መግለጫ፤ አሁን የክልሉ አቃቢ ህግ ተደርገዋል ይህ
ምክትል ምንትሶ የሚሉት ለማስታገሻ እንደ አሞሌ ጨው እዩት።
ይህን ምደባ የሚሠራው የጀዋርውያን ቡድን ነው፤ በአቶ ንጉሱ ጥላሁን አማካኝነት። አሁን እሳቸው አቶ ንጉሡ ጥላሁን በሚችሉት
መልክ ቦውዘውታል። የቀረው ደግሞ ቀስ እዬተባለ ቦታውን ከምርጫው በፊት ይይዛል።
በቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው ህልፈት ማግሥት ጠ/ሚር አብይ አህመድ እገታ ላይ በነበሩበት
ወቅት እንዲህ ባልተደመደ ሁኔታ ብአዴን ስብሰባ ተገኝተው ለቅሶ ደርሰው ነበር። አስታውሱትንም?
ከውስጣቸው እዝን ብለው ነበር የተገኙት - ዛሬም። ጥዋት እርር ኩምትር እንዳሉ ነው
ምሽት ላይ ባህርዳር ደግሞ የተገኙት። አቶ ንጉሡ ጥላሁን ግን አልተገኙም። እሳቸው መድፉን ያቀባብሉና የሉም በቦታው።
ደንብያና ጭልጋ ቤንዚን እና ክብሪቱን አሰናድተው ሲያረጋግጡ ክልሉን ለቀው ጠ/ሚር
ቢሮ ላይ ነበሩ። በነገራችን ላይ የቅማንት ተወካይ ነን የሚሉትንም ከOMN ጋር የሚያገናኙ እሳቸው ናቸው። ሚዲያው ምንም አክሰስ የለውም እነሱን ለማግኘት።
ለዚህ ነው አማራ አቶ በረከት ስምዖን ሲገላገል አቶ ንጉሡን ግዙፍ መከራ ቻል ተብሎ ነው የምለው።
ዛሬም ጥዋት የዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ሲከበር የኢትዮጵያን ሴቶች እርዱኝ የሚል
ተማህጽኖ አቅርበው ነበር ጠ/ሚር አብይ አህመድ። ማምሻ ላይ ደግሞ
ለአሸኛኜት ድርጊቱ ኢፍትሃዊ ስለሆነ ለማስተዛዘኛ ባህርዳር ም/ጠ/ ሚ/ር አቶ ደመቀ መኮነን
ተገኝተዋል። እኛም ተከታይ ነን ሲሉ አዋዝተው አቶ ደመቀ መኮነን
ተናገረዋል። ቀኑ መቼ እንደሆን አልታወቀም፤ ጠ/ሚር አብይም አህመድም ደግመውታል።
አዳሜ ለውጥ አለ ይላል። እርግጥ ነው የማይገመቱ ለውጦችን አይተናል ነገር ግን የለውጡ አቅም ሙሴውን እኛ በምንደገፍው ልክ ለኦነጋውያን ለኦርምያ አገራዊነት
እዬዋለ ስለመሆኑ ማንም ልብ ብሎ አያስተውለውም።
አማራ እዬተማራ ያለው በጃዋርውያን መንፈስ ነው። ወንድ ቢሆን ብአዴን በዚህ ስብሰባ አቶ ንጉሡ ጥላሁን አውርዶ የጃዋርውያን ኦዴፓም እንጥሽት ውሃውን
ማፍሰስ ነበር። ግን አቅም የለም። ሰጥ ለጥ ብሎ በተጨማሪ የቤት ስራ ትክሻን አሰናድቶ መገዛት ነው እንደለመደበት።
እግረ መንገዳቸውን አንዲት ነገር ሹክ ብለዋል ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንኳን ደስ አለህ
ይሁን ምን አይታወቀም ዶር ደብረጽዮን ደስታቸውን ያውራርዱ ዘንድ ደውለው እንደ ጋበዟቸው እና እንዳልቻሉ ጠቁመውናል። የሌሉቹ ማሟያ
ነገር ነው።
ጠረኑን ስታስቡት ያ ጠላፊ ቡድን ጉዞው እዬተሳከለት ይመስላል። አማራ ላይ በስፋት ተሳክቶለታል። ግን ሳያስጠጣ ነው በስል ገብቶ ሥራውን አቶ ጀዋር መሃመድ ክልሉን እንዲቆጣጠር
እዬተደረገ ያለው።
የዚህ ጉድ መካተቻው ደግሞ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው። እርግጥ ነው እንደ ቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው ህይወታቸው ሳያልፍ መገላገላቸው ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ቢያስደስተኝም ጥቃቱ ደግሞ የመላ
አማራ ህዝብ ነው። ተቀልዷል!
ዶር አንባቸው መኮንን በሚመለከት ታዝኖለት አይደለም ይህ ቦታ እንዲይዝ የተደረገው።
እሱም ተረኛ ነው። አሁን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቦታው ክፍት ሲሆን በቀጥታ ዶር አንባቸው መኮነን ይመለከታል። አማራ ጥያቄውን ያነሳል።
ነገር ግን ይህ እንዳይመጣ ኮሽ ሳያደርጉ ጀዋርውያን ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር በተለዬ
ድርድር እራሳቸውን ከሥልጣን እንዲያገሉ ተደርጎ ነገ ለሚመጣው ማዕበል ለመሰናዳት ዶር አንባቸው መኮነን
የክልሉ መስተዳደር ፕሬዚዳንት አድርገው ሾመዋል። ምክንያቱም ውጭ ጉዳዩን ለአቶ ለማ መገርሳ ወይንም እሳቸው ለፈቀዱት ሰው ለመስጠት። ይህም ሌላ
መሰናዶ አለበት።
በሌላ በኩል አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ከለወጥ ሐዋርያነት
ታሪክም ለማስገለል ሰፊ ሴራ ነው የባጀው።
ስለምን ሲባል ያው በውስጣቸው ታቁሮ ያለው የአማራ ጥላቻ ነው።
አማራ ሁልጊዜ የሚፈለገው ለማሸጋገሪያ ድልድይነት ነው። መቼም እኔ በዕድሜዬ እንደ
ኦደፓ አይነት ማተበ ቢስ ዓይን አውጣ ድርጅት አይቼ አላውቅም። እፍረት ይሉኝታ የሚባል አልሰራላቸውም። ያን ሁሉ ደክመን መና ነው
ያስቀረቱ። ህወሃት ከዶር ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ሳይሆን ከሌላ ጋር ብትሰራ ትመርጣለች።
በስፋት በጥርስ የተያዙ ሰው ናቸው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው። አሁን እሳቸውን አውጥቶ
አውላላ ሜዳ ላይ የመጣል ያህል ነው የተሠራው ግፍ። ለደህንነታቸው እራሱ ዋስትና የላቸውም።
የተመረጡበትን ጊዜ ሳይጨርሱ ነው በግፍ የተነሱት። ለህውሃት ለጃዋራዊው አቶ ንጉሡ
ጥላሁን ሲባል። ይህ ለአማራ ህዝብ ሹመትም ሽልማትም አይደለም። ሽንፈት ነው። ይህን ሴራ የሚተበትቡት ኦዴፓዎች ሌላም
የቀረ የበት ሥራ ይኖራቸዋል፡፤ ለነገሩ በዋዜማው ቀበሌ 5 ባህርዳር ቃጠሎም ነበር። ቅጣቱ በሁሉም ዘርፍ ነው። ጎንደር ማፈናቀል፤
ባህርዳር ቃጠሎ … ፋኖን እንደ አዋሳ ማስነሳት ስለማይችሉ …
ኦዴፓ የራሱ ሳይበቃ ብአዴንም እያዘረከረከው ነው። ስለምን? እንዳይፈታተነው ስለሚፈለግ። የሚመከተው አካል መንፈስ ያለው ከዚህ ማሀበረሰብ ስለሆነ። ያው ደበቡ ለይቶለታል
ኦደፓ በትኖታል።
ኦደፓ የያዘው ጠንካራ፤ ይፎካከረኛል የሚለውን ማዳከም ነው። ቁልፍ ፍላጎቱ ኦሮምያ የምታባል አገር አዲስ አባባ ላይ መመሥረት ነው። ልክ ጣሊያን የሚሠራውን ስትራቴጅ
ያህል ነው የተደራጀ ተግባር እዬከወነ የሚገኘው። ደቡብን ከሦስት ሸንሽኖ ሌላውን 53 ብሀረሰብ ሜዳ ላያ አፍሶታል በመንፈስ ደረጃ።
ተቃዋሚ/ ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ የሚባሉትን ደግሞ ፕላስተር ገዝቶ እዬበሉ እዬጠጡ እንዲቀመጡ
አድረጎ ለጎሟቸዋል- አዬ ጃዋር ወንዱ! ለመልካም ቢያውለው እኮ እንዴት ጥሩ ነበር … እሱን ማሸነፍ አይቻልም።
ጥቃቱን ሳያወጣም አይተኛም። ሁሉንም አለፈስፍሶ የአማራ ተጋድሎ አክቲቢስቱን ሳይቀር
አንከረባብሶ አቶ ንጉሡ ጥላሁን እንዳሻቸው ይፈንጩበታል ሰፊውን የተጋድሎ
አንባ። ሌላው ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ የሚባለው አማራ ተጋድሎ ለማለት ተስኖት ቄሮ ቄሮ ሲል አሁን ተስፋውን በአፍ ጢሙ እዬደፋለት
ይገኛል። ማስተዋል፤ ማመጣጠን ማመዛዘን አርቆ ማሰብ ይገባ ነበር።
ወደ ቀደመው ምልስት ሲሆን መከራ ችለህ ተሻገር ለማለት በዚህ ውስጥ አባብለውም አታለውም
እንዲያስፈጽሙ የሚገደዱት ደግሞ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ናቸው። ከታሠሩበት ገመድ ራሳቸውን ነፃ አድርገው
ነፃነታቸውን የሚያውጁበት ቀን በእጅጉ ይናፍቀኛል። ሰንበት በመጣ እና በታዬ ጉዳቸው። ወይ ዘርግፈውት ወይ ደግሞ አስምጠውት ወይ ደግሞ ሰምጠውበት …ብቻ የለዬለት ነገር እጠብቃለሁኝ እኔ በግሌ።
ከሐምሌ ጀምሮ እንዴህ ተምጦ አይዘለቅምና። በማህል እንደ ኩርድሾችም መሆን አለ …
ሌላው ግን አማራ ክልልን እንደ መጠለያ ያዩት ይመሰለኛል ጠ/ሚር አብይ አህመድ። ለነገሩ
እንኳን ኖረላቸው። እራሱ ዛሬ አቀማመጣቸው እጅግ አሳዛኝ ነበር። በሰው እጅ እንዳሉ ነው እኔ የሚገባኝ። በል የተባሉትን ብለዋል። መቀሌን እሽሩሩ፤
አንቦን እሽሩሩ ይሉ ዘንድ ዶር አንባቸው መኮነን አሳስበዋል። የሰው መሄድ እና መምጣት ሳይሆን ጉዳዩ የህሊና መለወጥ ጉዳይ ነው።
መቀሌም አንቦም ያለው ከልብ ውስጥ ነው። እኛ ውጭ ሆነን እኮ ነው ሌት እና ቀን በ
አገራችን ጉዳይ የምንባትለው። ለመሆኑ ዓመቱን ሙሉ የተደከመበትን „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ እንዴት ቆሻሻ ውስጥ ተቃጥሎ አመድ እንደሆነ
ጠፍቷቸው ነው ይህን ማመልከቻ እንደገና የሚያቀርቡት። ዲስክርምኔሽን እኮ ለዛውም ናዚያዊ በሆነ ሁኔታ በዶር ለማ መገርሳ አዳምጠናል
„ዶሞግራፊ“።
ከዚህ በላይ ምን እንጠብቅ? ታቦት ይቀረጽ የተባለለት መላክ አንደበቱ ይህን ሲያወጣ
እሳቸው እራሱ ከለማ የተለዬ ነገር የለኝም እሱ ጨርሶታል እኮ እንዳሉ ነው የተተረጎመው። … አይደለም ወይ? አሁንስ የምን አታሞ
ነው የሚደመጠው … የሴቶች ጉዳይ ጉዳዬ ነው … ሌላው ቢቀር …
ሰማይ እና መሬት ቢገናኝ እንደገና ኦሮማራ ይገኛል ብለው
አያስቡት። አቶ ታከለ ኡማ እኮ አማራ ክልል ሄደው ነበር ዜናው ስመለፈጠሩ እንኳን አላደመጥነውም። በነገራችን ላይ አኔ አቶ ታከለ
ኡማን አዳምጫቸው አላውቅም። ሰው እኮ አንድ ጊዜ ነው የሚታለለው።
አርባያ፤ እርማጭሆ ላሊበላ መከራውን ተሸክሞ ለኖረ ማህበረሰብ ምን አደረገለት ኦህዴድ
ያን ያህል በሽታ ሽቶ ሲጨፈጨፍ? ያ አልበቃ ብሎ በጣና ኬኛ ይኸው ንጉሥ ሆኗል እኮ ኦህዴድ ታሪኩን የራሱን ለሸለመ ማህበረሰብ
ምን ይሆን የተደረገለት? እሱን አማራን ለማጥፋት ሲታታር መሽቶ ይነጋል … ኦዴፓ።
ስንት አማራ ነው የተፈናቀለው ከጣና አባይ ኬና ከ ኦሮማራ ወዲህ ከዩንቨርስቲዎች እራሱ
… ምደባው ሁሉ እኮ ለአጋር ድርጅቶች ተሰጠ የሚባለው አማራን ወና አድርጎ ነው። የ አማራ ድርሻ እኮ ነው ለሱማሌ፤ ለቤንሻንጉል፤
ለአፋር የተከፋፈለው። ሥልጣን አያስፈልገንም ብለዋል ለካ ብአዴኖች .. ይህ የሚጣፍን ይመስላችሁልን? የሌላው ኮታ እኮ አልተነካም
ሁሉም የራሱን ይዞ ነው የሚቀልደው።
የሚገረምኝ ከውጭ አገር ሰዎች ጋር የሚደረገው ግንኙነት፤ ውጭ አገር ሲከድ በቃ ኦዴፓ
ብቻ ነው እኮ … ነው። ሌላው ማህበረሰብ እንዲገናኝ፤ ዕውቅና እንዲኖረው አይፈለግም። ለነገሩ ታላቋ ኦርምያ እኮ ሳናውቀው ተመስርታለች
… ምክክሩም አማራ ጠል ከሆኑ ሊሂቃን ስለመሆኑ አሳምረን እናውቃለን … ብአዴን ማዬት ኦዴፓ አይፈልግም!
ክስም ቢልለት ይወዳል። ከብአዴን ይልቅ ለኦዴፓ ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ የሚባሉት
ይበልጡበታል ሁሎችም አማር ጠል ስለሆኑ።
ስደተኛ ውሃ እና መብራት
ይገባለታል ከሁለቱ ክልል የመጡ /መጤ/ የሚጮኽላቸው ሚደያ ስላላቸው፤ ጎንደር አካባቢ ድሮም የታወቀ ሽፍታ ነው፤ ከጎንደር እና
ከወሎ የመጡ ዘራፊዎች፤ ወንበዴዎች፤ ቁማርተኞች እኮ ነው የተባለው። በጦር ሃይሎች ም/አዛዥ፤ በአዲስ አባባ ፖሊስ ኮሚሸነር፤ በለገዳዲ
ለገጣፎ ከንቲባ … በደል አይረሳም … ቅርብ እኮ ነው … የቀደመውን እንርሳ ሲባል በላይ በላይ ማከል ነው …
አዲስ አባባ ያለውስ ምልዕት ምን ሽብር እዬተነዛበት ነው? … እንዴ ሰው እኮ ነው
የአማራ ህዝብ … አንደ ሰው ይከፋዋል ብሎ ማሰብ ይገባል፤ የትናንቱ የተጨፈጨፈው አልበቃ ብሎ ዛሬም እኮ አና ተብሎ በጥርስ ተይዟል
…
ሌላው ከህወሃት ጋርም የሚኖረው ፖለቲካዊ ጋብቻ ለኦዴፓ የሥልጣን ዘመን ዘንቢል እንዲሆን ብአዴን ካለሆነ በስተቀር ሊቃናቱ በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ፈጽሞ የሚድን አይደለም ደዌ ነው ታመዋል በሽተኞች ናቸው።
ህዝቡ ግን ድሮም የተጋባ፤ የተዋለደ፤ የተሳሰረ ነው። የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና ጦርነት
ቢኖር እንኳን የአማራን ቁስለኛ የትግሬ ቤተሰብ፤ የትግሬ
ቁስለኛ የአማራ ቤተሰብ ሸሽጎ ያተርፋል። ለዚህ ምንም ጥርጥር የለኝም።
ምናችን ይለያል? ታሪካችን፤ ባህላችን፤ ወጋችን፤ ትውፊታችን ቀደምትነታችን ምናችን?
አገር በመገንባት በመመሥረት ሂደት ብዙ የተሳሰሩ ሁነቶች አሉን። ስሜን ኢትዮጵያን ያገለለ ፖለቲካ እኮ ነው ትልሙ ሁሉ አይገባቸውም
እንጂ እነ ታገሩ። የንጉሦች ንጉሥ አጤ ዮሖንስ አንገቱን የሰጠለት ህዝብ በምን አንጀቱ የተጋሩን ቁስለኛ አይቶ ረግጦ ሊያልፍ?
አይሆንም። ጸጸቱም የዘመን የትውልድ ነው የሚሆነው።
ሊሂቃኑ ግን አይድኑም። ይገርመኛል አረና ድርጅት አልፎ ተርፎ አማራ ክልል አገው ቅማንት
እያለ ይዳክራል፤ „የራሱ ሲያርበት የሰው ያማስላል“ … እነሱ አንድ ስብሰባ ለመናገር ትግሬ ሆነው እንኳን አይችሉም።
አማራ ክልል አርጎባ፤ ኦሮሞ፤ አገው፤ ቅማንት የራሳቸው ነፃነት አላቸው። በመላ ኢትዮጵያ
ይህ ነፃነት ያለው አማራ ክልል ብቻ ነው። ደቡብ እንኳን ይህ አልነበረም። በዬትኛውም መስፈርት አማራ ክልልን የመሰለ ሰላማዊ እና ሥልጡን ክልል
የለም። የእነሱ ሰው እኮ ነው የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ዶር አሚር አማን የማን ነው? የትኛው ክልል ነው ይህን የሚሠራው?
አማራ ውስጥ የሚኖሩ ኦሮሞዎች አመራር የሚያገኙት ከኦደፓ አይደለምን? ጉባኤ የሚሳተፉት
ከዛ አይደለምን? የትኛው አማራ ነው ይህ ነፃነት ያለው በዬትኛው ክልል? አማራው ክልልህ ተብሎ በተሰጠው እንኳን ይኸው ነው በዬዘመኑ
ማንም ነው የሚፈነጭበት። ገዱን መስቀጠል የማይችል የአማራ ክልል?
እንደ ኦዴፓ ፍላጎት ጃዋርውይው አቶ ንጉሡ ጥላሁን እንዲሆኑ ነበር የሚፈለገው ርእስ
መስተዳድር። ሰነባብቶም አይቀሬ ነው። አሁን ለዓይን ሽፋሽፍት ማሳረፊያ ነው ዶር አንባቸው መኮነን የሆነው። ለዚህ ፈቀድ ህወሃትም ሳይጠዬቅ አይቀርም። ማን ይሻላል ተብሎ? ድርድርን ዳር
ዳር እያለ ስለሆነ ኦዴፓ ከህወሃት ጋር።
ሌላ ከጃዋር ካህን ከ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ተወካይ የኦሮሞ ደም ያለበት አማራ ክልል ስለሌለው ነው እንጂ እሱን አምጥቶ ነበር የሚሾመው። ይሉኝታ የሚባል
መቼም አልሠራላቸውምና ኦዴፓዎች። ወጥ ፓርቲ ይሁን የሚባለውም ለዚኸው ነው - ከተሳካ። የራሱን ሰዎች አምጥቶ ለመሰክሰክ። የ አማራ ሊሂቃን መውጣት መከራ ነው ኢትዮጵያ መሬት ላይ ... የ አማራ ሊሂቃን ደግሞ አይገባቸውም ዘመናቸውን ሙሉ ልቦናቸውን የደፈነው አንዳች አዚም አለባቸው ...
የሆነ ሆኖ ግፉ መቼ ነው በአማራ ሊሂቃን ላይ የሚቆመው? ደባው መቼ ነው የሚያበቃው?
ሴራው መቼ ነው ልኩን የሚይዘው የ አማራ ሊሂቃንን በመግፋት በመቅበር እና በማስገለል? ተብሎ ተብሎ ደግሞ ጃዋርውያን እንዲህ ይፈንጩበት? ወዮልህ አማራ? ልብ ግዛ - አማራ!
አማራ ሆይ!
ሁለቱን ምሰው ሊቀብሩህ ተሰናድተዋል።
„አንከባበር“
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ