መጪው ሰንበት መሰንበቻ ወይንስ መሰናበቻ።

እንኳን ደህና መጡልኝ።
መሰበቻ
ወይንስ
መሰበቻ።

„በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሄርን ጠራሁት፤
ወደ አምላኬም ጮኽሁ።“
መዝሙር ፲፯ ቁጥር ፮
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።


ውዶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? በቅድሚያ እንኳን ለዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በሰላም ደረሳችሁ አደረሰን። ዛሬ በጀርመን ርስዕ ከተማ በበርሊን ዓለም ዓቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማደርግ ዝግ ሲሆን በሌሎች ክ/አገሮች ግን መደበኛ የሥራ ቀን እንደሆነ ከእንዴት አደርክ ዶችላንድ ዜና አዳመጥኩኝ። በሚኒስተር ደረጃ የማጽጃ ቱታቸውን ለብሰው ከአንድ የሴቶች ግብረ ሃይለ ጋር በመሆን በአካባቢ ጽዳት እንደሚሰማሩም በዜናው በጨረፍታ ተገልጧል።

በዚኸው በጀርመንኛው የጥዋት ዜናም የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳትን አቶ ባራክ አቦማ ወደ ጀርመን ጎራ እንደሚሉም ተደምጧል። ክቡርነታቸውን አውሮፓውያኖች የሚወዷቸው መሪ ነበሩ። ጭምቷ ሲዊዘርላንድ እንኳን የተለዬ አትኩሮት አላት ለአቶ ባራክ ኦባማ እና ለድንቋ ደልዳላ እመቤት ለወ/ሮ ሚሻኤል ኦባማ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ባላፈው ዓመት በሙሉ የሴቶች አቅም አርንጀንቲና በራራ ያደረገው የኢትዮጵያ አናብስት የአዬር መንገድ ቡድንም ዕለቱን ምክንያት በማድረግ ወደ ኦስሎ በረራ እንደሚያደርግ ተደምጧል። ወሸኔ ነው ማለፊያ።

ወደ ቤተ መንግሥቱ ጎራ ስንል ደግሞ ጠ/ሚር አብይ አህመድ የተኮራረፉ አቻ ጎረቤቶቻቸውን ሲያስታርቁ ሰነባብተው ሰንበትን ተንተርሰው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት እንደፈቃዱ ተደምጧል። እና ሥርጉትሻ ለመሰንበቻ የሚሆን ስንቅ ወይንስ ለመሰናበቻ ስትል መጠየቋ አልቀረም። 

ያው አንኳሩ ጉዳይ ኦሮምያን አገር ስለማድረግ ወይንስ ኢትዮጵያን ስለማስቀጠል? ወይንም በኦሮሞ የበላይነት ቅኝ የምትደረግ ኢትዮጵያ?! ለነገሩ ብዙው ነገር ቃናው እሱን እሱን ነው የሚለው።

ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ውስጥ ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ ከሚባሉት ተዳብሎ ወይንም ተካፍሎ ወጥ ፓርቲ መስርቶ ለመሄድ ወይንስ በስብርባሪው እነ ኢህአዴጎች እያነካከሱ ለመጓዝ ታሰበ? ያዬሁት የባዶ ወንበር ጉዳይ ተረገጡ ሊነገረን በድፍረት ወይንስ ተለዋጭ ሃሳብ ሊማጥበት። መቼስ ተጠልፌ ነው የባጀሁት አይሉ ነገር? ያው በገርደምዳሜ ውልብሊቢቱን ቢያስጨብጡ "ለአክ ወሬ" ሰለባዎች ትንሽ ... በደምሳሳው ከመንጎድ ይህም አለ ለካ ማለት ያስችላቸዋል ...  

ትናንት በተደመጠው ዜና ብዙ ሰው ደንግጧል። እኔ አልደነግጥም ወንበሩ በድርድር ለይስሙላ እንዳለ ህልሜ ብቻ ሳይሆን ሂደቱን በጥንቃቄ ስለምከታተለው የሊቀ ሊቃውንቱን የፕ/ አልማርያምን „የአክ ወሬ“ አፍዝ አደንዝዝ ትቼ በራሴ መንገድ ስለምከተል የሆነው ሁሉ አብይን የማስወገድ ሴራ ስለመሆኑ ጠንቅቄ አውቀዋለሁኝ። ድጋፉም ሲቸበቸብ የባጀው ባልሆነ ላልሆነ ቦታ ለኦነጋውያኑ ጡንቻ ነበር። 

ጠ/ሚሩ ለቀቅ ሲያደርጓቸው ገፋ ያለ ተግባር ሲከውኑ ወጠር ሲያደርጓቸው ደግሞ ከመስመረቻው ሲያስገቧቸው ዘንበል ቀና ያለ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው። የአብይ መንፈስ በሙሉ አቅሙ እንዲወጣ ፈቃድ አልተሰጠውም ነበር። ፈጽሞ አላሟኗቸውም፡ደጅ ደጁን ጉዞው መሬት የረገጠ ተግባር በኢትዮጵያ እንዳይከወን ይፈለግ ስለነበረ ነው። የውጭ ውጩ ጉዞ ደግሞ በእግር ብረት ነው … ካቴና አንገት ላይ ታስሮ፤ ትንፍሽ የለም። መሬት ላይም አቶ ንጉሡ ጥላሁንን ያህል የጉሮሮ አጥንት ሰንቅረዋል ... ዕድሜ ለግርባው ብአዴን።

እጅግ እሰጋ የነበረው የዶር ለማ መገረሳ እና የዶር አብይ አህመድ አንድነት ነበር። እሱም ጎሽቶ ጠርቷል። ጎሽቶ የጠራው የሚኒሶታ ስብሰባ ላይ በነበረው ንግግር ማስተዋል ይቻል ነበር። የመልስ የወልዮሽ ጉዞው ደግሞ መንገድ ላይ በይስሙላ ዕንባ ታጅቦ በተዘጋጀው ቹቻና ሰኔል ሲታሰብ አይሆኑ ሆኖ ሞት አሸንፎ መንፈስ ሲነሳ ሌላ እገታ እንደነበር ይታወቃል።

ስለዚህ የሚሆኑት ሁሉ የዚያ ቅሪት አካል ናቸው። እና ጠ/ሚር አብይ አህመድ የገመናውን ስውር ነገር ዘረጋግፈው ስንበት ሊያደርጉ ከልብ ወዳጆቻቸው ጋር ወይንስ በተሰጣቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በሽፍንፍን ጉዞ ዶር ብርሃነመሰቀል አበባ እንደነገሩን ወራሽነታቸውን የኦነግን ፍላጎት ታጥቀው ከምልዕት ፍቅር ጋር ስንበት ሊያደርጉ ይሆን ነው ጥያቄው።

ሌላው በዚህ ውስጥ የትኛው ጋዜጠኛ የት ላይ እንደቆመም የሚለይበት ሁኔታ ይሆናል። የሃይል አሰላለፉ ጥርት ብሎ ይታያል። ለጥቃት የተዘጋጀውም ነጥሮ ይወጣላቸዋል።
የሳቸውን አቋም ግን መተንበይ አይቻልም። 

መጨነቃቸውን ግን ውጭ ውጩን ሲሉ መሰነበታቸው ልክ እንደ ሻሻመኔው፤ እንደ ቡራዩ፤ እንደ አዲስ አባባው ጭፈጨፋ እና እንደ ቆሞስ ስመኘው በቀለ ህልፈት ነበር ትዕይንቱ። ተጠምጄ በሱማሌ ጉዳይ ያሉት ነገር ያን ጊዜ ትክክል አልነበረም። በቅደመ ሁኔታ ተከርቸችመው ነበር ተለጉመው ነበር፤ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በጠላፊዎቻቸው ሥር ነበር። ስልክ እንኳን በቁጥጥር ሥር ነው የነበረው። 

በሌላ በኩልም አዲስ አባባ ማለት ተስኗቸው ሰሞኑን ደግሞ „ሸገር“ ብለው አዲስ የግብዣ ጥሪ አውጀዋል፤ በሌላ በኩልም ስለ አድዋ በተናገሩት ላይ የድሉን አንኳር ለመንካት ድፈርቱ አልነበራቸውም። ስለዚህ ሽሽት ወይስ ሽርድድ፤ ስንድድ ወይንስ አንክርድድ፤ ዞማ ወይንስ  ኩርዲዳ እንድንል እንገደዳለን።

ሀምሌ፤ እና ነሃሴ ላይ የጻፍኳቸው ጹሑፎች ታፍነው የሚቀሩ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጽፌ ነበር። የቅርብህ ሰው መግደልን ካሰበ፤ የቅርብህ ሰው መጥለፍን ወይንም ማስጠለፍን ካሰበ፤ የቅርብህ ሰው ማገትን ወይንም ማሳገትን ካሰበ፤ የእኔ ያልከው ሰው ከቀናበህ እና ሊያጠፋህ በስውር ካደመ፤ የቅርብህ ሰው ባለሰበከው ሁኔታ ስታገኘው መናገር አይደለም ማሰብ እራሱ አይቻልም።

እሳቸው መሪ ሆነው ነው እንጂ እንደ እኛ ባተሌ ቢሆኑ ሰው የሚባል በምድር ያስጠላችሁ እና ብቻችሁን ዘግታችሁ መኖርን ትመኛላችሁ። ከባድ ነገር ነው። እራስህን የሰጠኽለት በክህደት ውስጥ ሲገኝ የሚሰማ ስሜት ለመግለጽ ቃላት አልተፈጠረለትም።

አብሶ ከደህንነት ጋር የተያያዘ ከሆነ እጅግ ከባድ ነው። አማራጩ አምቆ መያዝ ነው። እምቁ ደግሞ ውስጥን ይጎዳል እንደ ሰው፤ መሪ ሲኮን ደግሞ እንዲህ አገርን አይሆኑ ያደርጋል። ምንጩን እያወቅክ ንደቱ ሲቀጥል እያዬህ ዝምታ ደግሞ ሌላው ረመጥ ጉዳይ ነው … ለታሪክም ለሰብዕናም። አድራጊውን በፍርድ በህግ ለመጠዬቅ ደግሞ ሥልጣኑ የሌላ ነው፤ አንተ የሥምየለሹ ጠ/ሚር ተገዳጅ ነህ። ከዚህ ፍንገጣ ቀጣዩ ልጅን ማጣት ይመጣል፤ ይህ ደግሞ የመከራው ሁሉ የከፋ ነገር ነው። 

ከሁሉ በላይ ለህዝብ በሰጠኸው ተስፋ ልክ ለመሆን አለመቻልህን ለመንገር ወኔው ከሌላ ደግሞ ሌላ መራራ መከራ ነው። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ባሉት ልክ ስለመሆናቸው ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን ማዬት ነው። እሱን ለናሙና ወስዶ ማጥነት፤ በእሱ ላይ ምርምር መሥራት በቂ ነው ችሎት ሰበር ሳያስኬድ። 

ጥረቱ ኢትዮጵያን የማተለቅ ህልም ነው። ይህ ደግሞ ለኦነግም፤ ለህወሃትም መርግ ነው። ስለዚህ በወጥ ስውር ሃዲድ ማወክ ግድ ነው። ከሁሉ በላይ የሚበልጥ ሰው ህይወቱ ቀጥሎ ተደናቂነቱ ጎልቶ መውጣት ደግሞ የመከራው ማመንጫ ማሽን ነው ለኢጎኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ። 

አሁን ከሰሞናቱ ያቺ ዓለም አቀፍ ባለቅኔ አርቲስት ወ/ሮ እጅጋዬሁ ሽበባው ተሰወረች የሚል ዜና በዚህም በዚያም ይደመጣል። የአመኑት የከዳ ዕለት መሰወር ሲያንስ ነው። እኔ እማስበው እንደዛ ነው።

ዘግቶ መቀመጥ ብቻ ነው መፍትሄ። እራሱ አንደበትን ከፍቶ መናገር እንዴት ይከብድ ይመስላችሁዋል። ስልክማ አንጡራ ጠላት ነው። እርግጥ በዚህ ጊዜ ሰው ያስፈልጋል። ሁነኛ ሥጋ እህት፤ ወንድም ወይንም ጥሩ የትዳር አጋር። ነገር ግን የጥበብ ሰው ከሆነ ችግር ብዙውን ፈተና ጥበብ ይሸከምለታል። እጃችሁን ጥበብ ይዞ ነው የሚያወጣችሁ።

ወደ ዕንቋዋ ጂጂ ስንመጣ እሷ ሰዓሊ ናት፤ ገጣሚ ናት፤ ድምጻዊት ናት ስለዚህ እንዚህ መንፈሶች እዮር ናቸው። የጽናት መሰረቶች ናቸው። ጠ/ሚር አብይ አህመድም ባለቅኔ ናቸው። በተጨማሪም መልካም ትዳር አላቸው ስለዚህ ለዛች ለምትተርፋቸው ቆረጥራጣ ደቂቃ መንፈሳቸው ሰላሙን የሚያርግበት ሁኔታ አያጣም እንጂ እንደ ሴራውማ እኮ አልነበሩም።

እዛው የራሳቸው ሰዎች በሚያውቁት ገራገር ልባቸው፤ ሰው አማኝ ልባቸው ገብተው ነው እያመሷቸው የሚገኙት። ይጠፋል፤ ያልፋል፤ አይበረክትም ነበር ግን አልሆነም ፈጣሪ አልፈቀደም አልሞቱላቸውም። ይህን የህሊና ሪህ ለማስታገስ ሁሉ ነገር ይሞከራል። ትልቁ ማህበራዊ መሰረቱን ማደፍረስ ነው እሱ ተሳክቷል። ፌድራል መንግሥቱን ሽባ በማድረግ የማደረግ አቅሙን መስለል ነበር ይህን ሆኗል። 
  
የሆነ ሆኖ የግድያውን ሙከራውን ፈጣሪ ቢያከሽፈውም አሁን ግን ሁለት ወዶ አይሆንም።  ለኦሮሞ ኢንፓዬር ባርነት አልነበረም ሰው ሊያደርገው የማይገባውን ተጋድሎ ሁሉ ያደረግነው ሁለችንም በግል ብዙ በጣም ብዙ ነገር አድርገናል። 

ስለዚህ ጠ/ሚር አብይ አህመድ የለዬለት አቋም ይዘው፤ በጠራ መስመር መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል። አስፈላጊ ከሆነ ፓርላማውን ሁሉ የማፍረስ ሙሉ መብት አላቸው። ኦነጎች ሙሉ ኢትዮጵያን ተረክበው ኢትዮጵያ የምትባል አገር ከ እንግዲህ የለችም ያለው ኦሮምያ የሚባል አገር ነው ተብሎ እስካልታወጀ ድረስ የፈለገ ነገር ቢጠቀጠቅላቸው አይጠቅማቸውም። ከዛ ቀጥሎም ቀጣይ ናቸው። ኦርምያ እስላማዊ አገር ናት ብሎ ማወጅ ነው። መጪው ድርብ መከራ የአዲስ አባባ ጉዳይ ብቻ አይደለም የክርስትናም ፈተና ነው። የ አፍሪካ ህብረት ጉዳይም ነው። ከዛ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ሌላ መልክና ቅርጽ ይኖረዋል። ኤርትራም ብትሆን ወዬልሽ ነው። 

ሰፊ ነገር ነው ያለው ... አውሮፓውያኖች ይሁኑ ምዕራባውያን እራሱ በ አብይ ፍቅር ተነድፈው የተዳፈነው ጠለፋም ጠ/ሚሩ ትንፍሽ እንዳይሉ ስለተለጎሙ ይሆናል ብለው አላሰቡም፤ መንገዱ ግን ይኸው ነው። እራሱ ለኢትዮጵያዊው እስልምና የሚመች እስልምና አይሆንም ... ወረራው በብዙ መልኩ ዓለምን ጨምሮ የሚንጥ ነው የሚሆነው። 

ለዚህ ነው አቶ ጀዋርን አቃላችሁ አትዩት፤ ሳያሸንፍ የሚተኛ አይደለም እምለው። አሁን የ የእኛ ፖለቲከኞች ችግራቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድን ከ ኦነግ ጋር አዳምሮ የማዬት ነው። ይህ ጉዳዩን ከሥሩ ያለማጥናት ወይንም የጭፍን ጥላቻ ውጤት ነው። በሌላ በኩል አብረው የተሰለፉት አቶ ንጉሡ ጥላሁን ጉዳይም ከአቶ ግርማ ካሳ ትንሽ ጥርጣሬ በስተቀር ገባ ብሎ ለመመርመር የተደረገ ሙከራ የለም። እሳቸው ለ ኢትዮጵያዊነት ውጋት ናቸው። 

ጠ/ሚር አብይ አህመድ አብዝተው ከሚጫኑት የአማራ መንፈስ ጋርም እርቀ ሰላም ማውረድ ይኖርባቸዋል። እዬወደድናቸው ነው የሚጫኑን። ለእኛ የሚጭንቱን ያህል ለማንም አይጭኑም። እኛ ደግሞ ዕዳ የለብንም።
  
ወገኖቻቸውማ በሽታሽቶ መለመላቸውን አስቀሯቸው። አሁን ልብስ የለቡሰ ሊመስላቸው ይችላሉ። መለመላቸው ነው ያሉት ተነጥለው ተገለው ብቻቸውን። ሌላውን የተጠጉት አዲሱ ፍቅረኛቸውም ቢሆን በርክቶ የጸናበት አንድም የታሪክ ገጠመኝ ስሌለ አብሮ ንዶ በተናደው ማገዶ ላይ ጨምሮ አንድዶ አመድ መሞቅ ስለመሆኑም ልብ ሊሉት ይገባል ጠ/ሚር አብይ አህመድ።

አዲሱ ፍቅረኛቸው ካሰጠጉት ከአዲሱ መፈንቀለ መንፈስ ጋር ለመደራደር ዕድሉን ካገኜ አይኑን አያሻም፤ ትግል ሥሙን ራሱን አይወደውም። ስልቹ ነው። የሆነ ሆኖ በፖለቲካ ታማኝነት ቅርፊት ነው። ሁሉም ጠ/ሚር መሆን ይፈልጋል።

የዛጉት በመንፈስ ዶር አረጋይ በርሄ ሳይቀሩ ጠ/ሚር መሆን ይፈልጋሉ እንኳንስ ሌላው … ያው ዕድሉ ከተገኜ አባ ገዳ ጃዋር መሃመድ እና አባ ገዳ በቀለ ገርባም ሁለቱም የማን ደም ፈሰሰ መባላቸው አይቀሬ ነው፤ የጉለሌው መንግሥትም አለ … ምን አሁን ከሆነ እኔስ ከማን አንሼ ዶር/ ደብርጽዮን ገ/ሚኬኤልም ቀይ ምንጣፍ አስነጣፊ፤ ባለተክሊል ተኮፋሽ ናቸው … ምኑ ቅጡ … ቅርጫ ላይ ነው የ4ኪሎ ወንበር …

የሆነ ሆኖ … ሰንበትን ያዬ ብለናል … ጥቁር ድፍን፤ ጠይም፤ ዳማ፤ ግራጫ እንዴት ይሆን ሰንበት? የኦነግ ባለመዳሊያ አባ ገዳ አቶ ንጉሰ ጥላሁን ጉርጎራ ይለይለታል ወይስ ወይራ በድፍኑ?። እሳቸውም እኮ ቦታውን ይፈልጉታል … በነገራችን ላይ …

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።


                                             የኔዎቹ ኑሩልኝ።

                                             መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።