ሰበር ዜና ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ሹመታቸውን ለቀው ዶር አንባቸው መኮነን ተሾሙ።
እንኳን ደህና መጡልኝ።
ሹመት እና ሽኝት
በሆደ ቡብነት
ተስተናገዱ።
„ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣
የወይራ ሥራ ቢጓል እርሾችም መብልን ባይሰጡ
በጎችም ከበረት ቢጠፉ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ
እኔ ግን በ እግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤
በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።“
ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ ቁጥር ፲፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።
እግዚአብሄር ይስጥልን።
ብርታቱን ይስጥልን!
·
መነሻ።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን ያደረጉት ንግግር
ህዝቡን ያላቀሰው የተሰናባቹ የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ንግግር || የአማራ እና የትግራይ ህዝብን ማንም አይለያየውም||
ህዝቡን ያላቀሰው የተሰናባቹ የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ንግግር || የአማራ እና የትግራይ ህዝብን ማንም አይለያየውም||
የተቀላቀለ ስሜት ነው የተሰማኝ። ዶር ገዱ አንዳርጋቸው በመልቀቃቸው ሆዴን ባርባር ነው ያለው። ላደረጉት መልካም ነገር ሁሉ ድንግልዬ ትከተላቸው።
ዶር ገዱ አንዳርጋቸው እግዚአብሄር ይስጣቸው ራሳቸውን ገብረው ይህን ለውጥ ስላስመጡ፤ በሌላ በኩል ዶር አንባቸው መኮነን በሚመለከት እኔ ሰውም ከቁጥር ባላስገባቸው ወቅት ነበር አብሬ በጹሑፌ ሥማቸውን አጉልቼ ስጽፍ የነበረውም።
ለፕ/ሲታጩም አምርሬ ነበር የተቃወምኩት። እናም በፌድራል መገለላቸው፤ በኦዴፓ ሆነ በብአዴን ውስጥ ባሉ ስውር እጆች ሰፊ የሆነ የፈተና ጊዜ አሳልፈዋል።
በዚህ
አጣብቂኝ ችግሩ ባዬለበት በሱባኤ ጊዜ ደግሞ ፈተናውን ሊጋሩ ከፊት ለፊት ተገኝተዋል። መልካም የሥራ ጊዜ እንዲሆንላቸው እመኛለሁኝ።
ደግሜ
ደጋግሜ የአባቶቻችን አምላክ እማለምነው ደግሞ ዶር ገዱ አንዳርጋቸውን እንዲጠብቅልን ነው። ብዙ የማይናገሩ ሁሉንም በሆዳቸው መስጥረው እና
ታግሰው የደከሙ ሰው ናቸው እና ድንግል ትከተላቸው።
በቀጣይ
ደግሞ ዶር ለማ መገርሳ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ሆነው እናይ ይሆናል። ምክንያቱም ሂደቱ ማረገብ የሚፈለግ ነገር እንዳለ ሹክ ስለሚል። እሳቸውንም ቦታውን በጽናት ስለሚፈልጉት።
ኢትዮጵያዊነት
ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጥር።
ውዶቼ
ኑሩልኝ መልካም ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ