አችን ከትከት ብሎ ከልቡ ሳቀ - ሐሴቱን ስለጨበጠ። ተመስገን!
አችን! „የጻድቃን መንገድ ግን አንደ ንጋት ብርሃን ነው። ሙሉ ቀንም እስኪሆን ድረስ እዬተጨመረ ይበራል“ መጽሐፈ ምሳሌ ፬ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 19.11.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዝ · ጠ ብታ። አችን አማራበት። አችን ተሞሸረ። አችን ጫጉላ ላይ ነው። አችን ጠሐይ ፍንትው ብሎ ወጣለት። አችን ከልቡ ከትከት ብሎ ሳቀ ሐሴቱን ስለጨበጠ። አችን ደስታውን እያጣጣመ ነው። አችን ለእሱም ዘመንም አዬው ወጣለት፤ ወፊቱም የምሥራች አዋጣችለት። ተመስገን! ዘመን ጥሩ ነው። ዘመንም መስታውት ነው። ዘመንም ሂደት ነው። ዘመንም ዜና ነው። ዘመንም ታሪክ ነው። ዘመንም ህይወት ነው። ዘመንም መኖር ነው። ዘመንም ገላጭ ነው። ዘመንም ተነባቢ ነው፤፡ ዘመንም አናባቢም ነው። ዘመንም ህግ ነው። ዘመንም አይቀሬ ነው። ዘመን ሰጥ አዎንታዊ ሲሆን ደግሞ ሽልማት ነው። ለዛውም ሰው ሰራሽ ያልሆነ። · መ ሆን። የአፍሪካ ህብረት አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን እና አስከምልክቶ ጠ/ሚር አብይ አህመድ የሰጡትን መግለጫ በልዩ ተመስጥዖ ነበር ያዳመጥኩት። እኛዊነት በግርማ ሞገስ ስላአጨጌ። ነፍሴን የማረከው እንዲህ የሚለው ነው „ አችን “ አገራዊ ሃላፊነት ለተወጡት በፍጹም ቅንነት ከልብ እና ከነፍሳቸው በማቀረብ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በራሳቸው ውስጥ አጥልቀው ከአንጀታቸው ነበር እንዲህ ያሉት „ዲፕሎማቶቻ አችን፤ አሸከርካሪዎቻ አችን፤ የበራራ አስተናጋጆ አቻችን፤ ፓይሎቶቻ አችን፤ የአውሮፕላን ጣቢያ ሰራቶኞቻ...