አችን ከትከት ብሎ ከልቡ ሳቀ - ሐሴቱን ስለጨበጠ። ተመስገን!

አችን!
„የጻድቃን መንገድ ግን አንደ ንጋት ብርሃን ነው።
ሙሉ ቀንም እስኪሆን ድረስ እዬተጨመረ ይበራል“
መጽሐፈ ምሳሌ ፬ ቁጥር ፲፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
19.11.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዝ

·      ብታ።
አችን አማራበት። አችን ተሞሸረ። አችን ጫጉላ ላይ ነው። አችን 
ጠሐይ ፍንትው ብሎ ወጣለት። አችን ከልቡ ከትከት ብሎ ሳቀ 
ሐሴቱን ስለጨበጠ። አችን ደስታውን እያጣጣመ ነው። አችን 
ለእሱም ዘመንም አዬው ወጣለት፤ ወፊቱም የምሥራች አዋጣችለት። ተመስገን! 

ዘመን ጥሩ ነው። ዘመንም መስታውት ነው። ዘመንም ሂደት ነው። ዘመንም ዜና ነው። ዘመንም ታሪክ ነው። ዘመንም ህይወት ነው። 
ዘመንም መኖር ነው። ዘመንም ገላጭ ነው። ዘመንም ተነባቢ ነው፤፡ ዘመንም አናባቢም ነው። ዘመንም ህግ ነው። ዘመንም አይቀሬ ነው። ዘመን ሰጥ አዎንታዊ ሲሆን ደግሞ ሽልማት ነው። ለዛውም ሰው ሰራሽ ያልሆነ።

·      ሆን።

የአፍሪካ ህብረት አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን እና አስከምልክቶ  ጠ/ሚር አብይ አህመድ የሰጡትን መግለጫ በልዩ ተመስጥዖ ነበር ያዳመጥኩት። እኛዊነት በግርማ ሞገስ ስላአጨጌ።

ነፍሴን የማረከው እንዲህ የሚለው ነው „አችን“  አገራዊ ሃላፊነት ለተወጡት በፍጹም ቅንነት ከልብ እና ከነፍሳቸው በማቀረብ ጠ/ 
ሚር አብይ አህመድ በራሳቸው ውስጥ አጥልቀው ከአንጀታቸው 
ነበር እንዲህ ያሉት „ዲፕሎማቶቻአችን፤ አሸከርካሪዎቻአችን፤ 
የበራራ አስተናጋጆአቻችን፤ ፓይሎቶቻአችን፤ የአውሮፕላን ጣቢያ ሰራቶኞቻአችን፤ ባለሆቴሎቻአችን፤ የሆቴል ሠራተኞቻአችን፤ የትራፊክ ፖሊሶቻአችን፤ የጸጥታ አካላቶቻአችን፤ የአዲስ አባባ ወጣቶች ተማሪዎችን እና መላው የአገራችን ህዝቦቻአችን እና በተለይም
 የአዲስ አባባ ነዋሪዎአችን“ በማለት ነበር ከልብ በአክብሮት ያመሰገኑት።

EBC News today November 18,2018 Breaking Ethiopian News


በዚህ ውስጥ መስጠት ብቻ ሳይሆን ፍቅር የመቀበልን መክሊት አይቻለሁኝ። በዚህ ውስጥ ህዝቤ የእኔ የማለት ታላቅ ልባዊነት 
አለበት። በዚህ ውስጥ የሃላፊነት የመገለጫ አዲስ ጅረትን ታዝቢያለሁኝ። በዚህ ውስጥ ስኬት እና ውጤቱ አጀንዳ 
ስለመሆነ ያመላክታል። የ እኔ የሚል ሙሴ ሲኖር ሁሉም ትርጉም አለው። ሁሉም ዕሴት አለው። ሁሉም አቋጣሪ አለው። ተመስገን!

በዚህ ውስጥ ህዝቡ ጫና ቢኖርበት እንኳን የመንግሥትን የአገርን ብሄራዊ ጥሪ የማድመጥ አቅሙን አመሰጣረውበታል። በዚህ ውስጥ የህዝብን የመንግሥትን ሃላፊነት አውቆ እና ተረድቶ ከመንግሥት ጎን ለመቆም ያሳዬውን ቁርጠኝነት ባሊህ ብለውታል፤ አድንቀውታልም። 
በዚህ ውስጥ በእኛነት ውስጥ ያለውን ጨዋነት እና የልዩ ሰማያዊ ጸጋውን አቅሙን አንብበውታል። 

 በዚህ ውስጥ ማግስትን ፍቅርን ሊያመትር የሚችል አዲስ ጥሪጊያ መንገድ በጥበብ ከፍተዋል። የቤት ሥራም ሰጥተታዋል በቅኔ። እንዲህ ዓይነት ያሸተ ተመክሮ የማዬት ዕድሉን ዘመን ስለሰጠን አቤቶ ዘመን ራሱ በክብር ይመስገን። በውነቱ አርቱ ምቱ ቃናው ጣሙ ወዙ ለዛው ልዩ ወሸቤ ውብ ነው።  …

·      የነፍሶች ትንሳኤ በምድር።  

ዘመን ጥሩ ነው እንዲህ መልካም ያደረጉ ነፍሶች የሚመሰገኑበት ብቻ ሳይሆን የእኛ መባላቸው ልዩ ዓለም ነው። አላዛሯ ኢትዮጵያ በሊቢያ አሸባሪዎች ልጆቿ አንገታቸው ሲቀላ ቤተሰቦቻቸው አደባባይ ወጥተው ለማልቀስ ብትን አፈር የለመኑበትን ዘመን አሰተናግደናል። 

ይህን ደፍሮ ያዘጋጀው የኢንጂነር ይልቃል ሰማያዊ ፓርቲም ብዙ ዱላ ቀምሶበታል። ዛሬ ደግሞ እንዲህ ስላደረጋችሁልን እናመሰግናችሁዋለን የሚል ሙሴ አላዛሯ ኢትዮጵያ እንሆ አገኘች። የሚገርም ነው። ብቻ እኔ ብዙውን ነገር ሳስበው ፊልም ኪኖ ነው የሚመሰለኝ።

ከአንዱ ትዕይንት ወደሌላው ስንሸጋጋር እራሱ ደረጃው የሥልጣኔው ማለቴ ነው ህልም ህልም ነው የሚመስለው። በዬዕለቱ የአዲሳዊነት 
እሳቤ፤ የአዲሳዊነት የቃላት አጠቃቀም፤ የልሳኑ የምት አደረጃጃት፤ የአዳዲስ ቃላትን የማግሰስ ተስጥኦ ሁሉ ሳስበው ምርቃቱ እዬራዊ ነው እንደል እገዳደለሁኝ።

መቼም ይጨርስላቸው ከማለት ሌላ ምን ይባላል። እንዲህ ህዝብን አክብሮ የተነሳ መሪ ከብሮ ድርሻውን እንደሚወጣም ዕምነቴ የዛሬ ሳይሆን የቀደም እንዲሆን አምላኬ ስላደረገኝ አመሰግነዋለሁኝ።

ባለፈው ዓመት አብይ ኬኛን ክፍል 6 ሳጠቃልል የጻፍኩትን እንሁ በዚኸው ነው ዕለቱን የምከውነው። አስተውሎ የኔዎቹ ቅኖቹ አዱኛዎቼ የተጻፈው በ05.01.2018 ነበር። እንዲህም ይል ነበር … ሙሉውን ሊንኩን ስለምለጥፈው ቀሬውን ማንበብ ትችላላችሁ።
·         ክወና።
የተከበሩ ዶር. አብይ አህመድ ለዚህ የመንፈስ ንጽህና፤ ለዚህ የህሊና ቅድስና፤ ለዚህ የሩህ ጸአዳ ድንግልና፤ ለዚህ የነፍስ መዳህኒት ውስጥነት፤ ለዚህ የተስፋ ብርሃን ምዕራፍነት፤ ለዚህ የተመክሮ ቅኔ ርዕስነት፤ ለዚህ የበቀለ አዋቂነት፤ ለዚህ ለማይጠገብ ሐገራዊ ተቆርቋሪነት፤ ለዚህ ራሱን ዝቅ ላደረገ የጸዳላዊ ትህትና፤ ለዚህ ልስሉስ ለዛዊ ልሳን፤ ለዚህ ሩቅ፤ ዕንቁ ምናባዊ ምኞት ያለኝን ታላቅ አክብሮት፤ ያለኝን ፍቅር፤ ያለኝን ኩራት፤ ያለኝን ሙቀታዊ ውስጥን የመስጠት ፈቃድ ለመግለጽ ቃላት የለኝም። 

በገንዘብ ደሃ ነኝ። በቃላት ግን ተቸግሬ አላውቅም ነበር፤ ነገር ግን ስለ እርስዎ ውስጤ የሚለኝን ለማሳዬት ቃላት አነሰኝ፤ በውነቱ ፊደሎች አቅም አነሳቸው። ትርጉም ነዎት፤ አናባቢም ተነባቢም። ሌላ አቅም የለኝም ድንግል የዕለታዊ የፊደል ገበታዬ ናት እና ባሰብኳት ቁጥር አስበዎትአለሁ - ለምንግዜውም - ነይ እሲኪለኝ ድረስ። እግዚአብሄር ይስጥልን። እግዚአብሄርም ይመስገን። 

ይህን የሃሳብ ደስታና ፍሰሃ ከውስጤ ተቀብዬ የራሴ አደረገው ዘንድ አቅምና ሃይል ስለሰጠኝ ፈጣሪዬን አዶናይን አመሰግነዋለሁ። ዓላማችን ደግ አይበረክትባት እና አደራ ይጠንቀቁ። ከፈጣሪ በታች እራስዎትን ይጠብቁ። እንደ ምኞቶዎት ልዕልት ኢትዮጵያ የፍቅር ሐገር ሆና እናያት ዘንድ አማላክ ይርዳዎት። ይኑሩልን። I am Proud of You! Ich bin stolze auf sich! ደህና ይሰንብቱ።

አይዋ ወያኔ እባክህን አደብ ግዛ? እባክህን ልብ ግዛ? እኒህ ደግ ለሁላችን፤ ለሁሉም ነገር ፈውሳችን ናቸው። በወያኔ ሃርነት ውስጥ ያለው ለሳቸው ጥበቃና ከለላ በማድረግ ላይ የምትገኙ ወገኖቼም እጅግ አድርጌ አመሰግናችኋለሁ፤ ሳትታክቱ፤ ሳይደክማችሁ፤ ሳትዝሉ፤ ሳትዘናጉ የመፍትሄውን ብሌን ጠብቁ አደራ። አደራ። አደራ።

የቅንነት ማበርተኞች ወገኖቼ ቢያንስ በጸሎት እንርዳቸው። አይዞህ እንበላቸው። የፖቲካ ሊሂቅ በዚህ መልክ ጸድቶ ሲፈጠር እና ሳይ እኔ የመጀመሪያዬ ነው። ታሬና ቁንጮዬን ከርክሞ ያሳደገኝ ፖለቲካ ነው። 
እንዲህ አይነት ንጹህንት ግን ገጥሞኝ አይዋቅም። ሁሉ የተሟላ። 
ተመስገን። ውዶቼ ይህ መንፈስ ያላፈው ዓመት ነው የተጻፈው ዛሬ ቅኔው ግጣሙን አገኘ እና አብቼ አልላኬን አመሰገንኩበት። ተመስገን!

አብይ የኢትዮጵያ ፍላጎት።
የተጻፈው 05.01.2018

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት
ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
የኔዎቹ ክብረቶቼ ቅኖቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።