መምህር።
መምህር።
„እግዚአብሄር በአንድም በሌላም
ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።“
መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ፲፬
ከሥርጉተ©ሥላሴ
19.11.2018
ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።
„ተፈጥሮ አድሎ የሰጠንን ሀገር ተጠቅመን መቀየር ያልቻልነው እውቀትን የመፈለግ ዝንባሌያችን ሽርፍራፊ ፍራንክ ለመለቃቀም ከምናደርገው ጥረት በእጅጉ የተለያየ መሆኑ ነው፡፡… ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ነች፡፡ ከማንም የተሻለ የማድረግ አቅም እኛ ውስጥ አለ፡፡ እኛ ያጣነው ዊዝደም ነው፡፡” ከዶር አብይ አህመድ /አሜኑ/
የተወሰደ።
· መቅደም ዕሳቤ።
ሰሞኑን በመወሰድ ላይ ያለው እርምጃ መምህር ነው - ለእኔ። መምህርነቱ በሁለገብ ነው። መምህርነቱ
ጸያፍነት መጸዬፍ እንዲቻል የሚያደርግ ነው። ከሁሉ በላይ ማንም ሰው ከህግ በላይ አለመሆኑን ማሳዬት መቻል ሌብነት፤ ስርቆት ዶክትሪኑ
አድርጎት ለኖረው የወያኔ ሃርነት ትግራይ አውራ መንገድ ማክተሚያው የብሥራት መባቻው ነው። ትውልድ እንዲሞት የተፈለገበት ይህ መንገድ
ትውልዱን ከታማኝነት ትውፊታዊ ማዕቀፉ ያወጣ መቅሰፍት ነበር ሌብነታዊ ጉዞው እና መካተቻው።
ይህን ጠ/ሚር አብይ አህመድ የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ሚኒስተር ሚንሰተር
በነበሩበት ወቅት ከያንያንና እና ጋዜጠኞችን ባነጋገሩበት ወቅት እንዲህ ብለውት ነበር። እኔ የ ኢሳቱን የማማ እዘጋጅ ጋዜጠኛ አቶ ማስረሻ ዓለሙን የዛሬ ዓመት በሞገትኩበት ጊዜ
ማጠቀላዬን ስሰራ በዚህ መልክ ነበር። ያን ጊዜ አሰሪው ድርጅትም ተው አላለውም ነበር። አልቆነጠጠውም ነበር። የሆነ ሆኖ እንሆ ከዛ እንነሳ እና ወደ ዛሬው በኽረ ጉዳዬ እንገባለን።
- በጎ ህሊና እና ቅን ልቦና በዶር አብይ አህመድ ንጹህ መንፈስ።
ከአርቲስቶች አና
ከቅን ጋዜጠኞች ጋር
ሁለተኛው በጎ
ህሊና እና
ቅን ልቦና
የአትኩሮት መስካቸው
ነበር። ይህን በዚህ ጽፌው ነበር የዛሬ ዓመት።
https://sergute.blogspot.com/2018/05/05.html
አብይ የኢትዮጵያ ፍላጎት። ማጠቃለያ።
„መማር ከልብ ለልብ ግንኙነት ውጪ የሚሆን ስላልሆነ፤ ከሌብነት ጋርም ክፉ ሥር መሆኑን ማምን ያስፈልጋል - ሌብነት። በአንታይ ኮራብሽን ንቅናቄ ብቻ ሳይሆን፤ ክፉ ሥር ነው። ለምንድነው ክፉ ሥር የሚሆነው? ብዙ ለመስረቅ የሚሞክሩ ጓደኞቻችን ያዬነው ነገር፤ የመጀመሪያ ጥፋት ኢትዮጵያ ላይ አይደለም። ውሸት ነው እናንተ ተሰርቀናል ብላችሁ እንዳታስቡ። አልተሰረቃችሁም። በጣም ምስኪን ሰው ዲግሪ፤ ማስተርስ ከያዘ በኋላ ስልጣን ይይዝና፤ 11 ሰ ዓት 30 ሲሄድ ፍርፍር ሰርታ፤ ቡና አፍልታ፤ ውሃ አዘጋጅታ በጣም የምትቀበለው ሚስት ነበረችው። ልክ ስልጣን ሲይዝ በዚህኛው ኪሱ 10 ሺህ፤ በዚህኛው ኪሱ ደግሞ 29 ሺህ ያለውን፤ ማን እንደ ወሰደው አያውቅም። ከዬት እንደወደቀም አያውቅም። እሱ ሦስት ሰዓት በኮርቫ ሲገባ፤ እሷ ደግሞ በማርቸዲዝ „ዳዲ አይ ዊል ካም ሱን ብላ“ ቦሌ። እምትመለሰው አፍተር ሚድ ናይት፤ ወይንም ሲነጋጋ። ሰውዬው መጀመሪያ የሚያፈርሰው አኒስቲቲሹኑን ቤቱን ነው። ሰርቆ ያነን ክፉ ነገር ቤት ይዞ ይሄዳል። ምርጥ ሚስቱን ያጣል። ምርጥ ልጆቹን ያጣል። ስለዚህ ክፉ ሥር ነው የሚያጠፋው አንተን ነው። ሲደመር ቆይቶ ሀገር ሊበድል ይችላል። መጀመሪያ ግን የመትከስረው አንተ ነህ። ኢህን ማሳዬት ያስፈልጋል።“
ዶ/ር አብይ አህመድ ከአርቲስቶች እና ጋዜጠኞች ጋር ስለ ሙስና ክፍል አንድ
· ሌብነት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ዶክተሪን ነው።
ሌብነት ብሄራዊ ደረጃ አብነት ሆኖ 27 ዓመት ተቆዬ። ሌብነት በአገር ደረጃ ክብር ሆኖ 27 ዓመታትን ተንሰራፍቶ ባጀ። ሌብነት በብሄራዊ ደረጃ ማዕረግ ሆኖ
27 ዓመት ተዳነሰ። ሌብነት በአገር ደረጃ ሞገስ ሆኖ 27 ዓመት ፈነጠዘ።
ሌብነት ጸጋ ሆኖ 27 ዓመት ተዘማነነ። ሌብነት ሥልጣኔ
ሆነ 27 ዓመት በአላዛሯ ኢትዮጵያ ተሞሸረ። ሌብነት ልዩ ክህሎት ሆኖ 27 ዓመት ሙሉ ዘመነ። ሌብነት ሥርዓት አስተዳደሪ፤ መሪ
አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ ሲሽሞነሞን ሲንቆለበባስ ተኖረ ድፍን 27 ዓመት ሙሉ።
„ለማያውቅሽ ታጠኝ“ ይላል የጎንደር ሰው 27 ዓመት ብቻ አይደለም። ከዛም ያለፈ 40 ዓመት ሆኖታል።
የወያኔ ሃርነት ትግራይ የኢኮኖሚ መሠረት ሌብነት እና ዝርፊያ ነበር። የትግራይን የጎንደርን እና የወሎን ገበሬዎች እርሻ ከማሳቸው ሙልጭ አድርጎ ሰርቆ የካቲት ላይ በመፈርጠጥ ይታወቃል የወያኔ ሃርነት ትግራይ ድርጅት /ማሌሊት/፤
የመንግስት ካዝናዎችን በሌሊት በመዝረፍም ነበር ነፍሱ የሰነበተችው። ገራሚው ነገር ይህን ጸያፍ አረንቋ አሰር መዋቅሩን እና
ይህን ፍልስፍናውን ይዞ ከች ማለቱ ነው በግንቦት 20 የዶፍ የግዞት መባቻ።
ይህም ብቻ አይደለም ጫካ በነበረበት ጊዜ ያደረገው ነገር ከውጭ እርዳታ ያገኘውን አሽዋ ሞልቶ
ነበር ለትግራይ ህዝብ እርዳታውን ሳያደርስ ለጠበንጃ መሸመቻ ያደረገው። ይህን የዕውነት አርበኛው ደጉ አቶ ገ/መድህን አርያ በተለያዬ ጊዜ አሳውቀዋል። ይህን
መረጃ ይዞ በዓለም አደባባይ የሚሞገት ጀግና ጠፋ እንጂ። አሁን ሰሞኑን የሚደመጠውም ይህው ልማዱን እንዳሳከ ነበር። በጠጠር ስኳርነት። የኢትዮጵያ አንባሳደር በጁቡቲ የሚገልጹልን
አሁን ይኸውን ነው። ገና ሜቲክ ማረኝም እንልላን ብለውናል። እኔም ይህን ያህል አንድ ድርጅት ላይ ከተመዘበረ ሌላው ሲታከል ምን ይባል ይሆን ብዬም ነበር።
የመነሻው የወያኔ ሃርነት የፍልስፍና ማዕከል ስርቆት ስለሆነ መዳራሻዋም ስርቆት ነው። ስርቆት ለወያኔ
ሃርነት የማንፌስቶ ማህበርተኞች ልዩ ስጦታ፤ ልዩ መክሊት ነው። ማሳፈሩ - አንገት - ማስደፋቱ ቀርቶ ማቀራራሪያ። ከብሮ ይዞ የሚያስደልቅ ፈንድሻ የሚፈርሽበት የጎሽ ጎሽነትም ነው።
የድል አስገኝ ሃይል ሆኖ የሰማዕትነት ደረጃ የሚያሰጥም ዝርፊያ ወረራ ስርቆት ሰው ማጥፋት ነው።
አገርን ያህል ሊመራ ዕድል ያገኘ ዘራፊ ድርጅት በዬከተሞቹ ብርቅ የሆኑበትን ማናቸውም ነገሮች
ሁሉ በስግብግብነት እና በስስታምነት ወደ ትግራይ ለመጫን ፋታ አልወሰደበትም፤ ከወሎ ከጎንደር ሲገርመኝ በሰሞናቱ ከኢትዮጵያ መልስ የጉዞ ማስታወሻው
ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ከጅማም ይኸው ነገር እንደ ተፈጸመ ጥፎታል። ስለምን? የወያኔ ሃርነት ትግራይ የፍልስፍና ማዕከል ሌብነት ስለሆነ።
ታላቋ ትግራይን ለመፍጠር የቁስ ስርቆት ብቻ ሳይሆን የማንነትም ዓይን ያወጣ ዝፊያ አካሂዷል
ወያኔ ሃርነት ትግራይ። ከጎንደር ወልቃይት ጠገዴ ከወሎ ራያን ዘርፏል ሰርቋል። በቀጣይነትም ከጎንደር አርማጭሆን አክሎ እስከ ጋንቤላ
ድረስ በሾጣጣ አባይን እስከ አናቱ ለመቆጣጠር በሚያስችል መልኩ ካርታውን ሰርቶ ነበር አቤቶ ሰርቆ የማይጠግበው ወያኔ ሃርነት ትግራይ። ለእኔ ለሌባ የሰረቀውን ማስመለስ ነበር ቀላሉ መንገድ እና ፏ ፍንተው ያለው አውራ ጉዳና።
የላይኛው ማዕቱን አወረደ እና ገታው እንጂ እሱስ ልቡ ተራራ ነበር። ለ100 ዓመት ስርቆት እንደሚቀጥል አውጆልን ነበር እኮ። በቃ ጠቅላላው መለያችን ሌብነት እንዲሆን። አበስኩ ገበርኩኝ።
የሚያሳዝነው ነገር የትግራይ
ትውልድ ስርቆት መዝረፍ መውረር እንዲማር ተግቶ በመስራቱ በወልቃይት ጠገዴ ላይ ያተኮረ የመመረቂያ ጹሐፍ ለሚሰሩ ተተኪዎቹ ላቅ
ያለ ድጎማ ሊያደርግ እንዳሰብም ባለፉት ዓመታት ያስደመጠን የዕብደት ውሳኔ ነበር።
ስለሆነም ሌብነት ዲታ ማድረግ ከቻለ፤ ሌብነት ለታላቅነት አንቱነት መንገድ ከሆነ፤ ሌብነት የድሎት
ኑሮ ማስከበሪያ ከሆነ ስለምን የሰው ልጅ ስራን ይፈቀድ? ሳይሰራ
ሚሊዮን የሚያዝቅ ከሆነ እንዴት የሥራ ባህል ማደግ ይቻል?
ሌላው ቀርቶ የጥበብ ሰው እራሱ ከሌቦች ጋር አብሮ መስረቅን ከወደደ
እንዴት ያለ ትውልድ ይገንባ? አሁን የአርቲስት
ዝናህ ብዙ እዚህ ውስጥ መዘፈቅ ሌብነት እንዴት ቀስ እያለ ማህበረሰቡን ይዞ እዬሰመጠ እንደሆነ ያሳያናል። ማህበረሰቡ
እራሱ ረግረግ ውስጥ ነው ያለው።
ከሌብነት ሥርዓት ውስጥ ሃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ እንዴት ይፈጠራል? ይቻላልን?
ሥርዓቱ የቆመበት ባላ እና ወጋጋራው ሌብነት ከሆነ ከዚህ የሚያመልጥ ሊኖር አይችልም። የጥበብ ሰው ሌብነትም መጸዬፍ ካልቻለ ማን
መምህር ይሁን? የሰብዕዊ መብት ረገጣውም የመጣው እኮ እውነትን ፈላጊዎችን ለማፈን ነው።
ስለዚህ የችግሩ ቁንጩ ሥርዓቱ የቆመበት ፖሊስ ስርቆትን፤ መዋሸትን፤ ማጭበርበርን መርህ አድርጎ መቆሙ ነው። ጥበብ ሰው
ያልሰራበትን መብላትን ከፈቀደች፤ ጥብብ በወዟ ለመኖር ካልወሰነች፤ በኢትዮጵያ ጥበብ ቃሬዘ ላይ ነበረች ማለት ነው። ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ያላዬው ጉድ፤
ያለሰማው ጉድ።
ጥበብ እራሷ ቃሬዛ ላይ ሆነ እንዴትስ ስለ ዕውነት፤ እንደምንስ ስለ ተፈጥሮ፤ በምንስ ሁኔታ ስለ ስው ልጅ ትሞግት ልዕልት ጥብብ? እሷ እራሷ ልዕልት ጥበብ ተሰርቃ? ይህ የማይቻል ነበር፤
የማይቻልም ሆነ። ዛሬ አንቱ የተባሉ አዛውንት የጥበብ አውራዎች ስለ አውነት ምስክርነት ሲጠሩ ማቄን ጨርቄን የሚሉበትም ስለዚህም
ነው። ታላቋ ጥብብ እራሷ እውነትን ፈርታ ለሥጋዋ እንሆ አደላች። እግዚኦ!
የትውልዱ ብክነት መታዬት ያለበት ከዚህ አንጻር ነው። ትውልዱ ባለቤት አልባ ነበር ስንል የነበረውም
በዚህ ምክንያት ነው። ጥበብ እራሷ ከተፈጥሯዋ ወጥታ ብርቅርቅነት ሮቦትንት አሰኛት እና።
ትውልዱ መምህሩ ሌብነት ነው፤ ለትወልዱ ሐዋርያው ስርቆት ነው። ለትወልዱ ሰባኪው ወረራ ነው። በዚህ ውስጥ
የዕውነት ግድያ ይኖራል፤ በዚህ ውስጥ የፍትህ ሞት አለ። በዚህ ወስጥ የሚዛን ስቅላት አለ። በዚህ ውስጥ ሰው ከእንሳሳ የተለዬበት
የአንጎሎ አፈጣጠር ግልበጣም አለ።
ሰሞኑን ፍትህ ጠሐይን የማለም የመመኝት ጉዳይ ክብርት ወ/ሮ ማዕዛ አሻናፊ ሲገልጡ ስምቻለሁኝ።
በዳኞች፤ በጠበቆች፤ በአቃቢ ህጎች ላይ ሊኖር ስለሚገባው አትኩሮት አብክረው ሲገልጹ ትግሉ ቀላል አለመሆኑን ገልጠዋል። እኔ ይህን
ተቀብዬ ትልቁን ነገር ስተውታል ብዬ አስባለሁኝ።
ይህውም ማህብረሰቡ ህሊናዊ ለውጥ እንዲያመጣ ሊደሩጉ ስለሚገባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ምን
እዬተመከረ ነው ያሰኛል? የበከተ ሁኔታ ነው በዚህ ሥርዓት የኪሳራ ዘመን የታዬው። ታማኙስ አሳማኙስ ማነው? ዝንቅ መከራ ነው ያለው እኮ።
ይህን እኔ በፍቅራዊነት ፕሮጀክቴ ላይ ስጠይቀው ኑሬያለሁኝ። ህግ ማወቅ የህግ ባለሙያዎች ብቻ
መሆን የለበትም፤ ወይንም የህግ ሙያ ተማሪዎች ብቻ መሆን አይገባውም።
ህግን ማወቅ የማህበረሰቡም ጭምር መሆን አለበት። ማህበረሰቡ ህጉን ሲያውቅ መብቱን እና ግዴታውን በሚገባ ጠንቅቆ ይረዳል። መብቱን ካወቀ እሱን ራሱን ለዘረፋ አያስገበርም ማለት ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እኮ ተዘርፏል። ምኑን? ሁለመናውን።
በታቀደ ሁኔታ ለተማሪዎች በሳምንት አንድ ቀን በጋራ ክላስ ስለ ወንጀለኛ መቅጫ ህጉ እና ሥርዓቱ፤ ስለ ፍትሃብሄር ህግ እና ሥርዓቱ ተከተታታይ ማብራሪያ መሰጠት አለበት አንቀጽ በአንቀጽ። ቢያንስ ከ7 ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ ልጆች ወንጀሎች የሚከሰቱበትን
ሁኔታ እና ህጉን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
አሁን እኮ አንቱ የተባሉ ሊቀ ሊቃናት እራሱ ከህግ በላይነታቸው ክብራቸው እዬሆነ ያለው እኮ ማወቅ የሚገባቸውን ድንጋጌዎች ማወቅ ባለባቸው የልጅነት ጊዜያቸው ያለማዋቅ ችግር ነው።
የህግ ሰው ቢያንስ ከትዕቢት ጋር መፋታት ሰብዕናው እንዲሆን የሚፈቅው ህግ ከሁሉም በላይ ስለመሆኑ ማወቅ ሲችል ብቻ ነው። መታበይ እኮ መለያ እዬሆነ ነው።
ይህም ብቻ አይደለም የህግ ፋክሊቲዎች ራሳቸው የህሊና አብዮት ማካሄድ አለባቸው ብዬም አስባለሁኝ።
ይህ የዛገጠ 40 ዓመት በላይ ዶክተሬኑ አድርጎት የቆዬው የወያኔ ሃርነት ትግራይ የበከተ ፍልስፍና ለማስቀረት ተነጥለው የህግ ባለሙያዎች
ብቻ ተዋግተው፤ እነሱ ብቻ ተለውጠው የሚያልቅ አይደለም። መከራው ዝክንትል ነው።
ማህበረሰቡ እኮ ለመከበር ዓይን ልቡ ያለው በስርቆት ፍልስፍና
ነው። ሌላው ቢቀር ያልሰራበትን ደሞዝ ሲከፈለው ደስ ብሎት ይቀባላል፤ ያልሰራበትን የውሎ አበል ሲሰጠው ፍንሽንሽ ብሎ ይወስዳል፤
ይህ ለእኔ ነጠቃ ነው።
ሰዓት አሳልፎ ሥራ ሲጀመር ሌላኛው ስርቆት አለመሆኑን አያውቀውም ራሱ የመንግሥት ይሁን የግል ሰራተኛው። በአንድ ሰዓት ማለቀ የሚገባውን ሳምንት ሲያሰተኛው ስርቆት መሆኑን አይረዳውም
ሁሉም በሌላው ላይ እጅ ከመጠቆሙ በፊት በራሱ ላይ ለውጥ ለማምጣትም ለመለወጠም መቁረጥ ይኖርበታል።
አሁን የአገር ባህሉ አረቂ አቲካላ ሲወጣ እንፋሎቱ ተጠራቅሞ ነው። ትንሿ ጠብታ ስትጠራቀም ነው
አንድ ሊትር ውሃ የምትሆነው፤ አንድ ሊትር ከሌላው ሲታከል ሁለት ሦስት እያለ ይሄዳል። በዚህ 27 ዓመት ውስጥ በተገቢው ሰዓት
ስራው ገበታ ላይ ተገኝቶ በተሰጠው ጊዜ ተግባሩን የከወነ ቢሰላ ከፐርሰነት በታች ነው። ለዛውም በውጭ ብድር ነፍሷን በምታሳድር
አገር ነው ይህን ያህል የቀልድ ውረባ የነበረው።
በዚህ ስሌት ስንሄድ ኢትዮጵያን አዝኖላት ያልዘረፋት ለማገኘት አዳጋች ይሆናል። ለዚህም ነበር
አንድ ጊዜ ዶር አብይ አህመድ ስለ መንገድ ትራፊክ መብራት አንስተው
ስንቱ ጥሰት እንደሚፈጽም በምሬት የገለጹት። ለዚህም ነው ቢያንስ የሰራ ሃላፊዎች ስብሰባዎቻቸውን በቅዳሜ እና በእሁድ እንደ ገናም
6 ቀን ተኩል እንዲሰሩ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ አብከረው እዬገለጹ ያሉት እሳቸውም አብነት ሆነው ሰንበትን ሁልጊዜ በትጋት
እምናዬያቸው።
- ማጣቃሻ።
”የኦህዴድ ሞተር ~ ዶክተር አቢይ አህመድ ማን ናቸዉ? (ፍቅር ስንታየሁ)“
26/12/2017
አቶ ፍቅር ስንታዬሁ ጋዜጠኛ ነው። በሰብዕናው ትሁትም፤ በድፍረትም ስለ
ዕውነት የቆመ መሰካሪም ዋቢም ነው። ጋዜጠኛው ሁሉ ወለም ዘለም ባለበት ወቅት በዛ ወጀቡ ባዬለ የመከራ ዘመን የዛሬ ዓመት ነው
ፊት ለፊት ወጥቶ ስለ ዶር አብይ አህመድ ብቃት የሞገተው ጋዜጠኛ አቶ ፍቅር ስንታዬሁ።
„እግዚአብሄር በአንድም በሌላም
ይናገራል
ሰው ግን አያስተውለውም።“
ጋዜጠኛ ፍቅር ስንታዬሁ ታላቅ የዘመኑ እጬጌ ጋዜጠኛ ነው ልክ እንደ ጋዜጠኛ
አቶቶ አንተነህ ከበደ ለእኔ። ይህን ጹሑፍ ልብ ብሎ ላደመጠው ትውልድ እንዴት ሊገናባ እንደ ታሰበ የምርምር ተቋሙ ይሆናል። ተመስገን
የሚያሰኘው አሁን ዶር አብይ አህመድ ዕድሉን በብሄራዊ ደረጃ ማግኘታቸው ነው። ከብሄራዊ አልፎም ድንግሉ አቅማቸው አህጉራዊም እዬሆነ ነው። ተመስገን።
· ሞራላዊ የኩንታሮት እብጠት ወደ ፈውሳዊ ውጤት እንዴት?
የማህብረሰቡ የአማለካከት ሞራላዊ ለውጥ በፍጹም ሁኔታ ያስፈልገዋል። ሥርዓቱ እኮ የበከተ ነው።
በተዘረፈ ሃብት ነው ሁለመናውን ያዋቀረው ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንደ ድርጅትም እንደ አገር መሪ አውራ ድርጅትነትም።
ስለዚህ ሥርዓቱ እዬፈረስ በአዲስ እዬተተካ ቢሆንም በሂደቱ ውስጥ ሊዘለል የማይገባው መሰረታዊ
ጉዳይ የማህበረሰቡን ህሊናዊ ሁኔታ ወደ ትክክለኛው ሞራላዊ ትውፊቱ የመመለስ አቅምን አምጦ መወለድን ይጠይቃል።
ይህ ጉዳይ በቅንጥብጣቢ እርምጃዎች ብቻ ተነካክቶ የሚቀዬር አይደለም። እርግጥ ነው ቀጣይ እንደሆነ እርምጃው
ተደምጧል። ነገር ግን ከዚህ ከሌብነት ፖሊሲ ጋር እንዳይበቅሉ አረም የዋጣቸው አዎንታዊ አመክንዮች አሉ። እነሱም የሥራ ባህል፤ የማገልገል
ፈቃድ፤ የበጎ አድራጎት መንፈስ፤ ዕውነት፤ የሌላውን አለመመኘት፤ እንደ ራስ ለመኖር አለመፈቅደ ሁሉ ሙት መሬት
ላይ ነው ያሉት።
ራሱ ዝምድና የሥጋ እና የደም ትስስር ሁኔታ አሁን ከጥቅም ውጪ የማይታሰብ ነው። ስትጠቅሙት
ብቻ እህቱ ትሆናላችሁ፤ ስትጠቅሙት ብቻ ወንድሙ ትሆናላችሁ፤ ስትጠቅሙት ብቻ የአክስት የአጎቱ ልጆች ትሆናላችሁ ከዚህ ባሻገር ያለው ቤተሳዊ ዕሴት አሮ አመድ ሆኗል።
በዚህ የሌብነት ሥርዓት ውስጥ ያልቆሰል፤ ያልከሰለ አንድም ኢትዮጵያዊ ዕሴት የለም። ብሄራዊ
እርቅን በሚመለከት አንድ ኮሚሽን እንደሚቋቋም ሰምቻለሁኝ። ከሌብነት የጸዳ ማህበረሰብ ለመገንባትስ ምን ዓይነት ኮሚሽን ነው የሚያስፈልገን?
ያልተሰረቀ ምን ነገር አለንና? እስኪ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ከወጣ ጀምሮ ያሉትን የጋይዳንስ
መጸሐፍትን መርምሯቸው፤ የሌላ አገር ጸሐፍት የጻፉትን ሁሉ መርምሯቸው። ኢትዮጵያዊነት እራሱ ተስርቋል። የወል ዕሴታችን ሁሉ ተዘርፏል። ለዚህ ጥልቅ የሆነ
መከራ ጥልቅ የሆነ ጥናትም ያስፈልገዋል፤ ማስፈልግ ብቻ ሳይሆን ወደ ሥራ ለመግባት መጀመር ያለባቸው የተዘነጉ ወይንም ባሊህ ያልተባለ
አመክንዮ አለ ነው የዕኔ የእለቱ እድምታ። ማህበራዊ ዕሴት፤ ቤተሰባዊ ዕሴት፤ ትውፊታዊ ዕሴት ህመምተኞች ናቸው። የአልጋ ቁራኛ ሆነዋል። ፈዋሽንም ይሻሉ።
የዘራፊዎች መታሰር፤ የቀማኞች በቁጥጥር ሥር መዋል፤ የፍትህ አስፈጻሚ አካላት እንደ ገና መደራጀት
ብቻ ሳይሆን ሞራላዊ ዕሴታችን ተቀምተናል እና ይህን ወደ ነበረው ትውፊታችን የሚመለስ ጠንከር ያሉ፤ መሬት ያያዙ አሰሳዎች በሁሉም
መስክ መካሄድ አለባቸው ባይ ነኝ።
ሌላው ቀርቶ የሃይማኖት ተቋማት እራሱ ከዘረፋ ውጭ ናቸው ወይ?
ት/ቤቶች ከሌብነት ውጭ ናቸውን?
መምህራኖች በህዝባዊ አገልግሎት ውስጥ ባላቸው ቦታ ከስርቆት ውጭ ናቸው ወይ? አሁን ይህን የአርቲስት ዝናህ ብዙን ጉዳይ ስታስቡት በዚህ የዘገጠ የስርቆት፤ በሰው ሃብት የመበልጸግ ሱሰኝነት የጠራ ሰው ለማግኘት ዳገት ነው።
ጥብብ እራሷ ከሌቦች ጋር ከተባበረች፤ ጥብበ ራሷ ከገዳዮች ጋር ከመከረች እና ማህበረተኛ ከሆነች፤
ጥበብ እራሷ ከትወፊታችን ከጤነኛው ጋር ከተጣላች መከራችን መግዘፉን ማዬት ይቻላል።
ስርቆትን የሚጸዬፍ ትውልድ ለመጀመር ከህግ ተቋማት ጀምሮ በዬደረጃው ባሉ ት/ቤቶች፤ በዬመኖሪያ
አካባቢ ባሉ ተቋማት፤ በዬመሥሪያ ቤቱ እና ድርጅቶች ባሉ አደረጃጃቶች በራሱ በሚዲያውም ጋዜጠኛ ከሌባ ጋር መኖር መፍቅድ ማለት እንዴት
በነቀዘ ሥርዓት ውስጥ እንደ ተኖረ ትልቁ ምስክር ጉዳይ ነው።
ስለዚህ የመንገዱ ኮረኮንችነት ብቻ ሳይሆን እሾኻማነትም ግምት ውስጥ ገብቶ ሁሉም የእኔ - ለእኔ - ከእኔ - ስለእኔ - በእኔም -ብሎ ወገቡን ጠበቅ አድርጎ በመነሳት ከሌብነት የጸዳ ማህበረሰብ ለመመሰረት መትጋትን ይጠይቃል።
ሁሉም ከራሱ ከአካባቢው መጀመር ካልቻለ ማጽዳቱ ጉራማያሌ፤ ጌጡም ግንጥል ጌጥ ነው የሚሆነው። ከጥበብ ወዲያ ለአንድ ትውልድ
ማን ጠበቃ ማን ዋቢ ሊኖረው ነው? ጥበብ እራሷ እኮ ፍቀረ ንዋይ አስጎምጅቷት የዛች ደሃ አገር ዕንባ ሳይጎረብጣት አባሪ ተባባሪ
ሆነች እኮ? እና ማንስ ምኑስ ቀረና ነው? እፍረትን ለብሶ ከመኖር ሞት በስንት ጣዕሙ።
ይህ ትውልድን ገዳይ ስርቆት፤ ይህ ብክለት ግማት ሌብነት፤ ይህ ወረርሽኝ በሽታ ዝርፊያ ከሥረ
መሰረቱ እሰኪነቀል ድረስ እና የጸዳ ድንግል ማህበረሰብ እስኪፈጠር ድረስ ከእያንዳንዱ በግል ከሁላችን በጋራ ትጋት ይጠበቃል።
ትውልዳዊ ድርሻችን በትጋት እንወጣ!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ