ልጥፎች

ከሜይ 31, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ተስፋ {የወግ ገበታ}

ምስል

ተስፋ {የወግ ገበታ}

ምስል
 እንኳን ወደ ቀንበጥ በሰላም መጡልኝ  ተስፋ። „መዳህኒቴ እና ክብሬ በእግዚብሄር ነው። የረድኤቴ አምለክ ተስፋዬም እግዚአብሄር ነው።“ መዝሙር ምዕራፍ ፷፪ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ v      ተስፋ ጸጋ v      ተስፋ ምህረት v      ተስፋ መድህን ነው።     ምን ያህል እንደተጓዝኩኝ አላውቀውም? ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቀውም? አለማዋቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገለጸልኝ። ተስፋን እጠብቃለሁኝ። እ.አ.አ 2010 ተስፋ መጸሐፌ ላይ የጀርባው ሽፋን ላይ ያልኩት ነበር አሁንም እምለው ይኸው ነው ...  ·          እ ፍታ እንደ መግቢያ …   የኢትዮጵያ ቅኔዎች የእኔም የኔታዎች የቀንበጥ ብሎግ ክቡር ታዳሚዎቼ እንደምን አላችሁልኝ? ዕለቱን ከተሰፋ ፈላጊና ተስፋ ፈጻሚ ጋር ያለው ድልድይ አስመልክቶ አንድ ወግ ቢጤ ለማቅረብ ተሰናዳሁኝ እንሆ … የተስፋ ጥገት ለአላዛሯ ኢትዮጵያ በእጅጉ ያስፈልጋታል። ይህ ማለት የተሰፋ ጥገት ያለው ያው የፈረንጅ ላሞች ዝርያ ስለሆነ በገፍ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ እዮር ቢፈቅድላት ለእምዬዋ እንደማለት። የፈረንጅ ላሞች ወተተታም ናቸውና። ምኞት ...  ግን እኛ ለማይነጥፍ ጥገት ግሬራውን ወይንም ቆሬውን በገፍ ማሰናዳት ይጠበቅብናል። ታዲያ ምርቃታችን ሳንረጋግጥ ጥንቃቄ ከኖረን ነው። በስተቀር ምርቃትን የፈጠረም የሰጠም ኤልሻዳይ አምላክ ከከፋው ያነሳዋል … ምርቃቱን። አምላካችን ሲከፋው ምርቃቱን ማንሳቱ ባልከፋ፤ ቁጣው ካዬለ በዛው ልክ ደግሞ የርግማን ናዳ … ሊኖርም ይችላል … ማህከነ! በድምጽ https://www.youtube.com/watch?v=Tx-d1