ልጥፎች

ከኦክቶበር 29, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ኦነጋውያን ማቆላመጡን ማብቃት ይገባል።

ምስል
ግርዝዝ። „ይህ ትዕቢት ምን ጠቀመን፤ ከትዕቢት ጋር ያለ የኦሪትስ ባለጠግነት ምን አመጣልን።“ መጽሐፈ ጥበብ ፭ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ  29.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። በጠ/ሚር አብይ አህመድ የ100 ቀናት ክንውኖች ውስጥ ተካቶ ከነበረው የጉብኝት ቀጠና ወስጥ አንዱ ደንቢ ዶሎ ነበር ። ደንቢ ዶሎ ላይ የነበረው ህዝባዊ ስብሰባ የኩርፊያ፤ የቁጣ የውጡል ነበር ። ለምን መጣችሁብን ዓይነት ነበር። የሚገርመው እና የሚደንቅው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን እያለ ኢህአዴግ የሚያስጨፈረውም ከዛ ሰፈር ትውር አላለም ነበር። በቦታው የተገኙት ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ ነበሩ። ታዳሚዎች ግን ውስጣቸው ቅጥል እያለ ነበር ንግግሩን የተከታተሉት። ያቀረቡት ጥያቄ ሁሉ ወልደ ግራ ነበር። ፊታቸውን እንደ ኮሶ ኮስኩሰው ነበር አንግዶችን የተቀበሏቸው ። ፊታቸውን እንደኮሰኮሱም ነበር የሸኟቸው።  እና እኔ እህታችሁ ከልብ ስለሆነ ሁሉንም ነገር የእኔ ብዬ የምከታተለው  ደንቢሻ የምትፈልገው የደንቢን ንጉሥ ብቻ ነው። እዛ ሰፈር ዶር  መርራም አቶ ጃዋርም ቦታ የላቸውም ብዬ በተከታታይ ስቸከችክ ባጀሁኝ። ይህም ብቻ ሳይሆን ግንባር ስለሚባለው ፍልስፍናም የጠብታ ያህል የሚያውቁት ስለሌለ እባካችሁ እዛ አካባቢ ትንሽ የሚላስ የሚቀመስ የህሊና ተግባር ፈጽሙ ብዬ ኦህዴዶችን ተማጸንኩኝ። እርግጥ ነው የለማ ቡድን ሥራ በዝቶበታል። በዛ ላይ ልብ ለልብ የመሆንም አዳጋ አለበት። በተጨማሪም ጥድፊያ ላይም ነው የልቡን ለማድርስ ባገኘው የሥልጣን የበላይነት አጋጣሚ ለማስፈጸም። በዚህ 6 ወር ውሰጥ የሦስት አራት አመት ክንውኖችን ከውኗል። በሌላ በኩል ለውጡ ገና ሳይጠናም ነበር ዶር መርራ ጉዲና እና አቶ በቀለ ገርባ አ

ሥርዓት አልበኝነት ክብር ሳይሆን ውርዴትም ውርዴም ነው።

ምስል
ጨካኝነት ወደ እንሰሳነት የመቀዬር ዋዜማ ነው። „ከቀና ህግ ወጥተን ሳትነ የክርስቶስ ብርሃን ረድኤቱ አልተገለጠልንም፤ ክርስቶስም ለኛ አልተወለደልንም።“ መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 29.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።   መቅድም።  በምንም ሁኔታ ጭካኔ ዓይን ሊሰጠው አይገባም። በምንም መስፈረት አረመኔነትን ዝም ልንለው አይገባም። ወንጀልን ወንጀል ስለመሆኑ ልናወግዘው እንጂ ልንከባከበው ወይንም ግርዶሽ ልንሰራበት አይገባም።  ሰባዊነት ነው ሰውን 'ሰው' የሚአሰኘው። የሚያደርገውም። ርህርህና ነው ሰው የሚያሰኘው። አዘኔታ ነው ሰው የሚያሰኛው። የሰው ልጅ ከርህርህና፤  ከአዘኔታ ወጥቶ ጭካኔ መሪው ካደረገ ያ ሰው ወደ እንሰሳነት ተለወጧል ማለት ነው።  ከአዕምሮውም የጎደለ ነገር አለ ማለት ነው። እንደ ሰው ማሰብ ከልተቻለ ወደ እንሰሳነት የመለወጥ መለያነት ነው።  ሰው መሆን ማለት እኮ ከእንሰሳ ዓለም መለዬት ማለት ነው። በሌላ በኩል እናት የምትባል ልዩ ፍጥረት አለች። ሁልጊዜ እናት ልጇ ጎልማሳ ሆነ አዛውንት ልጇ ለእሷ ሁልጊዜ እምታዬው ልክ እንደ ህጻን ነው። እናት አብሶ የአላዛሯ ኢትዮጵያ እናት ባላባራ የዘመናት ጦርነት የልጅ ብርንዶ አቅራቢ ናት። መፍትሄ ለሌለው ማናቸውም በትረ ስልጣን ልጇኝ ስትገብር ኖራለች የኢትዮጵያ እናት። እናት የኢትዮጵያ እናት እንጨት ለቅማ ሽጣ፤ ኩበት ለቅማ ሽጣ፤ እንጀራ ጋግራ ሽጣ፤ በቀን ሰራተኝነት ተቅጣራ ላቧን አንጠፍጥፋ፤ የሰው ፊት ገርፏት ወጥታ ወርዳ፤ የረባ ልብስ ሳይኖራት፤ የረባ የለማ የጣመ ሳትመገብ፤ አንጀቷን አስራ፤ ሙሉ ቀን ስትባትል ውላ ስትባትል አድራ፤ ዓመት ይዞ እስከ አመት በታከተ እድል ፍዳዋን